Telegram Web Link
ት በኃጢአት ምክንያት ሮሜ 1፤24-27 እና በመጨረሻም በገዛ ምርጫቸው እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ልክ የተወሰኑ ሰዎች ለአመፀኝነት እና ሌሎች ኃጥአቶች ዝንባሌ ጋር እንደተወለዱ ምናልባት አንድ ሰው ለግብረሰዶማዊነት አደጋ ከትልቅ ተጋላጭነት ጋር አብሮ የተወለደ ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ሰውየው ኃጥአት በተሞላበት ፍላጎት ለኃጥአቱ ባደረገው ምርጫ በቂ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ አንድ ሰው ለቁጣ/ለንዴት ትልቅ ተጋላጭነት ጋር አብሮ ቢወለድ ለእነዚያ ፍላጎቶች መሰጠቱ ያ ትክክል ያደርገዋል? በእርግጥ አይደለም! ግብረ-ሰዶማዊነትም እንደዚያው ነው፡፡ 

ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ-ሰዶማዊነትን ከሌላው ከማንኛውም ነገር ይልቅ እንደ “ታላቅ” ኃጥአት አይገልጽም፡፡ ለእግዚአብሔር ሁሉም ኃጥአት አጸያፊ ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፡9-10 ውስጥ ከተዘረዘሩት ሰውን ከእግዚአብሔር መንግስት ከሚያስቀሩት ብዙ ነገሮች አንዱ ግብረ-ሰዶማዊነት ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የእግዚአብሔር ምህረት ልክ ለአመንዝራነት፣ ለጣዖት አምላኪዎች፣ ለነፍሰ-ገዳዮች፣ ለሌቦች ወ.ዘ.ተ እንዳለ ሁሉ ለግብረ-ሰዶማዊነትም አለ፡፡ እግዚአብሔር ፤ግብረ-ሰዶማዊነትንም ጨምሮ፤ ለደህንነታቸው በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ በኃጥአት ላይ ድል ለመቀዳጀት ጥንካሬን ሊሰጣቸው በተጨማሪ የንስሐ እድሜ በፊታቸው አስቀምጧልና ። በማናቸውም የሐጢአት ልምምድ ውስጥ ያለን ሰዎች በንስሃ ልንመለስ ያስፈልገናል ።

📝" በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው 1ዮሀ 1፡9

ኢየሱስ በንስሃ ለሚመለሱት ይቅር ባይ ነው ።
" ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።" 1 ቆሮ 6: 11

ማንም በኢየሱስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነውና
" ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።" 2 ቆሮ 5: 17

ወዳጄ ሁሉን የሚያስችለው ኢየሱስ አቅምህ ነው
" ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።" ፊል 4: 13

ኢየሱስ የምህረት የይቅርታ አምላክ ነው በንስሃ እንመለስ በወንድሞቻችን ላይ ጣት ከመጠቆሙ በዘለለ የፀሎታችን ርዕስ እንዳርጋቸው በጌታ ፊት ስለ እነርሱ እንውደቅ ጌታ የእኛን እንባ ተመልክቶ ታሪካቸውን ይለውጣለና ።


❤️❤️❤️በመጨረሻ .... ግብረ ሰዶማውያን ወንድሞቻችንን ሳንጠላ በፍቅር እየወደድናቸው ግብረ ሰዶምን ( ግብሩን ሐጢአቱን ) እየጠቃወምን እየተጸየፍን ወደ ስለ እነርሱም በቃተታችንን ሳንተው ፊት መዘርጋት መሮጥ ይሁንልን ። ❤️❤️❤️

በጌታ ወንድማችሁ ዘማሪ ሰለሞን አቡበከር ነኝ
የመፅሐፍ_ቅዱስ_ማጥኛ_እቅድ_bible_reading.pdf
182.9 KB
በ አንድ አመት ዉስጥ ሙሉ መፅሐፍ ቅዱስን 📖 አጥንተህ መጨረስ ትፈልጋለክ/ሽ?😱😱😱

👆👆👆👆 ይሄ pdf በ አሜዚንግ ፋክት ተዘጋጅቶ የቀረበ የተለየ የማጥኛ እቅድ ሲሆን:: በ አንድ አመት ውስጥ
ሙሉ መፅሐፍ ቅዱስን አንብቦ ለመጨረስ የሚረዳ የተለየ የማጥኛ እቅድ ነው::

📚 እያንዳንዱ ወር 25 የማጥኛ ቀናቶች አሉት:: ቀሪዎቹ 5 ቀናት ምናልባትም
የተዘለለ ቀን ካለ ወይም ለክለሳ እሚሆን ነው::

📝🔖 እያንዳንዱ ቀን ከ ብሉይ ኪዳን እና ከ አዲስ ኪዳን ሁለቱንም ያጠቃለለ ሲሆን
የመፅሐፍ ቅዱስ ውህደቱንም በሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል::

📌📌 የተቀደሰ ቃሉን በምትከፍቱበት ሰአት እግዚአብሄር አብሮአቹ ይሁን::
እንዲሁም ሁሌም ጥናታቹን ከመጀመራቹ በፊት መፅለይ አትርሱ!!🙏🙏🙏

ይሄ pdf የተዘጋጀው ከ JUNE - M A Y /ሰኔ-ግንቦት) ግን ከማንኛውም ወር መጀመር ይቻላል:: 📌📌
By : Aklil Tefera
#share

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌ባልሽ ወይም እጮኛሽ አንድ ነገር እንዲያደርግ ትፈልጊያለሽ እንግዲያውስ አንዴ ብቻ ሳይሆን ደጋግመሽ ጠይቂው

📌 በMark Gungor

#couples #married

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📌 ወሲብ የስጋ ፍላጎታችንን እና ስሜታችንን ብቻ የምናረካበት ጨዋታ አይደለም

📌 ወሲብ ያለምንም ስጋት ካፈቀርነው ሰው ጋር የምናደርገው የፍቅር መግለጫም አይደለም ፡፡

📌 ወሲብን ለመፈፀም ቅድመ ሁኔታው #መፋቀር_ሳይሆን_መጋባት_ነው ፡፡

ለሌሎች #ሼር ማድረግን አይርሱ 😊
#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
👉👉#ምክር_ለወጣት_ሴቶች👈👈

ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡
የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡
አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

👉አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ

👉ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!

👉ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"

ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡

የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር #በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡

በመጀመሪያ መንግስታችሁን (#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)

ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡

#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት

ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ እበረታቷቸው

ለሚመለከተው ሁሉ #ሼር ይደረግ

#General

👉@Appeal4purity👈
👉@Appeal4purity👈
ሰኔ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ያዘጋጀነው ኘሮግራም በፋና ቴልቪዥንና በፋና ሬዲዮ ተላልፏል።
በፋና ቴልቪዥን የተላለፈውን ኘሮግራም በዚህ ቻናል ይመልከቱ

መልካም ምሽት!

አብሮ መስራት ለምትፈልጉ
👉 📞 0962212861

👉  @eratchebecheba
😇 #ይራራልሃል !!🙏🙏

😔ቅዱስ የሆነው እግዚአብሄር እንዴት እንደኔ ያለውን ሃጢያተኛ ይቀበላል?

😕ትላንት ላለማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ቃል የገባሁትን ነገር ዛሬ ደግሜ አደረግኩት ታዲያ እንዴት ነው በፊቱ ልቀርብ የምችለው?

⛔️ እነዚህ ድምፆች ከሰይጣን ናቸው!!

🔵 መፅሀፍ ቅዱስ ሰይጣንን የውሸት አባት ይለዋል ፡፡

የሰይጣን ቁጥር አንድ ቅጥፈት ደግሞ እንዲህ የሚል ነው " አቤት😱 እንዳንተማ ያለ ሃጢያተኛ የለም ፡፡"

🗂 እንዲህ ብሎ ብቻም አያበቃም የክሰ ዶሴ ይዞ ያደረግካቸውን ነገሮች በፊትህ በመደርደር ይከስሃል ምክንያቱም እርሱ የወንድሞች ከሳሽ ነውና፡፡

👉 መፅሀፍ ቅዱስ ግን እግዚአብሄር ሃጢያትን እንጂ ሃጢያተኛውን እንደማይጠላ ነው የሚያስተምረው፡፡

እንደውም ስለ ሃጢያተኛ ሰው እንዲህ ነው የሚለው👇👇

(ዕብ 4 )
------------
15 ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም ፡፡

📌 አየህ እግዚአብሄር ይራራልሃል እንጂ አይጠላህም ወይም አይሰለችህም!!

📌 የእግዚአብሔር ርህራሄ ደግሞ እንደ ሰው ርህራሄ ከንፈር የመምጠጥን ያህል አይደለም፡፡

💢 እግዚአብሄር ራርቶልህ ብቻ ዝም አይልህም ፡፡ ከላይ ከተጠቀሰው ጥቅስ ቀጥሎ ያለው ጥቅስ ምን እንደሚል ታውቃለህ!? ይኸው 👇👇

📜" እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።"


😲 ዋው!! የሚያስፈልገንን ፀጋ እንዴት የሚደንቅ ነው!!

🙏 ከአንተ የሚጠበቀው በእምነት በእግዚአብሔር ፊት መንበርከክ ብቻ ነው!!

🤔 ከዛስ ?

👉 ከዛማ ታግለህ ማሸነፍ ያቃተህን ድካምህን ያሸንፍ ዘንድ የታመነውን ፀጋውን እግዚአብሄር ይሰጥሃል፡፡

#የሚደንቅ_ርህራሄ !!

👉ታዲያ የሰይጣንን የውሸት ክስ መስማት አቁምና ወደ እግዚአብሄር ፊት ቅረብ አይሰለችህምና!!

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
👁👁የሰውአይን 👁👁

መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር 1 ዮሐንስ 2 (1 John)
15-16፤ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።

🌟"የአይን አምሮት " ብዙ የመዝናኛ እና የporn ኢንዱስትሪ ዋነኛው የገቢ ምንጭ የሚያገኙት በዚህ ነገር ነው፡፡

በዚህ መንገድ ለአንድ ክርስቲያን ወገን ይቀርባሉ "እስኪ እየው " በማለት እንዲያይ ያደርጉታል ፡፡

🔶🔷ከዛ በኋላ ያለው ታሪክ እንግዲህ ይህ ነው 👇

🔑ጦርነቱ ያተኮረው በነብስ ለይ ሲሆን አይን ደግሞ ተግባሯን በመቀጠል ያለምንም ጥርጣሬ እና ያለምንም ገደብ በትኩረት መመልከትን ትጀምራለች፡፡

_📔መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር
ምሳሌ 27 (Proverbs)
20፤ ሲኦልና ጥፋት እንዳይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዓይን አይጠግብም።

👁የሰው አይን በሚያየው ነገር አይረካም(አይጠግብም );ለምን አሁንም ያያል

ከሚያየውም ነገር ደስታ ካላገኘ እና ሀሴትን የማያውቅ ይልቁንም እጅ መስጠት ፣ ተሰፋ መቁረጥ እና ጭንቀት የሚያስከትልበት ከሆነ ለምን ያያል

ይህ ከባድ ጥያቄ ነው ?
አይደለም !!

ምሳሌ 16 (Proverbs)
32፤ ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል።

💯 ሠው በመንፈስ ሲመራ አይኑን ይመራል ደግሞም ማየት የሌለበትን አያይም .........

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Forwarded from Sexual purity
😇 ሻሎም የ @Appeal4purity ቤተሰቦች

👉 ከዛሬ ማታ 3:00 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ስለ #ፍቅር እንማራለን

ትምህርቱ በዋናነት የተዘጋጀው ለባለትዳሮችና ለእጮኛሞች ቢሆንም ለሁሉም ጠቃሚ በመሆኑ #ሼር በማድረግ ወዳጅዎን_ይጋብዙ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
1⃣ ፍቅር ይታገሳል

👉 በጋብቻ ህይወት ብዙ ግጭት አለ ፡፡

🗝 በመካከላቸው ፍቅር ካለ ግን አንደኛው በንዴት ገንፍሎ "ያዙኝ ልቀቁኝ " ሲል ሌላው ይታገሳል ፡፡

💯 እንዳመጣጡ ክፉ በመመለስ ፈንታ ደግ ይመልሳል፡፡

👉 መረሳት እና መገፋት ከሚወደው ሰው ሲደርስበት በትዕግስት የሌላውን መሻሻል ይጠብቃል፡፡

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
2⃣ ፍቅር ደግ ነው

💯 ፍቅር ደግ ነው፤ ክፉ ሲዋልበት እንኳን የፍቅር ሰው ደግ ይመልሳል፡፡

👉 ርህራሄና በጎነትን ለማሳየት የሚያጋጥመውን ዕድል ሁሉ ይጠቀማል፡፡

🗝 ደግነትን የሚያሳየው ደግ ሲደረግለት ብቻ ሳይሆን ክፋት ሲደረግበትም ነው፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
record20190725082535.3gpp
12.9 MB
Virginity vs sexual purity
By Doctor Meskerem T . Kifetew
#Single
@Appeal4purity
3⃣ፍቅር አይመቀኝም

👉 የሌላው መሻሻልና ማደግ ደስ ይለዋል እንጂ ቅር አያሰኘውም ፡፡

👉 መመቅኘት ከሚፎካከሩና ከሚወዳደሩ ሰዎች መካከል የሚመጣ እነጂ በሚፋቀሩ ሰዎች መካከል አይደለም፡፡

በጣም የሚገርመው ደግሞ ሁለት ሰዎች እርስበእርስ ሲመቀኛኙ ሁለቱም በዚያ በተመቀኙበት ነገር ማደግ አለመቻላቸው ነው፡፡

🗝 ለአንድ ሰው በህይወቱ ለማደግ የሌላው ሰው ማሽቆልቆል ምን አስተዋጽኦ አይኖረውም ፡፡

👌 ይልቁንም ምቀኝነት በማስወገድና እርስበእርስ በመደጋገፍ ወደ ተፈለገው እድገት መድረስ እውነተኛ ፍቅርንም መለማመድ ይቻላል ፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
4⃣ ፍቅር አይታበይም

ፍቅር መታየትንና መታበይን ይጠላል፡፡

💯 በፍቅር የተሞላ ባል የሚስቱን ድካም አጋኖ ለማሳየት የራሱን ብርታታት አያወራም ፡፡

🚫 ስትሳሳት አይቶ "ይህን ስህተት እኔ ስሰራ አይተሽኝ አታውቂም" በማለት ሚስቱን ዝቅ አድርጎ ለማሳየት የሚሞክር ባል እውነተኛ ፍቅር የሌለው ሰው ነው፡፡

👉 ሚስትም ባሏን እንዲሁ የምታደርገው ከሆነ ፍቅር በእርሷ ዘንድ የለም ማለት
ነው፡፡

❤️ ፍቅር ማለት ሌላውን ከራስ አሳንሶ አለማየት ነው፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🌱🌱እነሆ ሐምሌ 22 ደረሰ

♻️ አዎ ለራሳችን ጥቅም የምንረባረብበት ቀን #ደረሰ‼️

አሻራዎን ለማሳረፍ ተዘጋጅተዋል⁉️

🌴 ለወለዷቸውና ወደፊት ለሚወልዷቸው ልጆችዎም ለምለምና አረንጓዴ ኢትዮጵያን ያውርሱ

ለበጎ ነገር መተባበር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡

💪 እኔ የዚህ ታሪክ ተጋሪ እሆናለው 💯
እርሶስ

#Share #ሼር

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
5⃣ ፍቅር አይኮራም

🛑 ኩራት ውስጣዊ ትዕቢት ነው ፡፡

⛔️ የትዕቢተኛ ሰው ትምክህቱ ባለው ነገር ላይ ብቻ ሳይሆን በሌለውም ነገር ላይ ነው ፡፡

ኩራት በሚዋደዱ ሁለት ሰዎች መካከል መጣጣምን የሚያሳጣ ነው ፡፡

👉 የራሱን የቅድስና ህይወት የሚያወራ ሰው ጓደኛው የማነስ ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል ፡፡

♻️ ይህ ደግሞ ፍቅርን ከሚያውቅ አንድ ክርስቲያን ሰው አይጠበቅም ፡፡


ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Purity Tube pinned a photo
6⃣ፍቅር ሥርዐተ ቢስ አይደለም፡፡

👉በፍቅር የሚመላለስ ሰው እርምጃው ከሥርዓት የወጣ አይደለም ፡፡

💢 በተለይ በሕዝብ መካከል በሚስታቸው (በባላቸው) ድካም የሚቀልዱ ሰዎች ራሳቸውን በሌሎች ዘንድ የተሻሉ እንደሆኑ ለማሳየት እንጂ ያ ሰው ድካሙን እንዲያስተካክል አይደለም ፡፡

🗝 ፍቅር ደግሞ በባህሪው ዝቅ ማለትን እንጂ ራስን መኮፈስን በፍፁም አያሳይም።

🗝 በተጨማሪም የፍቅር ሰው የትዳር አጋሩን በጓዳ በንግግር አሳምኖ ድካሙንም አበርትቶ በሰው ፊት ያሞግሳል እንጂ አይሳለቅም ፡፡

ምንጭ ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ | ጋብቻ እስከ ሞት ወይንስ እስከ መፋታት

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
2025/07/08 20:33:07
Back to Top
HTML Embed Code: