TIKVAH-ETHIOPIA
" አንድ መኪና አስቁመው 1 ሺሕ፣ 2 ሺሕ ብር የሚቀበሉ የወረዳ ታጣቂዎች አሉ። ከፍተኛ የገንዘብ ጥቅም ስላለ ቁሞ ካበቃ በኋላ ኬላው ተነስቶ ድንገት የሚፈትሹ አሉ " - ማኀበሩ ሕገ ወጥ በመሆናቸው እንዲነሱ ተደርገው የነበሩ ኬላዎች ተመልሰው በመዘርጋታቸው አሽከርካሪዎች በአንድ ኬላ ብቻ 2,000 ብር እየተጠየቁ በመሆኑ መማራቸውን አሽከርካሪዎቹና የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ…
" ኬላዎች ናቸው ሕገ ወጥ እንጂ ኬላዎችን ዘርግተው የሚሰበስቡ ግን የመንግስት ተቋማት ናቸው " - ጉምሩክ ኮሚሽን
ሹፌሮች በየአካባቢው ባሉ ሕገ ወጥ ኬላዎች ገንዘብ እየተጠየቁ መማረራቸውን፣ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበርም ድርጊቱ በክልሎችና ወረዳዎች እንደሚፈጸምና ጉዳዩን በቅጡ መቆጣጠር እንዳተቻለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ጭምር ገልጸዋል።
ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ፣ የ11 ወራት ሪፓርቱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት የጉዳዩን አሳሳቢነትና በጥናት ጭምር መዳሰሱን ተናግሯል።
ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘወው ጫኔ፣ "ሕገ ወጥ ኬላዎች ከሀገር በሚወጡና በሀገር በሚገቡ እቃዎች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በንግድ ስርዓቱ፣ በሎጂስቲክ፣ ከዋጋ ንረትም ጋር ጉልህ ሚና የሚጫወቱ አሉታዊ ተፅዕኖ አላቸው" ሲሉ ተደምጠዋል።
አክለው፣ "በጥናት የተረጋገጠ ስለሆነ ነው በዚህ ደረጀ የምናነሳው። ይሄ የክልልና ከተማ አስተዳደሮችን የሚመለከት ነው" ብለው፣ በሚያዚያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ትራንስፓርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሆነው ስለድርጊቱ በክልሎች ጥናት እንዳደረጉ ተናግረዋል።
ድርጊቱ እንዴት እንደሚፈጸም፣ ምን ያክል ሕገወጥ ኬላዎች እንዳሉ፣ የኬላዎቹ ስያሜ ጭምር በተመለከተ ጥናት መደረጉን፣ ከዚህ በፊት ኬላዎች እንዲነሱ አቅጣጫ እንደተሰጠ ገልጸው፣ "የተነሱ አሉ፤ አዲስ የተጨመሩም አሉ" ብለዋል።
ጥናቱ እስከተጠናበት ጊዜ 237 ሕገወጥ ኬላዎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ "በሕግ የቀመጠው ኬላን ማቋቋም የጉምሩክ ስልጣን ነው፤ ክልሎች ግን በተለያየ ምክንያት እነዚህን ኬላዎች አቋቁመው ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው" ሲሉም ተደምጠዋል።
"ኬላዎች ናቸው ሕገወጥ እንጂ ኬላዎችን ዘርግተው ግብር የሚሰበስቡት ግን የመንግስት ተቋማት ናቸው" ያሉት አቶ አዘዘው ፣ ይህም "በክልል ፓሊስ፣ በሚሊሻ መዋቅሮች፣ በአንዳንድ ቦታ በመንግስት የተቋቋሙ የሥራ እድል ፈጠራ፣ የወረዳ ግብረ ኃይል በሚል ጨምር" እንደሚፈጸም ተናግረዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ ኮሚሽኑ ብቻ ሳይሆን በመንግስት ደረጃ መፈጸም እንዳለበት፣ በጉዳዩ ዙሪያ የተጠናው ጥናት ለመንግስት እንደቀረበ ጠቅሰው፣ "በ2018 ዓ/ም ችግሩ ይቀረፋል የሚል እምነት አለን" ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopuiaFamilyAA
@tikvahethiopia

በመዲናዋ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይፋ ሆነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል።
የፈተናው ውጤትም ይፋ ተደርጓል።
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።
በ2017 ዓ.ም 79,034 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ተገልጿል።
Photo : AAEB

በመዲናዋ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይፋ ሆነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል። የፈተናው ውጤትም ይፋ ተደርጓል። በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።…
" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa6.ministry.et/#/result
ወይም በ @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ " - ትምህርት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 79,034 ተማሪዎች መካከል 75,085 ተማሪዎች ማለትም 95 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከ1 እስከ 4 የሚሆኑት ከመንግስት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው አመልክተዋል።
" በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል ያለዉን የውጤት ልዩነት እጅግ እየተቀራረበ መጥቷል " ሲሉ ገልጸዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል።
LINK ፦ https://aa6.ministry.et/#/result
Telegram Bot : @MinistryResultQMTBOT

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ከሲስተማችን ጋር በተያያዘ መጠነኛ ችግር፣ የሲስተም መዘግየት በወረዳ ጽ/ቤቶቻችን ላይ እየገጠመን ይገኛል " - CRRSA
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ከሲስተም ጋር በተያያዘ መጠነኛ ችግር፣ የሲስተም መዘግየት በወረዳ ጽ/ቤቶች እንደገጠመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
አገልግሎቱ የገጠመው ችግር ፦
- ቀድሞ የዲጂታል ምዝገባ ያደረጉ፣
- እድሚያቸው ከ12 በታች የሆኑ ህፃናትን፣
- በውክልና የሚስተናገዱ ተገልጋዮችን የማያካትት መሆኑን ገልጾ፣ ነዋሪዎች ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ የሲስተም መቅራረጡ ያጋጠማችሁ 119ኙ ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን ህዝብ የሚበዛባቸው በማንዋል አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩ ብዙ የዲጂታል ተመዝጋቢ ባለባቸው ክፍለ ከተሞች መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ከዚህ በፊት ዲጂታል ያልነበረባቸውና ባለፈው ሰኔ የጀመርንባቸው የካ፣ ንፋስ ስልክ እና አቃቂ ክፍለ ከተሞች በጣም መጨናነቅ ያለባቸው ቦታዎች ናቸው" ያሉን አቶ ዮናስ፣ "በሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ግን ሰላም ነው፤ ቀድመው ኢንሮል ስላደረጉ ነዋሪዎቹ ሰርቪስ ሲጠይቁ ጀነሬት ይደረጋል እንጂ እንደ አዲስ አሻራ፣ ፎቶ አንቀበልም " ሲሉ ተናግረዋል።
" አንዴ ዲጂታል የተመዘገበ ሰው ብዙም ችግር የለበትም፤ ያገኛል። ሲስተሙ ውስጥ ያልገባ የአዲስ ሰው ምዝገባ ላይ ነው ጫና የፈጠረብን። ነገ እስከ ከሰዓት እንፈታዋለን። ይህን ለማካካስም እሁድም ሥራ እንገባለን" ብለዋል።
" ከማንዋል ወደ ሲስተም እየገቡ ያሉ ሰዎች አገልግሎት ነው እየተዘገየ ያለው " ሲሉም አስረድተዋል።
ኤጀንሲው፣ ችግሩን ለመፍታት እየሰራን መሆኑን ጠቁሞ፤ " ለገጠመው የአገልግሎት መስተጓጎል ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን " ሲል ከወዲሁ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" በተፈጠረው እሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፤ አንዱ ሆስፒታል ገብቷል " - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ
በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተፈጠረ በተባለ የፍንዳታ አደጋ በሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ በሰጡን ቃል፣ "ትላንት ሁለት ሰዓት አካባቢ በተፈጠረው እሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፤ አንዱ ሆስፒታል ገብቷል" ብለዋል።
የችግሩን መንስኤ ሲያስረዱም አቶ ሀሚድ፣ "የችግሩ መንስኤ ማሽኑ ላይ በተነሳው እሳት ምክንያት ነው፤ ማሽኑ ላይ እሳት/ ቃጠሎ ተነስቶ በዚያ የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው የተጎዱት" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋው መድረሱን ትላንት በሰሙበት ወቅት ሦስት ሰዎች ተጎድተው እንደነበር፣ አንዱ ሆስፒታል እንደገባ፣ ሁለቱ እንደሞቱ ነው የገለጹት።
የሀዋሳ ከተማ ጸጥታ መምሪያ በበኩሉ፣ ችግሩ ተፈጥሯል መባሉ ትክክል መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጾ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፓሊስ እንዲጠየቅ ጠቁሟል።

Photo
" በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሶስቱም ከተሞች ያቋረጥናቸውን በረራዎች በድጋሚ አስጀምረናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
በዛሬው ምሽት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፖርቶ ወደ ተሰኘች የፖርቹጋል ከተማ አዲስ በረራ ይጀምራል።
አየር መንገዱ የፖርቹጋል ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ወደ ሆነችው ፖርቶ የሚያደርገው በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፓ ያሉትን የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 22 እንደሚያደርሰው ይፋ በማድረጊያ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አውሮፓ ከሚያደርጋቸው ጉዞዎች በሀገር ደረጃ ፖርቹጋል 17 ተኛዋ ሃገር ስትሆን ይህ በረራ ወደ ፖርቹጋል የተደረገ የመጀመሪያው በረራ መሆኑን ተነግሯል።
የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው " የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው አንድ ወር ጊዜ ወደ ወደ ዱባይ እና ቬትናም ተጨማሪ ሁለት መዳረሻዎችን ይፋ የሚያደርግ ይሆናል " ብለዋል።
በእስራኤል እና በኢራን መካከል ተቀስቅሶ የቆየውን ግጭት ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ቀጠናው የሚያደርገው ጉዞ ማቋረጡ ይታወሳል።
ተቋርጠው የቆዩት በረራዎች በድጋሚ መጀመራቸውን አቶ መስፍን ጣሰው አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ በዝርዝር ምን አሉ ?
" መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ አካባቢ ያሉ ሃገሮች ላይ ግጭት መኖሩን ተከትሎ የተወሰኑ ከተሞች በረራ አቋርጠን ነበር።
እስራኤል ውስጥ ወደ ቴልአቪቭ፣ ሊባኖስ ውስጥ ወደ ቤሩት እንዲሁም ዮርዳኖስ ውስጥ ወደ ኦማን ከተሞች ስናደርግ የነበረውን በረራዎች በጊዜያዊነት አቋርጠን ቆይተናል።
በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሶስቱም ከተሞች ያቋረጥናቸውን በረራዎች በድጋሚ አስጀምረናል።
ተቋርጦ በቆየበት ወቅት መንገደኞች ወደዛ አካባቢ መጓጓዝ ያቆማሉ ስለዚህ መጠነኛ የተጓዦች መቀነስ ይታያል በረራ ላይ ሲታይ ግን ትልቅ ለውጥ የነበረው አይደለም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

#HoPR🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል።
በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያፀድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጉባኤው ከጥዋት 2:30 ጀምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ይሰራጫል።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትናንት የተሰጠውን የእንግሊዘኛ ትምህርት ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች ሌሎች ትምህርት ፈተናዎችን ከወሰዱ በኋላ ይፈተናሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት በተሰጠው የመጀመሪያ ቀን ፈተናዎች ላይ የተወሰነ የኃይል እና የሲስተም መቆራረጥ አጋጥሞ እንደነበር የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። " ከሚመለከታቸው…
#NationalExam🇪🇹
ከሰኔ 23 እስከ 25/2017 ዓ/ም በበይነ መረብና በወረቀት ሲሰጥ የነበረው የአንደኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
ፈተናውን በወረቀት 231,761 በበይነ መረብ 43,367 በድምሩ 275,128 ተፈታኞች ወስደዋል፡፡
የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ፈተናውን በበይነ መረብ ሲወስዱ በተወሰኑ የፈተና ማዕከላት ላይ በተለያየ ምክንያት የእንግሊዘኛ ፈተና ያልወሰዱ ተፈታኞች አብዛኞቹ ነገ ሐሙስ ጥዋት ከሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ያልወሰዱት ፈተና የሚሰጣቸው እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በሁለተኛ ዙር ለመውሰድ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሶስተኛውና ከአራተኛው ዙር ተፈታኞች ጋር እንደሚወስዱ አመልክቷል።
" ፈተናውን በተለያዩ ዙሮች መስጠት መቻላችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተመደቡበት ዙር መፈተን ያልቻሉ ተፈታኞች በሌሎቹ ዙሮች ከሚፈተኑ ተፈታኞች ጋር መፈተን እንዲችሉ ዕድል ፈጥሯል " ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።
#EAES
@tikvahethiopia
ከሰኔ 23 እስከ 25/2017 ዓ/ም በበይነ መረብና በወረቀት ሲሰጥ የነበረው የአንደኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
ፈተናውን በወረቀት 231,761 በበይነ መረብ 43,367 በድምሩ 275,128 ተፈታኞች ወስደዋል፡፡
የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ፈተናውን በበይነ መረብ ሲወስዱ በተወሰኑ የፈተና ማዕከላት ላይ በተለያየ ምክንያት የእንግሊዘኛ ፈተና ያልወሰዱ ተፈታኞች አብዛኞቹ ነገ ሐሙስ ጥዋት ከሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ያልወሰዱት ፈተና የሚሰጣቸው እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በሁለተኛ ዙር ለመውሰድ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሶስተኛውና ከአራተኛው ዙር ተፈታኞች ጋር እንደሚወስዱ አመልክቷል።
" ፈተናውን በተለያዩ ዙሮች መስጠት መቻላችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተመደቡበት ዙር መፈተን ያልቻሉ ተፈታኞች በሌሎቹ ዙሮች ከሚፈተኑ ተፈታኞች ጋር መፈተን እንዲችሉ ዕድል ፈጥሯል " ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።
#EAES
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተፈጠረው እሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፤ አንዱ ሆስፒታል ገብቷል " - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተፈጠረ በተባለ የፍንዳታ አደጋ በሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ በሰጡን ቃል፣ "ትላንት ሁለት ሰዓት አካባቢ በተፈጠረው እሳት አደጋ…
" የውሃ ማሞቂያ ፈንድቶ ነው የሁለት ሰዎች ሕይወት ያልፈው " - የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ
➡️ " በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከአደጋው ጋር ተያይዞ የሚዘዋወሩት መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው !! "
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አሸናፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ትናንት ጠዋት በፓርኩ ሼድ 40 የውሃ ማሞቂያ (ቦይሌር) ባለሙያ ሰራተኞች መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ባሉበት ፈንድቶ የ62 እና 45 ዕድሜ ውስጥ ያሉ ሁለት ባለሙያዎች ሕይወታቸዉ ማለፉንና በሁሉት ሰራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ሁለቱም ባለሙያዎች ወንዶች ሲሆኑ ለረጅም ዓመታት በዘርፉ የሰሩና ልምድ ያላቸዉ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ማቴዎስ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል።
የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ እንዲያጣራ መርማሪ ቡድን መዋቀሩን የገለፁት የፓርኩ ስራ አስኪያጅ ከአደጋው ጋር ተያይዞ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች " ክስተቱ የእሳት አደጋ እንደሆነና መንስኤዉም ባለሙያዎች የልምድ ማነስ " ተደርጎ የሚሰራጩ መረጃዎች ፍፁም የተሳሳቱና ባለሙያዎችም የረጅም ዓመታት ማለትም ከ6 ዓመታት በላይ በዘርፉ ልምድ ያላቸው ስለመሆናቸው ተነግረዋል።
በዚህ ልክ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርስ የእሳት አደጋ ከዚህ ቀደም በፓርኩ ዉስጥ ተከስቶ እንደማያዉቅም አቶ ማቴዎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa