[የመስከረም ሰማይ ጫና የተፈጥሮ አደጋ]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቀንና ሌሊት እኩል በሚኾንበት Equinox በሚደረግበት በዚህ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር በመስከረም ለየት ባለ መልኩ ሰማይ በብዙ ምልክት የተመላበት ምድርም (የብሱም ባሕሩም) የተባበሩበትና በምድራችን ጫና የነበረበት ወር ነውና በሰማይ ላይ እየተከናወኑ ስላሉት ሰማያዊ አካላት ጥቂት ማለት ወደድኹ።
👉ረቡዕ መስከረም 8 (Sep. 18) የዐዲስ ዓመት ታላቋ ሙሉ ጨረቃና Super Harvest Moon እና ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ Partial Lunar Eclipse የተከሰተበት።
👉 ማግሰኞ መስከረም 14 (September 24) ሄለኔ ዐውሎ ነፋስ (Hurricane Helene) በፍሎሪዳ ግዛት ከፍተኛ ጉዳት በሰው ሕይወትና ንብረት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰበት
👉እሑድ መስከረም 19 (September 21) በመሬት ስበት አስትሮይድ 2024 PT5ን በመያዙ ላይ ሚኒ ጨረቃ (ሚጢጢ ጨረቃ) በመኾን እስከ ኅዳር በመቆየት የስበት ጫናቸውን በምድራችን አጠናክረዋል።
👉 ረቡዕ መስከረም 22 (October 2) ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ (annular solar eclipse) በደቡብ አሜሪካ፤ ጠፍ ጨረቃ (New Moon) በዕለቱ ሮሽ ሀሻናህ የእስራኤል ዐዲስ ዓመት ተባብሮበታል።
👉ኀሙስ መስከረም 23 (ኦክቶበር 3) - በሰባት ዓመታት ውስጥ ያልታየ በጣም ኃይለኛ ነበልባለ ፀሐይ X9.05 solar flare ከፀሐይ ነቁጥ sunspot የተነሣበት።
👉 በእኛ አንጻር ካየነው እሑድ መስከረም 26 በዐዲስ አበባ ርዕደ ምድር የተሰማበት።
👉 ሰኞ መስከረም 27 (October 7) ከፀሐይ ነቁጥ (Sunspot) AR 3842 እኩለ ቀን ላይ ከፍተኛ ሶላር ፍሌር (የፀሐይ ነበልባል) ተከሥቷል።
👉 ሰኞ መስከረም 27 (ኦክቶበር 7) የደራጎን ሕብረ ኮከብ ተብሎ ከሚጠራው ድሬኮ ሕብረ ኮከብ Draco constellation ውስጥ [Draconids Meteor Shower] (በሰዓት ወደ 10 ተወርዋሪ ከዋክብት) እየወጡ ይታያሉ። ሥነ ከዋክብታዊ ነገረ መለኮትን የሚያጠኑ ይኽንን የድሬኮ ሕብረ ኮከብ፦
✍️ “ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው”
— ራእይ 12፥4 ከሚለው ጋር አነጻጽረው ያዩታል (ስለዚኽ ለመረዳት ማዛሮት መጽሐፌን ያንብቡ)
👉 መስከረም 28 - 29 (October 8 - 9) በምድብ 5 ያለ ሚልተን የተባለ ከፍተኛ ዐውሎ ነፋስ ድጋሚ ወደ ፍሎሪዳ እየመጣ ያለበት።
👉 ቅዳሜ ጥቅምት 2 (ኦክቶበር 12) Tsuchinshan-ATLAS የተባለው ዥራታማ ኮከብ ምድርን የሚያልፍበት ነው።
👉 ኀሙስ ጥቅምት 7 (October 17) የጥቅምት ሙሉ ጨረቃ ሚጢጢ ጨረቃ የተባለው አስትሮይድ 2024 PT5ን ከመጣ በኋላ የመጀመሪያዋ ሙሉ ጨረቃ የምትወጣበት።
💥 እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እነዚኽ ሰማያዊ አካላት ለምልክትነት የተሾሙ ስለመኾናቸው ጌታ እንዲኽ ይላል፦
✍️ “በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።” (ሉቃስ 21፥25-26)

👉 የሕትመት ዋጋ በመጨመሩ አንባብያን በመጻሕፍት መሸጫ ዐጥተውት በጠየቁት መሠረት የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "888" መጽሐፍ ለአራተኛ ጊዜ ታትሞ ለአንባብያን ቀርቧል።
👉 መጽሐፉ በሀሁ የመጻሕፍት ማከፋፈያ እና በተለያዩ መሸጫዎች ይገኛል።
💥 መጽሐፉ በ27 ምዕራፍ የተከፈለ ሲኾን በኢትዮጵያ የፊደል ቀመር ውስጥ የሚገኙ:-
👉 የፊደላት ጂኦሜትሪ፣ ድምፅ፣ ቁጥር
👉 በመቅረዙ ውስጥ የተቀመጠው የ7 የብርሃን ቀመር
👉የ አ ቡ ጊ ዳ ሙሉ ቀመር
👉 በመጽሐፈ ሔኖክ የሚገኘው የስመ አምላክ ቀመር
👉 በገነት ውስጥ የነበሩ የዕፀ ሕይወት እና ዕፀ ጥበብ ቀመር
👉 በግእዝ ፊደላት ያለው የ3.14 የፓይ ቀመር
👉 የ DNA እና RNA ቀመር
👉 የፔሪዮዲክ ሠንጠረዥ የንጥረ ነገራት ቀመር
👉 የፕሩቶንና የኤሌክትሮን ቀመር
👉 የልብ እና የአእምሮ ዐይኖች መክፈቻ የግእዝ ቀመር
👉 በ182 የግእዝ ፊደላት የተቀመረው የኢኪውኖክስ (Equinox) ቀመር
👉 በፊደላችን የሚገኝ የሥርዐተ ፀሐይ ቀመር
👉 ከአድማስ እስከ ናጌብ የምድር ልኬት ቀመር
👉 በፊደላችን የተገለጸ የጨረቃና የምድር ራዲየስ ልኬት
👉 በግእዝ ፊደላችን የተገለጸ በሜትር ፐር ሰከንድ የሚቀመር የድምፅ ፍጥነት
👉 በፊደላችን የተገለጸ በሚክሮሜትር የሚቀመር የቀይ የደም ሴል፣ በደም ቧንቧ ውስጥ ያለው ቀመር
👉 በግእዝ ፊደላት ውስጥ የሚገለጸው ቀመረ ምጽአትና የርኅወተ ሰማይ (የሰማይ ደጃፍ) Portals መክፈቻ ቀመር እና ሌሎች ብዙ ድንቅ ምስጢራት ተካተውበታል።
👉 በውጪ ሀገር የምትኖሩ በቀላሉ በአማዞን ላይ ማግኘት ይቻላል። ሊንኩም https://www.amazon.com/dp/B0BGZ14FBD/ref=cm_sw_em_r_mt_dp_X81QK1M112XS84KPYFSY
#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር
አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705/0924408461

💥ታላቅ የምሥራች💥 በመቅደላ ጦርነት በእንግሊዞች ከተወሰዱት ውስጥ "የመቅደላ ጋሻ" (The Shield of Magdala) በመባል የሚታወቀው የንጉሠ ነገሥት የዐጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ዐርብ ጥቅምት 22/ 2017 ዓ.ም. ይገባል።
👉 ይኽ ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ እንግሊዝ ባለው "አንደርሰን ኤንድ ጋርላንድ" በኩል ጨረታ ላይ ቢወጣው በዐጼ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ በልዑል ኤርምያስ ሣሕለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ በኩል በተቋቋመው የሮያል ትረስት ተቋም በከፍተኛ ውይይት ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ መኾኑን ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት ነበረ።
👉 ጥረቱ በመሳካቱ የመቅደላ ጋሻ አሁን በሰሜን አሜሪካ በኦሀዮ ቶሌዶ የኪነ ጥበብ መዘክር እጅግ በርካት የውጪ ሀገር ተመራማሪዎች፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ቅዳሜ ጥቅምት 16 በሰሜን አሜሪካ በኦሀዮ ቶሌዶ የኪነ ጥበብ ቤተ መዘክር ከፍተኛ የአቀባበል ሥርዓት ተደርጓል። በዕለቱም በዶክተር አሉላ ፓንክረስት ከመቅደላ በተወሰዱት የኢትዮጵያ ቅርሶች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ የቀረበ ሲኾን እኔም በቦታው በክብር እንግድነት በመገኘት ጋሻው ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ዐርብ ጥቅምት 21 ከመግባቱ በፊት ለመጎብኘት ችያለኹ። 👉 በዚኹ አጋጣሚ የዐጼ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ቃለ መጠይቅ ያደረኩ ሲኾን በመቅደላ ጦርነት በ15 ዝኆኖች በ200 በቅሎዎች ከኢትዮጵያ የወጡት ውድ ቅርሶችና የብራና መጻሕፍት ወደ እናት ሀገራቸው እንዲመለሱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጠዋል ሊንኩን https://youtu.be/oSZrLtDqwlw?si=yKDltLnhJbupPJ3w
👉 የአቀባበል ሥርዓት የተደረገበት በቶሌዶ የኪነ ጥበብ ቤተ መዘክር ውስጥ እጅግ ብዙ ቅርሶች የሚጎበኙ ሲሆን በርካታ ጥንታውያት ብራና መጻሕፍት፣ መስቀሎች፣ ቅዱሳት ሥዕላት የሚገኙ ሲኾን ሰፊ ጉብኝት ለ2 ቀናት ለማድረግ ችያለኹ።
👉 የመቅደላ ታሪክን ለማስታወስ ያኽል ዐጤ ቴዎድሮስ ወደ ሺሕ የሚጠጉ በልዩ ልዩ ጌጥ ያጌጡ፤ በልዩ ልዩ ሐረግ የተንቈጠቈጡ የብራና መጻሕፍትን ከመላው ኢትዮጵያ ካሉ ገዳማትና አድባራት አሰብስበው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ነበር፡፡
👉 የእንግሊዝ ጦር በጄኔራል ናፒየር እየተመራ ድል ካደረገ በኋላ ስለተወሰዱት ቅርሶች ጆሴፍ ፍራንሲስ “Tewodros Prince of Ethiopia” በሚለው ጽሑፉና ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፋቸው እንደገለጡት፡-
✍️ “በንጉሣዊ ቤተ መጻሕፍት የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ጥንታዊ ድርሳናትና የብራና መጻሕፍት፤ ዐሥር አስደናቂ ታቦታት፣ መንበሮች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ሥዕላት፣ የተለያዩ ውብና ድንቅ የወርቅ ጌጣጌጦች፤ የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መስቀሎች፣ ለክብረ በዓላት ብቻ የሚወጡ አስደናቂ ቅርጽ ያላቸው መስቀሎች፣ የአቡኑ አክሊልና ታላቅ ማኅተም ተወሰዱ። የተወሰዱት ንብረቶች ቅርሶች በ15 ዝኆኖችና በ200 በቅሎዎች ጭነው ወሰዱ። የማይፈልጉትን ድርሳናትና ቅርሶችን እንዲጠፉ በአምባው በየአግጣጫው ወረወሩት፤ እነዚኽም በ፭ ኪሎ ሜትር ርቀት ሙሉ ተጥለው ይገኙ ነበር፤ የተወሰደው ቅርስ ከብዛቱ የተነሣ ለኹለት ቀናት ለፈጀ ጨረታ አቅርበውት ነበር፤ የእቃው ክምችት ግማሽ ኤከር (4,047 ካሬ ሜትር) ስፋት ያለውን መሬት ሸፍኖት ነበረ።
ዘመቻውን ተከትሎ የመጣው የእንግሊዝ ሙዚየም ባልደረባ የኾነው ሆልምስ ታላቁ ተጫራች ነበር፤ የተወሰዱ ቅርሶች በጊዜው በእንግሊዝ ገንዘብ ሠላሳ ሰባት ሚሊየን ፓውንድ ነበር ወይም አንድ ቢሊየን ብር ይገመታሉ” ይላል ፡፡
👉 ዐምስት መቶውንን ድንቅ የኢትዮጵያውያን የብራና መጻሕፍትን እንግሊዝ ባሉት ቤተ መጻሕፍት ተከፋፍለው እንዲቀመጡ ሲደረጉ፤ የመጻሕፍቱን ዝርዝር እንግሊዛዊዉ ዊሊያም እና ጀርመናዊዉ ዲልማን ጽፈዋቸዋል፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ ዐጤ ዮሐንስ ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ይልቁኑ የጌታችን ኲርዐተ ርዕሱ (ራሱ በዘንግ ሲመታ) የሚያሳየውን እጅግ የሚያስደንቅ ኢትዮጵያዊ ሥዕል እንዲመለስ የእንግሊዟን ንግሥት ቪክቶሪያን ቢጠይቁም እንግሊዞች ግን እንደማይመልሱ በመናገር ከመቅደላ ከወሰዷቸው ዐምስት መቶ የብራና መጻሕፍት ውስጥ መርጠው አንዱን “ክብረ ነገሥትን” ብቻ መልሰውልናል፡፡
👉 ዐጼ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ዐጼ ራሳቸውን በማጥፋታቸው የተበሳጩት አንግሊዞች የንጉሠ ነገሥቱን ሹሩባ (ቁንዳላ) ቆርጠው ከመቅደላ ወስደው በእንግሊዝ አርሚ ሙዚየም ውስጥ ከ 154 ዓመታት በላይ ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያውያን ቅርስ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በመጋቢት 2011 ዓ.ም ወደ ከብሪታኒያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ይታወሳል። ጥቀምት 22 ዐርብ ደግሞ ጋሻቸው ይገባልና
"ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም
ዐርብ ዐርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም"
ተብሎ በተገጠመላቸው ግጥም በማብቃት በሰሜን አሜሪካ በተገኙ ታላላቅ እንግዶች የነበረው ታላቅ የክብር አቀባበል ድንቅ ነበርና ወደ እናት ሀገሩ በዶክተር አሉላ ፓንክረስት ጥቅምት 22 ሲመለስ ደረጃውን የመጠነ ሀገራዊ አቀባበል ለንጉሠ ነገሥቱ ጋሻ እንደሚደረግ አምናለኹ።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
#RoyalEthiopiantrust

YouTube
(ሰበር) የቴዎድሮስ ጋሻ በ150 ዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ በልዑሉ የተደረገው ድንቅ ሥራ
"ዕውቀት እንደ ጎርፍ የሚፈስበት የደለዊ (አኳሪየስ) የነፋስ ዘመን ምድራችን ተቀላቅላለች። በአኳሪየስ ቴክኖሎጂ ጫፍ ላይ ዕውቀት በቀላሉ ይፈስሳል። በዓመታት ውስጥ ትምህርት ቤቶችም ላይኖሩ ስለሚችሉ፤ ወዳጄ ከዘመኑ ጋር ለመወዳደር ዕውቀትን አልፈህ ጥበብን ያዝ"
(ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
(ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)
[የቁስቋም ክብር በኢትዮጵያ ቀደምት ሊቃውንት]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖♥ ከ3 ዓመት የስደት ውጣ ውረድ በኋላ የአምላክ እናት ልጇ አምላካችን ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትላ ከመዐዲ ወደ ላዕላይ ግብጽ በጀልባ ደግሞ ከካይሮ በስተደቡብ 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በላዕላይ ግብጽ በምትገኘው ወደ ደብረ ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸው ድካም 6 ወር ከ10 ቀናት ዐርፈዋልና ኅዳር 6 በደመቀ መልኩ በዓሏ ይከበራል፡፡
❖ ♥በደብረ ቁስቋም ሳሉ ጨካኙ ሄሮድስ እንደሞተ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘኽ ወደ እስራኤል አገር ኺድ" ብሎታል (ማቴ 2፡19-20)።
❖ ♥ ይኽቺን ጌታ ከእናቱ ጋር ያረፈባትን የተቀደሰች ቦታን ጌታችን ባርኳት ወደ ናዝሬት ተመልሰዋል። ጌታችን ካረገ ከብዙ ዘመን በኋላ በኅዳር ስድስት ቀን “አስተጋብኦሙ እግዚእነ ለሐዋርያቲሁ ቅዱሳን ውስተ ዝንቱ ደብረ ቊስቋም ወቀደሰ ታቦተ ወቤተ ክርስቲያን ወሠርዐ ቊርባነ ወመጠዎሙ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ” ይላል (በዚኽ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል) ይላል፡፡
❖♥ በዚኽ ምክንያት ደብረ ቁስቋምን የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በግብጽ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ይሏታል፤ የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን በእጅጉ የሚወዷት የቁስቋም ገዳም ስትኾን በ1993 ዓ.ም. ላይ እመቤታችን በገዳሙ ተገልጣ እንደነበር ይናገራሉ፤ በዚኽችም ገዳም 100 መነኮሳት ይገኙበታል፤ ከቦታዋ ክብር የተነሣ "ዳግሚት ቤተልሔም" ይሏታል፤ በገዳሙም በቅዱሳት መጻሕፍት የተመላ ታላቅ ቤተ መጻሕፍት አለ፨
❖♥ በጌታ በተባረከችው ይኽቺ ቦታ ላይ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቅዱስ ጳኩሚስ ገዳምን የገደመ ሲኾን፤ የእስክንድርያ 23ኛ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በታናሿ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ምትክ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ባሰበ ጊዜ እመቤታችን ተገልጻለት የልጇ የክርስቶስ ትሕትናው በገዳሙ እንዲታሰብበት ባለበት እንዲኾን ነግራዋለች።
❖♥ በርካቶች የኢትዮጵያ ሊቃውንት እመቤታችን ከልጇ ጋር ወደ ቊስቋም የመግባቷን ነገር የጻፉ ሲኾን ለምሳሌም አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ በስፋት ሲዘረዝረው፡-
♥ [“በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ
ምስለ ዮሴፍ አረጋይ
ነገደት ቊስቋመ ናዛዚተ ሐዘን በብካይ”]
(የሰማዩ አውሬ ሄሮድስ ሕፃናትን መብላት ባሰበ ጊዜ፤ ከሐዘንና ከልቅሶ የምታረጋጋ ማርያም ከአረጋዊዉ ዮሴፍ ጋራ ወደ ቊስቋም ኼደች (ተሰደደች))
❖♥ “አሥረጸት ማርያም አክናፈ ረድኤት አምሳለ ዖፍ ለዐሪገ ቊስቋም
ህየ ከመ ትትዐቀብ ዘመነ ወአዝማነ ወመንፈቀ ዘመን በከመ ይቤ መጽሐፍ”
(ማርያም ወደ ቊስቋም ተራራ ለመውጣት እንደ ዎፍ የረድኤት ክንፎችን አበቀለች በመጽሐፍ እንደተናገረ በዚያ በዘመንና በዘመናት በዘመን እኩሌታም ትጠበቅ ዘንድ)
❖ ♥ “ብጽዐን ለኪ ኦ ደብረ ቊስቋም
እምኲሎን አድያም እምናዝሬት እስከ ቤተልሔም
ዘተጸወነ ላዕሌኪ መድኀኔ ኲሉ ዓለም”
(ከናዝሬት እስከ ቤተ ልሔም ካሉ አውራጆች ኹሉ የዓለም ኹሉ መድኀኒት ወደ አንቺ የተጠጋ የቊስቋም ተራራ ሆይ ክብር ይገባሻል)
❖♥ “በቃለ ውዳሴ ጥዑም ይደሉ ሰላም
ለዕበይኪ ፍጹም አድባረ ቊስቋም
ማኅደረ ልዑል ዘአርያም”
(በአርያም ያለ የልዑል ማደሪያው የኾንሽ የቊስቋም ተራራ ሆይ ፍጹም ለሚኾን ክብርሽ በሚጣፍጥ የምስጋና ቃል ሰላምታ ማቅረብ ይገባል) በማለት ዘርዝሮ ጽፎላታል፡፡
❖♥ ቅዱስ ያሬድም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ በስደቷ ወቅት በደብረ ቊስቋም ስለማረፏ በድጓው ላይ ሲጽፍ፡-
❖♥ “መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም
ወልደ ቅድስት ማርያም
ኀሠሠ ምእራፈ ከመ ድኩም
ንጉሥ ዘለዓለም
ግሩም እምግሩማን ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም
ኀደረ ደብረ ቊስቋም”
(ቅድመ ዓለም የነበረች ጌትነቱ ምልእት ስፍሕት የኾነች የቅድስት ድንግል ማርያም የባሕርይ ልጅ የዘለዓለም ንጉሥ ሲኾን እንደ ደካማ ማረፊያን ፈለገ፤ ከግሩማን ይልቅ ግሩም፤ የማይጨልም የሕይወት ብርሃን ርሱ በደብረ ቊስቋም ዐደረ)
❖♥ “መንክር ወመድምም ዘተገብረ በደብረ ቊስቋም
መንክር ወመድምም ዘይሴባሕ በአርያም
አምላክ ፍጹም ኀደረ ውስቴቱ መድኀኔ ዓለም
ዘሀሎ እምቅድም
ኀደረ ውስቴቱ ለዝንቱ ደብር ዘአብ ቃል
ምስለ እሙ ድንግል ደመና ቀሊል”
(በደብረ ቊስቋም የተደረገው የሚያስደንቅ እና የሚያስገርም ነው፤ በአርያም የሚመሰገን ፍጹም የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም በውስጡ ዐደረ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ የአብ አካላዊ ቃል ፈጣን ደመና ከተባለች ከድንግል እናቱ ጋር በዚኽ ደብር በውስጡ ዐድሯል) በማለት መስክሮላታል፡፡
❖♥ እኔም ለወንጌል አገልግሎት ወደ ግብጽ ኼጄ በነበረ ጊዜ እመቤታችን ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከድካም ያረፉበት ይኽቺን ቅድስት ቦታ ገዳመ ቁስቋምን ስረግጣትና ጌታችን ከእናቱ ጋ የተቀመጡበት ዋሻ ውስጥ ገብቼ የተቀደሰችውን ቦታ ስስማት መጀመሪያ ያሰብኩት ቅዱሱ አባት አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌው ላይ፦
“ተአምረ ግፍእኪ ለአርእዮ እምገጸ ሄሮድስ መስቴማ
አመ ጐየይኪ ማርያም በሐዊረ ፍኖት እለ ደክማ
ምስለ እግረ ጽጌኪ ልምሉም ኀበ አእጋርኪ ቆማ
ለምድረ ገዳምኪ ቅድስት ቊስቋም ስማ
እምፈተውኩ በጺሕየ በሰጊድ እሰዓማ”
(ማርያም የግፍሽን ተአምር ለመግለጥ ከጠላት ሄሮድስ ፊት በሸሸሽ ጊዜ ከለመለመች ከልጅሽ እግር ጋር መንገድን በመኼድ የደከሙ እግሮችሽ የቆሙባት ስሟ ቊስቋም የተባለ የተቀደሰች ገዳምሽን እኔም ደርሼ ብሳለማት እመኛለሁ እወዳለሁ) በማለት የጸለያት ጸሎትን ነበር፡፡
♥ የእመቤታችን በረከት ይደርባችኊ፤ ቦታዋን ያላያችሁ ለመሳለም ኹላችኹንም ያብቃችሁ እላለሁ፡፡♥
[ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ ፓስት ያረኩት]

[ኅዳር 8 የእግዚአብሔርን ዙፋን የሚሸከሙ የኪሩቤልና የሱራፌል ዓመታዊ በዓል፤ ክብራቸውና ስማቸው]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖♥ ክብራቸው ታላቅ የኾኑት የኪሩቤልን ነገር ሊቁ ኤጲፋንዮስ “ስሞሙ ኪሩቤል ካህናተ ቅዳሴ ወውዳሴ እምታሕተ ሐቌሆሙ አሐዱ ወእምላዕለ ሐቌሆሙ አርባዕቱ እለ ግሉፋን በአዕይንት” ብሎ እንደገለጸው ኹለተኞቹ አመስጋኞች የኾኑት ዐሥሩን ነገድ ስማቸው ኪሩቤል ሲባሉ ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት አድርጎ ሲፈጥራቸው ዐይናቸው ብዙ ነው፤ አለቃቸውም ኪሩብ ሲኾን የሰው መልክና የአንበሳ መልክ ያለው ነው፡፡
❖ ♥ ሦስተኛውን ዐሥሩን ነገድ ስማቸው ሱራፌል ሲባል የእነዚኽ አለቃቸው የንስር መልክና የእንስሳ መልክ ያለው ነው፤ አለቃቸውም ሱራፊ ሲባል ሲፈጥራቸውም ስድስት ስድስት ክንፍ አድርጎ ፈጥሯቸዋል፨
❖♥ ልዑል እግዚአብሔር ከነገደ ኪሩቤል ኹለት ገጸ ሰብእ እና ገጸ አንበሳን፤ ከሱራፌል ኹለት ገጸ ንስርና ገጸ እንስሳን አንሥቶ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት በላይ ከሰማይ ውዱድ በታች አቁሞ በነርሱ ላይ ሰማይ ውዱድን እንደ መረሻት ጫነባቸው፤ በላይም ሕብሩ በረድ የመሰለውን ዙፋን እንደ ሠረገላ ጭኖባቸዋል፤ እነዚኽንም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ በአራቱ መኣዝን ዠርባቸውን ወደ ውስጥ ፊታቸውን ወደ ውጪ እያደረገ አቁሟቸዋል።
❖♥ ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለዚኽ ነገር በምዕ ፩፥፲፪ ላይ “እያንዳንዱም ወደ ፊት ቀጥ ብሎ ይኼድ ነበር መንፈስም ወደሚኼድበት ኹሉ ይኼዱ ነበር ሲኼዱም አይገላመጡም ነበር” በማለት እንደተናገረ ገጽ ለገጽ ሳይተያዩ ሥላሴ በፈቀዱት ፍኖት አንዱ በኼደበት ሦስቱ እየተከታተሉ ይኼዳሉ፡፡
❖♥ እነዚኽንም እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል ገለጻ ፲፮ ሲኾኑ የቀሩት ከውስጥ ስለኾኑ ስለማይታዩ አራቱ ግን ብቅ ብቅ ብለው ስለሚታዩ ዮሐንስ አራት ብሏቸዋል እንጂ እንደ ሕዝቅኤል ገጻቸው ፲፮ ነው ይላሉ መተርጉማን፡፡
❖ ♥ ሊቁ “እምርእሶሙ እስከ ሐቌሆሙ አርባዕቱ ወእምሐቌሆሙ እስከ እግሮሙ አሐዱ ከመ ርእየተ እለ ቄጥሩ ዘውእቱ ዖፍ ዘይነብር በሀገረ ፋርስ” እንዲላቸው፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ከመ ርእየተ እለቄጥሩ ገጸ በገጽ ኢይትናጸሩ” ብሎ እንደገለጻቸው በፋርስ ሀገር የሚኖረው እለቄጥሩ የተባለውን ዎፍ ከወገቡ በታች አንድ ከወገቡ በላይ አራት እንደኾነ እነዚኽንም ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት አድርጎ ፈጥሯቸዋል ፡፡
❖ ♥ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 4:7-9 ላይ "ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል። አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም" ይላቸዋል።
❤ ኪሩቤልን “እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ” አላቸው፤ ከላይ እስከ ታች ድረስ ዐይንን የተመሉ ናቸውና፤ ይኽስ አይደለም እንደ ብርሌ እንደ ብርጭቆ እያብለጨለጨ ለዐይን ባልተመቸም ነበር ብሎ ዐልፎ ዐይን ዐልፎ ዐይን ነው፤ እንደ አልጋ መለበሚያ እንደ ሱቲ መጠብር እንደ ቀሽመሪ መታጠቂያ፣ እንደ ነብር ለምድ፣ እንደ ዐይነ በጎ፣ እንደ ማር ሰፈፍ ይላሉ፤ ይኽስ አይደለም ብሎ ዐይናቸው ከአንገታቸው በላይ ሰድ ነው፤ ይኽም እንደ መስታዮት እያወለወለ እንደ ብርጭቆ እያንጸበረቀ አይደለም ብሎ ኀላፍያትን መጻእያትን የሚያውቁ ስለኾነ እንዲኽ አለ እንጂ ዐይናቸውስ ኹለት ነው ይላሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት መተርጉማን ፡፡
❖ ♥ በኢሳ ፮፥፩-፫ ላይ፡- “ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየኹት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን መልቶት ነበር፤ ሱራፌልም ከርሱ በላይ ቆመው ነበር ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በኹለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ ይበር ነበር፤ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ኹሉ ከክብሩ ተመልታለች እያለ ይጮኽ ነበር” ይላል ይኽ መሸፈናቸው ያድናቸዋል ቢሉ? ትእምርተ ፍርሀት ነው፤ ዛሬ በዚኽ ዓለም ሴቶችን ሕፃናትን እንመታችኋለን ባሏቸው ጊዜ እጃቸውን መጋረዳቸው የሚያድናቸው ኾኖ ሳይኾን ትእምርተ ፍርሀት እንደኾነ ኹሉ፡፡
✔ ♥ አንድም በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው ፊትኽን ማየት አይቻለንም ሲሉ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን መሸፈናቸው ከፊትኽ መቆም አይቻለንም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ ያደርጋሉ አለ ትእምርተ ተልእኮ ነው፡፡
✔ ♥አንድም በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው ባሕርይኽን መመርመር አይቻለንም ሲሉ፤ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን መሸፈናቸው ባሕርይኽን መረማመድ መተላለፍ አይቻለንም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወዲያ ወዲኽ ያደርጋሉ ከእእምሮ ወደ አእምሮ ለመፋለሳቸው፡፡
✔ ♥ አንድም ኹለት ክንፋቸውን ወደ ላይ አድርገው ይታያሉ አለ ወደላይ ቢወጡ ቢወጡ አትገኝም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወደታች አድርገው ይታያሉ ወደታች ቢወርዱ ቢወርዱ አትገኝም ሲሉ፤ ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ ያደርጋሉ ወዲያና ወዲኽ ቢሉ አትገኝም ሲሉ፤
✔ ♥ አንድም ወደላይ መዘርጋት በሰማይ ምሉእ ነኽ ሲሉ ወደታች መዘርጋቸው በምድርም ምሉእ ነኽ ሲሉ፤ ወዲያና ወዲኽ መዘርጋታቸው በኹሉ ምሉእ ነኽ ማለታቸው ነው፤
✔ ♥ አንድም ወደላይ መዘርጋት ትእምርተ ተመስጦ ወደታች መዘርጋት ትእምርተ ትሕትና፤ ወዲያና ወዲኽ ረብቦ መታየት ትእምርተ ተልእኮ ነው
❖ ♥ በአጠቃላይ ኹለት ክንፋቸውን ወደላይ ኹለት ክንፋቸውን ወደታች ኹለት ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ አድርገው ትእምርተ መስቀል መሥራታቸው በብሉይ ኪዳን ከኾነ እንዲኽ ባለ መስቀል ተሰቅለኽ ዓለምን ታድነዋለኽ ሲሉ በዘመነ ሐዲስ የኾነ እንደኾነ እንዲኽ ባለ ትእምርተ መስቀል ተሰቅለኽ ዓለምን አድነኸዋል ሲሉ ነው፡፡
❖ ♥ የእነዚኽ አርባዕቱ እንስሳ መላእክት ፊታቸው በርካታ ምስጢራትን ሲያመለክቱ ገጸ ሰብእ በማቴዎስ፤ ገጸ አንበሳ በማርቆስ፤ ገጸ ላሕም በሉቃስ፤ ገጸ ንስር በዮሐንስ ተመስሏል።
❤ ዳግመኛም የሰው ፊት ያለው መልአክ ለሰው ልጆች ይማልዳል። የአንበሳ ፊት ያለው መልአክ ለዱር አራዊት ይለምናል። የላም ፊት ያለው መልአክ ለእንስሳት ይጸልያል። የንስር ፊት ያለው መልአክ ለሰማይ አዕዋፋት ኹሉ ይለምናል በማለት ሊቃውንት ያመሰጥራሉ።
❖ ♥ በሌላ ምስጢር የሰው ገጽ ያለው የጌታን ሰው የመኾንን ነገር፤ የላም መልክ ያለው በቀራንዮ ላይ ደሙን ማፍሰሱ፤ የአንበሳው መልክ ያለው የጌታችንን ትንሣኤ፤ የንስር መልክ ያለው የጌታን ዕርገት እንደሚያመለክቱ ቀደምት መተርጒማን ይተነትኑታል።
❖♥ ዐምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም እጅግ ምጡቅ በኾነው ዕውቀቱ ዕጓለ አንበሳ የተባለው የወልድ የባሕርይ አባቱን አብን በአንበሳ ይመስለዋል።
❖♥ ሥጋን ተውሕዶ ፍጹም ሰው የኾነው ወልድን የሰው መልክ ባለው መስሎ ገልጾታል፡፡
❖♥ በአምሳለ ርግብ ወርዶ በወልድ ራስ ላይ ተቀምጦ የታየው መንፈስ ቅዱስን የንስር መልክ ባለው መስሎ አብራርቶ ጽፎታል።