የትኛውም ሀይማኖት በሌላ ሀዘን መሳቅን አልመከረንም:: ማስትዋል የብርሀን ሁሉ ብርሀን ነው:: ከተማረ ብልጥ: ያስተዋለ መሀይም ንፁህ እውነት አለው : ምክሩም መድሀኒት የሆነ:: እንደኖርነው የሺህ ዘመናት ርቀት ከሆነ ይህ ባልተነገረን ነበር:: ነገር ግን ልብ ሲጠም ከዘመን ይርቃልና ቃሉን ከልባችን አጣነው:: ልብ እንበል:: ለራሱ ከሚያለቅስ ይልቅ ለሌላ የሚያዝን ለአምላኩ ቅርብ ነው:: ባለሀገርነትም ሩቅ ላልነው የሀገርሠው መኖር ማሰብ: ከራስ እልህ የሌላን ሠው ሀዘን ማስቀደም ነው:: የጎረቤት አባት ሚፈራበት ሚከበርበት ሰፈር ልጅ ሁሉ ጨዋ ነው:: አንዱ የሌላውን እንደራስ ስለሚያይ ስለሚጠብቅ:: የእናቶች እንባ ሚቆመው ሳይረፍድብን ያዘነ እኩያችንን ብንችል በፍቅር ባንችል ክፉ ባለመናገር ስናፅናና: ሀዘኑ እንዲሰማን ስንፈቅድ: ከአፍ በፊት ልብን ስንከፍት ብቻ ነው:: ያዘነ ልብ ለአምላክ ቅርብ ነው:: የእናት እንባ አይብዛብን ግድየለም:: ዛፍ በመሬት ምህረት እንደቆመ እኛም በፈጠረን ላይ ነን:: በምህረቱ ቆምን ብለን መልሰን ፈራጅ መሆን ለነገ ያጨልማል:: እናስተውል:: ለፍቅር ቦታ ከሌለን ከበር............::
.
.
.
Picture by IG-inas_hailuu aka Rinas.
.
.
.
Picture by IG-inas_hailuu aka Rinas.