Telegram Web Link
[የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል የታኅሣሥ ክብረ በዓል]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቅዱስ ገብርኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን፤ የሚኖርበት ሰማይም ራማ ነው። አርባብ በተባለ ነገድ ላይ የተሾመ በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም ብርሃናዊ መልአክ ነው (ሉቃ 1:19)።

💥 በግእዝ ገብርኤል፤ በዕብራይስጥ גַּבְרִיאֵל‎ በአረማይክ ܓ݁ܰܒ݂ܪܺܝܐܝܶܠ‎, በቅብጥ Ⲅⲁⲃⲣⲓⲏⲗ ሲባል ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ኃይሌ ነው" ማለት ነው።

💥 ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክን ሰው መኾን ደስ ብሎት ያበሠራት መልአክ ስለኾነ ከግብሩ (ከሥራው) የተነሣ
✍️ "መጋቤ ሐዲስ፣
✍️ ጸዋሬ ዜና ወምክር፣
✍️ መልአከ ፍሥሐ፣
✍️ እግዚእ ወገብር" በመባል ይታወቃል፡፡

💥 ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፦
"ጸዋሬ ዜና ወምክር ገብርኤል
ክቡር ምጽአቶ ለቃል ዜነዋ ለድንግል"
(የብሥራት ዜናና ምክርን የሚሸከም ገብርኤል የክቡር የባሕርይ አምላክ የአካላዊ ቃል አመጣጥን ለድንግል ነገራት) ይላል።

💥 የመልክአ ገብርኤል ደራሲም፦
"ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢየተረጎም ምስጢር
ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር"
(የማይተረጎም ምስጢር አባባሉ ፍቺው ጌታም አገልጋይም የሚመስል ለኾነ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል።

💥 የታኅሣሥ 19 ክብረ በዓሉን ስናስብ ነቢዩ ዳንኤል ለንጉሡ ለናቡከደነጾር ሕልሙን ከተረጐመለት በኋላ ዳንኤልንና ሠለስቱ ደቂቅን በባቢሎን አውራጃ ላይ ከፍተኛ ሹመትን በየደረጃቸው ሹሟቸዋል (ዳን ፪፥፵፰‐፵፱)፡፡

💥 ኾኖም ግን ናቡከደነጾር ቁመቱ ስሳ ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ የኾነውን የወርቁን ምስል አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ በማቆም ኹሉም ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰብስበው ሳሉ፤ ዐዋጅ ነጋሪው የዘፈን ድምፅ ሕዝቡ ሲሰሙ ንጉሡ ላቆመው ምስል ተደፍተው እንዲሰግዱ ትእዛዝን የማይቀበሉ ግን በሚነድደው እሳት እቶን እንደሚጣሉ ሲናገር ሕዝቡም አሕዛቡም ለምስሉ ይሰግዱ ይረበረቡ ዠመር (ዳን ፫፥፩‐፯)፡፡

💥 ሦስቱ ሕፃናት አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ግን አንሰግድም በማለታቸው “እሉ እደው ዘሤምኮሙ ለግብረ በሐውርተ ባቢሎን አበዩ ሰጊደ ለምስል ዘወርቅ ዘገበርከ” በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምካቸው እነዚኽ ሰዎች ወንዶች ላቆምኸው ምስል አይሰግዱም በማለት ነገሩት።

💥 ናቡከደነጾርም በብስጭትና በቊጣ እንዲመጡ በማዘዙ፤ መጥተው ከፊቱ ሲቆሙ “ላቆምኹት ለወርቁ ምስል አለመስገዳችኊ እውነት ነውን? ባትሰግዱ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችኊ፤ ከእጄስ የሚያድናችኊ አምላክ ማን ነው?” በማለት ሲናገራቸው የሚያመልኩት አምላክ ከሚነድደው እሳት ሊያድናቸው እንደሚችል ገለጹለት።

💥 ርሱም በቊጣ የእቶኑ እሳት ከሚነደው ይልቅ ሰባት እጥፍ ማለት 49 ክንድ አድርገው እንዲያነዱ በማዘዝ አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል፣ ታሥረው እንዲጣሉ በሰራዊቱ ውስጥ ላሉት ኀያላን መመሪያ ስላስተላለፈ፤ ወርዋሪዎቹም ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸው ጋር በእሳቱ ላይ ሲጥሏቸው ከወላፈኑ ከፍተኛነት የተነሣ ወታደሮቹ ተቃጥለዋል (ዳን ፫፥፲፫‐፳፫)፡፡

💥 ያን ጊዜ “ወወረደ መልአከ እግዚአብሔር ወዘበጦ ለነበልባለ እሳት ወረሰዮ ከመ ነፋስ ቆሪር ዘጊዜ ጽባሕ” ይላል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ በበትረ ብርሃን ቢመታው እንዳረረ ውርጭ ኾኗል፤ ያን ጊዜ ወአንሰሶሰዉ ማእከለ እሳት ወአእኰቱ እግዚአብሔርሀ ወባረክዎ ይላል በእሳቱ ጒድጓድ መኻከልም በመመላለስ እግዚአብሔርንም ፈጽመው አመስግነውታል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፩)፡፡

💥 ይኽም ከእሳቱ መኻከል ሳሉ የተገለጸላቸው አስደናቂ ምስጋና ልዩ የኾነ የነገረ ሥጋዌ ምስጢርን የያዘ እንደኾነ የነገረ ነቢያት ሊቃውንት አስተምረዋል፤ ይኸውም 49 ክንድ ወደ ላይ በወጣው በእሳቱ መኻከል ኹነው ለስድስት ጊዜ ብቻ፦
“ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”

★ (የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፤ የተመሰገነ ነው፤ ለዘለዓለሙም የከበረ ነው) በማለት አመሰገኑ (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፳፯‐፴፪)።

49 ክንድ ወደ ላይ የወጣው እሳት እና እሳት ውስጥ ኾነው 6 ጊዜ "ይትባረክ" (ይመስገን) ያሉት ቢደመር 55 ይኾናል (49+6=55)፤ ይኽም የ5500 ዘመን ምሳሌ ነው፤ ይኽም 5500 ዘመን ተፈጽሞ በ6ኛው ሺሕ አምላክ ሰው ኾኖ ከሲኦል እሳት ነፍሳትን ነጻ እንደሚያወጣ ያመለክታል።

በመቀጠልም፦
“ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”

★ (እግዚአብሔር የፈጠራችው ፍጥረቶች ኹሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ርሱ የተመሰገነ ነው ለዘላለሙም ከፍ ከፍ ያለ ነው) እያሉ “ያመሰግኑታል” የሚለውን ቃል ለ 33 ጊዜ ብቻ ያኽል ተናግረዋል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፴፫‐፷፭)፡፡

💥 በሊቃውንቱ ትንታኔ ሠለስቱ ደቂቅ ስድስት ጊዜ መላልሰው መናገራቸው ከ600 ዘመናት በኋላ ምስጉን የኾነው የባሕርይ አምላክ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ማጠየቃቸው ሲኾን፤ ከዚያው ቀጥለው ደግሞ ሠላሳ ሦስት ጊዜ “ያመሰግኑታል” እያሉ ቃሉን ደጋግመው ማለታቸው፤ ምስጉን የኾነው አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ ሠላሳ ሦስት ዓመት በዚኽ ዓለም የሚኖር እንደኾነ ተገልጾላቸው የተናገሩ መኾኑን አስተምረዋል፡፡

💥 ይኽነንም ምስጢር ቀደምት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሲተነትኑ፦
“...ወተነበዩ ስድስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ስድስቱ ምእት ዓመት ይትወለድ ክርስቶስ፡፡ ወእምድኅሬሁ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይብሉ ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም ዘንተኒ ተነበዩ ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ተወልደ ክርስቶስ ይነብር ውስተ ዓለም ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ”

(የሚነድደው እሳት ፈጽሞ አልነካቸውም የሚነድደውን እሳት እንደ ውሃ የቀዘቀዘ አድርጎታልና፤ በዚያን ሰዓት እግዚአብሔርን እንዲኽ እያሉ አመሰገኑት፤ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስን፤ ለዘለዓለሙ ክቡር ምስጉን ነው፤ እንዲኽ እያሉ ስድስት ጊዜ ተናገሩ፤ ከስድስት መቶ ዘመን በኋላ ክርስቶስ እንዲወለድ ለማጠየቅ። ከዚኽም በኋላ እንዲኽ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እግዚአብሔርን ፍጥረቱ ኹሉ ያመሰግኑታል ክቡር ምስጉን ነውና ለዘላለሙ ይክበር ይመስገን እያሉ፤ ይኽነንም ሠላሳ ሦሰት ጊዜ ተናገሩ፤ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ በዚኽ ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት እንዲኖር ለማጠየቅ) በማለት ልዩውን ምስጢር አስተምረውናል፡፡

💥 ንጉሡ ናቡከደነጾርም ባለመቃጠላቸው፤ በእሳት ውስጥ ኹነው በማመስገናቸው ተደንቆ አማካሪዎቹን “ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረም? እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መኻከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለኊ፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል” በማለት፤ ስማቸውን ጠርቶ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ውጡ ሲላቸው ሦስቱ ሕፃናት ከእሳቱ ወጡ፤ ያን ጊዜ መሳፍንቱ ኹሉ የራሳቸው ጠጒር እንዳልተቃጠለ፤ ሰናፊላቸው እንዳልተለወጠ፤ የእሳቱ ሽታ እንኳ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡
👍5448👏4
💥 ያን ጊዜ ንጉሡ “በርሱ የታመኑ ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅ የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ” በማለት ምስጋናውን አቅርቧል (ዳን ፫፥፳፱‐፴)፡፡ እነዚኽ ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በእቶነ እሳት ቢጣሉም እንኳ፣ ስለ እምነታቸው ብርታት ምስጢር ተገልጾላቸው በ፮፻ ዘመን አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፴፫ ዓመት በዚኽ ዓለም ኖሮ ነፍሳትን ከሲኦል እሳት ነጻ እንደሚያወጣ የተገለጸላቸውን ልዩ ምስጋና፣ ዛሬ ኹላችን በቃል ኪዳኗና በምልጃዋ ከገሃነመ እሳት ከምንድንባት ከምትራራልን እናት ከቅድስት ድንግል ማርያም አምላክ ተወልዶ ፈጽሞታልና፤ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በኆኅተ ብርሃን የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ ሠለስቱ ደቂቅን ዛሬ ባለነው በምእመናን በመመሰል:-

“መሃኪቶሙ እምውስተ እቶነ እሳት ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል በእደ ቅዱስ ገብርኤል” (በቅዱስ ገብርኤል እጅ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን በእቶን እሳት ውስጥ የራራሺላቸው አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን እንደወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡

💥 በተጨማሪም ሠለስቱ ደቂቅ በብሉይ ዘመን ያሉ የጻድቃን ምሳሌ፤ በውጪ ያሉት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ የኃጥአን ምሳሌ፤ የእሳቱ ጉድጓድ የሲኦል ምሳሌ፤ በውስጡ ያሉትን ትቶ በውጪ ያሉትን እንዳቃጠለ ኹሉ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ረድኤት ጻድቃንን ይጠብቅ ነበርና ምንም ሲኦል ቢወርዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን መከራው እንዳላገኛቸው፤ ኃጥአንን ግን መከራው የማግኘቱ ምሳሌ እንደኾነ መተርጉማን ያመሰጥሩታል፨

[የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በድጋሚ የተለጠፈ
የቴሌግራም ቻናሌ https://www.tg-me.com/Rodas9
[ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በረከቱ እንዲበዛልን በአስተያየት መስጫው ላይ አወድሱት]
105👍35👏1
[ታኅሣሥ 22 የአምላክ እናት ተአምሯን ለጻፈላት ለቅዱስ ደቅስዮስ በረከቷን የሰጠችበት]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ደቅስዮስ የተወለደው በ607 ዓ.ም. ሲኾን ከጊዜ በኋላ የቶሌዶ ጳጳስ የሆነው አጎቱ ዩጄኒየስ በወጣትነቱ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምረው ነበረ። ከዚያም በ632 ዓ.ም አካባቢ የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ ኤላዲዎስ ዲያቆን አድርጎ ሾሞታል። ከፍ ካለ በኋላ በቶሌዶ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአጋሊያ ገዳም በመግባት የገዳሙ አበምኔት ኾነ። ከዚያም በ657 የቶሌዶ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ ተመረጠ።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሣ በተቻለዉም ኹሉ ያገለግላት ነበር “ወእምንደተ ፍቅሩ አስተጋብአ መጽሐፈ ተአምሪሃ” ይላል ከፍቅሩም ጽናት የተነሣ ክብሯን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ተአምሯን የሚናገር መጽሐፍን ሰበሰበ።

💥 ደቅስዮስ መሰብሰብ ብቻ ሳይኾን ድርሰትም ደራሲ ነበረ። ከጻፋቸው ከደብዳቤዎቹ ሁለቱ እና አራቱ ጽሑፎቹ አሁንም ድረስ አሉ። በተለይ የመዠመሪያው እና ዋናው ክፍል ስድስት ድርሰቶችን ያቀፈና ልክ እንደ ጀሮም ርሱም ሄልቪደስን ተቃውሞ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና የጻፈው "De virginitate perpetuâ sanctae Mariae adversus tres infideles" (On the Perpetual Virginity of Holy Mary) በመባል የሚታወቅ ሥራው ነው። ይኽ የደቅስዮስ መጽሐፍ ለ3 የተከፈለ ሲኾን "ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ" ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ይተነትናል።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናዋ የልጇ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚገልጽ ምልክት እንደኾነ ሲገልጽ ልጇ እግዚአብሔር ነውና ብቻውን በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ሊወለድ ችሏል ብሏል።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በጽሑፉ ማርያም ብቻ ብሎ በስሟ አይጠራትም። ይልቁኑ ድንግሊቱ፣ የእኛ ድንግል ይላታል።

💥 ያን ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት “ይኽን መጽሐፍ ስለ ጻፍኽልኝ ደስ ብሎኛል” ብላው ባርካው ተሰወረች፡፡

💥 በተጨማሪም በ304 ዓ.ም. በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነትን በተቀበለችው በቅድስት ሊዮካዲያ (Saint Leocadia) የከበረ ዐፅም ፊት ሲጸልይ በተአምራት ተነሥታ የአምላክን እናት ስላከበራት አመስግናዋለች።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም ይኽነን ኹሉ ካየ በኋላ እጅጉን በመደሰት ለእመቤታችን ክብር ምን መሥራት እንዳለበት በማሰብ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረበት መጋቢት 29 ቀን የዐቢይ ጾም በመኾኑ ምክንያት ሰዎች ማክበር ያልተቻላቸውን በዓለ ብሥራትን ከልደት በዓል ስምንት ቀናት ቀደም በማድረግ ታኅሣሥ 22 ዕለት እንዲከበር ሥርዐትን ሠራ። በቶሌዶ በተደረገ ጉባኤ ለአምላክ እናት ክብር የተለየ የበዓላቷን ቀን ተደነገገ።

💥 ምእመናንም እጅጉን በመደሰት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ እግዚአብሔር በማሕፀነ ማርያም የተፀነሰበትን በዓል ለውጥ በማሰብ በዓሉን በድምቀት አከበሩ፡፡ ያን ጊዜ በወርኃ ታኅሣሥ በ665 ዓ.ም. በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ለደቅስዮስ ለብቻው ተገልጻለት “ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ፤ ሥራኽንም ወደድኊ፤ በዓሌን አክብረኽ ስለ እኔ ሰውን ኹሉ ደስ አሰኝተኻልና እኔም ዋጋኽን ልሰጥኽ እወዳለኊ ትቀመጥበትም ዘንድ ይኽነን ወንበር አመጣኹልኽ” በማለት በወንበሩም ላይ ማንም ሊቀመጥባት የሚቻለው እንደሌለ ነግራው ከርሱ ተሰወረች፡፡

💥 በሌላ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ከምእመናን ጋር የእመቤታችንን መዝሙር ሲዘምሩ ከፍተኛ ብርሃን ወርዶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲከብባት አብዛኞቹ ምእመናን ፈርተው ሲሸሹ ደቅስዮስ ከጥቂት ዲያቆናት ጋር ብቻ ቀረ። ያንጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግልን አስከትላ ወርዳ በኤጲስ ቆጶስ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አየ። እመቤታችንም ደቅስዮስን ለታማኝነቱ አመስግናው እጅግ የተለየ ልብሰ ተክህኖ በበዓላቷ ላይ ብቻ እንዲለብስ ሰጥታው በእመቤታችን በዓላት ይለብሰው ነበር።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም በ667 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በተለየ ጊዜ እመቤታችን የባረከችውን ልብስ በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት በክብር አኖሯት፤ ከርሱ በኋላ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ግን ያችን ልብስ ሊለብሳትና በደቅስዮስም ወንበር ሊቀመጥ ወደደ።

💥 ቀሳውስትና መምህራን ግን የልብሷን ክብር በመንገር ይኽነን እንዳያደርግ ቢለምኑት ርሱ ግን ልክ እንደ ዖዝያን በድፍረት ልብሷን ለብሶ በወንበሩ በተቀመጠ ጊዜ ሐናንያና ሰጲራ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ተቀሥፈው እንደሞቱ፤ ርሱም “ወድቀ በጊዜሁ እምላዕለ ውእቱ መንበር በቅድመ ኲሎሙ ሰብእ እለ ሀለዉ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወሞተ በእኩይ ሞት ወሕሡም ፈድፋደ” ይላል በዚኽ የድፍረት ኀጢአቱ ከዚያ ወንበር ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ኹሉ ፊት ወድቆ ክፉ አሟሟትን ሞቷል፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ተአምር ሕዝቡ በመደነቅ ምስጉን እግዚአብሔርን በማመስገን አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንን ስለ አደረገችው ተአምር እጅጉን አክብረዋታል፡፡ በግእዝ በብራና በተጻፉት ተአምረ ማርያም ላይ ይኽ የቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ተሥሎ ማየት የተለመደ ነው።

💥 ከዚያ በኋላ የሰጠችው ልብስ ቢሰወርም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለደቅስዮስ ስትገለጥለት እግሯን ያሳረፈችበት ድንጋይ ግን በቶሌዶ ካቴድራል ጸሎት ቤት ውስጥ ይከበራል።

💥 ንጉሥ ዳዊትም እንደነ ደቅስዮስ ላሉ እመቤታችንን ለሚወዷት ኹሉ በምልጃዋ ከልጇ ስለምታሰጣቸው ታላቅ መንፈሳዊ በረከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጦለት “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ) በማለት ከገለጠ በኋላ “ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር” (በምድርም ኹሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ) በማለት የሠያሜ ነገሥት፣ የሠያሜ ካህናት የክርስቶስ እናት መኾኗንና፤ ይኽነንም የአምላክ እናትነቷን ለመሰከሩ ለነ ደቅስዮስ ወንበር፤ ለነ ኒቆላዎስ ዐጽፍ፣ ለነ ቅዱስ ኤፍሬም “አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” (አቤቱ የጸጋኽን ማዕበል ግታው፤ ወስነው) እስኪሉ ድረስ በቃል ኪዳኗና በአማላጅነቷ ያሰጠቻቸው ታላቅ በረከት መንፈሳዊ ሹመትና ብቃት መኾኑን አሳይቷል፡፡

💥 “ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ” (ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ) በማለት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በርሷ ወላዲተ አምላክነት በማመን የጸና ያለፈውና የሚመጣው ትውልድ ኹሉ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያለ የተቀደሰ ስሟን ሳይጠራ የሚውል ማንም እንደማይኖር ቅዱስ ዳዊት በመንፈሰ እግዚአብሔር ገላጭነት ተናግሯል (መዝ ፵፬፥፱-፲፯)፡፡

💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ ሰላም ለኪ"
(ለኒቆላና ለደቅስዮስ ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድመሽ እንደሰጠሻቸው ሰላምታ የተገባሽ ማርያም የፍጹም ደስታና ተድላ ልብስን ስጪኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡

💥 የነገረ ማርያም ሊቃውንት የነበሩት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ እመቤታችን ተአምሯን ሰብስቦ ላዘጋጀላት ለደቅስዮስ ታላቅ ጸጋን በቃል ኪዳኗ እንዳሰጠች ሲገልጹ፦
52👍28🥰2
“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”

(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡
በቪዲዮ ለምትፈልጉ ሊንኩ https://youtu.be/sa0sRwZjV_4?si=xxF59XSZy-2yaMuY
[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ የተለጠፈ]
(ለቅዱስ ደቅስዮስ ይኽነን ታላቅ በረከት ያደለች የአምላክ እናት ለእኛም የማያልቀውን በረከቷን አብዝታ ታትረፍርፍልን፡፡ እናንተም በምትችሉት ምስጋና በአስተያየት መስጫው ላይ አቅርቡላት)
109👍39🥰9👏5
አባታችን ሔኖክ የተገለጠለትን ይኽነን ዕውቀትና ምልክት ለ10ኛው ትውልድ ለኖኅ ከጥፋት ውሃ በፊት መጥቶ ሰጥቶታል፤ይኸውም በመጽሐፈ ሔኖክ እንዲኽ ተገልጧል፡- ❖ “ከዚኽም በኋላ አያቴ ሔኖክ የተሰጡትን የምስጢሮችን ኹሉና የምሳሌዎችን ምልክት በመጽሐፍ ሰጠኝ፤ በእኔ ዘንድ ካለው የመጽሐፍ ቃል ጋርም ጨመራቸው” (ሔኖ 18፥42፤ መጽሐፈ ራዝኤል) ታላላቅ ምስጢራት የተጻፈበትን ይኽነን ዕውቀት (መጽሐፍ) ኖኅ ጽፎ ይወደው ለነበረው ለታላቁ ልጁ ለሴም ሰጥቶታል፡፡
37 አልፋ 73 መጽሐፌ የተወሰደ
👍8628👏4
The Joy of Christmas in Ethiopia
Dr Megabe Haddis Rodas Tadese (The Sun of Righteousness)
💥 As the days of fasting draw to a close, the Church enters the sacred night before Christmas, filled with reverence and joy. On this eve, the Church’s declaration echoes through its holy spaces:
✍️ "The Magi journeyed from distant lands, bearing gifts of gold, frankincense and myrrh; His mother laid Him in a manger carved from stone; she wrapped Him in the tender leaves of the fields and called Him ‘Savior of the World.’ Behold, today the Revealer of Light is born."

At 7:00 PM, the evening begins with songs of worship, celebrating the divine mystery of God taking on flesh. The voices of the faithful rise with hymns by St. Yared, the Church’s esteemed hymnologist, proclaiming: ✍️ "Shepherds beheld Him, born of the Holy Virgin Mary; angels praised Him, singing in heavenly choirs; the Heavenly God took on flesh and was laid in a manger." The congregation joins in the ageold chants, filling the night with praise as they contemplate the humble birth of the Creator of all things.

💥 As midnight approaches, the Eucharistic Liturgy begins. In this sacred moment, the Church brings forth the true Body and precious Blood of Christ and the faithful, prepared by fasting and prayer, receive Him in communion. It is an intimate and profound embrace of the Incarnation, as each believer becomes a living testament to the birth of Christ within.

💥 Through each hymn, prayer and ritual, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church teaches the faithful to experience Christmas not as a distant story but as a living reality. The prophetic observances of Sebekat, Bereehan and Nolawi cultivate a longing in the heart, mirroring the waiting of the prophets, the joy of those who witnessed His birth and the peace brought by the Good Shepherd. The nightlong vigil, filled with song and praise, embodies the Church’s collective adoration, lifting the spirits of the faithful and drawing them closer to the divine mystery.

💥 The Eucharistic Liturgy at midnight marks the culmination of this spiritual journey, transforming the Nativity celebration into a personal encounter with Christ. In receiving the Eucharist, believers affirm the Incarnation of God, recognizing that Christ comes not only to Bethlehem but to each heart that welcomes Him. — Through the Feast of the Nativity and every sacred holiday, the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church unfolds the mystery of Jesus Christ His love, humility and sacrifice.

💥 This annual cycle of worship, devotion and sacred remembrance leads the faithful into a deeper relationship with their Savior, who is both God incarnate and the Shepherd of their souls.

Order The Sun of Righteousness on Amazon
https://a.co/d/ckNQYB7

Dr Rodas Tadese
64👍21🔥2
[በ40 ምንጭና በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ እየነደደ የሚጓዘው ምን ይኾን? በሳይንስና በሃይማኖት]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ዛሬ ጥር 1/ 2017 ዓ.ም. በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የታየ በሰማይ እየተቀጣጠለ የሚኼድ በጣም በርካታ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በውስጥ መሥመር እየተላኩልኝ ነበርና ምልከታዬን ለማስቀመጥ እሞክራለኹ።
💥 ከሰማይ ላይ አብርተው ስለሚታዩ ስለሚወድቁ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አካላት መረዳት ግድ ይላል።
የተፈጥሮ የሕዋ ዐለቶችን አስቀድመን እንመልከት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. ሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-

1. አስትሮይድ
💥 በዋነኛነት በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው የአስትሮይድ ቀበቶ ውስጥ የሚገኙት ዐለታማ ሥሪትነት ያላቸው አካላት ናቸው። መጠናቸውን ለመረዳት ለምሳሌ አስትሮይድ ቬስታ መጠኑ 329 ማይል (530 ኪሎ ሜትር) ዲያሜትር ያለው ሲኾን ከታናናሾቹ ውስጥ ከ33 ጫማ (10 ሜትር) በታች የኾኑም ይገኙበታል። የኹሉም አስትሮይድ አጠቃላይ ክብደት ግን ከምድር ጨረቃ ያነሰ ነው።

👉 በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )

2. ሜትዮራይድ
💥 ሜትዮራይዶች በሕዋ ያሉ ትናንሽ ዐለቶች ሲኾኑ መጠናቸው ከከሸዋ ቅንጣት እስከ 1 ሜትር አካባቢ ይደርሳሉ። አንዳንድ ሜትዮራይድ ዐለቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብረታ ብረት ወይም የድንጋይ እና የብረት ውሕዶች ናቸው። ሜትዮራይድ ብዙ ጊዜ ከአስትሮይድ ወይም ከኮሜት ወይም ከሌሎች ፕላኔቶች ጭምር የሚመጡ ናቸው። በአጠቃላይ ሜትዮራይድ ስንል ገና በሕዋ ላይ ያሉትን ነው።

3. ሚትየር
💥 ከላይ እንዳየነው ሜትዮራይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ወይም ወደ ሌላ ፕላኔት በከፍተኛ ፍጥነት ሲገቡ እና ሲቃጠሉ ሚትዮር ይባላሉ። በሌላ አጠራር “ተወርዋሪ ኮከቦች” ብለን የምንጠራቸው ሲኾን አንዳንድ ጊዜ ሜትየሮች ከቬኑስ የበለጠ ብሩህ ኾነው ሊታዩ ይችላሉ። ያን ጊዜ “የእሳት ኳሶች” ተብለው ይጠራሉ። ብዙ ተወርዋሪ ከዋክብት በአንድ ላይ በሰዓታት ሲታዩ "ሜትየር ሻወር" በመባል ይታወቃሉ።

4. ሜትሮይት
💥 ሳይቃጠል የምድርን ከባቢ አየር ዐልፎ በምድር ላይ የሚያርፍ የሜትሮይድ ቁራጭ መጠሪያ ነው። በሰዓት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኃይለኛ ግፊት ወድቆ ሲበታተን ብሩህ ነበልባል ይመስላል።
ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
2) የብረት ሜትሮዮይትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው)
3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)

👉 ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው። ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።

👉በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።

👉 በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።

👉 በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ ከሚባሉት የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል። ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ።

👉 የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር። ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።

2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013 በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ። ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ። በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

💥 ሌላው በሰማይ እየተቃጠሉ ሲሄዱ ሊታዪ የሚችሉት ሰው ሠራሽ ነገሮች
👉 ከአሁን በኋላ የማይሠሩ በጠፈር ውስጥ ያሉ ሰው ሠራሽ ነገሮች Space debris, space junk, orbital debris በመባል ይታወቃሉ።
ለምሳሌ፡-
👉 የድሮ ሳተላይቶች
👉 የሮኬት ክፍልፋዮች
👉 የፈነዱ ወይም የተጋጩ ተሽከርካሪዎች ወይም የተቆራረጡ ቁርጥራጮች ይገኙበታል።
👉 ከጠፈር ተልእኮ በኋላ የተጣሉ ቁሶች ናቸው።
💥 በግምት ከ10 ሴንቲ ሜትር በላይ ከ36,500 በላይ ቁሶች ሲኖሩ፤ ከ1-10 ሴ.ሜ በላይ 1 ሚሊዮን ቁርጥራጮች እና ከ1 130 ሚሊዮን የሚጠጉ ትናንሽ ቁርጥራጮች ይገኛሉ።

ሊያመጡ የሚችሉት አደጋዎች፡-

1) የሚሠሩ ሳተላይቶችን፣ ዐለም ዐቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ወይም የጠፈር መንኮራኩሮችን በመግጨት ሊጎዳ ይችላል።

👉 አንዳንድ ቁርጥራጮች ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ ከገቡ መሬት ላይ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
👉 ለምሳሌ ሰኞ ታኅሣሥ 21/ 2017 ወይም December 30, 2024, በኬንያ፣ ሙኩኩ መንደር ውስጥ ከሮኬት የመለያያ ቀለበት በመባል የሚታወቅ አንድ ትልቅ ብረታማ ነገር የተከሰከሰ ሲኾን ቀለበቱ በግምት 2.5 ሜትር ዲያሜትር እና 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንደ እድል ሆኖ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰም።

💥 ሌላው በተለያዩ ሀገራት ታዩ የሚባሉት የማይታወቁ በራሪ አካላት (UFO ወይም UAP) ዙሪያ ብዙ ቪዲዮዎች በYoutube ላይ የሠራሁትን ማየት ይቻላል።

💥 በሃይማኖት መጻሕፍት ስንመለከት በተለይ በዮሐንስ ራእይ ላይ ለቁጣ የሚወድቁ እንደ ችቦ የተቃጠለ የሚመስል እንደሚወድቅ እንዲህ ይጽፋል፦
✍️ “ሦስተኛውም መልአክ ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፥ በወንዞችና በውኃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።”
— ራእይ 8፥10-11
✍️ “ሁለተኛውም መልአክ ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባሕር ተጣለ፤ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ”
— ራእይ 8፥8
👍7936
💥 ስለዚኽ አንባቢዎች የራሳችሁን ምልከታ በአስተያየት መስጫው ላይ ማስቀመጥ ትችላላችኹ።
(ስለ ሥነ ፈለክ ለመረዳት አንድሮሜዳ ክፍል 1፤ አንድሮሜዳ ክፍል 2፤ ማዛሮት መጽሐፍን ያንብቡ)
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
👍5821😁3🥰1
ዛሬ ጥር 5 የጥር ወር ሙሉ ጨረቃ ነውና የዛሬዋን ሙሉ ጨረቃ አንሥታችሁ በፎቶ በቴሌግራም ላይ አጋሩኝ
90👍27🥰1
በዚህ አጋጣሚ ቀይዋ ፕላኔት ማርስ አጠገቧ ማየት ትችላላችሁ
👍178🥰1
ፕላኔት ቪነስና ሳተርን በዐዲስ አበባ ሰማይ በምዕራብ አግጣጫ ከምሽቱ 1:53
106👍35🥰12🔥7
የ6 ፕላኔቶች ሰልፍ ደረሰ
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
👉 በመላው ዓለም የምትገኙ የከዋክብት ተመልካቾች በጥር ወር በ2017 ዓ.ም. የ6 ፕላኔቶች፦
በኢትዮጵያዊ ሥነ ፈለክ አጠራር
👉 መሪህ፣ መሽተሪ፣ ዝሁራ፣ ሳተርን ወይም በውጪው አጠራር ማርስ፣ ጁፒተር፣ ቪነስ፣ ሳተርን፣ ዩራነስ፣ ኔፕቱን
ድንቅ ሰልፍን በሰማይ ላይ የምታዩበት ምርጥ ምሽት መጣ።

👉 ያለምንም መሣሪያ በቀላሉ በዐይን ማየት የምንችለው ማርስ፣ ጁፒተር፣ ቬኑስ እና ሳተርን ናቸው።
👉 ዩራኑስ እና ኔፕቱን ለመመልከት ግን ቴሌስኮፕ ያስፈልገናል።

💥 በመኾኑም ፀሓይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ደቡብ ምዕራብ አድማስ ስንመለከት ፕላኔት ቬኑስ እና ሳተርን ተቀራርበው ሲታዩ ያለምንም መሣሪያ በዐይን ብቻ ማየት ትችላላችሁ። ከሁለቱም ብሩህ የሆነችው ደግሞ ኮከበ ምዕራብ ወይም በአቡሻሕር አጠራር አስታርቦ ሸሽ ቬነስ ስትኾን በብርሃን አነስ ብሎ የሚታየን ሳተርን ነው።

👉 በሰማይ ላይ ከፍ ብለን በዐይናችን ስንመለከት ከቬኑስ ቀጥሎ በምሽት ሰማይ ላይ ሁለተኛው ደማቅ ብርሃን በኢትዮጵያዊ የሥነ ፈለክ አጠራር መሽተሪ ወይም ፕላኔት ጁፒተር በሠውር (ታውረስ) መናዝል በቀንዶቹ መኻከል በቀዩ የሠውር ዐይን በአልዴባራን ትይዩ ደምቆ በዐይን ይታያል።

👉 በምሥራቃዊው አድማስ አቅራቢያ ደግሞ ቀዩ ፕላኔት በኢትዮጵያ የሥነ ፈለክ ሥያሜ "መሪህ" ወይም ፕላኔት ማርስ በቀይ ቀለም በድምቀት አብርቶ ለሁሉም በዐይን ይታያል።

💥 በተለይ ኀሙስ ጥር 8 (January 16) ቀይ ፕላኔቱ ወደ ምድር በጣም ቅርብ በሆነ አቀራረብ ላይ ስለሚኾን መልክአ ማርስ በፀሐይ ሙሉ በሙሉ ያበራል። በዓመቱ ውስጥ ከየትኛውም ጊዜ የበለጠ ብሩህ ይሆናል እናም ሌሊቱን ሙሉ ይታያል። ክቡራን የከዋክብት ተመልካቾችና አድናቂዎች ማርስን ለማየት እና ፎቶግራፍ ለማንሣት ይህ በጣም ጥሩው ጊዜ ነው። መካከለኛ መጠን ያለው ቴሌስኮፕ ካላችሁ በፕላኔቱ ብርቱካንማ ገጽ ላይ አንዳንድ ጥቁር ዝርዝሮችን እንድታዩ ያስችላችኋልና ምሽታችሁን ተጠቀሙበት።

👉 በቴሌስኮፕ ከኾነ በዐይን ባይተዩም ፕላኔት ዩራነስ በጁፒተር አቅራቢያ ሲኾን ኔፕቲዩን ደግሞ ወደ ቬኑስ እና ሳተርን ቅርብ በመሆን አስደናቂ ሰልፍን ይሠራሉ።

👉 ፕላኔቶች ሁል ጊዜ በሰማይ ማየት የተለመደ ነው። ብዙም ያልተለመደው ግን ስድስት ብሩህ ፕላኔቶችን በአንድ ጊዜ ማየት ነው። ይህም በየዓመቱ የማይከሰት መኾኑ ነው። በሳይንስ "አሰላለፍ" (alignment) ይባላል።

👉 በተለይ ጥር 9 እና 10 (January 17 - 18) የፕላኔት ዝሁራ ወይም ቪነስ እና የፕላኔት ዙሀል ወይም ሳተርን ግጥጥሞሽ በሰማይ ላይ (በ2 ዲግሪ አካባቢ) ማለት ምድር ላይ ኾነን ስንመለከት በኹለት የጣት ስፋቶች ርቀት ተቀራርበው ለዐይይ ይታዩናል እንደማለት ነው።

👉 ከሳይንስ ዕይታ በተጨማሪ የፕላኔት ሰልፍ እጅግ ብዙ መንፈሳዊ ዝርዝር ፍቺዎችን የያዘ ሲኾን በዐጭሩ ለመግለጽ የጠፈር ስምምነትን፣ ዐዲስ ጅምርን እና መንፈሳዊ መነቃቃትን፣ የሰማያዊ ሥርዐት ፍጹምነትን፣ የሥጋ የነፍስ የመንፈስ ጽምረታዊ ሰልፍን፣ ያንጸባርቃል። በተለይ መንገዳችንን አጽናፈ ዓለምን ወደፈጠረ ወደ የብርሃን አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንድናደርግ ምልክት ይኾናሉ። በተለይ እያንዳንዱ ፕላኔት ያላቸው ፍቺ እጅግ በርካታ በመኾኑ በዚህ ውሱን ጽሑፍ ላይ መግለጽ አይቻልም።
በዚህ ላይ ያለውን ሰፊ መንፈሳዊ ምሳሌ ከፈለጋችሁ "ማዛሮት" የሚለውን መጽሐፌን ሳይንሳዊ ትርጉም ከፈለጋችሁ "አንድሮሜዳ 1 እና 2 መጻሕፍትን አንብቡ።

👉 እኔም በነዚሁ ቀናት ከወዳጆቼ ጋር በመኾን የሰማይ ምልከታ በማድረግ ምሽታችንን ተፈጥሮን በማድነቅ የፈጠራቸውን አምላክ በማመስገን የምናመሸ ሲሆን ለዐዳዲስ የሰማይ ተመልካቾች በቴሌስኮፕ የጁፒተርን 4 ጨረቃዎች፣ የሳተርንን ቀለበትን በማሳየት ያላቸውን ሳይንሳዊና መንፈሳዊ ጉዳዮችን ለሚመጡ ተመልካቾች በማስረዳት ምርጥ ምሽቶች ይኾኑልናል።
✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
👍13752🔥9🥰5👏1
2025/07/10 11:24:55
Back to Top
HTML Embed Code: