Telegram Web Link
Today was the last day of the St. Paul’s 3rd Quality summit. Over 40 hospital managers, vice heads, and quality directors visited the exhibition.
They also visited the hospital departments and wards. The guests commented on how St. Paul Hospital has excelled in its service.
Endocrine and Breast surgery fellowship graduates of St. Paul, 2024.
አስደሳች ዜና
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከ Operation Smile ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመደበኛነት ሳምንቱን ሙሉ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?
እንግዲያውስ የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ችግር Cleft lip እና Cleft palate ያለባችሁ በመሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ 976 የነጻ መስመር ወይም በስልክ ቁጥር 0903573176 በመደወል እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን፡፡ በተጨማሪም ወደ ሆስፒታሉ በመሔድ መመዝገብ ይችላሉ;;
ሕክምናውን ለማግኘት የተመዘገቡ በሙሉ ዘወትር ሰኞ : ረቡዕእና አርብ ቅድመ ምርመራ ለማድረግ በኮሌጁ የተመላላሽ ሕክምና ማዕከል መገኘት አለባቸው፡፡
ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ ታካሚዎች የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲሁም ለሚያድሩት ;የአልጋ (መኝታ ) ወጪ ይሸፈናል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና Operation smile

Oduu Gammachiisaa
Koolleejiin Fayyaa hospitaala Qidus paulos dhabbata operation smile waliin ta’uun daa’immanii fi ga’eessota dhalootaan rakkoo baqaquu hidhii fi qoonqoo qabaniif tajaajila baqaqsanii yaaluu bilisaan itti fufiinsaan torbee guutuu akka kennu ni beektuu?
Kanaafu, namooti rakkoo baqaquu hidhii fi qoonqoo qabdan hundi Koolleejii Fayyaa hospitaala Qidus Paulositti toora bilbilaa bilisaa 976 tti ykn 0903573176 bilbiluun akkasumas qaamaan hospitaalicha dhaquun akka galmaa’uu dandeessan isin hubachiifna.
Yaalii kana argachuuf namoonni dursitanii toora 976n ykn 0903573176 galmooftan hundi guyyota Wiixata,Roobii fi jimaata ganama sa’a lamaan wiirtuu yaalii deddeebii hospitaala Paulos calallii duraatiif qaamaan argamuu qabdu.
Yaalamtoota magaalaa Finfinnee alaa dhufaniif baasiin geejjibaa fi dhiheessi nyaataa kan godhamu yoo ta’u yaalamtoota bakka bulti barbaachisuuf haalli kan mijatu ta’a.
Koolleejiin Fayyaa hospitaala Qidus paulos fi operation smile
ባለፈው ሐምሌ ወር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ከ90 ሺህ ወገኖች ነጻ የሕክምና ምርመራ ባገኙበት ብሄራዊ የክረምት በጎ ፍቃድ ጤና አገልግሎት የተሳተፉ ሠራተኞች የተመሠገኑበት የእውቅና መርሐግብር ዛሬ ተካሄደ: :

በተጨማሪም ለአራት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ባለፈው ሐሙስ የተጠናቀቀው እና በኤግዚቢሽን በፓናል ውይይቶች የታጀበው እና የክልል የሆስፒታል እና የፌዴራል ሆስፒታሎች ኃላፊዎችንም ጭምር ያሳተፈው 3ኛው የጥራት ጉባዔ ( 3rd Quality Summit ) የመዝጊያ ሥነ ሥርዓትም ተካሂዷል :: ጉባዔው " ልህቀትን መቀበል፡ ለጥራት፣ ለአገልግሎት እና ለዕውቅና የተሰጠ ቁርጠኝነት” በሚል መሪ ቃል ላይ ትኩረት ያደረገ ነው: :
በእነዚህ በኮሌጁ በተከናወኑ ሁለትዓበይት ኩነቶች የእውቅና እና የምሥጋና መርሐ ግብር በአስተዋጽአቸው ጉልህ ተግባር ላከናወኑ ሠራተኞችና የሥራ ክፍሎች የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ከኮሌጁ ፕሮቮስት ዶር ሲሳይ ስርጉ እጅ ተቀብለዋል::
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ዶር ሲሳይ ኮሌጁ ወደፊት ለማሕበረሰቡ የሚሠጠውን ነጻ የሕክምና አገልግሎት ብዙኃኑን ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል:: በመቀጠልም የሕክምና አገልግሎት በጥራት እና በላቀ ሁኔታ ለመስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ሁሉ እንሠራለን ሲሉ ተናግረዋል : :
Kalkidan selected as a best Adult ICU Nurse of the Year!
Sr. Sr Kalkidan Zerihun, Professional nurse, was selected by the Department of Critical care medicine as a best Adult ICU Nurse of the Year 2016 (2023/24). She is nominated by nursing and others the department staff to honor her for exceptional service over the past year.
ለ National Graduate Admission Test (NGAT) አመልካቾች በሙሉ፦

የመግቢያ ፈተናዉ የሚሰጠዉ ነሀሴ 30 እና ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም ከጧቱ፡ 2፡30 ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም ተፈታኞች ከፈተና ሰዓቱ ቀደም ብላችሁ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አካዳሚክ ግቢ በመገኘት የፈተና Username and Password መዉሰድ እና የመፈተኛ ክፍላችሁን ማወቅ ይጠበቅባችኋል፡፡

ማሳሰቢያ፡ ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝን አትርሱ፡፡
ነሐሴ 29/2016 ዓ.ም፤
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

ለወቅታዊ መረጃ ይቀላቀሉን፡
https://www.tg-me.com/SPMMC
St_paul_ngat_Exam_schedule.pdf
638.1 KB
#SPHMMC
ቀን፡ 30/12/2016 ዓ.ም
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ ‘NGAT’ ፈተና ማዕከል አድርጋችሁ ለመረጣችሁ ተፈታኞች በሙሉ
NGAT የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኮሌጃችን ለተመደባችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 (ስምንት ሰዓት) ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን ሁሉም ተፈታኞች ከ7:00 ጀምሮ የመፈተኛ ክፍላችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
በማእከላችን የምትፈተኑ ተማሪዎች ስማችሁ ተያይዟል፡፡
መልካም ዕድል!
በፈተና ወቅት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ አለባችሁ::

ለተጨማሪ መረጃ ይጎብኙን፡ https://www.tg-me.com/SPMMC
https://www.facebook.com/sphmmc
2025/07/10 05:35:10
Back to Top
HTML Embed Code: