💥❖ለአብርሃም የተገለጠ ምስጢረ ሥላሴ ❖💥
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥❖ “በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።”
— ዘፍጥረት 18፥1
👉 መምሬ በኬብሮን ያለች ሲኾን አብርሃም ለእግዚአብሔር መሠዊያ የሠራባት የተቀደሰች ቦታ ናት (ዘፍ 13:18)
👉 በዕብራይስጥ "መምሬ" ማለት ጥንካሬ ወይም የሰባ ማለት ነው። ይኽም የተትረፈረፈ እና መለኮታዊ ጸጋን ያመለክታል።
💥❖ የተገለጡለት ሰዓቱ ቀትር (ስድስት) ሰዓት በዕንጨት ሥር በሰው አምሳል መኾኑ ቀደምት ሊቃውንት ሲያራቅቁት በአብ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በራሱም ፈቃድ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ዘመኑ ሲፈጸም የአብርሃምን ባሕርይ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ በስድስት ሰዓት በዕንጨት መስቀል ላይ ለቤዛ ዓለም የሚሰቀል መኾኑን ያጠይቃል ይላሉ፨
💥❖ ይኽነን ይዞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሕማማት ሰላምታው፦
"ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ
ቀትረ ታሕተ ዕፀ ድርስ
ተሰቀልከ ከመ እቡስ ስብሐት ለከ"
(ምስጋና የተገባኽ ጌታ ድርስ በሚባል የዛፍ ዐይነት ሥር በስድስት ሰዓት ለአባታችን አብርሃም ቀድሞ የተገለጥኽለት ክርስቶስ ሆይ እንደ በደለኛ ተሰቀልኽ) ይላል፨
💥 ሌላው ቀትር (እኩለ ቀን) የፀሐይ ግለት ይበረታል። እግዚአብሔርም በእሳት እንደተፈተነ ወርቅ እምነቱ ተፈትኖ የጠራውን አብርሃምን የጎበኘው በቀዝቃዛ ጊዜ ሳይኾን እንደ እሳት በሚያቃጥል ሰዓት ነው።
👉 ያልታዘዘው አዳምን በሠርክ ሰዓት እግዚአብሔር በአትክልት ስፍራ ሊጎበኘው ሲመጣ በዛፍ ውስጥ ተደበቀ። ታዛዡ አብርሃም ግን በቀትር (ከቀኑ 6 ሰዓት) በዛፍ አጠገብ ሳለ እግዚአብሔር ወደ ርሱ ሲመጣ ቢያየው ለመቀበል ሮጠ።
💥 እኩለ ቀን ፀሐይ በአናታችን ትክክል ከፍተኛው ልዕልናዊ ቦታዋ ላይ የምትደርስበት ሰዓት ሲኾን ሙሉ ብርሃን ሰጥታ ጥላን የምታባርርበት ሰዓት ላይ የክሕደት ጥላ ባላጣላበት አማናዊ ፀሐይ ሥሉስ ቅዱስ ተገልጸውለታል።
👉 በሐዲስ ኪዳንም በተመሳሳይ መልኩ ቅዱስ ጳውሎስን የመለሰው ከሰማይ የታየው ብርሃን በስድስት ሰዓት (ቀትር) ላይ ነበረ (የሐዋ 22:6)።
✍️ “ዐይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ”
— ዘፍጥረት 18፥2
👉 ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው ቢያይ መሮጡ ድንቅ ነው። አርጅቶ 100 ዓመት መልቶት ከግዝረት ቁስል ያገገመ ሲኾን እስኪቀርቡ ሳይጠብቅ መሮጡ የመንፈስ ጥንካሬው፣ እንግዳ ማፍቀሩ፣ በመንፈስ የነቃ መኾኑን ያመለክታል (ዘፍጥረት 17፡24)።
👉 በዚኽ ደጉ አብርሃም አምላክን በመውደድ ፈጣን መንፈሳዊ ሩጫን ለሚሮጡ አብነት ነው።
✍️ “ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፤ ንጉሡ ወደ ቤቱ አገባኝ” እንዲል
— መሓልይ. 1፥4
💥❖ ስላቀረበው ስግደት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሰለዚኽ ነገር በድጓው ላይ፦
"ዮም አብርሃም ሰገደ ለፈጣሪሁ
ሶበ ነጸረ ዋሕደ በሥላሴሁ"
(ዋሕደ ባሕርይ የኾነ እግዚአብሔርን በአካላዊ ሦስትነቱ ባየው ጊዜ አብርሃም ዛሬ ለፈጣሪው ሰገደ) ይላል፨
💥❖ ከዚኽ በኋላ "አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…" በማለት ተናግሯል፡፡
✔"በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ" ብሎ አንድነታቸውን፤
✔"ውሃ ይምጣላችኍ፣ ዕረፉ፣ ትኼዳላችሁ" ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
💥❖ ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ፦
"አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ
ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ"
(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፦
💥❖ ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡-
"እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣
ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት"
(ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡
💥❖ ከዚኽም ምስጢር የተነሣ አብርሃምም ሳራን “ሦስት መስፈሪያ የተሠለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ” በማለት የተገለጸለትን የሦስትነት የአንድነት ምስጢርን አጒልቶ ተናግሯል፡፡
💥❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይኽነን ይዞ በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
"ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ነገሥተ ሰብዐቱ አብያት
እለ በላዕክሙ ውሣጤ ኀይመት
አሐደ ኅብስተ ትሥልስት"
(ከሦስት መስፈሪያ ዶቄት የተጋገረ አንድነት ያለው ኅብስትን በድንኳን ውስጥ የተመገባችሁ የሰባት ቤቶች (ሰማያት) ነገሥት ሆይ ለእናንተ መገዛት (ምስጋና) ይገባል) ይላል፨
💥❖ አብርሃምም በደስታ ኾኖ መዐር፣ ወተት፣ ያዘጋጀውን ጥጃ አመጣላቸው፤ እነርሱም ደስ ይበለው ብለው በግብር አምላካዊ ተመግበዋል፤ መላእክት ሎጥ ቤት፤ ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት ቤት ተመገበ የተባለው አንድ ነው፤ እሳት ቅቤ በላ እንደማለት ብቻ ነው፨
💥❖ ይኸውም ወተትና መዐር መመገባቸው ኦሪትን ወንጌልን መሥራታቸውን ሲያጠይቁ ነው፤ መዐር የኦሪት፤ ቅቤ የወንጌል ምሳሌ ነው፨ ማር ለጊዜው ሲይዝ የሚለቅ አይመስልም፤ ግን ይለቃል ኦሪትም ስትሠራ የምታልፍ አትመስልም ነበር ግን በኽዋላ ዐልፋለች፨ ወተት የወንጌል ምሳሌ ነው፤ ይኽ ወተት ለጊዜው የሚለቅቅ ይመስላል በኽዋላ ሲያጥቡት አይለቅም ወንጌልም ለጊዜው ስትሠራ የምታልፍ ትመስል ነበር፤ በኽዋላ ግን ጸንታ የምትኖር ኾናለችና በማለት መተርጉማን ያራቅቁታል፡
💥 ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ወልድ አብርሃምን "የዛሬ ዓመት እንደዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለኍ፤ ሚስትኽ ሳራም ልጅን ታገኛለች" በማለት ዘመኑ ሲፈጸም እግዚአብሔር ወልድ ከቤተ አብርሃም ከተገኘች ከእመቤታችን የመወለዱንና፤ በሳራ የተመሰለች ወንጌል ምእመናንን እንደምታስገኝ በምስጢር ገልጾለታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም አካላዊ ቃል በሰጠው ተስፋ መሠረት ከነገደ አብርሃም የመወለዱን ነገር ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ "በሕይወታቸው ኹሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ኹሉ ነጻ እንዲያወጣ፤ በሥጋና በደም እንዲኹም ተካፈለ፣ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" በማለት ገልጾታል (ዕብ ፪፥፲፭-፲፮)፡፡
💥❖ ይኽቺ ሥላሴ የገቡባት ኀይመተ አብርሃም (የአብርሃም ድንኳን) የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ይኸውም ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ኹሉ፤ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም፤ አብ ለአጽንኦ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመዋሐድ ዐድረዋል (ሉቃ ፩፥፴፭)፤ በመኾኑም አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ብቻ ናት፡፡

❤67👏3🥰2👍1
💥❖ ሊቁም በነገረ ማርያም ይኽነን ምስጢር ሲገልጽ "ወይእቲ ኀይመት ትትሜሰል በድንግል ወዕደው አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሙንቱ፤ አብ አጽንኣ፣ ወወልድ ተሰብአ እምኔሃ፣ ወመንፈስ ቅዱስ ቀደሳ ከመ ትጹር አምላከ በከርሣ" (ያቺ ድንኳንም በድንግል ትመሰላለች፤ ሰዎቹም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ አብ አጸናት፣ ወልድም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ቃል አምላክን ትሸከም ዘንድ ለያት) በማለት ተርጉሞታል፨
💥❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በሰላምታ መጽሐፉ ላይ መጽሐፉ፦ "ኀይመተ አብርሃም አብ ሰላም ለኪ፤
ዘኮንኪ ከመ ተድባብ ሰላም ለኪ"
(እንደ ጥላ የኾንሽ የአባት አብርሃም ድንኳን ሰላምታ ይገባሻል) በማለት አመስግኗታል፡፡
💥❖ ይኽ አብርሃም የተቀበለውን የተስፋ ቃል ሊቃውንት ሲተረጒሙት "ኦ አኃውየ በይነ መኑ እንከ ዘይቤ እግዚአብሔር ለአብርሃም አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ አኮኑ እግዝእትነ ማርያም ይእቲ ዘወፅአት እምነ ሥርው ለአዳም ..." (ወንድሞቼ ሆይ እግዚአብሔር አብርሃምን እንደዛሬው ኹሉ ወደአንተ ተመልሼ እመጣለኍ ያለው ስለማን ይመስላችኋል? ከአዳም ሥር ወጥታ፤ ከኖኅ አብራክ ተገኝታ፤ ወደ አብርሃም አብራክ ልትከፈል፤ ሥላሴ በአብርሃም ቤት በእንግድነት ተገኝተው፤ ከአብርሃም ዘር ከእመቤታችን የእግዚአብሔርን ልጅ ሰው መኾን ስለርሷ የተናገሩላት እመቤታችን ድንግል ማርያም አይደለችምን፤ ስለዚኽ እግዚአብሔር ስለ እመቤታችን ጥንታዊ የልደቷን አመጣጥ በየጊዜው ምልክት እንደሚሰጥ ልብ አድርገን ማስተዋል ይገባናል) በማለት አብራርተው ተርጒመዋል፡፡
💥❖ ሊቁ አባ ሕርያስቆስም በቅዳሴው በቊ ፴፪ ላይ "ተናግዶቱ ለአብርሃም" (የአብርሃም እንግድነቱ አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን ጠቅልሎ የገለጠውን ይኽነን ድንቅ ምስጢር፤ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ በስፋትና በጥልቀት፡-
♥ "ወዓዲ ኀይመት ዘአብርሃም ዘውስቴታ ተአንገደ እግዚአብሔር አኮ ከማሁ ዘኮነቶ ምጽላለ በእንተ ምዕር አላ ኮነቶ እመ ወተከድነ ሥጋሃ ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ"
(ዳግመኛም እግዚአብሔር (በሦስትነት) በዕንግድነት ያረፈባት የአብርሃም ድንኳን አንቺ ነሽ፤ ለጥቂት ጊዜ ብቻ መጠለያን፣ መጠጊያን የኾነቺው አይደለም፤ እናትን ኾናው ሥጋዋን ተዋሕዶ ከመለኮቱ አንድ አደረገው እንጂ) በማለት በአብርሃም ድንኳን ብትመሰልም እንኳ ክብሯ ከፍ ያለ፤ ለዘላለም የአምላክ ማረፊያውና እናቱ መኾኗን አብራርቶ ገልጧል፡፡
💥❖ ሊቅነትን ከንግሥና ጋር ያስተባበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በመጽሐፈ ሥላሴ መጽሐፉ ላይ፦
👉 "ኦ ብእሲ ዘትትከሓድ አይኑ ዕለት ለአግዚአብሔር ሰገዱ ሎቱ ምስለ መላእክቲሁ በዕሪና እምነ ኩሉ ፍጡራኒሁ..."
(ሥላሴን የምትክድ አንተ ሰው ሆይ ከፍጡሮች ወገን በመላ እግዚአብሔርን ከመላእክቱ ጋር በአንዲት ዕሪና የሰገዱለት በማናቸው ዕለት ነው? በማናቸው ዕለት እግዚአብሔር ከፈጠራቸው መላእክቱ ጋር ተካክሎ እግሩን ታጠበ? በማናቸው ዕለት በሰው መጠለያ በታች ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ ተጠለለ? በማናቸው ዕለት ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ እግዚአብሔር በላ? በማናቸው ዕለት ከአዳም ልጆች ወገን ሰው ወደ ፈጣሪው በለመነ ጊዜ መላእክቱ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር ተካክለው እንዲኽ አድርግ መቼ አሉ? አንተ ሥላሴን የካድኽ ከሓዲ ፍጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር በመተካከል እንዲሰገድላቸው ለምን ታመጣቸዋለኽ? ፈጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር ተካክለው በአብርሃም ቤት እንደተጠለሉ፤ እግራቸውን እንደታጠቡ፤ ዐብረው እንደበሉ አድርገኽ ለምን ታስተካክላለኽ? አንተ ከእኛ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የኾንኽ ክርስቲያን አንዱ እግዚአብሔር ነው፤ ኹለቱ መላእክት ናቸው አትበል) በማለት አስፍቶ ይጽፋል፨
✔❖በቤተ አብርሃም የገቡ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዘወትር በቤተ ልቡናችን ውስጥ ግቡልን፨❖✔
[ለበለጠ ምስጢር "መልክአ ሥላሴ ንባቡና ትርጓሜው" መጽሐፌን ያንብቡ]፨

❤156👍21🔥6
[ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡
❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡
❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡
❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡
❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሦስት ዓመቱ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል።
❖ ጥር ፲፮ በ304 ዓ.ም. ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ሌሎችም በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡
✔ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ
ወስምዖ መጥበቤ
ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ
ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ
ለአባልከ ሰላም እቤ”
(እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦
“ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ
በልደት ንዑስ፤
ንጹሕ ከመ ዕጣን
ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡
(በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል)
❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡
(ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨
[የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨
[ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)

❤210👏8👍3🥰1
💥 እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችኹ
👉 በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን
የውዳሴ ማርያም እና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
(ከነሐሴ 1 - 14)
👉 በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
👉 ከሰኞ - ዐርብ ከቀኑ 4:30 - 6:00 (ከቅዳሴ አስቀድሞ)
👉 ቅዳሜ እና እሑድ (ከጠዋቱ 2:00 - 3:00) (ከቅዳሴ በመቀጠል) ይከናወናል።
👉 በመላው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚኽ ሱባኤ በሰዓታት ለሚያድሩ ካህናትና ዲያቆናት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በረከት
👉 በስብሐተ ነግህ ለሚያገለግሉ ማሕሌታውያን የቅዱስ ያሬድ በረከት
👉 በቅዳሴ ማርያም የሚያገለግሉ አበው ካህናት የአባ ሕርያቆስ በረከት
👉 በትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ለሚያገለግሉ ሊቃውንት የቅዱስ ኤፍሬምን በረከት
👉 በትምህርተ ወንጌል ለሚያገለግሉ መምህራን የሐዋርያት በረከት
💥 በአጠቃላይ የመስቀል ሥር ስጦታቸውን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷን በመሻት ሱባኤዋን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በማስቀደስ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በመቀበል ለሚያሳልፉ ምእመናንና ምእመናት ኹሉ የወላዲተ አምላክ በረከቷ እንዲያድርባችኹ በመመኘት መልካም ሱባኤ እመኛለኹ።

❤266👍52🥰20👏4🔥3