❖✔ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዚኽ የፍልሰታ ሱባኤ ለምእመናን ስለ መገለጧ
❖✔ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖✔ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝ ፵፬፥፲፪ ላይ “ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር” (የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ኹሉ በፊትሽ ይማለላሉ) በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት ብዙዎች ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ብዙዎቹም ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው እጅግ አስደናቂ ውበቷን አይተዋል፡፡ ከነዚኽ አባቶች ውስጥ ቅዱስ ኤፍሬም፣ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ይሥሐቅ፣ አባ ቴዎፍሎስ እና በደብረ ምጥማቅ የነበሩ ምእመናን ሌሎችም ብዙዎች ንጹሓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል፡፡
❖✔ የመልክአ ማርያም ደራሲም የአምላኩን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ በናፍቆት ኾኖ፡-
“ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ
ዘያበርህ ወትረ
ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ
አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ
ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ”
(ኹልጊዜ (ዘወትር) የሚያበራ ፀሓይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ ፍቅረኛዬ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡
❖✔ ቅዱስ ያሬድ አባታችንም በማይ ኪራሕ ሳለ እመቤታችን ተገልጻለት ፊቷን ለማየት ታድሏልና ይኽነን በዐይኑ ያየውን ውበቷን በድጓው ላይ እንዲኽ ሲል ጽፎታል፡-
“አይ ይእቲ ዛቲ እንተ ትወርድ እምሰማይ፤ ብርህት ከመ ፀሓይ፤ አዳም ቆማ ወክሣዳ ከመ አርማስቆስ፤ መዐዛ አፉሃ ከመ ኮል” (ከሰማይ የምትወርደው እንደ ፀሐይም የምታበራው ርሷ ማን ናት! አንገቷ እንደ ግንብ ቀጥ ያለ ነው፤ የአፏም መዐዛ እንደ እንኮይ ነው) በማለት በተመስጦ የተመለከተውን ውበቷን ተናገረ፡፡
❖✔ ይኽ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ቅዱስ ያሬድ በዚኽ ሳያበቃ በመላእክት እየተመሰገነች ስለተገለጸችለት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ያየውን የውበቷን ነገር ሲናገር፦
✍ “እምኀበ መላእክት ትሴባሕ አዳም ሥና፤ መዐርዒር ቃላ ወኲሉ ነገራ በሰላም … እምወርኅ ወእምፀሓይ ይሤኒ ላሕያ …ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ወከመ ኮል መዐዛ አፉሃ ወከመ ሮማን ቂሐተ መላትሒሃ … " (በመላእክት ትመሰገናለች፤ ደም ግባቷ ያማረ ነው፤ ቃሏ እንደ ማር የጣፈጠ፤ ነገሯ ኹሉ በሰላም የተመላ ነው … ውበቷ ደም ግባቷ ከጨረቃና ከፀሓይ ይልቅ ያምራል፤ ከንፈሮቿ ፍሕሶ እንደሚባል አበባ ቀይ ናቸው፤ የጒንጯ ቅላትም እንደ ሮማን ቅርፍት ነው) እያለ ሊቁ ማሕሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ ይመሰክርላታል፤ አይ መታደል! አይ መባረክ!
✔❖ ውዳሴዋ በእጅጉ የበዛለት ስለ ርሷ ኆኅተ ብርሃን፣ እንዚራ ስብሐት፣ መዐዛ ቅዳሴ፣ አርጋኖን፣ ሰላምታ፣ መዝሙረ ድንግል እና ሌሎችም ብዙ ብዙ ለመሰከረላት ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ብዙ ጊዜ እየተገለጸችለት በዐይኑ ተመልክቷታልና የመልኳን ውበት በአርጋኖን ዘቀዳሚት ላይም፡-
✔“አልቦ ዘይሤንዮ ለላሕይኪ ኢ ጎሕ ወኢበርህ ኢ ፀሓይ ወኢወርኅ ኢ ዋካ ወኢጸዳል አልቦ ዘይበርህ እምጸዳለ ዐይንኪ ኢ ቤዝ ዘያንበለብል በገጸ ሰማይ ወኢባሕርይ ዘያንጸበርቅ ዲበ ርእሰ ነገሥት ወአልቦ ዘይምዕዝ እምጼና አንፍኪ ወእምጼና አልባስኪ ኢከልበኔ ወኢሐንክሶ ወኢአስጰዳቶስ ወኢናርዱ ቅድው ዘዕጹብ ሤጡ ወመዐድም ኲለንታኪ ወክሉል በጸጋ መንፈስ ቅዱስ”
✔(ደም ግባትሽን የሚያምረው (የሚበልጠው) የለም፤ የንጋት ውጋገንም ቢኾን! ብርሃንም ቢኾን! ፀሓይም ቢኾን! ጨረቃም ቢኾን! ወዝሽን ለዛሽን የሚመስለው የለም፤ ከዐይንሽ ብርሃን ይልቅ የሚበራ የለም፤ በሰማይ ፊት የሚንቦገቦግ ኮከብም ቢኾን! በነገሥታት ራስ ላይ የሚያንጸባርቅ ዕንቊም ቢኾን! ከአፍንጫሽም መዐዛ ከልብሶችሽም ሽታ የበለጠ የሚሸት የለም፤ ከልበኔም ቢኾን! ሐንክሶም ቢኾን! አስጰዳቶስም ቢኾን! ዋጋው ውድ የኾነ ናርዱ የሚባል ሽቱም ቢኾን! ኹለንተናሽ ያማረ ነው በመንፈስ ቅዱስ ጸጋም የተጋረደ ነው) ብሏታል፡፡
✔❖ ልክ እንደ ርሱ የአምላክን እናት ፊቷን ለማየት የተመኙ ብዙዎች ቅዱሳን ነበሩ፤ ለምሳሌም ያኽል ከቅዱሳን አበው መኻከል አባ ይሥሐቅ እመቤታችንን በፍጹም ልቡናው ከመውደዱ የተነሣ ከሠርክ ጸሎት በኋላ ሌሎች መነኮሳት ለመኝታ ወደ የበኣታቸው ሲኼዱ ርሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመኼድ በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቆሞ በፊቷ እየተማለለ ሦስት መቶ ስግደትን እየሰገደ፤ በእያንዳንዱ ስግደቱ ላይ “ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ” (ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትኽን አሳየኝ) እያለ በመጸለይ ለሰባት ዓመት ከቈየ በኋላ፤ በሰባተኛው ዓመት በታላቅ ግርማ ተገልጻለት የአምላክን እናት ፊት ለማየት በቅቷል፤ ርሷም ምን እንደሚሻ ብትጠይቀው በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በመኾን የንግሥተ ሰማይ ወምድር የርሷን ገጽ ያዩ ዐይኖቹ ሌላ ነገርን ማየት እንደማይፈልጉና ከልጇ እንድታማልደው ብቻ እንደሚፈልግ ነግሯት፤ ርሷም ከሦስት ቀን በኋላ እንደሚያርፍ ክፍሉም ከርሷ ጋር መኾኑን ገልጻለት ባርካው ዐርጋ፤ መልኳን አይቶ በሦስተኛው ቀን ይኽ ቅዱስ አባት ዐርፏል፡፡
✔❖ የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛለት አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ተገልጻ ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት ለርሱም ትገለጽለት ዘንድ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፉ ላይ፡-
❖“አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ
ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ
ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ
ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሑ መዓልተ
ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ”
(የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለዐምስት ቀናት ያኽል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያኽል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው) በማለት ተማፅኗታል፡፡
❖✔ የእመቤታችን ታማኝ ወዳጅ አባ ጽጌ ድንግል በተመስጦ በመኾን እጅግ ድንቅ የኾነችውን የአምላክን እናት ሥዕል ካየ በኋላ ይኽነን የምስጋና ቃላት ለርሷ ያቀርባል፡-
“ሥዕልኪ ጽግይተ ላሕይ ዘከመዝ ትኤድም በዓለም
እፎ ይሤኒ በሰማይ ላሕየ ገጽኪ ማርያም
ሐሤተ ትእምርትኪ እጽገብ አስተርእዪኒ በሕልም
እስመ አውዐየኒ ነደ ፍቅርኪ ፍሕም
አጥፍኦቶ ዘኢይክል ዝናም”
(ማርያም ሥዕልሽ በዓለም እንዲኽ የምታበራ ከኾነ በሰማይ የፊትሽ መልክ ምን ያምር! አንቺን ከማየት የሚገኘውን ደስታ እጠግብ ዘንድ በሕልም ተገለጪልኝ፤ ዝናብ ሊያጠፋው የማይቻለው የፍቅርሽ እሳት አንድዶኛልና) ብሏል፡፡
❖✔ በመኾኑም በዚኽ ሱባኤ ሐዋርያት የአምላክን እናት አይተው እንደተደሰቱ፤ ዛሬም ለእኛ ለልጆቿ በረድኤት ትገለጽልን ዘንድ አበው ካህናት ሌሊቱን በሰዓታት ምስጋና፦
✍ “ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ” (ድንግል ሆይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ወደ እኔ ነዪ እኛን ትባርኪ ዘንድ (በእኛ ላይ በረከትን እንድታሳድሪ) በማለት ይማፀኗታል፤ እኛም የማይጠገበው ውዳሴዋን ቅዳሴዋን በመተርጐም የቅዱስ ኤፍሬም የአባ ሕርያቆስ እመቤት ትባርከን ዘንድ እንለምናታለን፡፡

❤49👍27🔥3
❖✔ በገዳም በበረሓ ያሉት አበውም ምስጋናዋን በማድረስ ፍጹም በረከቷን ሽተው በፊቷ ይማለላሉ፤ ርሷም ለሱባኤዋ በወደቁበት በረሐ እየተገለጸች በረከቷን ታድላቸዋለች፤ ክቡራን ምእመናንም ከልጅ እስከ ዐዋቂ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሰብሰብ ቅዳሴ ማርያምን በማስቀደስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በመቀበል፤ እጅግ ድንቅ በኾነ መልኩ ሱባኤውን ይፈጽሙታል፤ በመኾኑም ትውልድ ኹሉ ብፅዕት የሚላት አጋንንትን የምታሸብራቸው የአምላካችን እናትም በቀንም ኾነ በሌሊት ከእኛ በረድኤት ባለመለየት ረድኤቷን በረከቷን ልታትረፈርፍልን የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ ደርሷልና የእውነተኛዪቷ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በእጅጉ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ፤ በሱባዔው ውስጥ ከእውነተኛ ልብ ከሚመነጭ እውነተኛ ዕንባ ጋር ጸሎታችንን እናቅርብ !!!፡፡
❖✔ የምእመናን ወዳጅ የመስቀል ሥር ሥጦታችን በዚኽ የፍልሰታ ሱባኤ ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን!!! ለበዓለ ዕርገቷ በሰላም ያድርሰን እስከዛው መልካም የበረከት ሱባኤ ይኹንልን!!!
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)

❤162👍22👎1
የጾመ ፍልሰታ የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ ከሰኞ - ዐርብ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ4:45 - 6:00 ድረስ በቲክቶክ የቀጥታ ሥርጭት መከታተል ትችላላችሁ።
https://www.tiktok.com/@tadeserodas?_t=8omvj8iXW4L&_r=1

👍51❤31🥰5
በስሜ የተከፈቱ ብዙ የቲክቶክ አካውንት ሲኖሩ ትክክለኛው እና የቀጥታ ሥርጭት የማስተላልፍት ከዚህ ቀጥሎ ያለው ብቻ ነው። ይወዳጁና ጥበብን ዕውቀትን ብቻ ይቅሰሙ
https://www.tiktok.com/@tadeserodas?_t=8oqPnOWmviw&_r=1

👍59❤18👏3😁3🥰1
"ሰላም ለዕርገተ ሥጋኪ"
👉 ኀሙስ ነሐሴ 16 ጠዋት በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አይቀርም።
💥 የአምላክን እናት የዕርገቷን በዓል በበዓለ ንግሥና 8ኛው የአመቤታችንን ጉባኤ በታላቅ ድምቀት የምናስብ ሲኾን፦
በዕለቱም፦
💥 ሥርዐተ ቅዳሴ
💥 ጠዋት 3 ሰዓት ታቦተ ኪዳነ ምሕረት እጅግ በታላቅ ድምቀት ታጅባ ትወጣለች።
💥 የገነት አበባ የተባለች የአምላክ እናት ዕርገቷን በማሰብ የከበረ ሥዕሏ በካህናት በዲያቆናት ታጅቦ በ10,000 አበባዎች፤ መለከት እየተነፋ ነጋሪት እየተጎሰመ በታላቅ ድምቀት ይወጣል።
💥 ሊቃውንት ያሬዳዊ ዝማሬን ያሰማሉ።
💥 ብዙ ሕሙማን የተፈወሱበት በግብጽ ፓርት ሳይድ የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ካለችው ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ላይ የሚፈሰው ፈዋሽ ወዝ ለመጡት ኹሉ በነጻ ይሰጣል። "ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማሕየዌ በጼዴንያ ወግብጽ ዘአውሐዘት በኢሕሳዌ" (በጼዴንያና በግብጽ ፈዋሽ ወዝን ያፈሰሰች ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) (መልክአ ሥዕል)
💥 በመኾኑም በዚኽ ታላቅ በዓል የአምላክ እናት ልትባርኮት ጠርታዎታለችና በጠዋቱ እንዳይቀሩ።
👉 የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ ከ4 ኪሎ ወደ ቀበና አደባባይ ሲመጡ ማደያው ጋር ከመድረሶት በፊት።

❤46👍20
[ደብረ ታቦር]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ የምስጢር ደቀ መዛሙርት የሚባሉት፣ በእምነት በተስፋ በፍቅር የሚመሰሉት፤ ዳግመኛ በነገደ ሴም በነገደ ካም በነገደ ያፌት የተመሰሉት ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ ወጣ።
💥 የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አምጥቶ፤ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)።
♥❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው ምክያቱም ከምስጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡
♥❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ፦ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡
♥❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች። በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ላይ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡
❤ በሲና ተራራ የአባቱን ክብር እንዳየን የርሱን ክብር ደግሞ በብሩህ ደመና በታቦር ገልጦታል።
♥❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ፦
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት ጌታችን የሙሴና የኤልያስ በአጠቃላይ የነቢያት ፈጣሪ የእግዚአብሔር ልጅ መኾኑን ሲገልጽላቸው ነው።
ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡
♥❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው።
♥❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡
♥❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡
♥❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦
1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት
2) በተራራ በተመሰለች በጉባኤ ቤት ብሉይና ሐዲስ እንደሚነገሩ ለመግለጽ፡፡
3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት
4) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡
5) እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ፦ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡
6) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨
7) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨
8) ሙሴ ከንጉሡ ፈርዖን ፊት ሸሽቶ እንደሄደ ኤልያስም ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል ፊት ሸሽቶ ሄዶ ነበር።
9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለኹ፥ አንተ ጴጥሮስ ነኽ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥኻለኹ፤ በምድር የምታስረው ኹሉ በሰማያት የታሰረ ይኾናል፥ በምድርም የምትፈታው ኹሉ በሰማያት የተፈታ ይኾናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡
♥❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡
♥❖ በዚህ በዓል በታቦር የታየው የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡

❤44👍27🥰3🔥1