Telegram Web Link
📘69:19 - መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡

69:20 - «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡

69:21 - እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡

69:22 - በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡

69:23 - ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡

69:24 - በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡

መፅሐፋቸው በቀኛቸው ከሚቀበሉት ዉስጥ አድርገን ያረብ 🤲
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📙69:25 - መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡

69:26 - «ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡

69:27 - «እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡

69:28 - «ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡

69:29 - «ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡

እዚ ምድር ላይ ምንሰራው ምንናገረው ምንፅፈዉን ሁሉ ነገ በእጃችን ይዘን እናነበዋለን የመፃፉ ደራሲ እኛው ነን ድርሰታችንን እናሳምር!
እባካችሁ share አድርጉት!

እኔን አስታምማለሁ ብላ አትሂጂ እያልኳት አረብ ሀገር ተደብቃኝ ሄዳ ተመልሳ መጣች ከመጣች በኋላም እንዲህ ሆነችብኝ ልጄ እንዲህ ሆና ከማያት እኔ በሞትኩላት በአይኔ ባላየኋት እያሉም ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ነው።

እህታችን ዘይቱን ሂያር ትባላለች ምትወደውን ትምህርቷን አቋርጣ ቤተሰቦቼን እረዳለሁ አባቴን አስታምማለሁ ብላ ወደ ሳውድ አረቢያ ሄዳ ለአራት አመታት ከሰራች በኋላ ወደናፈቋት ቤተሰቦቿ ለመጠየቅ ተመልሳ መጣች አመጣጧም ተመልሳ ለመሄድ ነበር እነሆ የፈጣሪ ፍቃድ ሆኖ ተመልሳ በመጣች በሁለተኛ ወሯ ድንገት ወደቀች በሶስተኛ ቀኗም ግራ እግሯ በጠና ታመመች እያለ እያለም ከወገብ በታች ሙሉ በሙሉ ፓራላይዝድ ሆነች።

በአሁን ሰአት ሽንቷንም መቆጣጠር አትችልም የተሻለ ህክምና ካገኘሁ እድናለሁ የሚል ተስፋ አለኝ እህት ወንድሞቼ ስለፈጣሪ ብላችሁ እባካችሁ ያላችሁን እርዱኝ ትለናለች እህታችን ዘይቱን ሂያር።

አላህ አፊያዋን ይመልስላት።
እሷን ቀጥታ ማግኘት ምትፈልጉ
ስልክ 09-63-05-65-31

CBE Bank/1000345183918 minsure Hiyar

ፈጣሪ መልካም ምንዳቹን ይመንዳችሁ

እባካችሁ ውድ ጓደኞቼ ሼር በማድረግ የቻልነውን የአቅማችንን በመርዳት እናግዛቸው"
"ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው" ስንል ዕውር ድንብ ጸለምተኛ ሙግት ይዘን ሳይሆን ጠቅሰንና አጣቅሰን በመሞገትና በመሟገት ነው። እስቲ ፍትሓዊነቱን በዚህ ደርስ እዩት! ይህንን ብርሃን ተመልክታችሁ ለሌላ እንዲመለከት ማድረግ ትልቅ እድል ነው።
Abdallah Omari ዛሬ የ23ተኛ ዓመት ልደቱ ነበር እሱ ግን ያለው ቀብር ዉስጥ ነው😥😥 አላህ ይዘንለት ቀብሩን የጀነት ጨፌ ያድርግለት!
ሁላችንም ቅርብ ወራጅ ነን ያለችንን ግዜ በአግባቡ እንጠቀምባት:: ሞት የማይቀር ቀጠሮዋችን ነው የግዜ ጉዳይ እንጂ ሁላችንም ተጓዥ ነን ተጓዥ ደሞ ስንቅ ያስፈልገዋል ከሞት ቡሃላ ለሚጠብቀን ረጅም ጉዞ ስንቅ እንያዝ ስንቃችን መልካም ስራችን ነው:: አላህ ባዘዘን ነገር ላይ ቀጥ ብሎ መታዘዝ ከከለከለን ነገር መከልከል ያቅማችንን ያክል የትንሳዬ ግዜ ሀብትም ልጅም አይጠቅምም ንፁ ልብ እንጂ ❤️

26:88-89
يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ

ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡
إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»
31:33

يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ وَاخْشَوْا يَوْمًا لَّا يَجْزِي وَالِدٌ عَن وَلَدِهِ وَلَا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَن وَالِدِهِ شَيْئًا ۚ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ ۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِاللَّهِ الْغَرُورُ

እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ወላጅም ከልጁ (በምንም) የማይጠቅምበትን፤ ተወላጅም እርሱ ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት አትሸንግላችሁ፡፡ በአላህም (መታገስ) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ፡፡
39:30

إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ

አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው፡፡
ሰዎች ሆይ!
የተባረከ ታላቅ ወር ረመዳን መጥቶላችኋል ይሉ ነበር የ አላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
2:83

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡

@Astentn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2:185 - (እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡
@Astentn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/05/27 19:10:04
Back to Top
HTML Embed Code: