Telegram Web Link
#FaydaforEthiopia

ያስተውሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም ባወጣው መመሪያ መሰረት ከታህሳስ 23፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ተደርጎ እየተተገበረ መሆኑ ይታወሳል።

በተመሳሳይ ከሰኔ 24 ፣ 2017 (July 1, 2025) ጀምሮ በተጠቀሱት ክልል ከተሞች ማለትም ፦
- ባሕር ዳር
- ጎንደር
- ሐዋሳ
- ድሬዳዋ
- ደሴ
- ደብረ ብርሃን
- ሀረር
- አርባ ምንጭ
- ኮምቦልቻ
- ሸገር
- ወላይታ ሶዶ
- ጅግጅጋ
- አዳማ
- ሻሸመኔ
- መቐለ
- አክሱም
- ቢሾፍቱ
- ባቱ
- ወራቤ
- ቡታጅራ
- ጅማ
- አምቦ
- አዲግራት
- ሆሳዕና
- ወልቂጤ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #Fayda #FaydaforEthiopia
643😡135👏29😭19🤔13😢13🕊8🙏5😱3
#SafaricomEthiopia

🌐 ቅመም ማይፋይ በአዲስ ዋጋ መጥቷል 🙌

💨 እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰  ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት
168😡30🙏13😢10🥰3
" 2.45 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል " - የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

ከሁለት አመቱ ደም አፋሳሽ ጦርነት ባላገገመው የትግራይ ክልል ውስጥ፣ 2 ሚሊዮን 450 ሺህ ህዝብ አስቸኳይ የነፍስ አድን እርዳታ እንደሚፈልግ ተገለፀ፡፡

የእርዳታ ፈላጊው ብዛት የታወቀው በጥቅምትና ታህሳስ ወራት የ2016/2017 የምርት ዘመን ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት መሆኑን፣ የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሐላፊ ዶ/ር ገብረህይወት ገ/እግዚአብሔር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ የሚመለከታቸው የሀገር ውስጥና አለምአቀፍ የእርዳታ ተቋማት የተሳተፉበት፣ በሁሉም ባለድርሻ አካላት የተገመገመና ሁሉም ተቋማት የተስማሙበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ ፦
- በእርሻ፣
- በትምህርት፣
- በጤና፣
- በመጠጥ ውሀ፣
- በምግብ አቅርቦት፣
- በሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት ያሉትንም ክፍተቶች የዳሰሰ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ከተጠቀሰው 2 ነጥብ 45 ሚሊዮን የእርዳታ ፈላጊ ውስጥ አንድ ሚሊዮኑ በመጠለያ ጣቢያዎች የሚኖር ተፈናቃይ ሲሆን፣ 1 ነጥብ 45 ሚሊዮኑ ደግሞ የዘላቂ ማቋቋሚያ ሳይደረግለት ወደ ፈረሰ ቤቱ የተመለሰ ህዝብ መሆኑን ሐላፊው አመልክተዋል፡፡

የአሜሪካው አለምአቀፍ የተራድኦ ድርጅት/ዩኤስኤይድ የእርዳታ አቅርቦት ከአራት ወራት በፊት በፕረዝደንት ትረምፕ ትእዛዝ በመቋረጡ፣ በትግራይ ያለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አደጋ ላይ ወድቋል ያሉት ዶ/ር ገብረህይወት፣ “ የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ወቅት የጥይት ድምፅ በሌለበት ጦርነት ውስጥ ነው የሚገኘው ” ሲሉም የሰብአዊ ቀውሱን አስከፊነት ገልፀዋል፡፡

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬያቸው አልተመለሱም፣ በስቃይ ውስጥ መኖር ከጀመሩ አምስተኛ አመታቸውን ይዘዋል ያሉት ሐላፊው፣ ወደ ቀዬያቸው ቢመለሱ ኖሮ፣ በመሬታቸው ላይ ሰርተው ራሳቸውን ማስተዳደር በቻሉ ነበር በማለት ገልፀዋል፡፡

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀዬያቸው በመመለስ ዘላቂ መፍትሔ እስኪሰጣቸው ድረስ ግን፣ አለምአቀፉ ማህበረሰብና የረድኤት ድርጅቶች የትግራይን የሰብአዊ እርዳታ ጉዳይ እንደገና ካላዩትና የፍላጎቱን መጠን ዳግም ካልከለሱ፣ እስካሁን በእርዳታ ያቆዩትን ማህበረሰብ ከዚህ በኋላ ለእልቂት መዳረግ ነው የሚሆነው ሲሉም ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡  

ዶ/ር ገብረህይወት ገብረእግዚአብሔር በዝርዝር ምን አሉ ?

" ቀደም ሲል በዩኤስኤይድ ሲሰጥ የነበረው እርዳታ በቂ ባይሆንም፣ የተሻለ የቀለብና የመድሐኒት አቅርቦት ነበር፡፡ በተወሰነ መልኩ የኑሮ ማሻሻያ ስራዎችም ሲከናወኑ ነበር፡፡ አሁን ግን ይህ አርዳታ ቀንሶዋል፡፡

ለምሳሌ የአለም ምግብ ፕሮግራም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ እርዳታ ማቅረብ ሊያቆም እንደሚችል ገልፆዋል፡፡ ለዚህ ያቀረበው ምክንያት ደግሞ በፕረዝደንት ትራምፕ የዩኤስኤይድ እርዳታ ማቋረጥን ተከትሎ የእርዳታ አቅርቦት በመቀነሱ እህል የለኝም የሚል ነው፡፡

የአለም ምግብ ፕሮግራም በ 30 የትግራይ ወረዳዎች በምግብና በጥሬ ገንዘብ እስከ 8 መቶ ሺህ ህዝብ ሲረዳ ነበር፡፡ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ 15 ወረዳዎች፣ የመቐለ 7 ክፍለ ከተሞች፣ በደቡብ ትግራይ 6 ወረዳዎች በዚህ ተቋም ነበር የሚታገዙት፡፡ ይህ የረድኤት ድርጅት ከዚህ ስራ ወጣ ማለት፣ እስከ 8 መቶ ሺህ የሚሆን ህዝብ ለሞት፣ ለችግርና ለበሽታ ይጋለጣል ማለት ነው፡፡ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ እነዚህ 30 ወረዳዎች ምንም አይነት ድጋፍና እገዛ አያገኙም ማለት ነው፡፡

የአለም ምግብ ፕሮግራም 80 በመቶ እርዳታ ከዩኤስኤይድ ነበር የሚገኘው፡፡ ሌላኛው የረድኤት ድርጅትም ሲሰጠው የነበረው እርዳታ በሙሉ በሚባል መልኩ ከዚሁ ከዩኤስኤይድ ነበር የሚያመጣው፡፡ ይህ እርዳታ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በመቋረጡ በትግራይ ትልቅ ችግር አስከትሏል፡፡ የዩኤስኤይድ እርዳታ መቋረጥ የፈጠረው ክፍተት በሌሎች ድርጅቶች የሚሸፈን አይደለም፡፡

ይህ ውሳኔ እንደገና ካልታየና ካልተሻሻለ፣ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር በቀላሉ መቅረፍ የሚቻል አይደለም፡፡ አሁን እየታየ ያለው ሰብአዊ ቀውስ በአብዛኛው የዩኤስኤይድ እርዳታ በመቋረጡ የመጣ ነው፡፡ በአጠቃላይ ያ እርምጃ በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ ስርዓቱን ነው ያናጋው፡፡ በህዝቡ እርዳታ አቅርቦት ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ ግዙፍ ነው፡፡

አሁን ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ ውትወታ የማናደርግና ጠንካራ ጥሪ የማናቀርብ ከሆነ፣ ችግር ላይ የሚወድቅ ህዝብ ነው ያለን፡፡ የትግራይ ህዝብ በረሀብ ሳይረግፍና፣ ለከፋ ማህበራዊ ቀውስ ከመጋለጡ በፊት ልንደርስለት ይገባል፡፡ አለምአቀፉ ማህበረሰብ ይህንን ሊገነዘብና ድጋፉን ሊቀጥልበት ይገባል፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
479😭131🕊34💔17😡14🙏8🤔7👏5😢4
" የህክምና ስርዓቱ እንዲሻሻል የታገለ፣ ዓይንና እውቀት የገለጠ፣ ለጤና ባለሙያው ህይወት መሻሻል የሚለፋው ዶ/ር ዳንኤል መታሰሩ የሚያሳዝንና በመላው ባለሙያ ላይ የተቃጣ እርምጃ ነው " - የህክምና ተማሪዎች

የባሕር ዳር ፈለገ ግዮን ሆስፒታል የማህጸን እና ፅንስ ስፔሻሊቲ የመጨረሻ አመት ተማሪ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ የመብት ጥያቄ በማንሳት ጤና ባለሙያዎች እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ ሳቢያ እንደታሰሩና፣ እንዲፈቱ የህክምና ተማሪዎችና የጤና ባለሙያዎች ጠየቁ።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ህክምና ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " መምህራችንን ፣ ሀኪማችንን፣ በዚህ የመብት ጥያቄ ምክንያት 'አስተባብራችኋል፣ ሕዝብ አሳምጻችኋል፣ መንግስትን በኃይል ለመናድ ከሚሰሩ አካላት ጋር ተመሳጥራችኋል' በሚሉ የበሬ ወለደ ክስ በግፍ የታሰሩ እንቁ የጤና ባለሙያዎች እንዲፈቱ እንጠይቃለን " ብለዋል።

" የህክምና ስርዓቱ እንዲሻሻል የታገለ፣ ዓይንና እውቀት የገለጠ፣ ለጤና ባለሙያው ህይወት መሻሻል የሚለፋው ዶ/ር ዳንኤል መታሰሩ በጣም የሚያሳዝንና በመላው የጤና ባለሙያ ላይ የተቃጣ እርምጃ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" በእውኑ መብትን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ወንጀል ነውን ? የጤና ሥርዓቱ ይሻሻል፣ የጤና ባለሙያዎች የልፋታቸውን ዋጋ ያግኙ ብሎ መጠየቅ ጥፋት ነውን ? " ሲሉም ጠይቀዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ጀምሮ አበርክቶ የተገበሩ፣ ለሥራ አጦች በጋራ ክሊኒክ መክፈት የሚያስችልን መፅሐፍ በማዘጋጀት ግንዛቤ ያስጨበጡ፣ ባለሞያዎች ከህክምና ውጭ ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲጠቀሙ በማሰብ " MAC Ethiopia " የተሰኘ ማህበር ካቋቋሙት አካላት መካከል ዋነኛው እንደነበሩም አብራርተዋል።

" ዶ/ር ዳንኤል በድንገት ጋውን የለበሰ ሃኪም አይደለም። ለመጀመርያ ጊዜ በህክምና ተማሪዎች የተዘጋጀ 'ደቦል' የተባለ የቀዶ ህክምና መፅሐፍ በግንባር ቀደምነት ያዘጋጀ፣ በተከታታይ Edition በማውጣት ያለምንም ክፍያ ሙሉ የኢትዮጵያን ተማሪዎች ያገዘ ድንቅ የሜዲካል ሰው ነው " ብለዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን የሰጡ ጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ " ተይዞ የታሰረው ረቡዕ 7 ሰዓት ተኩል ነው። የተያዘውም በደኅንነቶች ነው። ባለሙያዎች ወደ ሥራ ይመለሱ ተብሎ በተግባባነው መሠረት ወደ ሥራ ተመልሶ ግን (በእርግጥ ሆስፒታል ላይ ሳይሆን) ቤተሰብ ጋር በነበረበት ነው የወሰዱት " ሲሉ ተናግረዋል።

" አርብ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፤ ' ጤና ባለሙያዎችን በማስተባበር፣ አድማ በማስመታት፣ አመጽን በመቀስቀስ ' የሚል ክስ ቀርቦበታል " ብለዋል።

" ይህ እሱን የማይወክል ነበር ዶ/ር ዳንኤል እንደማንኛውም ባለሙያ ጥያቄ ጠይቋል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ320 ሺሕ በላይ እንዳሉ ይታመናል። ከእነዚህ አንዱ ነው " ሲሉ አስረድተዋን።

" ከሱም ውጪ እየታሰሩ ያሉ ባለሙያዎች አሉ። ምንም አላጠፋንም ጠቅላይ ሚኒስትሩም 'ጥያቄያችሁ የዳቦ ጥያቄ ነው፤ በቅደም ተከተል እንመልስላችኋለን' ብለዋል፤ ያንን እየጠበቅን ባለንበት ፊገር ባለሙያዎችን ማሰር ተገቢ አይደለም። በሚቀጥለው ሳምንት የማይፈቱ ከሆነ ባለሙያው አሁንም መብቱን ለመጠየቅ ይገደዳል " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.13K😭286😡54👏29🕊19💔16🙏6🤔5🥰4😱3
መገጭ መቼ ነው የሚጠናቀቀው ?

የመገጭ የመስኖ ግድብ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ።

በጎንደር ዙሪያ እየተገነባ ያለውና ከ16 ዓመታት በላይ የፈጀው የመገጭ የመስኖ ግድብ በቀጣይ በጀት አመት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

በ2001 ፕሮጀክቱ ሲጀመር፥ ለአከባቢው የመስኖ ፕሮጀክት እንዲሁም በጎንደርና አከባቢው በስፋት ለሚስተዋለው የመጠጥ ውኃ ችግር መፍትሔ ይሆናል ተብሎ እምነት ተጥሎበት ነበር።

ሥራው ሲጀመር ፕሮጀክቱ በ2.4 ቢሊዮን በጀት ቢሆንም በተባለው በጀትና ጊዜ መጠናቀቅ ባለመቻሉ የበርካቶች የዓመታት ጥናቄ ሆኖ ቆይቷል።

ፕሮጀክቱ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ከዚህ ቀደም ሥራ ላይ የነበረውን ተቋራጭ ውል በመሰረዝ ' ባይካ ' ከተባለ አዲስ ተቋራጭ ጋር በ14 ቢሊዮን ብር ካፒታል ውል ተገብቷል።

በዚህ ተቋራጭ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጌታቸው አረጋ፥ የመገጭ የመስኖ የግድብ ፕሮጀክት የስትራክቸር ሥራ በዚህ ዓመት ነሐሴ ወር ላይ እንደሚጠናቀቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ሥራ አስኪያጁ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የመገጭ ግድብ 185 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ የይዛል፤ ግድቡ ሲጠናቀቅ እስከ 5 ኪ.ሜ ወደ ኋላ ውኃ የሚተኛ ይሆናል።

የውኃ መቆጣጠሪያው (Intake Tower) አጠቃላይ 64 ሜትር (16 ፎቅ ርዝመት) ሲኖረው ከዚህ ውስጥ አሁን ላይ ቀሪ 14 ሜትር ግንባታ ይቀራል።

እንደዚህ አይነቱ ግንባታ በኢትዮጵያውያን ተቋራጭ ሲሰራ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፤ አብዛኛው ጊዜ ለቻይኖች ነበር የሚሰጠው።

ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ውኃ ቢመጣ በግድቡ ሳይሆን ማስተንፈሻ (Spillway) አለው። አጠቃላይ የስትራክቸር ሥራው በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል።

ፕሮጀክቱ አሁን ላይ 73.5 ከመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ ለሙሉ ትኩረታችንን ግድቡ ላይ አድርገን እንሰራለን።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ17 ሺ አስከ 20ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም ሲኖረው ከአጠቃላይ የውኃ መጠኑ ደግሞ 32 ሜትር ኪዩቢክ የሚሆነው ለጎንደርና አከባቢው ንጹሕ መጠጥ ውኃ ለማቅረብ ግብዓት የሚውል ነው " ብለዋል።

የፕሮጀክቱ አማካሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተጠሪ መሐንዲስ የሆኑት ወርቅነህ አሰፋ በበኩላቸው ፕሮጀክቱን በመጪው ዓመት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑን ገልጸውልናል።

ተጠሪ መሐንዲሱ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ይህ ፕሮጀክት ቀድሞ ከነበረው ተቋራጭ ስንረከብ 60.3 በመቶ ሥራው ተጠናቆ ነበር። ይሄ አሰሪው በሚያውቀው ነው። ወደኋላ ተመልሶ የተሰሩ ሥራዎች አሉ ይህ ወደፊት ይስተካከላል።

ዲዛይኑ አጠቃላይ 50 የደለል ዓመት አለው። ከዚህም በላይ ከዚህም በታች የአገልግሎት እድሜ እንዲኖረው የሚያስችለው የተፋሰሱ አከባቢዎች ላይ የሚሰሩ የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራዎች ናቸው። እኛ ሥጋታችን እሱ ነው በዚህ ዙሪያ ሰፊ የአከባቢ ጥበቃ ሥራ ይጠይቃል።

ለመጠጥ ውኃው 1.5 ኪሜ ከግድቡ እስከ ማጣሪያው እናወጣለን። የውኃ ማጣሪያው እና የስርጭት መስመሩ ሌላ ፕሮጀክት ነው" ብለዋል።

በተደጋጋሚ ለሚጠየቀው የጎንደር የመጠጥ ውኃ ችግር መፍትሄ ምን እየተሰራ ነው ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ደብሬ የኋላን አነጋግሯል።

ም/ከንቲባዋ ምን አሉ ?

" የጎንደር የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግር የቆየ ችግር ነው። ይህንን ለመፍታት ልዩ ልዩ አማራጮችን አቅርበናል አንዱ የመገጭ የውኃ ፕሮጀከት ነው።

አማራጮቹ በፌደራል መንግስት ሥር ያሉ አማራጮች ናቸው። አብሮ ከግድቡ ጋር እንዲመረቅ ካስፈለገ አብሮ በትይዩ መቀጠል አለበት።

ልዩ ልዩ የዲዛይን ሥራዎች አልቀዋል። አሁን ይጀመራል ብለን እናምናለን፤ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውሳኔ ነው የሚጠበቀው " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.05K😭88🙏41🤔37🕊29😡15👏10🥰8💔8😢3
" ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ከ400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ500 በላይ ደግሞ ቆስለዋል " - ኮሬ ዞን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ሰሞኑን የታጠቁ አካላት አደረሱት በተባለ ጥቃት ሁለት ንጹሐን መገደላቸውን ፤ ባለፉት ዓመታትም ከ 400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ተናግሯል።

በዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን የኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ አማረ አክሊሉ በሰጡን ቃል፣ " ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሁለት ሰዎች ህይወት በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ በጸረ ሰላም ኃይሎች ምክንያት አልፏል " ብለዋል።

በወረዳው ዳኖ ቀበሌ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ/ም አቶ ዮናስ ዱንአ፤ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም አቶ ፊቴ ፊጋ የተባሉ አርሶ አደሮች በግብርና ሥራ ላይ እያሉ በታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶባቸው ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ሰሞንኛውን ጥቃት የፈጸሙት፣ " የምዕራብ ጉጂ ዞን የጋላና ታጣቂዎች ናቸው። ማሳ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን ነው የሚያጠፉት። ፍላጎታቸው መሬቱን ማስለቀቅ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አካባቢው ዘራፊ ቡድኖች የሚፈነጩበት ነው፤ አደብ የሚያስገዛ መንግስት አልተገኘም። ችግሮቹ የሚባባሱት በስርቆት ምክንያት ነው " ያሉት አቶ አክሊሉ፣ " ዳኖ ቀበሌ በአንድ ቀን ብቻ ከ70 በላይ ከብቶች ተነድተዋል/ተወስደዋል የዛሬ ሁለት ወራት ገደማ " በማለት አስታውሰዋል።

በጥቃቱ እስካሁን በአጠቃላይ ስንት ሰዎች ተገድለዋል ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ሁለት ሰዎች እንደተገደሉ ገልጸው፣ " ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ከ400 በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ ከ500 በላይ ቆስለዋል " ሲሉ መልሰዋል።

ከግድያው ባሻገር፣ " ከ700 ሚሊዮን በላይ ንብረት ነው የወደመው። መንግስት ችግሩን አልፈታም። ሁለት ችግሮች አሉ፤ እነርሱም የወሰን ጥያቄና ጫካ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ናቸው " ብለዋል።

ግድያውና ውድመቱ የተፈጸመው ከነሐሴ 16 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ እስከትላንት ድረስ መሆኑን አስረድተው፣ " ከነሐሴ 16 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ጊዜያቶች እርቀ ሰላምም ተደርጓል፤ ግን እርቀ ሰላሞቹ ውጤታማ አልሆኑም። በተለያዩ አካባቢዎችም ስብሰባዎች ይካሄዳሉ የተወሰነ ሰላምም ያመጣሉ ግን ዘላቂ አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል።

" ፎሌ " የሚባሉ መደበኛ ያልሆኑ ሚሊሻዎች በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱና ጎርካ ወረዳ ላይ "የወሰን ይገባኛል" ጥያቄም። እንዳላቸው፣ "የሸኔ" ታጣቂዎችም በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ፣ ጉዳዩን አስመልክቶ በተደጋጋሚ እርቅ ቢፈጸምም መፍትሄ ስለማይቀመጥለት ጥቃቱ ለአመታት እያገረሸ እንደቀጠለ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
513😢113😭70🕊23😡16🙏7😱4💔4🥰3👏3🤔3
" አባት ተገድሏል ፤ እናት ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባታል " - ነዋሪዎች

አንድ የኤርትራ ወታደር ሁለት ሲቪሎች ላይ ተኩሶ አንድ ሰው ሲገድል ፤ ሌላ ሰው ማቁሰሉን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

የግድያና የማቁሰል ደርጊቱ የተፈጸመው በድንበር ከተማዋ ዛላኣንበሳ ሲሆን በአከባቢው የሚገኘውን ህዝብ ክፉኛ አሰቆጥተዋል።

ከትላንት በስቲያ አርብ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም በኤርትራ ወታደር በሲቪል የዛላንበሳ ነዋሪ ባልና ሚስት የተፈፀመውን ግፍ የሚመለከት መረጃ ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈቀዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ አጋርተውታል።

እንደ ነዋሪዎቹ ቃል ፥ በከተማዋ ሲቪል ለብሰው የአልኮል መጠጥ ሲቀማምሱ የዋሉ ሁለት የኤርትራ ወታደሮች ከሰዓት በኋላ ወደ መኖሪያ ካምፓቸው እያመሩ ሳለ ሁለት ህፃናት በቤታቸው አጠገብ ሲጫወቱ ያገኛሉ።

አንደኛው ወታደር ሰክሮ ስለነበር ህፃናቱን ከመስደብ አልፎ  ይመታቸዋል።

ይህንን ተግባር በቅርብ ርቀት ሲመለከት የነበረው የህፃናቱ ወላጅ አባት ቀረብ ብሎ " ለምን መታሃቸው ? " ብሎ ጠይቆ ሳይጨርስ የሰከረው ወታደር የታጠቀው ሽጉጥ አውጥቶ ይተኩስበታል። አባትም ይወድቃል።

ተግባሩ ያስደነገጣት እናት እየጮኸች ባልዋ ወደ ወደቀበት ስትጠጋ ወታደሩ እሷም ላይ እንደተኮሰባት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

አባት ትዳሩንና ልጆቹ ትቶ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ተቀጥፏል።

እናት በተተኮሰው ጥይት ቀላል ጉዳት ደርሶባታል።

" ሌላኛው አብሮ የነበረው ወታደር ጉዳዩን ወታደር ከአረመኔያዊ ተግባሩ ባያስጥለው ኖሮ የጉዳቱ መጠን ካጋጠመው በላይ ይሆን ነበር " ሲሉ በቅርብ ርቀት ክስተቱን ያዩ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😭804589😡167🕊56💔33🙏16😢14🥰7🤔6😱6👏5
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍትህ እንዲረጋገጥ እሻለሁ " - ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ ትላንት አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የተገደለበት 4ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 3ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በኦሮሞ አርት ውስጥ በዓመቱ ጉልህ አሻራን ያኖሩ እና በተለያዩ ጊዜያት በአርቱ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦች እውቅና አግኝተዋል፡፡ በዚሁ መድረክ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት እና…
ፎቶ ፦ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 5ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 4ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በኦሮሞ አርት ውስጥ በዓመቱ ጉልህ አሻራን ያኖሩ እና በተለያዩ ጊዜያት በአርቱ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦች በመርሃግብሩ እውቅና አግኝተዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ፎቶ ክሬዲት ፦ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን እና ኦኤምኤን

@tikvahethiopia
750😡282😭69😢65🤔53🕊20🙏15👏13🥰8😱3
2025/07/13 21:00:10
Back to Top
HTML Embed Code: