የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 15 ቀን “ March 24” ይከበራል፡፡ በዓሉ ዘንድሮ በዓለም ለ412 ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ ለ18ኛ ጊዜ ከሚካሄደው ብሔራዊ የቲቢ ምርመር ጉባኤ ጋር ተቀናጅቶ ይከበራል፡፡ የዘንድሮው የዓለም ቲቢ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በእባምንጭ ከተማ ተከብሯል፡፡ ፡የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ የሚከበርበት ዋና ምክንያት በሽታው ዛሬም በሰው ዘር ላይ ከፍተኛ ሕመምና ሞት እያስከተለ መሆኑን ለማስገንዘብና የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር የሚከናወኑትን ሁሉን አቀፍ ተግባራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተጠናከረ መልክ እንዲቀጥል ለማስቻል ነው፡፡ ዕለቱ መጋቢት 15 ቀን እንዲሆን የተመረጠውም የዛሬ 142 ዓመት “March 24, 1882” ታዋቂው ጀርመናዊ ተመራማሪ ዶ/ር ሮበርት ኮች፣ “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” ተብሎ የሚታወቀውን የቲቢ በሽታ መንስኤ ማግኘቱን ለዓለም ያበሰረበትን ቀን ለማስታወስ ሲባል ነው፡፡
3 የቲቢ በሽታ ምንድን ነው?
የቲቢ በሽታ በአገራችን በተለምዶ የሳምባ ነቀርሳ የሚባለው በሽታ ሲሆን ቲቢ የተባለውን የአሁኑን ሲያሜ ያገኘው ቲዩበርክሎሲስ ተብሎ ከሚጠራው የበሽታው የእንግሊዘኛው ቋንቋ አህጽሮተ-ቃል ነው፡፡ መንስኤም አልፎ አልፎ እንደሚነገረው ብርድ ወይም ንፋስ ሳይሆን ረቂቅ የሆነና ቀደም ሲል እንደተገለጸው “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” የተባለ ባክቴሪያ ነው፡፡ ቲቢ “ማይኮባክቴሪያም ቦቪስ” በተባለ ባክተሪያ የተጠቁ የቤት እንስሳት ወተት ሳይፈላ ቢጠጣ ከእንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እንደሚችልም ተረጋግጧል፡፡
4 ቲቢ የትኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ያጠቃል?
ቲቢ ዕድሜን፣ ፆታን፣ ዘርንና ቀለምን ሳይለይ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ምንም እንኳን በሽታው ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ቢያጠቃም በበሽታው በበለጠ የሚጠቁት በአምራች ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙና የቤተሰብ ኃላፊ የሆኑ ዜጎች ናቸው፡፡
በተያያዘም ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት፣ አረጋዊያን፣ የሰውነት መከለከያ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ለምሳሌ ኤች አይ ቪ፣ የካንሠር እና የስኳር ሕሙማን፣ የምግብ እጥረት ያለባቸው፣ በአክታ ምርመራ ቲቢ እንዳለባቸው ከተረጋገጠ ሕሙማን ጋር አብረው የሚኖሩ እንዲሁም በተጨናነቁና በተፋፈጉ ቦታዎች የሚኖሩ/የሚሠሩ/የሚሰባበሱ ሰዎች እንዲሁም የአልኮንና የትምባሆ ሱሰኞችም ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡
5 የቲቢ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?
ቲቢ የሚተላለፈው በአብዛኛው በትንፋሽ አማካኝነት ነው፡፡ ይኸውም አንድ በሳምባ ቲቢ የተያዘ ሕመምተኛ በሚስልበት፣ በሚያስነጥስበት፣ በሚተፋበት፣ ወይም በሚናገርበት ወዘተ... ወቅት የቲቢ በሽታ አምጪ ባክቴሪያን የያዙ የአክታ ብናኞች ወደ አየር ስለሚረጩና ብናኞችም በአቅራቢያው ያሉ ሰዎች አየር ወደ ውስጥ በሚተነፍሱበት ጊዜ በቀላሉ ወደ ሳንባው ውስጥ ገብተው ለማጥቃት ዕድል ስለሚያገኙ ነው፡፡
6 የቲቢ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
የቲቢ በሽታ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነውን የሚያጠቃው ሳምባን በመሆኑ የሳንባ ቲቢ በሽታ ዋናው ምልክት ሁለት ሳምንትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ የዘለቀ ሳል ነው፡፡ ሳሉ አክታ ያለውና ደም የቀላቀለ ወይም ያልቀላቀለ ወይም ደረቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ሕመምተኛው ከሳሉ በተጨማሪ በደረቱ አካባቢ የውጋት ስሜት፣ መጠነኛ የሆነ ትኩሳት፣ ሌሊት በመኝታ ጊዜ ማላብ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስና የሰውነት መድከም የመሳሰሉ አጠቃላይ የሆኑ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ የበሽታም ምልክቶች እንደተጠቃው የሰውነት ክፍል ዓይነት ይለያያሉ፡፡
7 የቲቢ በሽታን ማዳን ይቻላል?
ቲቢ መድኃኒት ስለአለው በአግባቡ ከታከሙት የሚድን በሽታ ነው፡፡ የበሽታው ምርመራም ሆነ ሕክምና በመንግሥታዊና ሕክምናውን እንዲሰጡ በተፈቀደላቸው የግል ጤና ተቀቋማት በነፃ ማግኘት ስለሚቻል ማንኛውም ሰው የበሽታው ምልክቶች ሲታዩበት አገልግሎቱን ወደሚሰጥ ጤና ድርጅት መሄድ ይኖርበታል፡፡ የቲቢ መድኃኒት በታዘዘው መጠንና ጊዜ ባይወሰድ ችግር ያስከትላል፡፡ ስለሆነም ሕመምተኛው የታዘዘለትን መድኃኒት ሳያቋርጥ በየቀኑ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ሕክምናው ከተቋረጠ ግን የበሽታ መንስኤ የሆነው ባክቴሪያ የፀረ-ቲቢን መድኃኒቶችን በመላመድ በመደበኛው የቲቢ ሕክምና ዘዴ መዳን የማይችል የቲቢ ዓይነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
8 መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ምንድን ነው?
መድኃኒትን የተላመደ ቲቢ በሽታ መድኃኒት ያልተላመደ ቲቢን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን የተላመደ የቲቢ በሽታ ዓይነት ነው፡፡ በሽታው የሚከሰተው ታካሚዎች መድኃኒቶችን በታዘዘው መሠረት ካላመውሰድና የክትትል ጉደለት ቢሆንም በሽታው መድኃኒት እንዳልተላመደው ቲቢ ሁሉ በትንፋሽ አማካይነትም ይተላለፋል፡፡ መድኃኒት ያልተላመደውም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢ ዓይነቶች መንስኤያቸው፣ መተላለፊያ መንገዶቻቸውና ምልክቶቻቸው ተመሳሳይ ቢሆኑም መድኃኒትን ለተላመደ ቲቢ ሕክምና የሚሰጡ መድኃኒቶች ዓይነትና ብዛት እንዱሁም ሕክምናው የሚፈጅበታ ጊዜ ይለያል፡፡ ይሁን እንጂ መድኃኒትን የተላመደው ቲቢም በአግባቡ ከታከሙት መዳን ይችላል፡፡
9 የቲቢ በሽታን መከላከል ይቻላል?
መድኃኒት ያልተላመደውንም ሆነ መድኃኒት የተላመደ ቲቢን መከላከል ይቻላል፡፡ ስለሆነም የቲቢ ሕሙማን፣ ቤተሰቦቻቸውና በአጠቃላይ ሕብረተሰቡ የግልና የጋራ ኃላፊነታቸውንና ድርሻቸውን በታማኝነት ቢወጡ የበሽታው የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ እንደሚፋጠን ይታመናል፡፡

የዓለም የቲቢ ቀን ተከበረ
በዓለም ለ28ኛ ጊዜ በኢትዩጲያ ለ19ኛ ጊዜ የዓለም ቲቢ ቀን በአርባምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ "በርግጥም የቲቢን በሽታ መግታት እንችላለን! ቃል በተግባር ፣ ሐብት ለውጤት በሚል መሪቃል ተከብሯል፡፡የዓለም የቲቢ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ በማድረግ ተከብሯል።
ጤና ሚኒስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ከቲቢ ምርምር አድቫይዘሪ ካውንስል"TRAC" እንዲሁም ከአለም ጤና ድርጅትና የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጤና ጉባዔ ማጠናቀቂያ መድረክም ተካሂዷል።
በዓለማችን ከሚገኙ ህዝቦች 1/4ኛ የሚሆነው ህዝብ በቲቢ አምጪ ተዋህሲ የተያዙ ሲሆን በ2024 እ.ኤ.አ በወጣው የዓለም ጤና ድርጅት ሪፓርት መሰረት ወደ 10.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ወደ 1.3 ሚሊዩን የዓለማችን ህዝቦች ደግሞ በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
የቲቢ በሽታ በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጩና ከፍተኛ ሞት ከሚያስከትሉ ተላላፊ በሽታዎች አንዱ ነው፡፡
አገራችን ኢትዮጲያ የቲቢ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጨባቸው 30 ያዓለም አገራት ውስጥ ትገኛለች ፡፡
(የከብረ በዐሉን ፎቶ ይመልከቱ) @StopTB

Meet this year’s top graduating medical student, Dr. Ruth Feyessa! With an impressive GPA of 3.82, she plans to specialize in internal Medcine. We are incredibly proud of you, Ruth! She has earned a remarkable distinction, and we couldn’t be more thrilled for her achievements! On April 6th, 2025, we will celebrate her and all of our other graduates at a ceremony at the Sheraton Addis.
የኮሌጁ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማእከል ከቱርክ በንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት ከሚሰራ ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አደረገ፡፡
ከቱርክ “Turkish Transplant Foundation’’ ከሚባል በአካል ንቅለ ተከላ ዙሪያ ከሚሰራ ድርጅት የመጡ የልኡካን ቡድን ከኮሌጁ ፕሮቮስት ዶር ሲሳይ ስርጉ እና በመሰኩ ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር በትብብር ለመስራት ውይይት አድርጓል፡፡
የቱርክ ንቅለ ተከላ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ዶር ኢየፕ ካህቫሲ ጋር በተደረገው ውይይት እንደተገለጸው የኮሌጁ ንቅለ ተከላ ሕክምና ማእከልን በአፍሪካ የንቅለ ተከላ የልህቀት ማእከል እንዲሆን ለመስራት ፋውንዴሽኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
በመስኩ ሰፊ ልምድ ካላት ቱርክ በዚሁ ረገድ በሀገራችን ለሚወጡ የ ንቅለ ተከላ መመሪያዎችን ፣ ልዩ ልዩ ሰነዶችን እና ሕግጋቶችን አሰመልክቶ የአለም አቀፍ ደረጃዎችን የጠበቁ እንዲሆኑ ፋውንዴሽኑ ያማክራል፡፡ እንዲሁም በኮሌጁ የሚሰጠው የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብአትን ለሟሟላት ፋውንዴስኑ በሚሰራበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓል፡፡ የንቅለ ተከላውንም አድማስ በማስፋት
የጉበት እና ሌሎችም የንቅለ ተከላ ዘርፎችን ለማስጀመር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በተጨማሪም ንቅለ ተከላን አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የምዝገባ ቋትን ዲጂታል ለማድረግ እና በመስኩ የላቀ የስራ ግኑኙነት ከኮሌጁ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ በልኡካን ቡድኑ ጋር የመጡ የኩላሊት ቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች በወቅቱ በኮሌጁ በመደበኛነት ከሚሰሩት ሦስት ንቅለ ተከላዎች በተለይ በአንዱ የቀዶ ህክምና ላይ በlaparoscopy የታገዘ የንቅለ ተከላ ሕክምና ሰጥተዋል፡፡ ይህም የልምድ ልውውጥ በስልጠና እንደሚደገፍ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማእከል በኢተዮጵያ የመጀመሪያው ማእከል ሲሆን፡ ዜጎች አገልግሎቱን በሀገራቸው እንዲያገኙ አድርጓል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የጤና ሚኒስቴር ዶር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ከቱርክ በኢትዮጵያ አምባሰደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ባደረጉት ውይይት በቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ማእከል ለማቋቋም በሚያስችል ፕሮጀክት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ዶር መቅደስ ከቱርክ አምባሳደር በሚመራው የTurkish Transplant Foundation ጋር ባደረጉት ወይይት እንደተገለፀው በኮሌጁ የአካል ንቅለ ተከላ ማእከል በተጨማሪ የንቅለ ተከላ ሲሙሌሽን ማሰልጠኛ ማእከልን ማቋቋምን ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ የተሰማሩ የኮሌጁን ባለሙያዎችንም ማሰልጠንም ይመለከታል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ የጤና ሚኒስቴር ዶር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ከቱርክ በኢትዮጵያ አምባሰደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ባደረጉት ውይይት በቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ማእከል ለማቋቋም በሚያስችል ፕሮጀክት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ዶር መቅደስ ከቱርክ አምባሳደር በሚመራው የTurkish Transplant Foundation ጋር ባደረጉት ወይይት እንደተገለፀው በኮሌጁ የአካል ንቅለ ተከላ ማእከል በተጨማሪ የንቅለ ተከላ ሲሙሌሽን ማሰልጠኛ ማእከልን ማቋቋምን ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ የተሰማሩ የኮሌጁን ባለሙያዎችንም ማሰልጠንም ይመለከታል፡፡

Meet this year’s top graduating medical student, Dr. Haset Legesse! With an impressive GPA of 3.85, she plans to specialize in Gastroenterology. We are incredibly proud of you, Haset ! She has earned a remarkable distinction and is ranked 2nd in her class. We couldn’t be more thrilled about her achievements! On April 6th, 2025, we will celebrate her and our other graduates at a ceremony at the Sheraton Addis.
Meet this year’s top graduating medical student, Dr. Hony Godana! With an impressive GPA of 3.92, she plans to specialize in Pediatric Surgery. We are incredibly proud of you, Hony! She has earned a remarkable distinction and is ranked 1st in her class. We couldn’t be more thrilled about her achievements!
Recently, her accomplishments were recognized by the Ethiopian Medical Association (EMA).
On April 6th, 2025, we will celebrate her and our other graduates at a ceremony at the Sheraton Addis.

General Surgery graduates of St. Paul’s Millennium Medical College, 2025