Telegram Web Link
ለይሁዳ ወልዱ ወውሉደ ወልዱ ይደምሰስ

ዘደብረ ምሕረት አርብ ሚያዝያ ፳፭/፳፻፲፱ ዓ.ም

የማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ይቀላቀሉ👇

የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት መገናኛ ብዙኃን ( መራሒ ሚዲያ )

👉 የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com /profile.php?id=100069444095761

👉 የቴሌግራም አድራሻ: @SaintGebrielSundaySchool

👉 የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared
ገብረ ሰላመ ቀዳሚት ሥዑር ዘደብረ ምሕረት

የበዓሉ ነገር እንደ ምን ነው ቢሉ

#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤  #ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ)
#ሰንበት_ዐባይ #ቅዱስ_ቅዳሜ#ቀዳሚት_ሰንበት

#ቀዳሚት_ሰንበት፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ያረፈባት ስለሆነች፤ የእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት፤ ቀዳሚት ሰንበት (የዕረፍት ቀን) ትባላለች፡፡

#ሰንበት_ዐባይ (ታላቋ ሰንበት)፤ የመጀመሪያዋ ሰንበት በመሆኗ ታላቋ ሰንበት ትባላላች፡፡

#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤ እግዚአብሔር ሥነ ፈጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በከርሰ መቃብር አርፎባታል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡

፠ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡

#ቅዱስ_ቅዳሜ፤ ለ5500 በሲኦል ሲማቅቁ የነበሩ ነፍሳትን ሰላም ለሁላችሁን ይሁን ብሎ ወደ ገነት አስገብቷቸዋልና፤ ይህች ቅዳሜ ቅዱስ (የተለየች) ቅዳሜ ትባላለች፡፡

አውረድዎ፥ አውረድዎ፥ አውረድዎ እምዕፅ፤
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕዉስ፡፡
ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ፤
በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን፡፡

©የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-
መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ት/ቤት

የማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ይቀላቀሉ👇
የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት መገናኛ ብዙኃን ( መራሒ ሚዲያ )

👉 የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com /profile.php?id=100069444095761

@SaintGebrielSundaySchool

👉 የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared
የ"ገብረ ሰላመ" በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ።

በየዓመቱ በበዓለ ትንሣኤ ዋዜማ "በቀዳም ስዑር" የሚከበረው የገብረ ሰላመ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአከኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ዛሬ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓተ አምልኮ ተከበረ።

በዓሉ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን መፈጸሙ የሚዘከርበት፣ በመስቀል ላይም በፈጸመው የማዳን ሥራ ለዓለም ድኅነትን መስጠቱ የሚታወጅበት ታላቅ ሃይማኖታዊ በዓል ነው። በኖኅ ዘመን መጥቶ የነበረው ጥፋት ማብቃቱ ርግቧ ይዛ በመጣችው የወይራ ቅጠል እንደታወቀ ሁሉ በአዳም በደል ምክንያት በሰው ልጆች የውድቀት ዘመን ማብቃቱ የሚታወጅበት ቄጤማም በቅዱስ ፓትርያርኩ ለበዓሉ ታዳሚዎች ሁሉ ከመልካም ምኞት ጋር ታድሏል።

በቅዱስ ያሬድ ለዕለቱ የተዘጋጀው "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ..." የሚለው ቃለ እግዚአብሔርም ለዕለቱ በተመደቡት በመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሊቃውንት ደርሷል።

መራሒ ሚድያ 👇 
👉 የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com /profile.php?id=100069444095761

👉 የቴሌግራም አድራሻ: @SaintGebrielSundaySchool

👉 የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared
2024/05/20 00:08:24
Back to Top
HTML Embed Code: