Telegram Web Link
🖥 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት አስባችኀል?

📍እንግዲያውስ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ከመግዛቶ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ 10 ነገሮች!

1. ካገለገለ ኮምፒውተር ይልቅ አዲስ ኮምፒውተር ይምረጡ....

2. PCI Express x16 slot ያለው ማዘረቦርድ መሆን አለበት ይህም ሌሎች ካርዶችን ለመጨመር ይረዳዎታል::
- ለምሳሌ ቲቪ ካርድ፣ ግራፊክስ ካርድና ሌሎች....

3. ሚሞሪው ቢያንስ 4GB RAM መሆን አለበት ይህም ኮምፒውተሮ እንዳይጨናነቅና ፈጣን እንዲሆን
ያደርገዋል.....

4. ፕሮሰሰሩ Quad-core processor ያለውን ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ፈጣንና ብዙ ፕሮግራሞችን ባንዴ
የማስተናገድ አቅም እንዲኖረው ያረጋል...

5. ኮምፒውተሮን ለቤት ከሆነ የፈለጉት ፉኑ የማይጮህና የማይረብሽ ይምረጡ::

6. An All-in-one PC ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ ኮምፒውተር ይምረጡ (ሞኒተሩ ፍላት ስክሪን፣እና
ሌሎችንም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች ያሟላ)

7. A Single, High Powered Graphics card ያለው
ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅሞታል

8. የሃርድ ዲስኩ ሳይዝ 500GB እና ከዛ በላይ ቢሆን ይመረጣል ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ብዙ ፋይሎችን እንዲያስቀምጡ ይረዳዎታል...

9. ሃይል ቆጣቢና አነስተኛ ወጪ የሚያወጣ ይምረጡ...

10. ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው External Hard Drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ (መጠባበቂያ)
ለማረግ ይረዳዎታል

@simetube @simetube
@simetube @simetube
✳️ ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ በ WiFi ፍጥነት ለተቸገራችሁ ጥቂት ነገር ልበላችሁ።

🔻የ WiFi ፍጥነት ችግር ባሁኑ ጊዜ ሁላችንም የመረረን ነገር ነው። ይህንንም ችግር በቀላሉ ለመፍታት...

1⃣. VPN መጠቀም

🔻VPN በ ኢንተርኔት ፍጥነት ላይ በጣም አስተዋጽኦ ያደርጋል። አስካሁን ካየሁትም አሪፍ ቪፒኤን Super Vpn Pro በጣም አሪፍ ነው።

2⃣. የ WiFi DNS መቀየር

🔻የ WiFi DNS መቀየር ለ ዋይፋችን ፍጥነት የጎላ ሚና አለው። የ ዋይፋይ DNS ለመቀየር ትንሽ ፕሮሰሱ በዛ ይላል እና ዩቱዩብ ላይ "How to change WiFi DNS" ብላቹ ሰርች በማረግ ማግነት ትችላላቹ።

3⃣.Background ላይ የሚሮጡ አፕችን መቀነስ።

🔻ይህም ማለት ለምሳሌ ቴሌግራም እየተጠቀማቹ ከሆነ Play Store ያለ ፍቃዳቹ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ማገድ ማለት ነው። ይሄንንም ለማረግ አንደ "Net Guard" ባሉ አፕኦች መተግበር ይችላሉ።
✳️ የዓለማችን Top 10 ሀብታሞች 2020

1) Jeff Bezos

🔺የተጣራ ሀብት: $113 Billion
🔺እድሜ: 56
🔺ምንጭ: Amazon
🔺ዜግነት: United States

2) Bill Gates

🔺የተጣራ ሀብት: $98 Billion
🔺እድሜ: 64
🔺ምንጭ: Microsoft
🔺ዜግነት: United States

3) Bernard Arnault

🔺የተጣራ ሀብት : $76 Billion
🔺እድሜ: 71
🔺ምንጭ: LVMH
🔺ዜግነት: France

4) Warren Buffet

🔺የተጣራ ሀብት: $67.5 Billion
🔺እድሜ: 89
🔺ምንጭ: Berkshire Hathaway
🔺ዜግነት: United States

5) Larry Ellison

🔺የተጣራ ሀብት: $59 Billion
🔺እድሜ: 75
🔺ምንጭ: Software (Oracle)
🔺ዜግነት: United States

6) Amancio Ortega

🔺የተጣራ ሀብት: $55.1 Billion
🔺እድሜ: 84
🔺ምንጭ: Zara
🔺ዜግነት: Spain

7) Mark Zuckerberg

🔺የተጣራ ሀብት: $54.7 Billion
🔺እድሜ: 36
🔺ምንጭ: Facebook
🔺ዜግነት: United States

8) Jim Walton

🔺የተጣራ ሀብት: $54.6 Billion
🔺እድሜ: 72
🔺ምንጭ: BWalmart
🔺ዜግነት: United States

9) Alice Walton

🔺የተጣራ ሀብት: $54.4 Billion
🔺እድሜ: 70
🔺ምንጭ: BWalmart
🔺ዜግነት: United States

10) Rob Walton

🔺የተጣራ ሀብት: $54.1 Billion
🔺እድሜ: 75
🔺ምንጭ: BWalmart
🔺ዜግነት: United States

◽️ ከላይ ማየት እኖደሚቻለው በሚገርም ሁኔታ አብዛኞቹ በTech ነክ ነገር ነው ሀብታቸውን ያካበቱት።


#Share
@simetube @simetube
@simetube @simetube
💢ሰላም ውድ የ TimeTech ቤተሰቦች SD ፣ HD ፣ 4K እና 8K ምንድን ናቸው❓
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔆የቴክኖሎጅ ርቀት እና ምጥቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በተለይ ከእይታ (ምስል) ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ደግሞ ለማመን የሚከብዱ ተአምራት እየሆኑ መጥተዋል ።
የምስል ጥራት በፒክስል የሚለካ ሲሆን በ3 ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላል።

#እነሱም፦
➀ SD [standard_definition]-መደበኛ ጥራት
➁ HD [High definition] - ከፍተኛ ጥራት
➂ UHD [Ultra high definition ]- ከመጠን ያለፈ ጥራት ናቸው።

ፒክስል ስንል አንድን ምስል ለመስራት የሚያስችል ትንሿ ነጥብ(ስኩዌር ◾)ማለታችን ነው።
✅የፒክስሎች ስብስብ #ሪዞሉሽን ሊሰኝ ይችላል።

#ለምሳሌ ፦ ከአንድ ምስል ላይ አንድ ስኩየር (ልክ ኬሚስትሪ ላይ atom እንደምንለው) ወስደን ብንመለከት የወርድ ነጥቦች ስብስብ ብዛት × የቁመት ነጥቦች ስብስብ ብዛት ፒክስል ይባላል ማለት ነው ።

🔴720 × 480 pi ሲባል
720=የወርድ(w)ነጥቦች ብዛት እና
480= ቁመት(h) ነጥቦች ብዛት በአንድ ሊከፈል በማይችል ስኩዌር ውስጥ ማለታችን ነው ። ፒክስል በበዛ ቁጥር ጥራት ይጨምራል። በሌላ በኩል የምስሉ MB ም ይጨምራል ።⬆️

📌በየዘመናቱ የመጡ የምስል ጥራት እድገትን ብንመለከት ከመጀመሪያው እስከ አሁን ድረስ የሚከተሉትን ይመስላል።

✅SD= 720 × 480
◾PAL= 768 × 576
◾NTSC= 720 × 534 (የድሮ ሪሲቨሮች)
✅HD= 2K
◾HD = 1280 × 720
◾Full HD =1920 x 1080
✅UHD=
◾4K= 3840 × 2160 (16:9 YouTube size)
◾5K= 5120 × 2700
◾6K = 6144 × 3160
◾8K = 7680 × 4320 አሁን የደረስንበት የመጨረሻው ቴክኖሎጅ።

📌ሀገራችን ላይ በስፋት በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው ሰው ቤት የሚገኘው Full HD እና 4K ሪሲቨር ሲሆን አልፎ አልፎ 8Kም ይኖራል። ነገር ግን እዚ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ቢኖር ባለ 8K ቻናልን ለመመልከት ሪሲቨራችን እንዲሁም ቲቪያችን የግዴታ 8K ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ የቻናሉ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ ለመለየት እንቸገራለን ። ያ ማለት HD ቻናሎችን በAV ኬብል እንደመመልከት ይሆናል ማለት ነው።

📌በዚህ ጊዜ 8K እንኳን ቀርቶ 4K ቲቪ ራሱ የሚገዛ ሰው ኪሳራ ላይ እንደወደቀ ይሰማኛል፤ ምክንያቱም በ4K Quality Broadcast የሚያደርጉ የቲቪ ቻናሎች የሉንም‼️

📌ለ1 8K TV እስከ 300ሺ ብርና ከዛም በላይ ሲወጣ ይታያል‼️

@simetube @simetube
@simetube @simetube
የውድድር ጥሪ ማስታወቂያ
=============
ኢኖቬሽን ለልማት (Innovation for Development) በሚል ፕሮግራም ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሌሎች የልማት አጋር ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል፡፡
በዚህ ፕሮጅክት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያሉ ስታርታፖችንና ጥቃቅንና አነስተነኛ ተቋማትን (CT and ICT related startups and SMEs) በማወዳደር እና በመመምረጥ የማልማት ስራ ሲሆን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ጋር በመሆን የተዘጋጀ ፕሮግራም ነው፡፡
አመልካቾቸ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
• ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው/ያላት
• በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ተዛማጅ ዘርፎች ላይ ሀሳብ ያለው/ያላት
• ኢኖቫቲቭ የቢዝነስ ሀሳብ ያለው/ያላት
• በተጠየቀው የፕሮፐዛል ይዘት መሰረት ሃሳቡን ማቅረብ የሚችል/የምትችል
ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ወር በ www.mint.gov.et መመዝገብና ማመልከት ትችላላችሁ።
ለበለጠ መረጃ ፡ +251 -967 -944 -500 ይደውሉ
ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ!!!
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
https://www.tg-me.com/simetube
የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብን ለማጠናከር በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እስካሁን ለክለቡ ድጋፍ ከ162 ሚሊየን ብር
በላይ ቃል መገባቱን አዘጋጆች አስታውቀዋል።
"ስፖርት ለኢትዮጵያ ሕብረት'' የፋሲል ከነማ ገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እስካሁን ለክለቡ ድጋፍ ከ162 ሚሊየን ብር በላይ ቃል መገባቱን አዘጋጆች አስታውቀዋል።

@Asrat_News
@Asrat_News
ይህንን ሊንክ ይጫኑት&Share
👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

https://www.tg-me.com/learnGeez1
https://www.tg-me.com/learnGeez1

👆 Join ያድርጉና የግእዝ ቋንቋን ይማሩ!!!!

@learnGeezbot
👆👆👆
ለአስተያየት ይጠቀሙ
Forwarded from Job Ethiopian
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ።
#share
👇👇👇👇join here
https://www.tg-me.com/JobCome
የአለማችን ኮኮብ ክርቲያኖ ሮናልዶ በኢንስታግራም 300 ሚሊዮን በላይ ተከታይ በማግኘት የመጀመሪያው ሆነ።

ከሮናልዶ በመቀጠል ከፍተኛ ተከታይ አክተሩ ዘሮክ ሲሆን 246 ሚሊዮን ተከታይ አለው፣ ሌላኛው የአለማችን ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በ219 ሚሊዮን ተከታይ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን 1ሚሊዮን ተከታይ ማግኘቷን ተዋናይት ሃናን ታሪቅ ከሳምንታት በፊት ኬክ ቆርሳ ማብሰሯን ዘግበን ነበረ። ከእሷ በመቀጠል ተዋናይት አዲስአለም ጌታነህ እና የቃና ቴሌቪዥኗ ዳናይት ወደ አንድ ሚሊዮን የተጠጉ ዝነኞች ናቸው።

@simetube @simetube
@simetube @simetube
✅🔸የ Facebook ስማችንን እንዴት ባዶ ማድረግ እንችላለን ??

በመጀመርያ ስም መቀየርያ Setting ትሄዳላቹ
🔻1. (ՙՙ) ቅንፍ ውስጥ ያለውን ምልክት Copy አርጉትና ስም መቀየርያው ላይ First Name እና Last Name ላይ Paste አርጉት።

🔻2. ከዛ Review Name የሚለውን ንኩት

🔻3. ከዛ የፌስቡክ ፓሰዋርዳቹን ፅፋቹ Continue/Confirm የሚለውን ነኩት።

⚠️ይሄ Trick የሚሰራው በፌስቡክ Lite እና App ላይ ነው።
══════❁✿❁ ═══════ 🎮▩♦️. @simetube
🎯▩♦️. @simetube
🚀▩♦️. @simetube

📑አዲሱን ብዙ መረጃዎችን የያዘዉን ቦታችንን ለማግኘት 👇👇
https://www.tg-me.com/simetube
https://www.tg-me.com/simetube

🔶 ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇
@simetube

📣#Mute ያደረገችሁ #Unmute በማድረግ መረጃዎችን ቶል ያግኙ✅
══════❁✿❁════════
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
◈◂▴△ Sime Tech | | ሲም ቲች ▽▴▸◈
🅣🅔🅒🅝🅞🅛🅞🅖🅨
🔆ለቴሌግራም አዲስ ገቢዎች ቴሌግራምን ልናስተዋውቃችሁ ነው አብራችሁን ሁኑ።

1.user_name ቢኖራችሁ ይመረጣል፤ ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ባትፈልጉ ይህን username ቢሰጡት ማንም እናንተን በቀላሉ ማግኘት ይችላል።

⚠️ setting ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

2.የሆነ ሰው እያዋራችሁ ስልክ ቁጥሩን ለማወቅ ከፈለጋችሁ ቀላል ዘዴ ልንገራችሁ። 👇

🤔እናንተ ብቻ ስልክ ቁጥራችሁን ላኩለት ያ ሰው ቁጥራችሁን contact ወይም dialer ውስጥ ካስገባው የእሱ ቁጥር በቀጥታ ለናንተ ይታያችኋል።

⚠️ስልኳን አልሰጥ ላለች ሁላ ቁጥራችሁን ስትልኩ ዋሉ አሏችሁ ደሞ 😜

3.አዲስ Chanel (በፌስቡክኛ page የምንለውን) ወይም group ለመክፈት ከፈለጉ new group ወይም new channel የሚለውን በመጫንና ያላችሁን contact add በማድረግ ማስጀመር ትችላላችሁ።. . 👇👇👇

4.ብዙ አይነት ቴሌግራም አፕ አለ ለምሳሌ telegram, plus, mobogram, supergram, multigram...

እነዚህ 👆 ሁሉም የየራሳቸው feature አላቸው።

5.የሆነ ሰው አካውንት ውስጥ ስትገቡ start secret chat የሚል ይመጣል ከ normal chat ጋር ልዩነቱ ምንድነው?

✔️ከ 1ቀን በኋላ መልእክቱ ከእናንተም, ከተላከለትም ሰው, ከቴሌግራም ሰርቨርም ላይ ይጠፋል። ❌

✔️እናንተ የላካችሁለትን መልእክት ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ(forward) ማድረግ አይችልም።

6. ፌስቡክ ላይ የምትጠቀሙበት chat off (ቻት ላይ እንደሆናችሁ ሌላ ሰው እንዳያውቅ ማድረጊያ) እዚህም አለ።

✅Setting ➡️ privacy and security ➡️ last seen

እዚህ 👆 ውስጥ በመግባት...

✔️ሁሉም ሰው እንዲያያችሁ (everybody)

✔️ስልካችሁ ላይ ስልካቸው የተመዘገበ ሰዎች ብቻ እንዲያያችሁ (only contacts)

✔️እንዲሁም ማንም እንዳያያችሁ (nobody) ማድረግ ትችላላችሁ።. . .

7.በቴሌግራም ማንኛውንም አይነት ዶክመንት መላክ ትችላላችሁ።

⚠️ከታች ያለውን attachment ምልክት በመንካት 👆

8.ቴሌግራም በየደቂቃው backup ስለሚይዝ ስልክዎ 📱 ቢጠፋ፣ ቢበላሽ 😭 መረጃዎ እንዳለ ይቆያል።

9.አሁን ያሉበትን ቦታ ⤴️ ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ።

⚠️ከታች ያለውን attachment በመንካት 👆

10.ቴሌግራም በራሱ ምንም አይነት አሰልቺ ማስታወቂያዎችን ለተጠቃሚዎቹ አይልክም። ❌

⚠️(AD-free)

11.አፑን ለራስዎ እንደሚመችዎ theming ውስጥ በመግባት personalize ማድረግ ይችላሉ።

_________________.

12.ቴሌግራምዎን ከእርስዎ ውጭ ማንም እንዳይከፍተው password 🔑 መስጠት ከፈለጉ 👇

💢Setting ➡️ privacy and security ➡️ passcode lock ➡️ on ያድርጉና password ይስጡት ከዛም ✔️

13.አንዳንድ ሰዎች ያለፍላጎትዎ ግሩፕ/ቻናል ላይ እያስገቡዎት ከተቸገሩ 👇

💢Setting ➡️ privacy and security ➡️ groups/channels ➡️ no one ✔️

14.አፑን ሲከፍቱት ያለእርስዎ ትእዛዛት audio, video, document download እንዳያደርግ 👇

💢 Setting ➡️ data and storage ➡️ auto download media off ❌

15. እርስዎ ባያዙትም 😡 ቴሌግራም ላይ ያዩዋቸውን ፎቶዎች 📸, ቪድዩዎች 🎥... አፑ በራሱ የስልክዎን 📲 storage በመጠቀም ያስቀምጣል፤ ቦታ እንዳይጨናነቅብዎ ለማጥፋት ❌

💢Files ➡️ internal storage ➡️ telegram ...delete

________________
📢: ✅Credit :- @simetube

📌Share And Support Us.📌
📌Sime Tech📌

@simetube @simetube
በስማርት ስልካችን ውስጥ የሚገኙ #Mobile_Hotspot_and_Tethering ጥቅማቸው ምንድነው?
ዩኤስቢ ቴዘሪንግ እና ሆትእስፖት ዛሬ ብዙዎቻችን እስማርት ፎን ስልክ ዉስጥ ስለሚገኝ እና ብዙ ትኩረት ስለማንሰጠዉ ነገር እናወራለን፡፡
'ዩኤስቢ ቴዘሪንግ እና ሆትእስፖት' ሁለቱም በስልኮ ኢንተርኔት -- ኮምፒተሮ እና ሌሎች ስልኮች ፡ ታብሌቶች ኢንተርኔት እንዲጠቀሙ ማድረጊያ መንገዶች ናቸዉ፡ የሚለያቸዉ ነገር ቢኖረ ዩኤስቢ ቴዘሪንጉ በ ኬብል የሚሰራ ሲሆን ሆትእስፖት ግን ዋይርለስ ወይም ገመድ አልባ መልክት ማስተላለፊያ መንገድ ይጠቀማል፡፡

እስቲ በመጀመረያ ስለዩኤስቢ ቴዘሪንግ አጠቃቀሙን ልንገራችሁ ዩኤስቢ ቴዘሪንግ ጥቅሙ ስልካችንን እና ኮምፒዩተራችንን አገኛኝተን በኮምፒዩተራችን ኢንተርኔት የምንጠቀምበት ቀላል መንገድ ነው፡፡ እንደ ዲያላፕ ኮኔክሽን ማለት ነው፡፡
ዲያላፕ ኮኔክሽን ማለት ኮምፒዩተራችንን በቤት ስልክ አገኛኝተን ኢንተርኔት የምንጠቀምበት
መንገድ ነው፡፡ ዩኤስቢ ቴዘሪንግ መጠቀም ሲፈልጉ ይህን መንገድ በስልኮ ላይ ይከተሉ .
--› ዩኤስቢ ቴዘሪንግ
1. ዩኤስቢ ቴዘሪንግ የምንጠቀም ከሆነ መጀመሪያ ስልኮ እና ኮምፒተሮን በኬብል ያገናኙት
2. Setting >> mobile networks >>> wireless and network >>>usb tethering
በመሄድ usb tethering የሚለዉን ይምረጡ

3. የስልኮን ድራይቨር እስኪጭን ኮምፒተሩን ይጠብቁት
4. ከዛም ኮምፒተሮ ላይ የኔትዎረክ ምልክት ይመጣል

5. Enjoy !!!!
--› ሆትእስፖት ሆትእስፖት ይሄ ደግሞ በጣም ተመራጭ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ብዙ ሰው አያውቀውም፡ ይኔን ምንድነው ጥቅሙ ትሉኝ ይሆናል የሆትእስፖት ጥቅም እኔ ሞባይል ውስጥ ብዙ ብር ቢኖር አንተ ጋር ደግሞ ምንም ብር ባይኖር የኔ ሞባይል እንደ ዋይፋይ ሆኖ ያንተን ስልክ ኢንተርኔት ያስጠቅማል ማለት ነው
ይህን ካልኩ እስቲ እስቴፑን ላሳያችሁ

1. Setting >> mobile networks >>> wireless and network >>> HOTSPOT የሚለዉን አክቲቭ ያድርጉት

2. Configure (የሚለዉን በመምረጥ ፓስዎርድ እና ስም ይስጡት )

3.ሆነ ማለት ነዉ፤፤
4. የጓደኞት ስልክ ካርድ ከሌለዉ በእርሶ ዋይፋይ መጠቀም ይችላል ማለት ነዉ ፡፡
ኖኪያ ስልክ ያላችሁ ሰዎች ኖኪያ ፒሲ ሲዉትን ተጠቅማችሁ በኮምፒተሮ ኢንተርኔት መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

@simetube @simetube
⚛ ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ላይ Sleep, Hibernate, Shutdown ልዩነታቸው ምንድን ነው?

ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል።

ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች በዝርዝር እንመለከታለን።

♐️“ስሊፕ”

በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ” የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።

ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።

ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ። በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ ማድረግ ተገቢ ነው።

♐️“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።

♐️“ሀይበርኔት”

ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው። “ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥ ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው። በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው ሀይል ተመሳሳይ ነው።

ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።

✅ መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?

በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።

ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።

ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን” ማድረጉ ተመራጭ ነው።

ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው። ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ። “ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።

@simetube @simetube
ከወደዱት ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ
✅ውድ ወዳጆቻችን ዛሬ እነሆ አሪፍ የተባሉ የ #ቴሌግራም #ቦት ዎች ጋበዝናችሁ!

🔰 @utubebot - #ዩቲዩብ ላይ ያሉ ቪድዮዎች በቴሌግራም ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን #ቦት ተጠቀሙ! ከናንተ ሚጠበቀው ልታወርዱት የፈለጋችሁት #የቪዲዮ ው ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው!
♻️GoTo Official YouTube App -> Search You're Favorite Videos -> Click 3 Dot (፧) -> Share -> CopyLink Or Share To Telegram (utubebot).

🔰 @spotify_to_mp3_bot - በSpotifybot ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሙዚቃዎች ይገኛሉ! የምትወዱትን መርጣችሁ #Download አድርጉ!

🔰@XompressorBot - ማንኛውም Mp3 ፎርማት ሳይዛቸው ለመቀነስ ይጠቅማል!

🔰 @pdfbot - ይህ ቦት የፈለጋቹትን #Pdf_File ለመስራት እና ለማንበብ የሚያስችል ነው!

🔰 @Uloadit_bot - ወደ ቴሌግራም #file #Upload ለማድረግ ይጠቅማል!

🔰 @ScreenShotTGBot - የፈለጋችሁት ማንኛውም አይነት #ቪዲዮ #Screenshots በማድረግ ይልካል! ፊልም ለምታወርዱ ደግሞ ይህ አሪፍ ማረጋገጫ ነው!

🔰 @GmailBot - #Gmail አፕ አያስፈልጋቹህም ይሄ ቦት አለ መልክት መላክ መቀበል የሚያስችል በGmail #Verify የሆነ ቦት ነው!

🔰 @silentcbot - ይህ #ቦት የቴሌግራም #ቻናል ላላቸው እና ከሁለት በላይ አድሚኖችን ለመቆጣጠር ይረዳል! ለምሳሌ አላስፈላጊ #ጹሁፍ #እስቲከር ወይም #ሊንክ እንዳይልኩ ያደርጋል!

🔰 @encoderbot - ይህ #ቦት ደግሞ #Telegram ላይ ልናወርዳቸው የፈለግናቸው #ኦዲዮዎች ብዙ #Mb በሚሆንብን ጊዜ ለመቀነስ ይረዳናል!
⚠️ማሳሰቢያ⚠️ ይህ #ቦት በቀን ውስጥ ከ4 ወይም ከ5 በላይ #Audio #Convert ማድረግ አይችልም!

🔰 @MathCalcBot - የቴሌግራም #Calculator #ቦት ነው ይጠቅማቹሀል!

🔰 @GHAnnunciBot - ቻናል ላላችሁ ጠቃሚ የሆነ #ቦት ነው!

🔰 @NoteOfficialBot - ማስታወሻ ለመያዝ የሚጠቅም ምርጥ #ቦት ነው!

🔰 @virus_total_scan_bot - ፍይሎቻችንን #Scan በማድረግ ከቫይረስ ነፃ መሆናቸውና አለመሆናቸውን የሚነግር አሪፍ #ቦት ነው!

⚠️የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #UnMute🚫 በማድረግ የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ!
👇👇👇#join_us & #share
@simetube @simetube
@simetube @simetube
🌟በስልካችን ቪዲዮዎችን በማቀናበር ፕሮፊሽናል ኤዲተር መሆንእንዴት እንችላለን?
🌟ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም! ዘመን አፈራሽ የሆነው ስልክዎ ከኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮዎችን ለማቀናበር አንዲያደርጉ ያስችሎታል!

🌟 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የሚያገለግሉ 8 አፖች እነሆ!

🌟1ኛ፦ FilmoraGo
በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የAndroid ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው! የመቁረጥ (Trim/Cut) ገጽታዎችን መቀየር፣ሙዚቃን ወዘተ... የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ በዚህ መተግበሪያ ሊያከናወኑ ይችላሉ!

🌟2ኛ፦ VideoShow
ብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ አስደናቂ መተግበሪያ ሲሆን PlayStore ውስጥ ከሚገኙ ነፃ ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው! ለአጠቃቀም ቀላል ነው! ከዋና ዋና ተግባራቶቹ ውስጥ ፊልተሮችን፣ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም በቀጥታ ስርጭት ጊዜ ቪዲዮዎን መቆጣጠር፣ማስዋብ ይችላሉ!

🌟3ኛ፦ PowerDirector
ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ገራሚ የቪዲዮ ኤዲተር ነው! በቸኮሉ ጊዜ አልያም ፈጣን ግዜያዊ (ቋሚ) ቪዲዮዎችን በሰአታት ውስጥ ለመስራት ግሩም የሆነ አማራጭ ነው!

🌟4ኛ፦ KineMaster
ከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነ-ገጽ ጋር በመጣመር #KineMaster ለAndroid ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው! የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ ❝Copy Paste❞ አገልግሎትን መጠቀም ይችላሉ! ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር የKineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ተመራጭ ነው! የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን (ብሎግ) ማስገባት ይችላሉ! ብቻ ይሄ መተግበሪያ የግድ ስልክዎ ላይ ሊኖር ይገባል! የኤዲቲንግ ፍላጎት ካላችሁ!

🌟5ኛ፦ Quik
እጅግ በጣም ገራሚ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ሌላው ብልጥ መንገድ ነው! ፈጣን እና ነፃ ነው። የራሳችሁን ታሪክ በQuik ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ! ሌላው #ለQuik ይተውት! በጣም ጥሩው ነገር ደግሞ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎን ማሳደግ መቻሉ ነው! ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ውስጥ ቪዲዮዎችን #Crop ማድረግ፣ማሳመሪያዎችን፣ጽሑፎችን መጨመር እና ቪዲዮዎችን ከሙዚቃ ጋር ለማመሳሰል ፈጣን የሆነ አማራጭ ነው!
🌟6ኛ፦ VivaVideo
ብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት! መተግበሪያው በቀጥታ በስልክዎ ፕሮፌሽናል የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው! ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ! በውስጡ ዘገምተኛ (#SlowMotion) ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ስሪት እና የተንሸራታች ማሳያ #SlideshowMaker አለው!

🌟7ኛ፦ FuniMate Video Editor
በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል! የዕለት ተዕለት ኑሮዎን በቀጥታ ወደ ፈጠራ ቪዲዮዎች ለመለወጥ እና የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት! አጭር ቪዲዮዎችን #ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ የላቁ አማራጮች አሉት!

🌟8ኛ፦ Magisto
መደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው! ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፎቶግራፎችን ሙዚቃን ጽሑፎችን (የቪዲዮ ውጤቶችን) እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል!

@simetube @simetube
@simetube @simetube
☝☝☝#join_us
አዲስ ተለቀቀ የተባለው window 11 ይሄን ይመስላል።

@simetube @simetube
@simetube @simetube
✳️ስልክዎ #ቀርፋፋ እየሆነ ተቸግረዋል?

1⃣. የስልክዎ📱 Internal Storage ሲሞላ

✅ፋይል ይቀንሱ፤ ትልልቅ ፋይሎችን ወደ Sd Card➡️ #Move ያድርጉ።

2⃣. ስልክዎ📲 ውስጥ #Virus ሲገባ

3⃣. ከራሱ ከስልኩ📲 ሌላ #launcher ሲጠቀሙ

✅የራሱን #Launcher ይጠቀሙ።

4⃣. የያዙት ስልክ #Original ካልሆነ

✅ስልኩ📲 #ኮፒ ከሆነ መንቀራፈፉ ወይም ስታክ ማድረጉ ማይቀር ነው።

5⃣. ተጨማሪ ⬇️⬇️⬇️

✅መጀመሪያ #Setting ውስጥ ትገባላችሁ በመቀጠል *developer option ውስጥ ትገባላችሁ አንዳንድ ስልኮች ላይ developer option በቀጥታ ስለማናገኘው *about phone ውስጥ ገብተን build number የሚለየውን ደጋግመን ስንነካው👆 developer option ይመጣልናል በመቀጠልም *window animation scale, transition animation scale & animation duration scale 3ቱንም #Off እናደርጋቸዋለን።

@simetube @simetube
✳️ማይክሮሶፍት ቀጣዩ ዊንዶውስ ዊንዶውስ 11 ተብሎ ሊጠራ የሚችል ሰኔ 17 ቀን ሊገለጥ ነው ፡፡ የሶፍትዌሩ ግዙፍ ኩባንያ ቀደም ሲል እንደገለጸው ዊንዶውስ 10 በዓለም ላይ በሁሉም ስፍራ የሚገኝ ኦፕሬቲንግ ሲስተም “የመጨረሻው ስሪት” እንደሚሆን ቀደም ሲል ገልፁዐል፡፡ ኩባንያው ሀሳቡን እንደለወጠ የሚጠቁሙ ፍንጮች

◽️የማይክሮሶፍት ዋና ምርት ኦፊሰር ፓኖስ ፓናይ በእነማው ላይ ቁጥር 11 ላይ ፍንጭ የሚሰጥ ፍንጭ በትዊተር ላይ ለጥፎ የነበረ ሲሆን ማይክሮሶፍት አዲስ የዊንዶውስ 11 ጅምር ድምፅን የሚያሾፍ የ 11 ደቂቃ ቪዲዮ በዩቲዩብ ላይ በቅርቡ አሰራጭቷል።

@simetube

🏷 @simetube ||
🏷 @simetube ||

▬▬▬▬▬▬ 📌sʜᴀʀᴇ📌▬▬▬▬▬▬
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/05/15 09:47:20
Back to Top
HTML Embed Code: