[በጥበብ እንድመቅ]
እጅግ ድንቅና እርስዎን ወደ ጥበብ ከፍታ የሚያደርሶት በብዙ ምስጢር የተመላው "የግእዝ ቀመረ ፊደል" (Geez Gematria) የኦንላይን ትምህርት
👉 በዶክተር ሮዳስ ታደሰ ሊጀመር ነው።
💥 ትምህርቱ፦ ቅዳሜ ለ1 ሰዓት ተኩል
💥 ሰዓት፦ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር
👉 1 PM EST (NY) Time
👉 10 AM PST (LA) Time
💥 የመጀመሪያው ሴሚስተር የካቲት 22 (March 1) - ግንቦት 23 (May 31)
💥 አስትሮኖሚ (ሥነ ፈለክ፤ ሥነ ከዋክብት)
✍️ በዶክተር ጌትነት ፈለቀ
✍️ እሑድ ሰዓቱ በተመሳሳይ
💥 ለበለጠ መረጃ (ለምዝገባ) በሰሜን አሜሪካ ላሉ፦
+12028484781 ወይም
(202) 643-3620 ይደውሉ።
በሀገር ውስጥ ላሉ ስልክ፦ 0911827336 ወይም 0925354271
👉 ለምዝገባ፦
🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happy to extend some discounts to our future students*
🔥 *For those who are applying from overseas [Europe, America, Canada, etc] ... PLEASE use these links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*
👉 *1. This Link gives you a $30 Discount for Numerology [Qemere Geez]*
https://buy.stripe.com/4gw2bA32V7Qy4hi001
👉 *2. This Link gives you a $30 Discount is for Astronomy [Sine-Feleg]*
https://buy.stripe.com/bIYdUi5b35Iq8xyeUW
👉 *3. This Link gives a $90 Discount for those who are taking both Courses*
https://buy.stripe.com/00g5nM6f75Iqg003cf
ይጠቀሙ።
👉 በሕይወት ዘመንዎ ከጥበብ ጋር የሚገናኙባት ዕለት ምርጥ ናት። ይመዝገቡ ለጥበብ ወዳጆችም ሼር ያድርጉ።

👍57🔥4👏4
"እግዚአብሔር ከጥበብ ጋር ከሚኖር ሰው በቀር የሚወድደው የለምና" (መጽሐፈ ጥበብ 7:28)
👍75❤53
"ስሙ አንድ ነው። ምሰሶዎቹ 2 ናቸው። ኃይሉ 3 ነው። ቅርጹ 4 ነው። ነጸብራቁ 8 ይሰጣል። ለ3 ሲባዛ 24 የጥበብ መናብርት (ዙፋኖች) ይሰጥሃል። በእያንዳንዱ ዙፋን ላይ 3 ጨረሮች ያሉበት ዘውድ ያርፍበታል"
(መጽሐፈ መራኁተ ሰሎሞን)
(መጽሐፈ መራኁተ ሰሎሞን)
👍85❤36🥰3
🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happily extending some discounts to our future students*
🔥 *If you are applying from thee USA, PLEASE use the links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*
👉 *1. This Link gives you a $30 Discount for Qemere Geez I [Geez Gematria]*
https://square.link/u/0159Z1RY
👉 *2. This Link gives you a $30 Discount for Sine-Felek I [Astronomy]*
https://square.link/u/ZKoKVCcK
👉 *3. This Link gives an additional $90 Discount for those who are taking both Courses*
https://square.link/u/1IfOhLnQ

checkout.square.site
Qemere Geez I [Geez Gematria] taught by Dr Rodas Tadese - Alpha Bete-Geez
description
❤27👍25
[ዓለምን እያነጋገረው ስላለው ስለ 2024 YR4 አስትሮይድ ዐጭር መረጃ]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ የሕዋ ዓለት (አስቴሮይድ) እየመጣ እንደኾነ በመሠራጨቱ ብዙዎች ይኽ የሚሠራጨው መረጃ እውነት ነው ወይስ አይደለም? የሚሉ ብዙ መልእክቶች በውስጥ መሥመር በመላካቸው ትክክለኛው መረጃን ለማጋራት ወደድኹ።
👉 አስትሮይድ 2024 YR4፣ በ100 እና 300 ጫማ (40 እና 90 ሜትር) ስፋት መካከል ያለ ሲኾን በተመራማሪዎች የታየው እ.ኤ.አ በታኅሳስ 27፣ 2024 ዓ.ም. ላይ ነበረ።
👉 በሃዋይ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ፈለክ ተመራማሪ የሆኑት ጆን ቶኒ ለሳይንቲፊክ አሜሪካዊ እንደተናገሩት ምድር ላይ ቢወድቅ ፍንዳታው ከ10 ሜጋቶን ቦምብ ጋር እኩል ሊሆን ይችላል። ወይም ከሄሮሺማ ላይ ከወደቀው ቦምብ 500 ዕጥፍ እንደማለት ነው። በሦስት ወይም በአራት ኪሎ ሜትር ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል። ምናልባት እስከ 10 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ነገር ሁሉ ይሰባብራል›› ብሏል።
👉 አስትሮይድ 2024 YR4 ምድርን ሊመታ የሚችልበት እድል በ1.3% አለ፣ በናሳ ስሌት መሠረት ይኽ የሚከሰተው ግን አሁን ሳይኾን እ.ኤ.አ በታኅሳስ 22, 2032 ማለትም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ረቡዕ ታኅሣሥ 13/ በ2025 ዓመተ ምሕረት ከ8 ዓመት በኋላ ነው።
👉 ምናልባት ምድር ላይ ቢወድቅ ምሥራቃዊ የፓስፊክ ውቅያኖስ፣ ሰሜናዊው የደቡብ አሜሪካ ክፍል ፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ ፣ አፍሪካ ፣ የአረቢያ ባሕር ፣ ደቡብ እስያ ይገመታል።
👉 መልካሙ ዜና ግን 2024 YR4 በደኅና በዚህ ቀን በምድር ላይ በሰላም የማለፍ እድሉ 99% ያህል ነው። 1.3% የመጋጨት እድሉ ትንሽ ሊመስል ቢችልም፣ ለሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ግን በቁም ነገር እንዲያስቡበት ከበቂ በላይ ነው።
👉 እንደውም ከ8 ዓመት በኋላ ከሚመጣው አስትሮይድ 2024 YR4 ይልቅ አስትሮይድ 99942 አፖፊስ በመባል የሚታወቀው 1,200 ጫማ (370 ሜትር) ስፋት ያለው፣ በትልቅነቱ ምክንያት “ከተማ አውዳሚ” ተብሎ የተመደበ ሲኾን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በሚያዝያ 13, 2029 በእኛ አቆጣጠር ደግሞ ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም መሬትን በ19,400 ማይሎች ወይም 31,200 ኪሎሜትር ያልፋል። ይህም ከጂዮስቴሽነሪ ሳተላይቶች ይልቅ በመቅረብ ሲኾን በዐይን የመታየት ዕድል ይኖረዋል።
👉 በጊዜው አፖፊስም ቢሆን ከመሬት ጋር የመጋጨት እድሉ 2.7% ብቻ ነው። እንደ ጎርጎርዮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2029፣ ቀጥሎ በ2036 ከዚያም በ2068 ላይ አፓፊስ በዑደት እንደሚመለስ ታውቋል። ቢኾንም 2.7% እንደ ቀላል የሚቆጠር አይደለም (ስለ አስትሮይድ አፓፊስ አንድሮሜዳ ቁጥር 2 መጽሐፍን ያንብቡ)።
👉አደጋን ካሰብን እ.ኤ.አ. በ1908 የቱንጉስካ ክስተት ሲሆን ከ30-50 ሜትር የሚደርስ ሜትየር በሳይቤሪያ ላይ ፈንድቶ በ770 ስክዌር ማይል የሚገኙ 80 ሚሊዮን ዛፎችን እንዳወደመ የሚታወቅ ነው።
👉 እ.ኤ.አ የካቲት 15፣ 2013 ሩሲያ ቼልያቢንስክን የመታው ሜትየር መጠኑ (ከ17 እስከ 20 ሜትሮች ወይም ከ56 እስከ 66 ጫማ) በዲያሜትር ይገመታል። በክስተቱም 1,500 የሚያህሉ ሰዎችን አቁስሎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበረ። አስትሮይድ 2024 YR4 ግን በዲያሜትር ከ40 ሜትር እስከ 90 ሜትር (ከ130 ጫማ እስከ 300 ጫማ አካባቢ) መካከል ነው።
👉 በቼልያቢንስክ ላይ የተለቀቀው ኃይል ወደ 500 ኪሎ ቶን TNT ተመሣሣል ተብሎ ይገመታል—ከሂሮሺማ አቶሚክ ቦምብ በ30 እጥፍ ይበልጣል። 2024 YR4 ቢመታ ከ8 እስከ 10 ሜጋ ቶን ያህል ሊሆን ይችላል ሲሉ በአሪዞና ዩኒቨርሲቲ የካታሊና ስካይ ጥናት ዳይሬክተር የሆኑት ካርሰን ፉልስ ተናግረዋል። ከእንደዚህ ዓይነት ተጽእኖ የሚፈነዳ ሞገድ የብዙ ማይል ራዲየስ ይኖረዋል።
👉 እንዲህ ዓይነት ክስተት ለአብዛኛው አስፈሪ ቢኾንም ለከዋክብት ተመራማሪዎች ግን በቅርበት ለማጥናትና ለማየት ምቹ ስለሚኾኑ ታላቅ ዕድል ነውና እንደ መልካም ዜናም ይታያል። በመጨረሻም ሰማይን ማየት፣ ሰማይን መመልከት እንውደድ እንልመድ በማለት ስለ ሰማያዊ አካላት የተጻፉትን
አንድሮሜዳ ቁጥር 1 እና 2/ ማዛሮትን እንድታነቡ በመጋበዝ ጽሑፌን አበቃኹ።
✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (የ29 መጻሕፍት ጸሐፊ)

👍54❤28👏2
በጥበብ እንድመቅ
እጅግ ድንቅና እርስዎን ወደ ጥበብ ከፍታ የሚያደርሶት በብዙ ምስጢር የተመላው "የግእዝ ቀመረ ፊደል" (Geez Gematria) የኦንላይን ትምህርት
👉 በዶክተር ሮዳስ ታደሰ ሊጀመር ነው።
👉 በዶክተር ጌትነት ፈለቀ (ሥነ ፈለክ)
💥 ትምህርቱ፦ ቅዳሜ ለ1 ሰዓት ተኩል
💥 ሰዓት፦ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር
👉 1 PM EST (NY) Time
👉 10 AM PST (LA) Time
💥 የመጀመሪያው ሴሚስተር የካቲት 22 (March 1) - ግንቦት 23 (May 31)
💥 ለበለጠ መረጃ (ለምዝገባ) በሰሜን አሜሪካ ላሉ፦
(202) 643-3620 ይደውሉ።
በሀገር ውስጥ ላሉ ስልክ፦ 0911827336 ወይም 0925354271
👉 ለምዝገባ በውጪ ላሉ፦
🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happily extending some discounts to our future students*
🔥 *If you are applying from out side of Ethiopia, PLEASE use the links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*
👉 *1. This Link gives you a $30 Discount for Qemere Geez I [Geez Gematria]*
https://square.link/u/L21tk5AM
👉 *2. This Link gives you a $30 Discount for Sine-Felek I [Astronomy]*
https://square.link/u/eOBVh9L1
👉 *3. This Link gives an additional $90 Discount for those who are taking both Courses*
https://square.link/u/1IfOhLnQ
👉 በሕይወት ዘመንዎ ከጥበብ ጋር የሚገናኙባት ዕለት ምርጥ ናት። ይመዝገቡ ለጥበብ ወዳጆችም ሼር ያድርጉ።
እጅግ ድንቅና እርስዎን ወደ ጥበብ ከፍታ የሚያደርሶት በብዙ ምስጢር የተመላው "የግእዝ ቀመረ ፊደል" (Geez Gematria) የኦንላይን ትምህርት
👉 በዶክተር ሮዳስ ታደሰ ሊጀመር ነው።
👉 በዶክተር ጌትነት ፈለቀ (ሥነ ፈለክ)
💥 ትምህርቱ፦ ቅዳሜ ለ1 ሰዓት ተኩል
💥 ሰዓት፦ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር
👉 1 PM EST (NY) Time
👉 10 AM PST (LA) Time
💥 የመጀመሪያው ሴሚስተር የካቲት 22 (March 1) - ግንቦት 23 (May 31)
💥 ለበለጠ መረጃ (ለምዝገባ) በሰሜን አሜሪካ ላሉ፦
(202) 643-3620 ይደውሉ።
በሀገር ውስጥ ላሉ ስልክ፦ 0911827336 ወይም 0925354271
👉 ለምዝገባ በውጪ ላሉ፦
🔥 *Considering the high volume of future Students who have expressed interest to take these Online Courses, we are happily extending some discounts to our future students*
🔥 *If you are applying from out side of Ethiopia, PLEASE use the links shown below. Each link Registers you to the corresponding course, or courses.*
👉 *1. This Link gives you a $30 Discount for Qemere Geez I [Geez Gematria]*
https://square.link/u/L21tk5AM
👉 *2. This Link gives you a $30 Discount for Sine-Felek I [Astronomy]*
https://square.link/u/eOBVh9L1
👉 *3. This Link gives an additional $90 Discount for those who are taking both Courses*
https://square.link/u/1IfOhLnQ
👉 በሕይወት ዘመንዎ ከጥበብ ጋር የሚገናኙባት ዕለት ምርጥ ናት። ይመዝገቡ ለጥበብ ወዳጆችም ሼር ያድርጉ።
checkout.square.site
First Semester Qemere Geez I [Geez Gematria] taught by Dr Rodas Tadese - Alpha Bete-Geez
description
👍69❤22👏12
[የካቲት 5 (February 12) በዓሏ የሚታሰብላት ሉቃስ የሣላት ከጒንጯ ደም የሚፈስሳት ተአምር አድራጊዋ የእመቤታችን ሥዕል እጅግ አስደናቂ ታሪክ (መነበብ የሚገባው)]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥ የዚኽች አስደናቂ ሥዕልን ድንቅ ታሪክ ከመጻፌ በፊት ለወንጌል አገልግሎት ከ8 ዓመት በፊት ወደ ኖርዌ በኼድኊ ጊዜ ከጒንጮቿ ላይ ደም የሚፈስሳት ኾና የምትታየው ኹላችንም የምናውቃት የእመቤታችንን የታተመች ሥዕሏን በአንድ ወንድም ቤት ውስጥ በክብር ባማረ መልኩ ተቀምጣ አይቼ በመደነቅ፤ ሥዕሏን ከየት እንደገዛት ጠየቅኹት።
❤ እርሱም በኖርዌ የዕቃ መሸጫ አጠገብ ወድቃ አግኝቶት ቶሎ ብሎ በገንዘቡ ገዝቷት፤ ቤቱ ወስዶ መብራት አብርቶ፤ ሽቱ ረጭቶ በክብር ባስቀመጣት ጊዜ ሌሊቱን ኹሉ እጅግ ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኝ የዕጣን ሽታ ሲሸተውና የማዕጠንትና የምስጋና ድምፅ ሲሰማ እንዳደረ ነገረኝ። እኔም ልዑል እግዚአብሔርን በማመስገንና የተቀደሰ ሥዕሏን በመሳለም፤ ጉንጮቿ ላይ ያለውን ታሪክ ታውቀዋለህ? ብዬ በጠየኩት ጊዜ ቀዩ ነገር በአጋጣሚ ከሥዕሉ ጋር ዐብሮ የተሣለ እንደመሰለው ብቻ ነገረኝ።
❤ እኔም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተለይ በቅዱሳት ሥዕላት ትውፊት የሚነገረውን የሥዕሏን ታሪክና ያደረገችውን ተአምር ይልቁኑ ስትሣል ጉንጯ ላይ ለምን የደም ነጠብጣብ እንደሚደረግ ነገርኩት፡፡ ልጁ የገዛት ሥዕል ግን ዋናዋ የጥንቷ ናት ማለቴ ሳይኾን ያው አኹን የምንጠቀምባት ፖስት ያደረግኳት ዓይነት በዚያች በዋናዋ አምሳል የታተመችውንና የምትሸጠውን ሥዕል እንደኾነች ለማስታወቅ እፈልጋለኊ።
♥ ይኽን በጥንት ጊዜ የነበራትን የተቀደሰ ታሪክ ለኹሉም መጻፍ እንዳለብኝ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበርና እነሆ ጊዜው ገጥሞልኝ በየካቲት 4 በመላው ዓለም በዓሏ የሚታሰብላትን ታሪኳን በበዓሏ ዕለት እነሆ ብያለኊ፡፡
♥ ስለዚኽች ድንቅ ተአምር አባ ጽጌ ድንግል አስቀድሞ በማሕሌተ ጽጌ ላይ እንዲኽ ብሏት ነበር፡-
“ሥዕልኪ ማርያም ጸገየት ሥጋዌ
ከመ ዕፀ ገነት ትጸጊ ጽጌያተ ለሥርጋዌ
ሣሕለ ተአምርኪ እኩን ለትውልደ ትውልድ ዜናዌ
ቅብዕኒ ሐፈ ሥዕልኪ ወፈውስኒ እምደዌ
እስመ በኅምዙ አቊሰለኒ አርዌ”
(የገነት ዛፍ አበቦችን ለሽልማት እንደምታብብ ማርያም ሥዕልሽ ግዘፍን አበበች (ሥጋን የለበሰች መስላ ታየች)፤ የተአምርሽን ዜና ለልጅ ልጅ የምነግር እኾን ዘንድ የሥዕልሽን ወዝ ቀቢኝ፤ ከበሽታም አድኚኝ፤ አባብ አውሬ በመርዙ በኀጢአት አቊስሎኛልና) በማለት ተማፅኗታል፡፡
♥ ይኸውም ከ829-842 ዓ.ም. በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት ተነሳሥቶ ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮቹ በርሱ ትእዛዝ በእያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት ፍተሻ ያደርጉ ነበር፤ በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች፤ ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡
♥ የከሓዲው ንጉሥ ወታደሮቹም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ፤ ከመካላቸውም አንዱ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕሏን በያዘው ጦር ጒንጯ ላይ ወጋት፡፡ ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ፤ ከተወጋው ከአምላክ እናት ፊት ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡
♥ ይኽን ግሩምና ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮቹ ደንግጠው ሸሽተዋል፤ ሴቲቱም ይኽነን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራትን አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ ዐደረች፤ በነጋታውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጒንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕሩ ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘችና አስቀመጠቻት።
♥ ሥዕሏም በባሕሩ ላይ በመንሳፈፍ በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች፡፡ ጊዜያቶች ካለፉ በኋላ ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ ፀሓይ ሲያበራ ተመለከቱ፡፡
♥ ይኽም ተአምር ለተካታታይ ቀናቶች በመቀጠላቸው በዚያ የተቀደሰ ተራራ በምናኔ ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድ ላይ ተሰባስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል በላዩ ላይ ወደ ተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመውረድ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሷት አልተቻላቸውም፡፡
♥ በዚያው የአይቮሪዮን ገዳም ረድእ (የጉልበት አገልጋይ) ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል Gabriel the Iberian የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው፤ በተመሳሳይም ለአባ ገብርኤል እመቤታችን ተገልጣለት “ወደ ባሕሩ ኺድ፤ ማዕበሉንም ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ፤ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለኝን ፍቅርና ርኅራኄ ምስክር እንዲኾኑ፤ ሥዕሌን ከባሕር አውጣ” በማለት ነገረችው፡፡
♥ ከዚያም በአቶስ ተራራ ያሉት መናንያን ኹሉ አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፣ እያመሰገኑ፤ በማዕጠንታቸው ዕጣን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኼዱ፤ አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ ውስጥ በመግባት በናፍቆት ኾኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን በደረቱ ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕር ዳርቻ ይዟት ወጣ፤ እነርሱም በደስታ ኾነው እጅ ነሷት፡፡
♥ ከዚያም ማግሰኞ በጠዋቱ ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ ላይ በሚያመሰግኑበት ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው፡፡ ከዚያም የእመቤታችንን ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኼድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት፡፡
♥ ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ የእመቤታችን ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኟትም፤ ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገኟት፤ እነርሱም መልሰው በቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገኟት ነበር።
❤ ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት “ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው፤ ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም፤ የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን እኔን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ልጋርዳችኊ እንጂ፤ ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም” አለችው፡፡
❤ በዚህ ምክንያት ሥዕሏ በነገረ መለኮት ሊቃውንት "አቃቢተ ኆኅት" (ደጃፍን የምትጠብቅ) Όδηγήτρια Panagia Portaitissa ("She who resides by the door" or "Keeper of the gate" ትባላለች።
♥ መነኮሳቱም ይኽነን ሰምተው በእጅጉ በመደሰት ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ክብር በገዳሙ በር አጠገብ አነስ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ገባሪተ ተአምራት ወመንክራት (ድንቅ ተአምር አድራጊዋን) የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን ወደ ውስጥ አገቧት፤ የተቀደሰች የሥዕሏ መጠሪያም “የአይቬሮኗ የአምላክ እናት” (the Iviron Theotokos) ስትባል በግሪክ “ፓርታኢቲሳ” Παναγία Πορταΐτισσα; ትባላለች። ዛሬም የተቀደሰ ሥዕሏ በግሪክ በአቶስ ተራራ ላይ በሚገኘው በአይቬሮን ገዳም ውስጥ

YouTube
ከጉንጯ ደም የሚፈሳት ሥዕለ ማርያም በኢትዮጵያ ዐይን አበራች
ሽቱ ታፈልቃለች/ የአይቬሮኗ ማርያም/ ደጃፍ ትጠብቃለች
❤44👍40🥰32👎3
ትገኛለች።
❤ ከዚያም አካቲስት በሚባል ለአምላክ እናት በተደረሰ ምስጋና "ለጻድቃን የገነትን ደጆች የምትከፍት የተባረክሽ በር ጠባቂ ሆይ ደስ ይበልሽ።" የሚል ምስጋና ተደርሶላታል።
♥ ከዚያም በአይቬሮን ገዳም ያለችው የእመቤታችን ሥዕል ድንቅ ተአምር በዓለም ኹሉ ላይ ከተሰማ በኋላ በረከቷን ለማግኘት ክርስቲያኖች ወደዚያች ገዳም መኼድን ጀመሩ፤ ይኽ የተቀደሰ ሥዕሏና ታሪኳም ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለሙ ኹሉ ላይ ተሰማ፤ ምእመናንም ይህንን ሥዕሏን በመላው ዓለም በማሣል መማፀን ጀመሩ። ዛሬም በዚህች ሥዕል ምእመናን ይማፀኑበታል፡፡ የዚኽችን የተቀደሰ ታሪክ የያዙ በርካታ ቅዱሳት ሥዕላት ኦንላይን ላይ ስላሉ ጉግል በማድረግ ማየት ትችላላችኹ፡፡ በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ሰበታ ጌቴሴማኒ ማርያም ገዳም በጼዴንያ ማርያም በክብር የተቀመጠች ሥዕሏን ለመመልከት ችያለሁ። አኹን ፓስት ያደረኳትን የእመቤታችንን ሥዕል አቶስ አይቬሮን ገዳም ያለችውን ሥዕል ስካን በማስደረግ በስጦታ የላከችልኝን ዶክተር ራሔል ዓለሙን አመሰግናለኹ፡፡
❤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ዐይናቸው ማየት አቁሞ የነበሩት ወይዘሮ አልማዝ ስለዚኽች የተቀደሰች ሥዕል ታሪክ ልጆቻቸው ሲያነቡላቸዎ ሥዕሏን ፕሪንት እንዲያደርጉላቸው በመናገር ዐይናቸው ላይ ማደረጉት ጊዜ የጠፋ ዐይናቸው በርቶላቸው ይኽንን ምስክርነታቸውን በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳምና በሰአሊተ ምሕረት ደብረ ምጥማቅ ማርያም ወክርስቶስ ሠምራ ቤተ ክርስቲያን በነበረን የእመቤታችን ጉባኤ የተቀደሰ ሥዕሏን አጅበን ተባርከንበታል። እርሳቸውም በዐውደ ምሕረት ላይ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
https://youtu.be/ppsVn-IAFH8?si=v1vf25ywm043cnYx
❤ ለአባ ገብርኤል የተለመነች እና በረከቷን እንዳሳደረችበት ዛሬም በረከቷ ምንም ሳንይዝ ባዷችንን ጥለነው በምንሄደው በዚኽ ኃላፊ ጠፊ ዓለምና፤ በማያልፈውም በወዲያኛውም ዓለምም እንዳይለየኝ በመማፀን አባ ጽጌ ድንግል ስለዚኽች ሥዕል በማሕሌተ ጽጌ ላይ ባመሰገናት ምስጋና፦
“ቦ አመ ትትረከብ ምስለ ቃለ ነገር ጥዑም
ወቦ አመ ትትረአይ በለቢሰ አባል ልምሉም
ሥዕልኪ ማርያም ጽጌ ተአምር አዳም
ወአመ ዘበጣ በሰይፍ አይሁዳዊ ርጉም
እምኔሃ አንጸፍጸፈ ደም”
(ሥዕልሽ ቃልን ደስ ከሚያሰኝ ነገር ጋራ የምትገኝበት ጊዜ አለ፤ የለመለመ አካልንም ለብሳ የምትታይበት ጊዜ አለ፤ ማርያም ሥዕልሽ የተአምር አበባ ናት፤ ርጉም አይሁዳዊ በሰይፍ በመታት ጊዜ ከርሷ ሥዕል ደም ተንጠባጠበ) በማለት አመሰግናታለሁ፡፡
❤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ክብር ዘወትር በምታቀርበው የመልክአ ሥዕል ምስጋና ስለዚኽች ሥዕል ክብር፦
"ሰላም ለሥዕልኪ ቦ ጊዜ ዘትትናገር
ወቦ ጊዜ ዘትክዑ ደመ ተአምር"
(አንዳንድ ጊዜ የምትናገር፤ አንዳንድ ጊዜ የተአምር ደምን ለምታፈስ ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) በማለት ውዳሴ ታቀርባለች።
❤ በመጨረሻም በጽሑፌ የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በምልጃሽ እና በቃል ኪዳንሽ የማይጠገበው በረከትሽን ዕጽፍ ድርብ አድርገሽ አሳድርቢን በማለት "በኢትዮጵያ ወግብጽ ወሶርያ በአንጾኪያ ወሮም
ለሥዕላትኪ ዘሀለዋ ማርያም ሰላም"
(በኢትዮጵያና በግብጽ፤ በሶርያ በአንጾኪያና በሮም ላሉ ሥዕሎችሽ ማርያም ሆይ ሰላም እላለሁ) በማለት በሊቁ ሰላምታ ለከበረ ሥዕሏ የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ ጽሑፌን አበቃለሁ።
❤ እስቲ እናንተም በተቻላችኊ መጠን በተሰማችኊ ልክ አመስግኗት። እመቤታችንም በዓለም ላይ ከፈሰሰው መቅሠፍት በቃል ኪዳኗ ትጠብቀን።
(ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ) በድጋሚ ፓስት የተደረገ

❤116👍42🥰16
እንደሚታወቀው የየካቲት ሙሉ ጨረቀ ከ6:35 PM ወይም በኢትዮጵያ ሰዓት ከ12:35 በኋላ ዛሬ ረቡዕ ትወጣለችና ከያላችሁበት ሀገር በምሽት የምታነሡትን ፎቶ https://www.tg-me.com/+xN518gdGKvswNzE0
ላይ መላክ ትችላላችሁ።
(ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
ላይ መላክ ትችላላችሁ።
(ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
Telegram
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (Dr Rodas)
You’ve been invited to join this group on Telegram.
👍41❤12🔥5
Forwarded from Zemenai
እንደምን ከረማችሁ የግዕዝ ቀመር ቤተሰቦች ::
እህቶቻችን እግዚአብሔር ይስጥልን በእዉነት ሁሌም በመሪነት በመቆም ለምታገለግሉን ::
የእኔ የግዕዝ ቀመር ግንዛቤ እንደገለጻችሁት ከፊደል በላይ ነው :: ግዕዝ ቀመር የራሱ ዓለም ያለው ሆኖ ነው የተሰማኝ :: ወደ ግዕዝ ዓለም ስገባ ይችን ዓለም ትቼ በፊደላቱ ዉስጥ በመንሸራሸር ታሪክ አነባለሁ :: ግዕዝ ሕይወት ያለው መሳሪያ ነው ብል ማጋነን አይሆንም። ግዕዝ የፍቅርም ቋንቋ ሆኖ ነው ያገኘሁት :: ልጄን የተማርኩትን ላካፍለው ስሞክር ለእኔ የበለጠ የሚገለጽልኝ ነገር አለ :: አንዳንድ ጊዜ በመገረም ፣ በመደንገጥ ቆም ብዬ አስበዋለሁ ። የግዕዝ ቀመር በጣም ኃይል ያለው በመሆኑ ራስን ለበለጠ ደረጃ ማዘጋጃትም ያስፈልጋል :: ዘመኑ የነፋስ ዘመን በመሆኑ የመጀመሪያውን ክፍል ብቻ ነው የውስድኩት እናም recording'ኦቹን ሁሌ ቃል በቃል ነው ደጋግሜ የምሰማው ::
መምህራችንን መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስን ቸሩ አምላካችን ይጠብቅልን :: የአገልግሎት ዘመኑንም ይባርክልን ::

👍78❤30
ትላንት ከመላው ዓለም የሙሉ ጨረቃ ፎቶ የላካችሁልኝን በእጅጉ አመሰግናለሁ እጅግ በእናንተ ደስ ብሎኛል። ሰማይን መመልከት ከፍታ ነው።
የሚቀጥለው የመጋቢት ወር ሙሉ ጨረቃ ግን በተለየ መልኩ ደም መስላ የምትታይበት ክስተት ስለሚሆን ቀርጾ ለማስቀረት ሆነ ለመመልከት ከአሁኑ በጉጉት የምንጠብቀው ይሆናል።
(ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
የሚቀጥለው የመጋቢት ወር ሙሉ ጨረቃ ግን በተለየ መልኩ ደም መስላ የምትታይበት ክስተት ስለሚሆን ቀርጾ ለማስቀረት ሆነ ለመመልከት ከአሁኑ በጉጉት የምንጠብቀው ይሆናል።
(ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
👍109❤38🥰11🔥1👏1
ዛሬ ኀሙስ ከምሽቱ 3 ሰዓት (9 PM) ላይ Manyazewal Eshetu Youtube ላይ ኒኮላ ቴስላ
"If you want to find the secrets of the universe, think in terms of energy, frequency, and vibration."
(የአጽናፈ ዓለምን ምስጢር ለማግኘት ከፈለክ በኃይል፣ ድግግሞሽ (ዝውተራ) እና ንዝረት በኩል ዐስብ) ብሎ በተናገረው አስደናቂ አባባል እጅግ ምርጥ ፓድካስት ይኖረኛልና በሰዓቱ ይህ ምርጥ መርሐ ግብር አያምልጦት።
ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

👍81❤42