❖ መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው፤ የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖✔💥 በ290 ዓ.ም. በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ስላረፈችው ስለ ቅድስት አርሴማ በአርሜንያ Հռիփսիմէ
ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በስሟ በተሰየመው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች ካለ ካታኮምብ ግበበ ምድር በአርመንያ አለ፡፡
❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ፤ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ መካነ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፨
❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨

❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል።
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከ37 አልፋ 73 መጽሐፍ የተወሰደ
✍️ በዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 በግእዝ ቀመረ ፊደል ዙሪያ በቀደሙ ሊቃውንተ ኢትዮጵያ የተጻፉ እንደ "ህላዌ ዘአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ኆኅተ አእምሮ ዘሔኖክ፤ ህላዌ መለኮት፣ መጽሔተ መንፈስ ቅዱስ ..." የመሳሰሉና ሌሎችም በርካታ የግእዝ የፊደል ቀመር መጻሕፍት እና ጸሎታት ይገኛሉ፡፡
ፊደላቱን ወደ ቀመረ ግእዝ ስንለውጥ የሚመጡልን ቀመራት አስደናቂ ናቸው፡፡ ይልቁኑ በነዚኽ መጻሕፍት ውስጥ እንደምንረዳው ፊደላቱ በሙሉ “መለኮታዊ ስሞች” Divine Names የያዙ ናቸው፡፡
በመኾኑም በነዚኽ ፊደላት የተዋቀሩ የተቀደሱ ቃላት ታላቁን የእግዚአብሔርን ስሞች የያዙ ናቸውና በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረ የሰውን አእምሮ፤ በዕውቀት ብርሃን የሚያበሩ፣ ልቡናን የሚያነቁ፣ የማስተዋል ደጅን የሚከፍቱ በከፍታ ያሉ ረቂቅ ዕውቀቶችን ከአልፋ የሚያሰጡ ተብለው በሊቃውንት ይታመንባቸዋል።
ለምሳሌ ያኽል “ኆኅተ አእምሮ ዘሔኖክ” (የሔኖክ የአእምሮ ደጃፍ) የተባለው የግእዝ መጽሐፍ ሲዠምር፡- “በስመ አብ ወወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ኆኅተ አእምሮ በጸፍጸፈ ሰማይ ጽሑፍ፤ ዝንቱ ፊደል ዘአለበዎ ለሔኖክ፤ ወከብደ እንግድዓሁ ወልቡናሁ፤ ወርእየ ኀዋኅወ ሰማይ …” (በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ በሰማይ ሰሌዳ የተጻፈ የዕውቀት በር፡፡ ይኽ ፊደል ሔኖክን የሚያስተውል ያደረገው ነው፡፡ አእምሮውና ልቡናው ከበረ (በረታ) የሰማይ ደጃፍ ተከፍቶ አየ …) በማለት በፊደል [አ] [በ] [ገ] [ደ] … የሚዠምር ሲኾን የእነዚኽን የፊደላትን ዕውቀት አካኼዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው ሔኖክ እንደተረዳው ይገልጣል፡፡
“መጽሔተ መንፈስ ቅዱስ” የተባለው የቀመረ ፊደል የግእዝ መጽሐፍ ይኽነን የፊደል ቀመር ማወቅ ወደ ከፍተኛ የአእምሮ ልዕልና ስለማድረሱና ለእግዚአብሔር የቀረቡ ቀደምት ነቢያት ኹሉ ጠንቅቀው ይኽን ያውቁ እንደነበር ሲገልጽ፡- ....
በሚያልፍ ጊዜዎ የማያልፍ ዕውቀትን ቀድመው ያግኙ መጽሐፉን በሀሁ የመጻሕፍት መደብር 0911006705
ወይም በአማዞን 37 Alpha 73 (Amharic Edition) https://a.co/d/hzWq57M
ገዝተው ያንብቡ

[ታኅሣሥ 8 በዓሏ የሚከበረው ቃል ኪዳኗ ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ድንቅ ታሪኳ፤ በቀደምት ኢትዮጵያውያን የቀረበላት ውዳሴና ዓለም ዐቀፍ ክብሯ]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥❖♥ ከክርስቶስ የተቀበለችው ቃል ኪዳን ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው በመላው ዓለም ከጥንት ጀምሮ የምትታወቀው ከ273-306 ዓ.ም የነበረችው ሰማዕቷ ቅድስት በርባራ በሌሎች ሃገራት Αγία Βαρβάρα, Great Martyr Barbara በመባል ትታወቃለች።
💥 ከ305-311 በነገሠው በከሓዲው መክስምያኖስ (emperor Maximian) ዘመነ መንግሥት መስፍን የነበረው የዲዮስቆሮስ ልጅ ናት። እጅግ ውብ ስለነበረች ሰው እንዳያያት ጣዖት አምላኪ የነበረ አባቷ ለርሷም ለብቻዋ ሰገነት ያለው ማረፊያ ታላቅ ሕንፃ አሠርቶላት አንድ አረማዊ መምህር ብቻ ወደርሷ እንዲገባ አደረገ።
♥❖♥ ያሠራላት ሰገነት ከፍ ያለ ስለነበር አበባዎችን ይልቁኑ በምሽት የሚያበሩትን ከዋክብት የምሽቱ አስደናቂ ግርማ እየተመለከተች መደነቅ ጀመረች። በዚህ ጊዜ እነዚህ የአባቷ ጣዖታት አስደናቂ ዓለማትን እንደማይፈጥሩ ተረዳች። በሕይወቷ የዓለማት ፈጣሪን ለማወቅና በድንግልና ሕይወት ለመኖር ወሰነች። ብዙ የጋብቻ ጥያቄን ውድቅ አደረገች። በዚህ ምክንያት አባቷ ውጪውን እንድትለምደው ከግቢ እንድትወጣ ፈቀደላት።
♥❖♥ በዚህ ጊዜ ከክርስቲያን ሴቶች ጋር በመገናኘቷ ስለ ምስጢረ ሥላሴ፣ የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢርን አስረዷት። እውነተኛውን የድኅነት መንገድ በመረዳቷ ከእስክንድር ወደ ሄሊዎፓሊስ መጥቶ በነበረ ካህን በድብቅ ተጠመቀች።
♥❖♥ በዚያ ወቅት አባቷ በመታጠቢያ ክፍሏ ላይ ደግሞ ኹለት መስኮቶችና ቅንጡ የሆነ መታጠቢያ እንዲሠሩላት ዐናጺዎችን አዘዘ፤ ርሷ ግን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመኗና በመጠመቋ ምስጢረ ሥላሴን አስባ ሦስተኛ መስኮትን እንዲጨምሩ ዳግመኛም አዳኝ የኾውን የመስቀሉን ምልክት በውሃ መታጠቢያው ላይ እንዲሠሩ ሐናጺዎችን አዘዘቻቸው፡፡
♥❖♥ አባቷም ወደዚኽ ሕንጻ በገባ ጊዜ ልጁ ያሠራችውን አይቶ ዐናጺዎችን ሲጠይቃቸው፤ ይኽነን እንዲሠሩ ያዘዘቻቸው ልጁ መኾኗን ነገሩትን ርሱም “ለምን እንደዚኽ አደረግሽ” ብሎ ጠየቃት፡፡ “ወትቤሎ አእምር ወለቡ ኦ አቡየ እስመ በሥሉስ ቅዱስ ይትፌጸም ኲሉ ግብር በእንተዝ አግበርኩ ሣልሲተ መስኮተ፤ ወዘንተኒ መስቀለ በአምሳለ ስቅለቱ ለመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ” ይላል ርሷም “አባቴ ሆይ አስተውል፤ ልዩ ሦስት በኾነ በሥላሴ ስም ሥራ ኹሉ ይፈጸማልና ስለዚኽ ሦስተኛ መስኮት አሠራኊ፤ ይኽም መስቀል ዓለሙ ኹሉ በርሱ በዳነበት በመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አምሳል ነው አንተም አባቴ ሆይ ከስሕተትኽ ተመልሰኽ የፈጠረኽን አምላክ አምልከው” በማለት ተናገረችው፡፡
♥❖♥ አባቷም ከርሷ ይኽነን በሰማ ጊዜ በንዴት ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ ሮጠ፤ ያን ጊዜ ሸሽታ በዐለት ውስጥ ገብታ ለጊዜው ብትሸሸግም በኋላ ግን ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ርሱም እንድትሠቃይ ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት፤ ርሱም እየገረፈ በጊዜው አሉ በተባሉ በታላላቅ ሥቃይን ቢያሠቃያትም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ግን አልካደችም፤ ከዚያም ብቻዋን ወደ ወህኒ ተጣለች፤ በዚያም ኾና “ጌታዬ አምላኬ ሆይ አትተወኝ” ብላ ጸለየች፤ በእኩለ ሌሊትም የእስር ቤቱን ደማቅ ብርሃን መላው፤ “ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ” የሚለውን የአምላክን ድምፅ ሰማች፤ ከዚያም ጌታችን ቊስሎቿን ኹሉ ፈወሰላት፡፡
♥❖♥ በነጋታው ቅድስት በርባራን በማርቲያኑስ ፊት አቆሟት፤ ኹሉም ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደዳነችና ፊቷም እንደ ፀሓይ ጨረር ሲያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ መኰንኑም “አማልክቶቻችን ስለፈወሱሽ የምስጋና መሥዋዕትን ሠዊ” አላት፤ ቅድስት በርባራም ለአገረ ገዢው “በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የዳንኩት” አለችው፡፡ ማርቲያኑስም በቊጣ ኾኖ በአስከፊ ኹኔታ ቅድስት በርባራ እንድትሠቃይ አዘዘ፤ በዙሩያዋ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሕዝቦች ርሷን ለመከላከል ምንም ቃል አልወጣቸውም፡፡
♥❖♥ በዚያም የሂሊኦፓሊስ ነዋሪ ዮልያና የምትባል ሴት ነበረችና ቅድስት በርባራን ሲያሰቃይዋት አይታ ከርሷ ጋር በክርስቶስ ስም መከራን ለመቀበል በመወሰን አብራት መከራ መቀበል ጀመረች። ሁለቱም ሰማዕታትን በምስማር ሰውነታቸውን እየወጉ ያሰቃይዋቸው ነበር። ለመዘባበት ዕርቃናቸውን በአደባባይ ሊወስዷቸው ቢሞክሩም በቅድስት በርባራ ጸሎት ጌታ መልአኩን ልኮ በአስደናቂ መጎናጸፊያ ሰውነታቸውን ጋርዶታል።
♥❖♥በመጨረሻም ጨካኙ መኰንን ብዙ ዐይነት ሥቃይ ቢደርስባቸው እነዚኽ ቅዱሳት አንስት በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንደማይለውጡ ባየ ጊዜ አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘ።
♥❖♥ ከወታደሮቹ መኻከል አንዱ አንገታቸው ለመቊረጥ ሰይፉን መዘዘ፤ በአባቷ ወደተዘጋጀው ወደመግደያው ስፍራ ይዟቸው ኼደ፤ ያን ጊዜ ቅድስት በርባራ እንዲኽ ብላ ጸለየች “ዘላለማዊ እግዚአብሔር ሆይ ከእኔ ሞት በኋላ እኔንና መከራዬን ለሚያስቡ ኹሉ ሥጦታኽን ስጣቸው፤ ድንገተኛ ሕመምና ብርቱ (አስጨናቂ) ሞትን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ አታምጣባቸው” አለች፡፡
♥❖♥ ከዚያም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መሻቷን ኹሉ እንደሚፈጽምላት ቃል ኪዳን ሲገባላት በሰጣት ቃል ኪዳን የሚታመኑ ኹሉ ድንገተኛ ሞት እንደማያገኛቸው ቃል ኪዳን ገባላት።
♥❖♥ በመጨረሻም አባቷ የርሷንና የባልንጀራዋ የዮልያና አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘና ታኅሣሥ 8, በ306 ዓ.ም. አንገታቸው ተቈርጦ የሰማዕትነት አክሊል ሲቀዳጁ፤ ቅድስት ዮልያናንም በኹለት ጡቶቿ በኩላብ ሰቅለው ሰይፈዋታል፡፡ በዚያን ጊዜ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የኾነ መኰንን መርትያኖስን አቃጠላቸው፤ ከዚኽ የተነሣ በዓለም ባለው ሥዕሏ ላይ የመብረቅ ብልጭታ ይሣላል፡፡ ቅድስት በርባራም በዚህ ምክንያት በአማላጅነቷ ከጥንት ጀምሮ ባሉት ክርስቲያኖች ከመብረቅ አደጋና ከእሳት የምትጠብቅ እንደሆነች ይነገራል።
♥❖♥ ያም በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በመስቀል ምልክት ያሠራቸው መታጠቢያ ለታመመ ኹሉ ከርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን ኾነ፤ ከዚኽም በኋላ የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጪ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሯቸው፤ ይኽ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና በዮሐንስ በምስር አገር ባለ ቤተ ክርስቲያን ተቀመጠ፡፡
♥❖♥ ይኽነን ተጋድሎዋን ለማዘከር በመላው ዓለም በሚሣለው ሥዕሏ ላይ ሦስት መስኮት ያለው ሰገነት፣ ዘንባባ፣ ጽዋ፣ መብረቅ፣ የሰማዕትነት አክሊል ይዛ ይታያል፡፡ በዐዲስ አበባ በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ባሉት የግድግዳ ላይ ሥዕላት ላይ ቅድስት በርባራና ቅድስት ዮልያና ተሥለዋል። በዓለም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ የታነጹላት ሲኾን በሩሲያ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናት በስሟ ሲሠየሙላት አንደኛው በሞስኮ ከቅዱስ ባስልዮስ ካቴድራል አጠገብ ይገኛል::
♥❖♥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 8 በሚነበበው መዝገበ ቅዱሳን በሆነው ስንክሳር ላይ ቅድስት በርባራና ዮልያናን ታስባለች።
♥❖♥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅድስት በርባራን አመስግነው በቃኝ አይሉም ነበር፤ ለምሳሌ ያኽል ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ቅዱስ አርከ ሥሉስ እንዴት እንዳመሰገኗት ብናይ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምሆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡-

“ሰላም ለበርባራ ወዮልያና በፍኖተ ስምዕ እለ ቆማ፤
በድሮን እለ ፈጸማ
እለ ተጋደላ ከመ ሐራ
አርዑተ መስቀሉ ለክርስቶስ እለ ጾራ
መርዓዊሆን እስከ ረከባ
ድንግልናሆን እለ ዓቀባ”፡፡
(ሙሽራቸው ክርስቶስን እስኪያገኙ ድረስ ድንግልናቸውን የጠበቁ፤ የክርስቶስ መከራ መስቀሉን የተሸከሙ፤ እንደ ጭፍሮች የተጋደሉ፤ ሩጫቸውንም የፈጸሙ፤ በምስክርነት ጐዳና የቆሙ ለኾኑ ለበርባራና ለዮልያና ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል፡፡
♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ፡-
“ሰላም ለበርባራ እንተ አግሀደት ሃይማኖታ
እንዘ ታርኢ ሥላሴ በመስኮተ ቤታ
ኢያፍርሃ መጥባሕት ወሞሠርተ ሐጺን ኢያሕመመታ
ወሰላም ካዕበ ለዮልያና ካልዕታ
እንተ ሰቀልዋ በክልኤ አጥባታ”
(በቤቷ መስኮት የሥላሴን ምሳሌ እያሳየች ሃይማኖቷን የገለጠች ለኾነች ለበርባራ ሰላምታ ይገባል፤ ሰይፍም አላስፈራትም የብረት መጋዝም አላሳመመቻትም፤ ዳግመኛም በኹለት ጡቶቿ የሰቀሏት የርሷ ኹለተኛ ለምትኾን ለዮልያናም ሰላምታ ይገባል) በማለት የተቀበሉትን ጽኑ መከራ ጽፏል፡፡
♥❖♥ ቅድስት በርበራ እመቤታችንን ለምና የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁት ላይ ያደረገችውን የመስከረም 25 ተአምሯን ደግሞ፦
"ሰላም ለበርባራ ወለዮልያና አምሳላ
በዛቲ ዕለት ዘአስተርአየት ኀይላ
በክልኤ ዕደው ዘሰረቁ መጽሐፈ ገድላ
ፈደየቶ ለአሐዱ እንባዜ እምኀበ ማርያም ስኢላ
ወለዐይነ ቢጹ ካልዕ አጽለመት ጸዳላ"
(የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁ በሁለት ወንዶች ላይ በዚህ ዕለት ኃይሏን ያሳየች ለሆነች ለበርባራና ርሷን በተጋድሎ ለምትመስል ለዮልያና ሰላምታ ይገባል። ከእመቤታችን ማርያም ለምና ለአንዱ መቅበዝበዝ የሁለተኛው ጓደኛውን ዐይን ብርሃኑን አጨለመች) በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ ተመሳሳይ ተአምርን እንደሠራች ይጽፋል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስ በመስከረም 25 ስንክሳር አርኬ።
💥 ❖የቅድስት በርባራ ዐለም ዐቀፍ ክብሯ❖💥
♥❖♥ በእጅጉ የሚገርመው ከጥንት ጀምሮ በየክፍላተ ዘመናቱ እስከ ዛሬ ድረስ በበርካታ የዓለም ክፍሎች በቅድስት በርባራ ከሚፈነዱ የጦር መሣሪያዎች፤ ከመብረቅ አደጋና ከድንገተኛ ሞት በቃል ኪዳኗ እንደምትጠብቅ ሲታመን፤ በጣሊያን የባሕር ኀይላችን ጠባቂ (the patron of the Italian Navy.) ይሏታል።
♥❖♥ በቃል ኪዷና በእጅጉ ከመታመን የተነሣ በጊዜያችን ያሉ በርካቶች ኀያላን ሀገራት ብሪታኒያ (Royal Artillery, RAF Armoures, Royal Engineers) በካናዳ (Explosiv Ordance Technicaians) በአውስራሊያ (RNZAF Armourers) በኒውዝላንድ፤ በስፔን፣ በአሜሪካ፣ በግሪክ የቅድስት በርባራን በዓል በዐየር ኀይላቸው፣ በጦር ካምፓቸው፣ በባሕር ኀይላቸው ዲሴምበር 4 ላይ እንደሚያስቡ ጥናቶች በግልጽ ያሳያሉ::
♥❖♥ በስፓኒሽና በጣሊያን ይታተም የነበረው መጽሔት መርከበኞች ከድንገተኛ አደጋ መርከባቸው ይጠበቅ ዘንድ ሥዕሏን ይይዙ እንደነበር ይጽፋል።
♥❖♥ በሰሜን አሜሪካ የጦር ኃይልም ቅድስት በርባራ የምትታሰብ ሲሆን በጦር ኃይሉ ላይ ከፍተኛ ጀብዱ ለሠሩ ምርጥ ወታደሮች በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ የቅድስት በርባራ ሥዕል ያለበት ሜዳልያ (ANCIENT ORDER OF SAINT BARBARA) ይበረከትላቸዋል። (https://www.fieldartillery.org/awards)
💥 (United States Field Artillery Association, fieldartillery.org. retrieved 23 January 2010,) (Cyprus Army notes on Saint Barbara, Army)
♥❖♥ በሰሜን አሜሪካ ከሎስ አንጀለስ ሰሜን ምዕራብ 100 ማይልስ በሚገመት አግጣጫ ያለችው በቅድስተ በርባራ ስም ሳንታ ባርባራ Santa Barbara በመካከለኛው ካሊፎርንያ ከተማ ተሠይሞላታል፤ በተመሳሳይ መልኩ በስፔንና ፖርቱጋል ቦታ ላይ በብራዚል፣ በቺሊ፣ በኮሎምቢያ፣ በሆንዱራስ፣ በሜክሲኮ፣ በቬንዝዌላ፣ በፊሊፒንስ በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ አለ። በሊባኖስ ክርስቲያኖችም በጣም ትታሰባለች (Hammond Atlas of the World.1997.)፡፡
♥❖♥ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ ሊቁ አርከ ሥሉስ ያወደሷት፤ ክብሯ በስንክሳር ላይ የተጻፈላት በርካቶች ቃል ኪዳናትን የተቀበለች ቃል ኪዳኗም ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ጥንታዊ ሥዕላት በብራና ላይ እንዳሉ ባውቅም በስሟ የተሰየመ ታቦት እንዳለ ግን ጥናቱ የለኝም።
💥 እኔ ከክብሯ በዐጭሩ በረከቷን ለመሳተፍ ያህል እንደጻፍኩ እናንተም ታኅሣሥ 8 በስሟ ለነዳያን በመመጽወት በቃል ኪዳኗ በመማጸን በረከቷን ተሳተፉ።
💥 ቅዱስ ጳውሎስ “ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።”
— (ሮሜ 13፥7) እንዳለ
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ ፓስት ያደረኩት)

♦️እነሆ መልካም እራት በሥላሴ እጅ ♦️ This Evening is nice With Holy Trinity♦️
https://youtube.com/live/TJUc-WCxWsI?si=DvrPjGyCG9lgbx0S

Youtube
- YouTube
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
12/24/24
,
In biblical and spiritual numerology, the date 12/24/2024 carries profound symbolism when broken down, especially considering its connections to key biblical numbers:
1. Month: 12
The number 12 in the Bible signifies divine governance, order, and completeness.
12 tribes of Israel symbolize God's chosen people.
12 apostles reflect the foundation of the Church.
12 gates of the New Jerusalem indicate God's eternal kingdom (Revelation 21:12).
In this context, 12/24 could represent the alignment of heavenly order and earthly events.
2. Day: 24
The number 24 is associated with priestly service and heavenly worship.
In Revelation 4:4, 24 elders surround God’s throne, representing divine worship and authority.
It reflects God's perfect leadership and unbroken connection with His people.
3. Year: 2024
Breaking the year down:
2024 = 2 + 0 + 2 + 4 = 8
The number 8 symbolizes new beginnings, resurrection, and eternal life.
Jesus rose on the 8th day (the first day after the Sabbath), marking the dawn of a new creation.
Circumcision, a sign of covenant with God, occurs on the 8th day (Genesis 17:12).
Thus, 2024 could signify a time of spiritual renewal and covenantal restoration.
4. Total Date: 12/24/2024
Adding the numbers: 12 + 24 + 2024 = 2060 → 2 + 0 + 6 + 0 = 8
Once again, the number 8 emerges, emphasizing renewal, rebirth, and eternal life.
This ties beautifully to Christmas Eve, symbolizing the imminent birth of Christ, the bringer of new life and salvation.
Spiritual Meaning
Harmony of Heaven and Earth:
The combination of 12 (heavenly order) and 24 (priestly worship) reveals the interconnectedness of God's divine plan for creation.
The overarching presence of the number 8 emphasizes that this date resonates with Christ's role as the light of the world, offering renewal, hope, and eternal life.
As this day precedes Christmas, it symbolizes the anticipation of God's promise being fulfilled through Jesus, connecting deeply with themes of hope, joy, and divine grace.
In conclusion, 12/24/2024 in biblical numerology represents a spiritually significant moment, highlighting the harmony of God's divine order, the fulfillment of His promises, and the renewal of life through Christ.

The list of books published by Dr. Rodas Tadese:
1. The Symbol of Mary in the Old Testament, Volume 1 (Amharic)
2. The Symbol of Mary in the Old Testament, Volume 2 (Amharic)
3. Mariology in the New Testament, Volume 1 (Amharic)
4. Mariological Thoughts of the Early Church Fathers (1st to 4th Century) (Amharic)
5. Mariological Thoughts of the Early Church Fathers (4th to 9th Century) (Amharic)
6. Christology, Volume 1 (Amharic)
7. Alpha and Omega (Amharic)
8. The Commentary on the Effigy of Mary (Amharic)
9. The Commentary on the Effigy of Mary, Second and Third Volumes (Amharic)
10. The Commentary on the Effigy of Jesus (Amharic)
11. The Commentary on the Effigy of the Trinity (Amharic)
12. The Commentary on the Effigy of the Passion of Christ (Amharic)
13. The Commentary on the Book of Hours (Amharic)
14. The Commentary on the Salutation of Saints (Amharic)
15. The Commentary on the Anaphora of Mary (Meaza Qeddase) (Amharic)
16. The Commentary on the Salutation of Mary (Amharic)
17. The Book of Fisalogos (Amharic)
18. The Philosophy of Hikar and the Revelation of Sabela (Amharic)
19. The Nativity of Jesus by Jacob of Serugh (Amharic)
20. The Perpetual Virginity of Mary and On the Mother of God by Jacob of Serugh (Amharic)
21. Bible and Medical Science (Amharic)
22. Andromeda 1 by Rodas Tadese and Getinet Feleke (Amharic)
23. Andromeda 2 by Rodas Tadese and Getinet Feleke (Amharic)
24. The Ethiopian Calendar by Rodas Tadese and Getinet Feleke (Amharic)
25. Mazzaroth (Amharic)
26. 888 (Amharic)
27. 37 Alpha 73 (Amharic)
28. The Sun of Righteousness (English)

[የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል የታኅሣሥ ክብረ በዓል]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቅዱስ ገብርኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን፤ የሚኖርበት ሰማይም ራማ ነው። አርባብ በተባለ ነገድ ላይ የተሾመ በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም ብርሃናዊ መልአክ ነው (ሉቃ 1:19)።
💥 በግእዝ ገብርኤል፤ በዕብራይስጥ גַּבְרִיאֵל በአረማይክ ܓ݁ܰܒ݂ܪܺܝܐܝܶܠ, በቅብጥ Ⲅⲁⲃⲣⲓⲏⲗ ሲባል ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ኃይሌ ነው" ማለት ነው።
💥 ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክን ሰው መኾን ደስ ብሎት ያበሠራት መልአክ ስለኾነ ከግብሩ (ከሥራው) የተነሣ
✍️ "መጋቤ ሐዲስ፣
✍️ ጸዋሬ ዜና ወምክር፣
✍️ መልአከ ፍሥሐ፣
✍️ እግዚእ ወገብር" በመባል ይታወቃል፡፡
💥 ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፦
"ጸዋሬ ዜና ወምክር ገብርኤል
ክቡር ምጽአቶ ለቃል ዜነዋ ለድንግል"
(የብሥራት ዜናና ምክርን የሚሸከም ገብርኤል የክቡር የባሕርይ አምላክ የአካላዊ ቃል አመጣጥን ለድንግል ነገራት) ይላል።
💥 የመልክአ ገብርኤል ደራሲም፦
"ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢየተረጎም ምስጢር
ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር"
(የማይተረጎም ምስጢር አባባሉ ፍቺው ጌታም አገልጋይም የሚመስል ለኾነ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል።
💥 የታኅሣሥ 19 ክብረ በዓሉን ስናስብ ነቢዩ ዳንኤል ለንጉሡ ለናቡከደነጾር ሕልሙን ከተረጐመለት በኋላ ዳንኤልንና ሠለስቱ ደቂቅን በባቢሎን አውራጃ ላይ ከፍተኛ ሹመትን በየደረጃቸው ሹሟቸዋል (ዳን ፪፥፵፰‐፵፱)፡፡
💥 ኾኖም ግን ናቡከደነጾር ቁመቱ ስሳ ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ የኾነውን የወርቁን ምስል አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ በማቆም ኹሉም ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰብስበው ሳሉ፤ ዐዋጅ ነጋሪው የዘፈን ድምፅ ሕዝቡ ሲሰሙ ንጉሡ ላቆመው ምስል ተደፍተው እንዲሰግዱ ትእዛዝን የማይቀበሉ ግን በሚነድደው እሳት እቶን እንደሚጣሉ ሲናገር ሕዝቡም አሕዛቡም ለምስሉ ይሰግዱ ይረበረቡ ዠመር (ዳን ፫፥፩‐፯)፡፡
💥 ሦስቱ ሕፃናት አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ግን አንሰግድም በማለታቸው “እሉ እደው ዘሤምኮሙ ለግብረ በሐውርተ ባቢሎን አበዩ ሰጊደ ለምስል ዘወርቅ ዘገበርከ” በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምካቸው እነዚኽ ሰዎች ወንዶች ላቆምኸው ምስል አይሰግዱም በማለት ነገሩት።
💥 ናቡከደነጾርም በብስጭትና በቊጣ እንዲመጡ በማዘዙ፤ መጥተው ከፊቱ ሲቆሙ “ላቆምኹት ለወርቁ ምስል አለመስገዳችኊ እውነት ነውን? ባትሰግዱ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችኊ፤ ከእጄስ የሚያድናችኊ አምላክ ማን ነው?” በማለት ሲናገራቸው የሚያመልኩት አምላክ ከሚነድደው እሳት ሊያድናቸው እንደሚችል ገለጹለት።
💥 ርሱም በቊጣ የእቶኑ እሳት ከሚነደው ይልቅ ሰባት እጥፍ ማለት 49 ክንድ አድርገው እንዲያነዱ በማዘዝ አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል፣ ታሥረው እንዲጣሉ በሰራዊቱ ውስጥ ላሉት ኀያላን መመሪያ ስላስተላለፈ፤ ወርዋሪዎቹም ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸው ጋር በእሳቱ ላይ ሲጥሏቸው ከወላፈኑ ከፍተኛነት የተነሣ ወታደሮቹ ተቃጥለዋል (ዳን ፫፥፲፫‐፳፫)፡፡
💥 ያን ጊዜ “ወወረደ መልአከ እግዚአብሔር ወዘበጦ ለነበልባለ እሳት ወረሰዮ ከመ ነፋስ ቆሪር ዘጊዜ ጽባሕ” ይላል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ በበትረ ብርሃን ቢመታው እንዳረረ ውርጭ ኾኗል፤ ያን ጊዜ ወአንሰሶሰዉ ማእከለ እሳት ወአእኰቱ እግዚአብሔርሀ ወባረክዎ ይላል በእሳቱ ጒድጓድ መኻከልም በመመላለስ እግዚአብሔርንም ፈጽመው አመስግነውታል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፩)፡፡
💥 ይኽም ከእሳቱ መኻከል ሳሉ የተገለጸላቸው አስደናቂ ምስጋና ልዩ የኾነ የነገረ ሥጋዌ ምስጢርን የያዘ እንደኾነ የነገረ ነቢያት ሊቃውንት አስተምረዋል፤ ይኸውም 49 ክንድ ወደ ላይ በወጣው በእሳቱ መኻከል ኹነው ለስድስት ጊዜ ብቻ፦
✍ “ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”
★ (የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፤ የተመሰገነ ነው፤ ለዘለዓለሙም የከበረ ነው) በማለት አመሰገኑ (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፳፯‐፴፪)።
♥♥♥ 49 ክንድ ወደ ላይ የወጣው እሳት እና እሳት ውስጥ ኾነው 6 ጊዜ "ይትባረክ" (ይመስገን) ያሉት ቢደመር 55 ይኾናል (49+6=55)፤ ይኽም የ5500 ዘመን ምሳሌ ነው፤ ይኽም 5500 ዘመን ተፈጽሞ በ6ኛው ሺሕ አምላክ ሰው ኾኖ ከሲኦል እሳት ነፍሳትን ነጻ እንደሚያወጣ ያመለክታል።
♥♥♥ በመቀጠልም፦
✍ “ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”
★ (እግዚአብሔር የፈጠራችው ፍጥረቶች ኹሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ርሱ የተመሰገነ ነው ለዘላለሙም ከፍ ከፍ ያለ ነው) እያሉ “ያመሰግኑታል” የሚለውን ቃል ለ 33 ጊዜ ብቻ ያኽል ተናግረዋል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፴፫‐፷፭)፡፡
💥 በሊቃውንቱ ትንታኔ ሠለስቱ ደቂቅ ስድስት ጊዜ መላልሰው መናገራቸው ከ600 ዘመናት በኋላ ምስጉን የኾነው የባሕርይ አምላክ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ማጠየቃቸው ሲኾን፤ ከዚያው ቀጥለው ደግሞ ሠላሳ ሦስት ጊዜ “ያመሰግኑታል” እያሉ ቃሉን ደጋግመው ማለታቸው፤ ምስጉን የኾነው አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ ሠላሳ ሦስት ዓመት በዚኽ ዓለም የሚኖር እንደኾነ ተገልጾላቸው የተናገሩ መኾኑን አስተምረዋል፡፡
💥 ይኽነንም ምስጢር ቀደምት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሲተነትኑ፦
“...ወተነበዩ ስድስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ስድስቱ ምእት ዓመት ይትወለድ ክርስቶስ፡፡ ወእምድኅሬሁ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይብሉ ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም ዘንተኒ ተነበዩ ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ተወልደ ክርስቶስ ይነብር ውስተ ዓለም ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ”
❖✔ (የሚነድደው እሳት ፈጽሞ አልነካቸውም የሚነድደውን እሳት እንደ ውሃ የቀዘቀዘ አድርጎታልና፤ በዚያን ሰዓት እግዚአብሔርን እንዲኽ እያሉ አመሰገኑት፤ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስን፤ ለዘለዓለሙ ክቡር ምስጉን ነው፤ እንዲኽ እያሉ ስድስት ጊዜ ተናገሩ፤ ከስድስት መቶ ዘመን በኋላ ክርስቶስ እንዲወለድ ለማጠየቅ። ከዚኽም በኋላ እንዲኽ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እግዚአብሔርን ፍጥረቱ ኹሉ ያመሰግኑታል ክቡር ምስጉን ነውና ለዘላለሙ ይክበር ይመስገን እያሉ፤ ይኽነንም ሠላሳ ሦሰት ጊዜ ተናገሩ፤ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ በዚኽ ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት እንዲኖር ለማጠየቅ) በማለት ልዩውን ምስጢር አስተምረውናል፡፡
💥 ንጉሡ ናቡከደነጾርም ባለመቃጠላቸው፤ በእሳት ውስጥ ኹነው በማመስገናቸው ተደንቆ አማካሪዎቹን “ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረም? እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መኻከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለኊ፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል” በማለት፤ ስማቸውን ጠርቶ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ውጡ ሲላቸው ሦስቱ ሕፃናት ከእሳቱ ወጡ፤ ያን ጊዜ መሳፍንቱ ኹሉ የራሳቸው ጠጒር እንዳልተቃጠለ፤ ሰናፊላቸው እንዳልተለወጠ፤ የእሳቱ ሽታ እንኳ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡

Telegram
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
💥 ያን ጊዜ ንጉሡ “በርሱ የታመኑ ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅ የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ” በማለት ምስጋናውን አቅርቧል (ዳን ፫፥፳፱‐፴)፡፡ እነዚኽ ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በእቶነ እሳት ቢጣሉም እንኳ፣ ስለ እምነታቸው ብርታት ምስጢር ተገልጾላቸው በ፮፻ ዘመን አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፴፫ ዓመት በዚኽ ዓለም ኖሮ ነፍሳትን ከሲኦል እሳት ነጻ እንደሚያወጣ የተገለጸላቸውን ልዩ ምስጋና፣ ዛሬ ኹላችን በቃል ኪዳኗና በምልጃዋ ከገሃነመ እሳት ከምንድንባት ከምትራራልን እናት ከቅድስት ድንግል ማርያም አምላክ ተወልዶ ፈጽሞታልና፤ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በኆኅተ ብርሃን የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ ሠለስቱ ደቂቅን ዛሬ ባለነው በምእመናን በመመሰል:-
✍ “መሃኪቶሙ እምውስተ እቶነ እሳት ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል በእደ ቅዱስ ገብርኤል” (በቅዱስ ገብርኤል እጅ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን በእቶን እሳት ውስጥ የራራሺላቸው አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን እንደወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡
💥 በተጨማሪም ሠለስቱ ደቂቅ በብሉይ ዘመን ያሉ የጻድቃን ምሳሌ፤ በውጪ ያሉት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ የኃጥአን ምሳሌ፤ የእሳቱ ጉድጓድ የሲኦል ምሳሌ፤ በውስጡ ያሉትን ትቶ በውጪ ያሉትን እንዳቃጠለ ኹሉ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ረድኤት ጻድቃንን ይጠብቅ ነበርና ምንም ሲኦል ቢወርዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን መከራው እንዳላገኛቸው፤ ኃጥአንን ግን መከራው የማግኘቱ ምሳሌ እንደኾነ መተርጉማን ያመሰጥሩታል፨
[የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በድጋሚ የተለጠፈ
የቴሌግራም ቻናሌ https://www.tg-me.com/Rodas9
[ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በረከቱ እንዲበዛልን በአስተያየት መስጫው ላይ አወድሱት]
✍ “መሃኪቶሙ እምውስተ እቶነ እሳት ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል በእደ ቅዱስ ገብርኤል” (በቅዱስ ገብርኤል እጅ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን በእቶን እሳት ውስጥ የራራሺላቸው አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን እንደወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡
💥 በተጨማሪም ሠለስቱ ደቂቅ በብሉይ ዘመን ያሉ የጻድቃን ምሳሌ፤ በውጪ ያሉት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ የኃጥአን ምሳሌ፤ የእሳቱ ጉድጓድ የሲኦል ምሳሌ፤ በውስጡ ያሉትን ትቶ በውጪ ያሉትን እንዳቃጠለ ኹሉ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ረድኤት ጻድቃንን ይጠብቅ ነበርና ምንም ሲኦል ቢወርዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን መከራው እንዳላገኛቸው፤ ኃጥአንን ግን መከራው የማግኘቱ ምሳሌ እንደኾነ መተርጉማን ያመሰጥሩታል፨
[የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በድጋሚ የተለጠፈ
የቴሌግራም ቻናሌ https://www.tg-me.com/Rodas9
[ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በረከቱ እንዲበዛልን በአስተያየት መስጫው ላይ አወድሱት]
Telegram
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
[ታኅሣሥ 22 የአምላክ እናት ተአምሯን ለጻፈላት ለቅዱስ ደቅስዮስ በረከቷን የሰጠችበት]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ደቅስዮስ የተወለደው በ607 ዓ.ም. ሲኾን ከጊዜ በኋላ የቶሌዶ ጳጳስ የሆነው አጎቱ ዩጄኒየስ በወጣትነቱ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምረው ነበረ። ከዚያም በ632 ዓ.ም አካባቢ የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ ኤላዲዎስ ዲያቆን አድርጎ ሾሞታል። ከፍ ካለ በኋላ በቶሌዶ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአጋሊያ ገዳም በመግባት የገዳሙ አበምኔት ኾነ። ከዚያም በ657 የቶሌዶ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ ተመረጠ።
💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሣ በተቻለዉም ኹሉ ያገለግላት ነበር “ወእምንደተ ፍቅሩ አስተጋብአ መጽሐፈ ተአምሪሃ” ይላል ከፍቅሩም ጽናት የተነሣ ክብሯን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ተአምሯን የሚናገር መጽሐፍን ሰበሰበ።
💥 ደቅስዮስ መሰብሰብ ብቻ ሳይኾን ድርሰትም ደራሲ ነበረ። ከጻፋቸው ከደብዳቤዎቹ ሁለቱ እና አራቱ ጽሑፎቹ አሁንም ድረስ አሉ። በተለይ የመዠመሪያው እና ዋናው ክፍል ስድስት ድርሰቶችን ያቀፈና ልክ እንደ ጀሮም ርሱም ሄልቪደስን ተቃውሞ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና የጻፈው "De virginitate perpetuâ sanctae Mariae adversus tres infideles" (On the Perpetual Virginity of Holy Mary) በመባል የሚታወቅ ሥራው ነው። ይኽ የደቅስዮስ መጽሐፍ ለ3 የተከፈለ ሲኾን "ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ" ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ይተነትናል።
💥 ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናዋ የልጇ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚገልጽ ምልክት እንደኾነ ሲገልጽ ልጇ እግዚአብሔር ነውና ብቻውን በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ሊወለድ ችሏል ብሏል።
💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በጽሑፉ ማርያም ብቻ ብሎ በስሟ አይጠራትም። ይልቁኑ ድንግሊቱ፣ የእኛ ድንግል ይላታል።
💥 ያን ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት “ይኽን መጽሐፍ ስለ ጻፍኽልኝ ደስ ብሎኛል” ብላው ባርካው ተሰወረች፡፡
💥 በተጨማሪም በ304 ዓ.ም. በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነትን በተቀበለችው በቅድስት ሊዮካዲያ (Saint Leocadia) የከበረ ዐፅም ፊት ሲጸልይ በተአምራት ተነሥታ የአምላክን እናት ስላከበራት አመስግናዋለች።
💥 ቅዱስ ደቅስዮስም ይኽነን ኹሉ ካየ በኋላ እጅጉን በመደሰት ለእመቤታችን ክብር ምን መሥራት እንዳለበት በማሰብ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረበት መጋቢት 29 ቀን የዐቢይ ጾም በመኾኑ ምክንያት ሰዎች ማክበር ያልተቻላቸውን በዓለ ብሥራትን ከልደት በዓል ስምንት ቀናት ቀደም በማድረግ ታኅሣሥ 22 ዕለት እንዲከበር ሥርዐትን ሠራ። በቶሌዶ በተደረገ ጉባኤ ለአምላክ እናት ክብር የተለየ የበዓላቷን ቀን ተደነገገ።
💥 ምእመናንም እጅጉን በመደሰት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ እግዚአብሔር በማሕፀነ ማርያም የተፀነሰበትን በዓል ለውጥ በማሰብ በዓሉን በድምቀት አከበሩ፡፡ ያን ጊዜ በወርኃ ታኅሣሥ በ665 ዓ.ም. በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ለደቅስዮስ ለብቻው ተገልጻለት “ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ፤ ሥራኽንም ወደድኊ፤ በዓሌን አክብረኽ ስለ እኔ ሰውን ኹሉ ደስ አሰኝተኻልና እኔም ዋጋኽን ልሰጥኽ እወዳለኊ ትቀመጥበትም ዘንድ ይኽነን ወንበር አመጣኹልኽ” በማለት በወንበሩም ላይ ማንም ሊቀመጥባት የሚቻለው እንደሌለ ነግራው ከርሱ ተሰወረች፡፡
💥 በሌላ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ከምእመናን ጋር የእመቤታችንን መዝሙር ሲዘምሩ ከፍተኛ ብርሃን ወርዶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲከብባት አብዛኞቹ ምእመናን ፈርተው ሲሸሹ ደቅስዮስ ከጥቂት ዲያቆናት ጋር ብቻ ቀረ። ያንጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግልን አስከትላ ወርዳ በኤጲስ ቆጶስ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አየ። እመቤታችንም ደቅስዮስን ለታማኝነቱ አመስግናው እጅግ የተለየ ልብሰ ተክህኖ በበዓላቷ ላይ ብቻ እንዲለብስ ሰጥታው በእመቤታችን በዓላት ይለብሰው ነበር።
💥 ቅዱስ ደቅስዮስም በ667 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በተለየ ጊዜ እመቤታችን የባረከችውን ልብስ በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት በክብር አኖሯት፤ ከርሱ በኋላ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ግን ያችን ልብስ ሊለብሳትና በደቅስዮስም ወንበር ሊቀመጥ ወደደ።
💥 ቀሳውስትና መምህራን ግን የልብሷን ክብር በመንገር ይኽነን እንዳያደርግ ቢለምኑት ርሱ ግን ልክ እንደ ዖዝያን በድፍረት ልብሷን ለብሶ በወንበሩ በተቀመጠ ጊዜ ሐናንያና ሰጲራ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ተቀሥፈው እንደሞቱ፤ ርሱም “ወድቀ በጊዜሁ እምላዕለ ውእቱ መንበር በቅድመ ኲሎሙ ሰብእ እለ ሀለዉ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወሞተ በእኩይ ሞት ወሕሡም ፈድፋደ” ይላል በዚኽ የድፍረት ኀጢአቱ ከዚያ ወንበር ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ኹሉ ፊት ወድቆ ክፉ አሟሟትን ሞቷል፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ተአምር ሕዝቡ በመደነቅ ምስጉን እግዚአብሔርን በማመስገን አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንን ስለ አደረገችው ተአምር እጅጉን አክብረዋታል፡፡ በግእዝ በብራና በተጻፉት ተአምረ ማርያም ላይ ይኽ የቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ተሥሎ ማየት የተለመደ ነው።
💥 ከዚያ በኋላ የሰጠችው ልብስ ቢሰወርም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለደቅስዮስ ስትገለጥለት እግሯን ያሳረፈችበት ድንጋይ ግን በቶሌዶ ካቴድራል ጸሎት ቤት ውስጥ ይከበራል።
💥 ንጉሥ ዳዊትም እንደነ ደቅስዮስ ላሉ እመቤታችንን ለሚወዷት ኹሉ በምልጃዋ ከልጇ ስለምታሰጣቸው ታላቅ መንፈሳዊ በረከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጦለት “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ) በማለት ከገለጠ በኋላ “ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር” (በምድርም ኹሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ) በማለት የሠያሜ ነገሥት፣ የሠያሜ ካህናት የክርስቶስ እናት መኾኗንና፤ ይኽነንም የአምላክ እናትነቷን ለመሰከሩ ለነ ደቅስዮስ ወንበር፤ ለነ ኒቆላዎስ ዐጽፍ፣ ለነ ቅዱስ ኤፍሬም “አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” (አቤቱ የጸጋኽን ማዕበል ግታው፤ ወስነው) እስኪሉ ድረስ በቃል ኪዳኗና በአማላጅነቷ ያሰጠቻቸው ታላቅ በረከት መንፈሳዊ ሹመትና ብቃት መኾኑን አሳይቷል፡፡
💥 “ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ” (ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ) በማለት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በርሷ ወላዲተ አምላክነት በማመን የጸና ያለፈውና የሚመጣው ትውልድ ኹሉ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያለ የተቀደሰ ስሟን ሳይጠራ የሚውል ማንም እንደማይኖር ቅዱስ ዳዊት በመንፈሰ እግዚአብሔር ገላጭነት ተናግሯል (መዝ ፵፬፥፱-፲፯)፡፡
💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ ሰላም ለኪ"
(ለኒቆላና ለደቅስዮስ ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድመሽ እንደሰጠሻቸው ሰላምታ የተገባሽ ማርያም የፍጹም ደስታና ተድላ ልብስን ስጪኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡
💥 የነገረ ማርያም ሊቃውንት የነበሩት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ እመቤታችን ተአምሯን ሰብስቦ ላዘጋጀላት ለደቅስዮስ ታላቅ ጸጋን በቃል ኪዳኗ እንዳሰጠች ሲገልጹ፦

YouTube
ታኅሣሥ 22 የእመቤታችን ሽልማት፤ በእጇ ልዩ ልብስ ይዛ ተገለጠች
“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”
(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡
በቪዲዮ ለምትፈልጉ ሊንኩ https://youtu.be/sa0sRwZjV_4?si=xxF59XSZy-2yaMuY
[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ የተለጠፈ]
(ለቅዱስ ደቅስዮስ ይኽነን ታላቅ በረከት ያደለች የአምላክ እናት ለእኛም የማያልቀውን በረከቷን አብዝታ ታትረፍርፍልን፡፡ እናንተም በምትችሉት ምስጋና በአስተያየት መስጫው ላይ አቅርቡላት)

አባታችን ሔኖክ የተገለጠለትን ይኽነን ዕውቀትና ምልክት ለ10ኛው ትውልድ ለኖኅ ከጥፋት ውሃ በፊት መጥቶ ሰጥቶታል፤ይኸውም በመጽሐፈ ሔኖክ እንዲኽ ተገልጧል፡- ❖ “ከዚኽም በኋላ አያቴ ሔኖክ የተሰጡትን የምስጢሮችን ኹሉና የምሳሌዎችን ምልክት በመጽሐፍ ሰጠኝ፤ በእኔ ዘንድ ካለው የመጽሐፍ ቃል ጋርም ጨመራቸው” (ሔኖ 18፥42፤ መጽሐፈ ራዝኤል) ታላላቅ ምስጢራት የተጻፈበትን ይኽነን ዕውቀት (መጽሐፍ) ኖኅ ጽፎ ይወደው ለነበረው ለታላቁ ልጁ ለሴም ሰጥቶታል፡፡
37 አልፋ 73 መጽሐፌ የተወሰደ
37 አልፋ 73 መጽሐፌ የተወሰደ
The Joy of Christmas in Ethiopia
Dr Megabe Haddis Rodas Tadese (The Sun of Righteousness)
💥 As the days of fasting draw to a close, the Church enters the sacred night before Christmas, filled with reverence and joy. On this eve, the Church’s declaration echoes through its holy spaces:
✍️ "The Magi journeyed from distant lands, bearing gifts of gold, frankincense and myrrh; His mother laid Him in a manger carved from stone; she wrapped Him in the tender leaves of the fields and called Him ‘Savior of the World.’ Behold, today the Revealer of Light is born."
At 7:00 PM, the evening begins with songs of worship, celebrating the divine mystery of God taking on flesh. The voices of the faithful rise with hymns by St. Yared, the Church’s esteemed hymnologist, proclaiming: ✍️ "Shepherds beheld Him, born of the Holy Virgin Mary; angels praised Him, singing in heavenly choirs; the Heavenly God took on flesh and was laid in a manger." The congregation joins in the ageold chants, filling the night with praise as they contemplate the humble birth of the Creator of all things.
💥 As midnight approaches, the Eucharistic Liturgy begins. In this sacred moment, the Church brings forth the true Body and precious Blood of Christ and the faithful, prepared by fasting and prayer, receive Him in communion. It is an intimate and profound embrace of the Incarnation, as each believer becomes a living testament to the birth of Christ within.
💥 Through each hymn, prayer and ritual, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church teaches the faithful to experience Christmas not as a distant story but as a living reality. The prophetic observances of Sebekat, Bereehan and Nolawi cultivate a longing in the heart, mirroring the waiting of the prophets, the joy of those who witnessed His birth and the peace brought by the Good Shepherd. The nightlong vigil, filled with song and praise, embodies the Church’s collective adoration, lifting the spirits of the faithful and drawing them closer to the divine mystery.
💥 The Eucharistic Liturgy at midnight marks the culmination of this spiritual journey, transforming the Nativity celebration into a personal encounter with Christ. In receiving the Eucharist, believers affirm the Incarnation of God, recognizing that Christ comes not only to Bethlehem but to each heart that welcomes Him. — Through the Feast of the Nativity and every sacred holiday, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church unfolds the mystery of Jesus Christ His love, humility and sacrifice.
💥 This annual cycle of worship, devotion and sacred remembrance leads the faithful into a deeper relationship with their Savior, who is both God incarnate and the Shepherd of their souls.
Order The Sun of Righteousness on Amazon
https://a.co/d/ckNQYB7
Dr Rodas Tadese