Telegram Web Link
ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤት አንገባም ያሉ ነዋሪዎች !

" መንግስት መጥቶ ጥያቄያችንን ካለመለሰልን ወደ ቤት ላለመመለስ ወስነን ሜዳ ላይ ተሰብስበናል " - ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

" ሰሚ እስክናገኝ ወደ ቤታችን አንመለስም ! "


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ አከባቢ ነዋሪዎች " በአዲስ የመዋቅር ጥናት እና ልማታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወረዳዉ መንግስት እንዲያነጋግን ብንጠይቅም ተገቢዉን ምላሽ ባለማግኘታችን በአደባባይ ወጥተን ድምፃችንን ለማሰማት ተሰብስበናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የአከባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሀዋሳ ከተማ አዲስ የመዋቅር አደረጃጀት ጋር በተያያዘ የተናገሯቸው መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ሕዝቡ የወረዳው መንግስት ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ነገር ግን የሚያናግር አካል ባለመምጣቱ 18 የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ባለሃብቶችን ያካተተ የሕብረተሰቡ ተወካዮች ተሰይመዉ በየደረጃው የመንግስት አካላትን እንዲያነጋግሩ ቢላኩም ተገቢው ምላሽ ስላልተሰጣቸው ሕዝቡ ሜዳ ላይ ተሰብስቦ መዋሉን አስረድተዋል።

የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄ " ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ዶሬ ባፋኖ አከባቢ ያሉ አምስት ቀበሌያት በአዲስ መልክ ይዋቀራል በተባለዉ የሀዋሳ አንድ ክፍለ ከተማ ስር ተካተዋል " መባሉ ነዉ ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ " ይህ የወረዳዉን አቅም ያዳክመዋል የሚል ቅሬታ ሕዝቡ ዘንድ ፈጥሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዛሬዉ ዕለትም ' የሚያናግራችሁ የመንግስት አመራር ይመጣል ' ተብለን ቀኑን ሙሉ ብንጠበቅም እንደተባለው ባለመምጣቱ ሕዝቡ በነቅስ ወደ ወረዳ አስተዳዳሪዉ ቢሮ ሄዷል ' አመራሩ ተነጋግሮ ያነጋግራችኋል ' ተብለን ምላሽ ባለመምጣቱ ሕዝቡ ' የሚያነጋግረን የመንግስት አካል እስኪመጣ ወደ ቤታችን አንመለስም ' በማለት ምሽቱንም በአንድ ቦታ ላይ ተሰባስቦ ይገኛል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ባደረገዉ ሙከራ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊን በስልክ አግኝቷቸው ነበር። ግን " የወረዳ አስተዳዳሪ አነጋግሩ " በማለታቸዉ ወደ አስተዳዳሪዉ የእጅ ስልክ ደጋግመን ብንደዉልም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ምላሻቸው ሳይካተት ቀርቷል።

ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.06K👏124😭51😱43🕊30😢24🤔20🙏12🥰11😡10💔2
#SouthEthiopia

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የማሽንጋ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የወላይታ ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ወደ ገበያ እየሄዱ የነበሩ አራት አርሶአደሮችን የዉሃ ሙላቱ ወስዷቸዉ እንደነበር የገለፁት አቶ ዳዊት ሁለቱ በሕይወት መትረፋቸውን ሁለቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመሬት ናዳ ሰዎች እንደሞቱ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ከእዉነት የራቄ ነዉ ያሉት ኃላፊዉ ከሰሞኑ በዞኑ በየትኛውም ቦታ በመሬት ናዳ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በዛው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ አሪ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ዲሜገሮ ቀበሌ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ምሶሶ ለመትከል በቁፋሮ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ ሦስት ወጣቶች ወዲያውኑ መሞታቸውን የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዳጁ ጨነቀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የደረሰዉ በአከባቢው የከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ታዎር ለመትከል DCGG በተባለ ኮንትራክተር አማካኝነት በተቆፈሩ ጉድጓዶች የዝናብ ዉሃ መሙላቱን ተከትሎ ዉሃዉ በጄኔሬተር ፓንፕ እንዲወጣ ተደርጎ ሰራተኞች ግንባታ እየሰሩ በነበረበት የአፈር መደርመስ ተከስቶ እንደሆነ አስረድተዋል።

በአደጋው ሦስት ወጣቶች ሲሞቱ በሁለቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታዉቀዋል።

የሦስቱ ወጣቶች አስከሬን በእስካቫተር ተቆፍሮ መዉጣቱንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
😭628554💔45🕊30😢29🙏19👏13🤔12🥰10
#SafaricomEthiopia

በፈጣኑ እና በማይቆራረጠው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ BET-WiFi ከቤት እንስራ ውጤታማ እንሁን!
#SafaricomEthiopia
116🙏18😡13👏2😢1
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የጋዜጠኝነት የክረምት ስልጠና የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም ይጀመራል።    
በስልጠናው፦
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሖች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል፡፡

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram Tiktok Linkedin
128🙏5😭2😡1
#Tinsae #IDEXX

ትንሳኤ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ከአይዴክስ (IDEXX) ላቦራቶሪስ ጋራ በጋራ በመሆን የውሃ ጥራት መመርመሪያ መሳሪያዎች ላይ ያተኮረ ዎርክሾፕ ከሰሞኑን አካሂዶ ነበር።

ወርክሾፑ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት ተሳታፊ እንደነበሩ ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" መሳሪያዎቹ እጅግ በጣም ቀላል፣ ጊዜ ቆጣቢና በቀላሉ በአጭር ጊዜ ስልጠና በቀላሉ ለመስራት የሚያስችሉ " ናቸው ያለ ሲሆን " በተለይ Tecta B4 እና Teta B6 የተባሉት መሳሪያዎች እጅግ ዘመናዊ ከእጅ ንኪኪ ውጪ የሆኑ፣ ባንድ ጊዜ አራት ወይም ስድስት ናሙናዎችን ለመመርመር የሚያስችሉና ውጤቱንም በኢሜል ለሚመለከተው አካል የመላክ አቅም ያላቸው " ናቸው ሲል ገልጧል።

" ይኼንን የመሳሰሉት መሳሪያዎች በስፋት ወደ ስራ በሚገቡበት ጊዜ የሀገሪቱን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና ተደራሽነት ከፍ በማድረግ በተለይም በውሃ ወለድ የሚመጡ በሽታዎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሱ ይሆናሉ " ብሏል።

ትንሳኤ ኢንተርናሽናል ከአይዴክስ (IDEXX) በተጨማሪ ሀክ (HACH) እና ሌሎች አለማቀፍ የውሃ መመርመሪያ አምራች ድርጂቶች ጋር ብቸኛ አቅራቢ በመሆን የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳለውና በዚህ ረገድ በሃገሪቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ያለ ተቋም መሆኑም አመልክቷል።

@tikvahethiopia
231🙏6🤔5🕊3🥰2😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ
(ለሚመለከተው አካል - አዲስ አበባ)

" በሰውና መኪና ላይ ወድቆ ጉዳት እንዳይደርስ መፍትሄ ይፈለግለት ! "

" ይህ በቪድዮው ላይ የምትመለከቱት የመብራት ኮንክሪት ፖል ታቹ ተበልቶ አልቆ ለመውደቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ከጎኑ ትራንስፎርመርንም አለ።

ቦታው ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር ነው ሲሆን ብዙ ሰው የሚመላለስበት መኪናም የሚንቀሳቀስበት ነው።

ፖሉ ወድቆ በሰው እና በመኪና ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት። ወቅቱም ክረምት በመሆኑ ዝናቡና ንፋሱ ኃይለኛነውና ፈጣን መፍትሄ ይፈለግለት። " - ዮሴፍ (ከአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
699🙏225👏44😭39🕊19😱14🤔3😡1
" ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል" - ፖሊስ

በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ የጅብ መንጋ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ስምዖን ለንበቦ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ገደማ የጅብ መንጋ በወረዳዉ ወይደ መላቶ ቀበሌ በሰዎች ላይ ጉዳት ሰንዝሮ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

በአከባቢው ከከተማ በቅርብ ርቀት ጥብቅ ደኖች መኖራቸውን የገለፁት ፖሊስ አዛዡ ጅቦች በጫካዉ ዉስጥ እንዳሉ ቢታወቅም እስካሁን በሰዉ ላይ ጉዳት አድርሰው እንደማያውቅና የትናንት ምሽቱ ጥቃት ድንገተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አዛዡ ገልጸው ማምሻዉን ጥንቃቄና ጥበቃ ሲደረግ ማደሩንና ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ የፀጥታ አባላት ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አሰሳ እያደረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
444😭155😢27😱25🙏23🤔12🕊10🥰9👏9
TIKVAH-ETHIOPIA
" አንድ ሃገር ለመብረር ፈቃድ ያስፈልጋል ያንን ፈቃድ ጠይቀን ሲፈቀድልን ነው የምንበረው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደርገውን የመጀመሪያውን በረራ በዛሬው ዕለት ምሽት ያስጀምራል። አየር መንገዱ አፍሪካን ከ ኤዥያ ጋር ያገናኘው የዛሬ 52 አመት እ.ኤ.አ በ 1973 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ በመብረር  እንደነበር የአየር መንገዱ ዋና…
" አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው  መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚያስገነባው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ መገለጹ ይታወሳል።

3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ የአየር ማረፊያ ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አየር መንገዱ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአሁኑ ሰአት ለ2,500 አባውራዎች መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን እና በመስከረም ወር ለማስረከብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ስለ አዲሱ አየር መንገድ እና በሃገር ውስጥ ያሉ መዳረሻዎችን ለማስፋት እየተሰራ ስላለው ስራ በዝርዝር ምን አሉ ?

" አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው እንደተጠናቀቀ ወደ ተሰራላቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ይዘዋወራሉ ስራቸውንም በአዲስ መልክ ይጀምራሉ።

ቦታው ሲለቀቅልን የግንባታ ስራ እንጀምራለን የአየር መንገዱ ዲዛይንም በብዙ አድቫንስ አድርጓል እየቆራረጥን በቅደም ተከተል ነው የምንሰራው የመጀመሪያውን ዙር ስራ ህዳር ውስጥ ለመጀመር እቅድ ይዘናል።

የሃገር ውስጥ በረራን ለማስፋት እና የአገልግሎት ጥራቱን ከፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ጥቂት አመታት በርካታ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።

ከስራዎቹ  መሃል ዛሬ ላይ ያሉን የአውሮፕላን ጣቢያዎች ማሻሻል ነው የአውሮፕላን መንደርደሪያው ጥሩ ካልሆነ እሱን በአዲስ መልክ መስራት።

መንገደኞች የሚስተናገዱባቸው ተርሚናሎችም አንዳንዶቹ ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና አሮጌ ፣ ወይም በቆርቆሮ የተሰሩ ነበሩ እነሱን እያፈረስን በዘመናዊ መንገድ እየሰራን ነው ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማይቻል በቅደም ተከተል ነው የምንሰራው።

ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ብቻ እንደ ጎዴ እና ጂንካ ያሉ 3 ተርሚናሎችን ሰርተን ስራ ላይ አውለናል።

አገልግሎቱን ለማስፋትም አዳዲስ ኤርፖርቶችን በመስራት ላይ እንገኛለን በአሁኑ ሰአት ስድስት ተርሚናሎች እየተሰሩ ይገኛሉ አንዳንዶቹ ለምረቃ ደርሰዋል።

ለምሳሌ ፦ ያቤሎ መንደርደሪያው አልቋል በሁለት ወር ውስጥ በረራ እምጀምራለን እሱ 23ኛው የሃገር ውስጥ መዳረሻችን ይሆናል ማለት ነው።

ነገሌ ቦረና፣ መቱ ፣ሚዛን አማን እና ደብረ ማርቆስም በመገንባት ላይ ናቸው በሚመጡት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.53K😡169👏97😭37🥰33🙏32🕊21🤔17😢12💔3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ካምፓኒዎቹን መቀመቅ የሚከት እብደት እንዲቆም የሚመለከተው አካል ሃላፊቱን ይወጣ " - አቶ በየነ ምክሩ አሁን ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙትና የትእምት (EFFORT) ዋና ስራ አስፈፃሚ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ በየነ መክሩ ' ላዛ ትግርኛ ' ለተባለ የዩቱብ ሚድያ ቃለ መጠይቅ ሰጥተው ነበር። በዚህም " ህገ-ወጥ " ሲሉ የጠሩት የደብረፅን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት በትእምት ካምፓኒዎች ላይ ከፍተኛ…
#EFFORT

" ነባሩ ቦርድ ህጋዊ ነው ፤ በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " የሚል ውሳነ መሰጠቱ ተሰማ።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታማኝ ምንጮች በላኩት መረጃ ነባሩ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር " ህገ-ወጥ የምክር ጉባኤ አካሂዶ ህገ-ያልተከተሉ አመራሮች መርጦ በተቋሙ ላይ የጀመረው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ይታገድልኝ " ሲል ለክልሉ የፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት አግኝቷል።

" በስራ ላይ ያለው ህጋዊ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር ነኝ " የሚል አካል ለፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ምን ይመስላል ?

በአቶ ቴድሮስ ሓጎስ የሚመራው የትእምት ባለ አደራ ቦርድ አመራር " በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህገ-ወጥ ነው ፤ በጉባኤው  የተመረጠ በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራ ቦርድ በተቋሙ ላይ እያካሄደ የሚገኘው እንቅስቃሴም ህገ-ወጥ መሆኑ ተጣርቶ ይታገድልኝ " ሲል ለፍትህ ቢሮ አቤታቱ አቅርቧል።

ሦስት አጣሪ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም  ላለፉት 10 ቀናት የቀረበለት አቤቱታ ሲመረምር የቆየው የፍትህ ቢሮ " በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራ ቦርድ ህጋዊ  አይደለም " በማለት በትእምት ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንዲያቆም የእግድ ውሳኔ ሰጥቷል።

" የትእምት ምክር ቤት ባለፈው የካቲት 2017 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ መርጦኛል " በሚል በመንቀሳቀስ ላይ ያለውና  የተቋሙ ዋና ስራ  አስፈፃሚ በየነ መክሩ ህጋዊ ርክክብ ባላካሄዱበት ሁኔታ በላያቸው ላይ አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለመቅጠር በሚድያዎች እስከማስነገር የደረሰው በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራው አካል " ህጋዊ  አይደለህም " የሚል የፍትህ ቢሮ ውሳኔ ያከብር ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።

ባለፈው መጋቢት 2017 ዓ.ም በተፈጠረው የፓለቲካ ቀውስ ምክንያት የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከትግራይ መውጣታቸው ተከትሎ የትእምት ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስፈፃሚና የባለ አደራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ መክሩና አቶ ቴድሮስ ሓጎስ ከክልሉ ውጪ ናቸው።

የትእምት ዋና ስራ ስፈፃሚ በየነ መክሩ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላዛ ትግርኛ ለተባለው ሚድያ ከአዲስ አበባ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ " ህገ-ወጥ ቡድኑ በሃይል ካስቀመጣቸው አመራሮች የተደረገ ርክክብ የለም ፤ ዋና ስራ አስፈፃሚና ቦርድ የነበረው ነው ያለው " ማለታቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
432🕊19😡12👏10🥰6🤔6😢3😭3😱2
2025/07/14 15:33:07
Back to Top
HTML Embed Code: