Telegram Web Link
የዓለም የቲቢ ቀን ተከበረ
በዓለም ለ28ኛ ጊዜ በኢትዩጲያ ለ19ኛ ጊዜ የዓለም ቲቢ ቀን በአርባምንጭ ከተማ በደማቅ ሁኔታ "በርግጥም የቲቢን በሽታ መግታት እንችላለን! ቃል በተግባር ፣ ሐብት ለውጤት በሚል መሪቃል ተከብሯል፡፡የዓለም የቲቢ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ በማድረግ ተከብሯል።
ጤና ሚኒስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ከቲቢ ምርምር አድቫይዘሪ ካውንስል"TRAC" እንዲሁም ከአለም ጤና ድርጅትና የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጤና ጉባዔ ማጠናቀቂያ መድረክም ተካሂዷል።
በዓለማችን ከሚገኙ ህዝቦች 1/4ኛ የሚሆነው ህዝብ በቲቢ አምጪ ተዋህሲ የተያዙ ሲሆን በ2024 እ.ኤ.አ በወጣው የዓለም ጤና ድርጅት ሪፓርት መሰረት ወደ 10.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ወደ 1.3 ሚሊዩን የዓለማችን ህዝቦች ደግሞ በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
የቲቢ በሽታ በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጩና ከፍተኛ ሞት ከሚያስከትሉ ተላላፊ በሽታዎች አንዱ ነው፡፡
አገራችን ኢትዮጲያ የቲቢ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጨባቸው 30 ያዓለም አገራት ውስጥ ትገኛለች ፡፡
(የከብረ በዐሉን ፎቶ ይመልከቱ) @StopTB
Meet this year’s top graduating medical student, Dr. Ruth Feyessa! With an impressive GPA of 3.82, she plans to specialize in internal Medcine. We are incredibly proud of you, Ruth! She has earned a remarkable distinction, and we couldn’t be more thrilled for her achievements! On April 6th, 2025, we will celebrate her and all of our other graduates at a ceremony at the Sheraton Addis.
የኮሌጁ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማእከል ከቱርክ በንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት ከሚሰራ ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አደረገ፡፡
ከቱርክ “Turkish Transplant Foundation’’ ከሚባል በአካል ንቅለ ተከላ ዙሪያ ከሚሰራ ድርጅት የመጡ የልኡካን ቡድን ከኮሌጁ ፕሮቮስት ዶር ሲሳይ ስርጉ እና በመሰኩ ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር በትብብር ለመስራት ውይይት አድርጓል፡፡

የቱርክ ንቅለ ተከላ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ዶር ኢየፕ ካህቫሲ ጋር በተደረገው ውይይት እንደተገለጸው የኮሌጁ ንቅለ ተከላ ሕክምና ማእከልን በአፍሪካ የንቅለ ተከላ የልህቀት ማእከል እንዲሆን ለመስራት ፋውንዴሽኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በመስኩ ሰፊ ልምድ ካላት ቱርክ በዚሁ ረገድ በሀገራችን ለሚወጡ የ ንቅለ ተከላ መመሪያዎችን ፣ ልዩ ልዩ ሰነዶችን እና ሕግጋቶችን አሰመልክቶ የአለም አቀፍ ደረጃዎችን የጠበቁ እንዲሆኑ ፋውንዴሽኑ ያማክራል፡፡ እንዲሁም በኮሌጁ የሚሰጠው የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብአትን ለሟሟላት ፋውንዴስኑ በሚሰራበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓል፡፡ የንቅለ ተከላውንም አድማስ በማስፋት
የጉበት እና ሌሎችም የንቅለ ተከላ ዘርፎችን ለማስጀመር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም ንቅለ ተከላን አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የምዝገባ ቋትን ዲጂታል ለማድረግ እና በመስኩ የላቀ የስራ ግኑኙነት ከኮሌጁ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ በልኡካን ቡድኑ ጋር የመጡ የኩላሊት ቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች በወቅቱ በኮሌጁ በመደበኛነት ከሚሰሩት ሦስት ንቅለ ተከላዎች በተለይ በአንዱ የቀዶ ህክምና ላይ በlaparoscopy የታገዘ የንቅለ ተከላ ሕክምና ሰጥተዋል፡፡ ይህም የልምድ ልውውጥ በስልጠና እንደሚደገፍ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማእከል በኢተዮጵያ የመጀመሪያው ማእከል ሲሆን፡ ዜጎች አገልግሎቱን በሀገራቸው እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የጤና ሚኒስቴር ዶር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ከቱርክ በኢትዮጵያ አምባሰደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ባደረጉት ውይይት በቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ማእከል ለማቋቋም በሚያስችል ፕሮጀክት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ዶር መቅደስ ከቱርክ አምባሳደር በሚመራው የTurkish Transplant Foundation ጋር ባደረጉት ወይይት እንደተገለፀው በኮሌጁ የአካል ንቅለ ተከላ ማእከል በተጨማሪ የንቅለ ተከላ ሲሙሌሽን ማሰልጠኛ ማእከልን ማቋቋምን ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ የተሰማሩ የኮሌጁን ባለሙያዎችንም ማሰልጠንም ይመለከታል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ የጤና ሚኒስቴር ዶር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ከቱርክ በኢትዮጵያ አምባሰደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ባደረጉት ውይይት በቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ማእከል ለማቋቋም በሚያስችል ፕሮጀክት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ዶር መቅደስ ከቱርክ አምባሳደር በሚመራው የTurkish Transplant Foundation ጋር ባደረጉት ወይይት እንደተገለፀው በኮሌጁ የአካል ንቅለ ተከላ ማእከል በተጨማሪ የንቅለ ተከላ ሲሙሌሽን ማሰልጠኛ ማእከልን ማቋቋምን ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ የተሰማሩ የኮሌጁን ባለሙያዎችንም ማሰልጠንም ይመለከታል፡፡
Anesthesiology,critical care and Pain Medicine of St.Paul's,2025
Meet this year’s top graduating medical student, Dr. Haset Legesse! With an impressive GPA of 3.85, she plans to specialize in Gastroenterology. We are incredibly proud of you, Haset ! She has earned a remarkable distinction and is ranked 2nd in her class. We couldn’t be more thrilled about her achievements! On April 6th, 2025, we will celebrate her and our other graduates at a ceremony at the Sheraton Addis.
Meet this year’s top graduating medical student, Dr. Hony Godana! With an impressive GPA of 3.92, she plans to specialize in Pediatric Surgery. We are incredibly proud of you, Hony! She has earned a remarkable distinction and is ranked 1st in her class. We couldn’t be more thrilled about her achievements!
Recently, her accomplishments were recognized by the Ethiopian Medical Association (EMA).
On April 6th, 2025, we will celebrate her and our other graduates at a ceremony at the Sheraton Addis.
General Surgery graduates of St. Paul’s Millennium Medical College, 2025
Pediatric and Child Health Graduates of St.Paul's,2025
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው ዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
2025/07/01 11:47:21
Back to Top
HTML Embed Code: