Telegram Web Link
[እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም ዐጼ ምኒልክ በአምላክ እናት ስም ያደረጉት የክተት ዐዋጅና ቀደምት ነገሥታት ለአምላክ እናት ያላቸው ፍቅር]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በየካቲት 23፤ 2010 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተጽፎ በድጋሚ አሁን ፓስት የተደረገ]
በምንኖርበት ምድር ካሉ ሀገራት ሁሉ ስናወዳድር ለእመቤታችን ጥልቅ ፍቅር የነበራቸው ነገሥታት የነበሩባት ታላቋ ሀገር ኢትዮጵያን በቀዳሚነት እናገኛታለን፨ በኢትዮጵያ ነገሥታት ሢመት እመቤታችን በስደቷ ከልጇ ጋር የተገኘችበት ጣና ቂርቆስን ጨምሮ አክሱም ጽዮን ማርያም፣ ተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው።

ይኸውም ከ3000 ዓመት በፊት የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል እንድትመጣ እግዚአብሔር ስለፈቀደልን፤ የአማናዊት ታቦት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌዋን አስቀድሞ በኢትዮጵያ ሀገር ላይ አስቀመጠ፨ ለታቦቲቱ መምጣት ቀዳማዊ ምኒልክ ተጠቃሽ ነው።

ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም አምላካችን ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ይዘው እመቤታችንን ከልጇ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በዐይናቸው ካዩ ከነገሥታት ሰብአ ሰገል ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ እነ ዳዊት በመዝ 71 (72)፥10፤ እነ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምዕ 60፥1-6 ሲናገሩ ብዙ የታሪክና የነገረ መለኮት ሊቃውንት ጽፈዋል፨ https://youtu.be/Am5xFV51AtA

ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳኗ በረከት በዚች ሀገር ላይ አለና በኢትዮጵያ ሀገራችን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በኹለቱ ወንድማማቾች ነገሥታት በአብርሃ እና በአጽብሐ ከ1680 ዓመት በፊት በ330 ዓ.ም. ላይ በአክሱም ላይ ሲያሠሯት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ሲኾን በዚያን ጊዜ ስትሠራ ባለ 12 መቅደስ ኾና በወርቅና በዕንቁ ያጌጠች ነበረች፨ በዚኽም ወንድማማቾች ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ ለአምላክ እናት ያላቸውን ታላቅ ፍቅር ገልጸዋል።

አብርሃ እና አጽብሐ በ331 ዓ.ም. በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በጎጃም ደግሞ ርእሰ ርኡሳንን መርጡለ ማርያምን ያነጹ ሲኾን "ወእምድኅረዝ ፈቀዱ አብርሃ ወአጽብሐ ከመ ይሕንጹ መቅደስ በህየ ወሐነጹ ማኅደረ ሠናይተ ወገብሩ አረፋቲሃ ዘወርቅ ወዘብሩር ... ወሰመይዋ ለይእቲ መቅደስ መርጡለ ማርያም ” (ከዚኽ በኋላ ነገሥታቱ አብርሃና አጽብሐ በዚያ ቦታ ቤተ መቅደስን ይሠሩ ዘንድ ወደዱ። ያማረች ማደሪያን ሠሩ። ግንቧን በወርቅ በብር ሠሩ። ... መቅደሷንም መርጡለ ማርያም ብለው ጠሯት) ይላል።

ከ515-529 ዓ.ም. የነገሠው ዐጼ ገብረ መስቀል ሲኾን በርሱ ጊዜ የነበሩት ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ ነበሩ። ከሊቁ ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ ጋር ንጉሡ ዐጼ ገብረ መስቀል ደብረ ዳሞ ድረስ በመውጣት ለእመቤታችን ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ በተራራዋ ላይ እጅግ የምታስደንቅ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያንን አሠራ።

ቅዱስ ያሬድም ዐጼ ገብረ መስቀል ያሠራትን ይኽችን የእመቤታችን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ተመልክቶ "ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንጼሃ" (ዞርኳት ዟርኳት ያማረ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗን ውበት አየሁ) እያለ ዘምሯል፨

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ያፈቅሩ ከነበሩት ነገሥታት መኻከል አንዱ ከቋጥኝ ደንጊያ ከዐለት ዓለም የሚደነቅባቸውን አብያተ ክርስቲያንን ያነጸው ከ1157-1197 ዓ.ም. ለ40 ዓመታት የነገሠው ዐጼ ላሊበላ ነው። ንጉሡ ለእመቤታችን ከነበረው ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ከሌሎች ኹሉ አስበልጦ የእመቤታችንን መቅደስ እጅግ ውብ አድርጎ በብሩህ ቀለማት በቅዱሳት ሥዕላት አስጊጦ በ12 ዐምዶች ያነጻት ሲኾን በውበቷ ተወዳዳሪ የላትም፨

እመቤታችንን ይወዱ ከነበሩ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከ1365-1395 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ዳዊት በጣም የሚታወቁ ሲኾን ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት የእመቤታችንን ተአምር ከዐረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ካስተረጎሙ በኋላ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አድርገዋል፨

ንጉሥ ዳዊት የእመቤታችን ፍቅር ውስጣቸው ድረስ ጠልቆ በመግባቱ ተአምሯ በወርቅ ቀለም በሚጻፍ ጊዜ ንጉሠ ነገሥት ዐጼ ዳዊት ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር እንዲቀላቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንባቸውን ከቀለሙ ጋር ጨምረው የእመቤታችን ተአምርን ያጻፉ የምድራችን የመጀመሪያው ንጉሥ ነበሩ ማለት ይቻላል፨

የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛላቸው ሌላው ንጉሥ የዐጼ ዳዊት ልጅ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ሲኾኑ በግብጽ የምትገኘው የእመቤታችን የደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን በግብጹ ንጉሥ ባርስባይ በግፍ መፍረሷን የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ፲፩ኛ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ለእመቤታችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቁ ለርሳቸው ደብዳቤን በጻፉ ጊዜ ዐዝነው ካይሮ በፈረሰችው በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ስም ተጒለት ውስጥ አሠሩ፤ ከዚኽ ተነሥተው ዛሬ ድረስ በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ማርያም እመቤታችንን "የዘርዐ ያዕቆብ እመቤት" ይሏታል።

ብሔራውያን ሊቃውንት አባታቸው ዐጼ ዳዊት እመቤታችንን ከመውደድ የተነሣ መልክአ ማርያምን “ለዝክረ ስምኪ” ከሚለው ዠምሮ “ለገቦኪ” እስከሚለው እስከ ኹለተኛው ቤት “በከመ ዳዊት ይዜኑ” እስከሚለው ደርሰው ሲያቆሙ ፤ ልጃቸው ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ደግሞ “ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ሥኑ” በማለት ቀጥለው እስከ መጨረሻው እንደፈጸሙት ይናገራሉ ፡፡ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ ንጉሡ ዐጼ ናዖድም እንደጻፈላት የሚገልጹ መምህራን አሉ፨ በዚኹ አጋጣሚ ሦስት የተለያዩ ዓይነቶች የመልክአ ማርያም መጻሕፍት ሲኖሩ እኔም ከአምላክ እናት በረከት ለማግኘት "መልክአ ማርያም ቀዳሚት፣ መልክአ ማርያም ካልዒት፣ መልክአ ማርያም ሣልሲት ሙሉ ትርጓሜያቸውን አዘጋጅቼ ለአንባብያን እንደቀረቡ መጽሐፉን ያነበቡ ያውቃሉ።

በአምላክ እናት ፍቅር ልባቸው በመቃጠሉ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በኹሉም አብያተ ክርስቲያናትን በእሑድ እና በበዓላት የእመቤታችን ተአምር እንዲነበብ ሲያደርጉ፤ ልክ እንደ አባታቸው እንደ ዐጼ ዳዊት የእመቤታችንን የተአምር መጽሐፍ ለተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሲያጽፉ ዕንባቸው ከመጻፊያው ቀለም ጋር እንዲደባለቅላቸው ለጸሐፊዎቹ በመንገር ዕንባቸውን በማፍሰስ ታማልዳቸው ዘንድ ይማፀኗት ነበር፨

ከ1500-1532 ዓ.ም. የነገሡት ዐጼ ልብነ ድንግል የቀደሙት ነገሥታትን ሕይወት በመከተል ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ጥልቅ ፍቅር በመነሣት በመጽሐፈ ሰዓታት ላይ የሚገኘውን "ለኖኅ ሐመሩና ስብሐተ ፍቁር ዘማርያም የሚለውን ድንቅ የምስጋና ድርሰት ለእመቤታችን ደርሰውላታል።

ሌላዋ በጣም የእመቤታችን ፍቅር በልባቸው ያደረባቸው ከ1723-1748 ዓ.ም. የነገሡት የዐጼ በካፋ ሚስት እቴጌ ምንትዋብ ሲኾኑ የእመቤታችን የስደቷና ቁስቋም የመቀመጧን ነገር ኹሌ የሚያስቡ ንግሥት ነበሩ፤ እመቤቴ ልጇን ይዛ ከሀገሯ ወጣ ብላ ቁስቋም እንደቆየች እኔም ከከተማው ወጣ ብዬ መቀመጥ እሻለሁ ብለው 5ት ኪሎ ሜትር ከከተማ ርቀው በአንድ ሺሕ የኢትዮጵያ የግንባታ ጠበብት የእመቤታችን የመንበረ ፀሓይ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያንን ሲያሠሩ 500ው ቆመው ስሕተቶችን በመንገር ያስገነቡ ነበር።
61👍32🥰7😁1
ንግሥት ምንትዋብ የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ዕንባቸውን ያፈሱ የነበሩ ንግሥት ሲኾኑ የእመቤታችን ስደቷን አስበው የፈቃድ ጾም የኾነውን ጾመ ጽጌን መጾም የጀመሩ ንግሥት ርሳቸው እንደነበሩ ሊቁ ዶክተር ሥርግው በመዝገበ ቃላታቸው ላይ ይገልጻሉ።

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ይወዱ የነበሩት ታላቁ ንጉሥ ዐጼ ምኒልክ ሲኾኑ ከሚስታቸው ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በመኾን በእመቤታችን ፍቅር እንጦጦ ማርያምን ካሠሩ በኋላ ለቅዳሴ ቤቷ ብዙ ሺሕ ሰንጋዎችን ያሳረዱ ሲኾን ጠጁ በገንዳ እንዲመላ በማድረግ ፍቅራቸውን ገልጠው ነበር። በበዓሉ ሰማዩ ጠቁሮ ሊዘንብ ሲል እመቤታችን ከልጇ እንድታማልዳቸው "ይድረስ ለድንግል ማርያም" የሚል ደብዳቤ ጽፈው የእመቤታችን መንበር ላይ እንዲቀመጥ ሲያደርጉ ወዲያው ዝናብን የቋጠረው ደመና ተበትኖ ፀሐይ በመውጣት ድንቅ ተአምር እንደተደረገ የታሪክ ምሁራን ይመሰክራሉ።

ኢትዮጵያን ለመውረር ወራሪው ጣሊያን ወደ ሀገራችን በከባድ መሣሪያ ታግዞ በዕብሪት ሲመጣ ንጉሡ የክተት ዐዋጅን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያውጁ የዐዋጃቸው ማተሚያ ኹሌም በፍቅር የሚወዷት እመቤታችንን በመጥቀስ "እግዝእትነ ማርያምን ለዚኽ አማላጅ የለኝም" በማለት ነበር ክተት ያወጁት።

በክተት ዐዋጅ ስሟን የጠሯት አፍጣኒተ ረድኤት የኾነችው የእመቤታችንን ታቦትና የፍጡነ ረድኤት የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስይዘው በመኼድ ጨረቃ ሙሉ ኾና በታየችበት የካቲት 23 በ1888 ዓ.ም. የጣሊያንን ጦር በመደምሰስ እጅግ አስደናቂ ድልን በአህጉሪቱ በአፍሪካ በማስመዝገብ ለመላው የአፍሪካ ሕዝቦች የነጻነት ጮራ ዋና ወጊ በመኾን፤ መላው አፍሪካ የተጫነበትን የቅኝ ግዛት ቀንበርን ሰባብሮ እንዲጥል መርህ ኾነውታል፤ በእውነት ስሟን የጠሯት ወላዲተ አምላክ አላሳፈረቻቸውም።
https://youtu.be/owQnvzufsN0

ይኽ ፍቅራቸው በልጃቸው በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዐልፎ በአታ ለማርያምንና ሌሎች በእመቤታችን ስም የተሠየሙ አሠርተው፤ በሚያልፍ ዐጭር የሹመት ዘመናቸው የማያልፍ ታላቅ ሥራ ሠርተው ዋጋን ወደሚከፍለው ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተጠርተው ኼደዋል፨

[በመጨረሻም ጽሑፌን ዐጼ ምኒልክን በቃል ኪዳኗ የተራዳችውን እመቤታችንን፤ በፈጣን ተራዳኢነቱ ያልተለያቸው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን አስቀድሞ በ530 ዓ.ም. ባመሰገነው በቅዱስ ያሬድ ቃል አበቃለሁ፦
"ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወላዕሌነ ይኩን ምሕረት በጸሎተ ጊዮርጊስ ዐቢይ ሰማዕት ወማርያም ወላዲተ አምላክ" [በሰማያት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን በታላቁ ሰማዕት በጊዮርጊስና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ጸሎት የእግዚአብሔር ምሕረት በእኛ ላይ ይኹን] [ቅዱስ ያሬድ]
[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ ፓስት አረኩት]
YouTube Channel https://www.youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg
👍14681🥰11👏9🔥4😁2
የ7ተኛው ወር የመጋቢት ሙሉ ጨረቃ ዛሬ መጋቢት 5 ደምቃ ታበራለች። በተለይ የጨረቃ ግርዶሽ ዛሬ በሀገራችን ኢትዮጵያ ባይታይም በሌሎች ሀገራት ግን የሚታይበት ጭምር ነው።
በኢትዮጵያ አቆጣጠር 12:48 ወይም 6:48 PM ጀምራ ሙሉዋ ጨረቃ መታየት ስለምትጀምር የውቧ ጨረቃ አድናቂዎች እንደተለመደው ፎቶ በማንሣት ከታች ባለው ሊንክ አጋሩን።
https://www.tg-me.com/+xN518gdGKvswNzE0
👍4614
💥 ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረው የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን" መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለአንባብያን ቀረበ።
👉 ይህ ድንቅ መጽሐፍ ቅድስት ድንግል ማርያም ከማቴዎስ ወንጌል እስከ ዮሐንስ ራእይ እንዴት እንደተገለጸች በ5 ምዕራፍ በ42 ንኡስ ምዕራፍ በ402 ገጾች የተዘጋጀ ነው።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ:-
1) የቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ - ዕርገቷ ያለው የተቀደሰ ታሪኳ
2) የቅድስት ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ንጽሕት ስለመሆኗ ትንታኔ
3) የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና
4) የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት
5) በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ላይ የተገለጸ ክብሯንና ቅድስት ድንግል ማርያምን አስመልክቶ ለሚነሡ ጥያቄዎች ሰፊ መልሶችን የያዘ መጸሐፍ ነው።
ይህንን ድንቅ መጽሐፍ ሀሁ መጻሕፍት መደብርና በተለያዩ መጻሕፍት ቤቶች ታገኙታላችሁ።

የሀሁ መጻሕፍት መደብር አድራሻ፦
ቁ.1፦ ስታድየም  ናሽናል ታወር ፣
ቁ.2፦ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ፊት ለፊት
ቁ.3 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን እንገኛለን።
ስ.ቁ  09 11 00 67 05
           0924408461
70👍21🔥3
ኃሙስ ማታ በኢትዮጵያ ሰዓት ከምሽቱ 2:22 ላይ ለዓለም ታላቅ ምስጢር ስለሆነው ስለ ግብጽ ፒራሚድ ምርጥ ፕሮግራም በDr Rodas Tadese Andromeda YouTube Channel ላይ ይኖረናልና እንዳያመልጦት። በዝግጅቱ ምን ቢነሣና ቢዳሰስ ይፈልጋሉ። አስተያየትዎን በአስተያየት መስጫው ላይ በዚህ ይጻፉልን።

https://www.tg-me.com/+xN518gdGKvswNzE0
64👍32😁6👏5👎1
[በዓለ ሆሣዕና]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸሙት ጌታ በትሕትና በአህያና በውርንጫይቱ በትሕትና ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡

ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡

በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡

በልደቱ ማንም ያልገባባት የማይገባባት የሕዝቅኤል የታተመች መቅደስ የተባለች ዘላለማዊት ድንግል እመቤታችንን እንደመረጠ ዛሬም በሆሣዕና ማንም ሰው ያልተቀመጠባት አህያን ከውርንጫዋ ጋር እንዲያመጡ አዘዘ።

ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና።

ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡”

ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑን ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል።

አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ። ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ፡፡ በተጨማሪም ልብስ በልጅነት ይመሰላልና የተገፈፍነውን የጸጋ ልብሳችን (ልጅነትን) ትመልስልናለህ ሲል፨

ቅዱስ ኤፍሬም ይኽነን ሲተረጉም "ልብሳቸውን አውልቀው ያነጠፉለት ሰዎች አሮጌውን ማንነታቸውን ትተው ዐዲሱን ልብስ ክርስቶስን መልበሳቸውን ያስረዳል። ሐዋርያ ጳውሎስ “አሮጌውን ሰውነት አስወግዳችሁ አዲሱን ሰው ልበሱት” እንዳለው (ኤፌ.4፣23) ይኸውም ጥምቀት ነው" ይላል።

ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡

ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ። በተጨማሪም መተርጉማን እንዳመሰጠሩት በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡

በተጨማሪም አህያ ሲፈጥራት በጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ያላት ናትና ትእምርተ መስቀል ያለባት እእርሷ እንድትፈታ ማዘዙ ከ5 ቀን በኋላ በመስቀል ተሰቅሎ በሲኦል የታሠሩትን የሰው ልጆችን ነጻ ሊያወጣ መጥቷልና አህያን መርጧታል፨

ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት አመስጥሯል፡፡

ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው (መዝ.49፡12)፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደ አህያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጿል፡፡

ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነበር። እንስሳዋ እንኳን ጌታ ቢቀመጥባት እንዲህ ክብር ያገኘች ከሆነ ያደረባቸው ቅዱሳንማ የሚገባቸው ክብር ምን ያህል ይሆን? ይልቁኑ 9 ወር ከ5 ቀናት በማሕፀኗ የተሸከመችው ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የሆነውን አምላክ የወለደችው የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርማ እጅጉን ታላቅ ነው።

ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
👍5820👏2
2025/10/21 14:30:23
Back to Top
HTML Embed Code: