Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ (ለሚመለከተው አካል - አዲስ አበባ) " በሰውና መኪና ላይ ወድቆ ጉዳት እንዳይደርስ መፍትሄ ይፈለግለት ! " " ይህ በቪድዮው ላይ የምትመለከቱት የመብራት ኮንክሪት ፖል ታቹ ተበልቶ አልቆ ለመውደቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ከጎኑ ትራንስፎርመርንም አለ። ቦታው ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር ነው ሲሆን ብዙ ሰው የሚመላለስበት…
#Update

አ/አ ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር የመብራት ኮንክሪት ፖል ለመውደቅ ጫፍ ላይ መድረሱን በመጠቆም መፍትሔ ይፈለግለት ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች መጠየቃቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደረሰው መረጃ መሰረት ይህንን ፖል የመቀየር ሥራ በምሽት እየተሰራ ይገኛል።

" ባለሞያዎቻችን አሁንም እዛው ሳይት ናቸው " ሲል ጥገናው ምሽቱን እየተከናወነ መሆኑን የገለጸልን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ ፖሉ ተበልቶ ሳይሆን በመኪና ተገጭቶ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር መረጃውን አጋርቶናል።

@eeuethiopia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
21.42K👏696🙏117🤔20🕊17😡14😢13🥰10😭7
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ እንዲመለስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ይህ ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የለሌው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል…
" ቅሬታችንን ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት አስገብተናል " - የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ

የ‎ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ በመቃወም ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል።

ክለቡ ቅሬታዉን በየደረጃ ለፌዴሬሽኑም አስገብቶ ምላሽ ባለማግኘቱ ወደ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ማለፉን የገልጿል።

ሲዳማ ቡና ከወላይታ ዲቻ ጋር ባደረጉት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጫወታ የሲዳማ እግር ኳስ ክለብ 2ለ1 አሸንፎ ዋንጫዉን ቢያነሳም " ያለ አግባብ ተጫዋቾችን አሰልፏል " በሚል ፌዴሬሽኑ ቡድኑ የወሰደዉን ዋንጫ ለወላይታ ዲቻ ተመላሽ እንዲያደርግ የሚል ዉሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
596🤔103🙏37👏24😭17😡17😢16🕊9🥰6💔6😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
" አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው  መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚያስገነባው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ መገለጹ ይታወሳል። 3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ የአየር ማረፊያ ስራ የቅድመ…
" በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ትናንሽ አውሮፕላኖች እናስመጣለን "-የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያዊ አየር መንገድ መጋቢት 17/2017 ዓም ላይ አርቸር አቪዬሽን ከተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ጋር ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አርቸር አቪዬሽን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋል ሲሆን በመኪና ከ60-90 ደቂቃ የሚወስድ ጉዞን ወደ 10 ደቂቃ ዝቅ የሚያደርግ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

የዚህ ስምምነት ትግበራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጥያቄ አቅርቧል።

ዋና ስራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ " በፈርንጂዎቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ትናንሽ አውሮፕላኖች እናስመጣለን በዋነኛነት የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ እንጠቀምባቸዋለን ብለን አቅደናል " ብለዋል።

የኢ-ኮሜርስ ንግድን ከማስፋፋት አኳያ አየር መንገዱ ከአለም አቀፎቹ አማዞን እና አሊባባ እንዲሁም ከሃገር ውስጡ " ዘመን ገበያ " ጋር በአጋርነት ለመስራት አስቧል ወይ ? ምን አይነት እንቅስቃሴዎችንስ እያደረገ ይገኛል ? የሚል ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ መስፍን ፤ አየር መንገዱ የተወሰነ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሚገኝ ነገር ግን ገና በሚባል ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን በተጨማሪ ምን አሉ ?

"እኛ እስካሁን ድረስ ኢ-ኮሜርስን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመስራት የሚያስችለንን ፋሲሊቲ ገንብተናል።

ይህ ፋስሊቲ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አካሉን ብቻ ነው የሚሰራው እኛ ኢ-ኮሜርስ ውስጥ አንገባም ኢ-ኮሜርስ ንግዱን የሚሰሩት ሌሎች ድርጅቶች ናቸው እኛ ትራንስፖርቱን ነው የምናቀላጥፈው።

ከመነሻው ማጠናቀቁን እና መዳረሻውን ላይ ደግሞ የመጨረሻውን ከሚያከፋፍሉ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅተን ቦሌ ኤርፖርት ካርጎ ተርሚናላችንን ተጠቅመን ይህንን ለማሳለጥ ነው የምንሰራው የተወሰነ የተጀመረ ስራ አለ ነገር ግን ገና መሰራት ያለበት ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
1.31K😡196👏78🤔77🙏44😭37😱16🕊15😢12💔11🥰9
Calling all #Ethiopian Innovators!

The second round of the Immunisation Innovation Accelerator is now open - offering up to $100,000 in grants to solutions that improve #vaccine access.

📅 Application deadline: July 27
🔗 https://www.stc-accelerator.org/

#ChildHealth #InnovationInAction #HealthInnovation #Ethiopia
82🙏6😱5🤔2😢2🥰1👏1
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያን ይፋ አደረገ !

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ ይፋ ባደረገው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ ውስጥ ካቀዳቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የሆነውን ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ የማብሰሪያ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡

ይህ ለደንበኞች የተሟላ፣ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ንብተራ ኦንላይን ሱፐር አፕ መተግበሪያ ከሐምሌ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

መተግበርያው ደንበኞች ከባንክ አገልግልት በተጨማሪ ግብይቶችንና ክፍያዎችን በቀላሉ የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም መፈጸም እንደሚያስችላቸው በዚሁ የማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጻል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት ባንኩ ለደንበኞቹ ዘመኑ የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በውጤት የታጀበ አገልግልት ለመስጠት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን አዲሱ የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድም ከባለድርሻ አካላትና ከመላው ደንበኞቹ ጋር በመሆን የላቀ ውጤት የሚመዘገብበት ይሆናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ይህ በውስጥ አቅም በልጽጎ ወደ ተግባር የገባው ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያና አዲሱ የሶስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማበልፀግና ወደ ሥራ እንዲገባ ላደረጉ የባንኩ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ምሰጋና ያቀረቡት የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሊ/መንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ አዲሱ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምክክር አድርገውበትና ጸድቆ ወደ ሥራ መግባቱን አመልክተዋል፡፡

በይፋዊ የንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፣ ደንበኞች፣ የባንኩ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://www.nibbanksc.com/wp-content/uploads/2025/07/Press-release-NIB-Tera.pdf

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

#Nib #DigitalBanking #Nibinternationalbank #nibbank #nibtera #nibsuperapp

Facebook  / Instagram / linkedin / X / Youtube / Tiktok / Website
325👏35😡15🥰4😢4😭3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሦስት 5Lሚኒባሶች ናቸው የተወሰዱት ፤ ሦስት ሆነው ነበር ያደሩት አንዱ ጥበቃ አብሮ ጠፍቷል " - ባለንብረቶቹ ትላንት (ረቡዕ ለሐሙስ) ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ ፓርክ ከተደረጉበት ሦስት 5L ሚኒባሶች እንደተወሰዱባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ ባለንብረቶች ተሽከርካሪዎቹን ያየ ሁሉ እንዲጠቁማቸው በአጽንኦት ተማጽነዋል። ባለንብረቶቹ " ሦስት 5L ሚኒባሶች ናቸው የተወሰዱት፤ ሦስት ሆነው ነበር ያደሩት…
" አንዱ መኪና ተገኝቷል " - ባለንብረቶች

ከቀናት በፊት ለሊት 9 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቃሊቶ ቶታል ኮንዶሚየም ግቢ ውስጥ የቆሙ ሶስት 5L ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ እንደተወሰዱ፣ አንደኛው እንደተገኘ ሌሎቹን ያየ ሰው እንዲቆጥማቸው ባለንበረቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች አሳውቀው ነበር።

መልዕክቱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ አንዱ መኪና ማለትም ኦሮ ኮድ 03 34021 ጀሞ 2 አካባቢ መገኘቱን ገልጸዋል።

" መረጃዉን አይቶ ለደወለልን ግለሰብ እንዲሁም ለአቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ አባላት ምስጋናችንን አድርሱልን " ብለዋል።

አሁን ላይ ተሽከርካሪውን በእጃቸው ለማድረግ ከፖሊስ እየጠበቁ መሆናቸውን አመልክተው " ተሽከርካሪዎቹን ይወስዳሉ ተብለው የተጠረጠሩት አልተያዙም ክትትል እየተደረገ ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።

አሁንም ቀሪ አንዱን ተሽከርካሪ ኦሮ ኮድ 03 41867 ያየ እንዲጠቁማቸው ተማጽነዋል።

ከዚህ ቀደም ባለንብረቶቹ በጥበቃና ቀጣሪ ኤጀንሲው ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸው የነበረ ሲሆን በዚህ ላይ ገና ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
541🙏76🕊14🥰10😡9👏7😢4🤔3😭3
#AddisAbaba

በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።

አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማት የትኞቹ ናቸው ?

- ንግድ ቢሮ፣

- ገቢዎች ቢሮ፣

- መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣

- መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣

- ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣

- ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

@TikvahethMagazine @tikvahethiopia
😡1.32K1.15K👏272😭116🤔41💔31🙏27🕊23😱22🥰14
" የታርጋ ቁጥሩ ኮድ3-48279 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ተሰርቆብናል " - ድርጅቱ

ሮሜል ጀነራል ትሬዲንግ የተሰኘ ድርጅት ጃፓን ሰራሽ 5L የ2002 ሞዴል ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-48279 አ.አ የሆነ ሚኒባስ መኪና መሰረቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መኪናው ሀምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር በሚወስደው አዲሱ አስፓልት ላይ ' ሰላም አደባባይ ' ከመድረሱ በፊት ባለው ቦታ ከቆመበት በሌቦች እንደተሰረቀ አመልክቷል።

ድርጅቱ ይህንን በዕለቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳመለከተ ገልጿል።

" የመኪናው ልዩ ምልክት ዕቃ ለመጫን እንዲመች ከገቢና ቀጥሎ ያለው ወንበር ብቻ ያለው ሲሆን ሌላው የተፈታ ነው " ብሏል።

" መኪናችን ያለበትን ለጠቆመ ወይም ለያዘ ወረታ እንከፍላለን " ያለው ድርጅቱ " ለጥቆማ ስልክ ቁጥሮቻችን +251930078032 ፣ 0913324134 እና +251115620212 ናቸው " ሲል አመልክቷል።

@tikvahethiopia
363🤔60😢35🕊23😱18🥰3👏2
የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ሞሐመዱ ቡሃሪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የ82 ዓመቱ ቡሃሪ በብሪታኒያ ዋና ከተማ ለንደን በሚገኝ ክሊኒክ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የቀድሞ ቃል አቀባያቸው ገርባ ጋሹ ገልጸዋል።

ሁለት የፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ያገለገሉት ቡኻሪ ሥልጣን ያስረከቡት እኤአ በ2023 ነበር።

በናይጄሪያ ታሪክ ቡሃሪ በምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኝ ፕሬዝደንት ያሸነፉ የመጀመሪያው የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ነበሩ። እኤአ 2015 ሥልጣን የያዙት የቀድሞውን ፕሬዝደንት ጉድላክ ጆናታን በምርጫ አሸንፈው ነው።

ይሁንና ናይጄሪያን የመሩባቸው ዓመታት በጤና ዕክል ምክንያት አሉባልታ በብዛት ይናፈስባቸው ነበር።

ቡሃሪ ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ አድርገው ከመቀየራቸው በፊት በ1980ዎቹ ጠንካራ አምባገነን ሆነው ናይጄሪያን መርተዋል።

ቡሃሪ ከሦስት ያልተሳካ ሙከራ በኋላ ጉድላክ ጆናታንን አሸንፈው ፕሬዝዳንት ሲሆኑ በናይጄሪያ ፖለቲካ የለውጥ ዕድል ተፈጠረ ተብሎ ተስፋ ተሰንቆ ነበር።

ይሁንና በስልጣን ዘመናቸው በናይጄሪያ የበረታውን ሙስና እና የመረጋጋት እጦት መቅረፍ ተስኗቸዋል። የሥልጣን ዘመናቸው ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና የጤና ዕክል የበረታባቸው ነበሩ። መንግሥታቸው በተቃዋሚዎች ላይ በወሰዳቸው ርምጃዎች ከፍተኛ ትችት ይሰነዘርባቸው ነበር።

በሰሜናዊ እና ደቡባዊ ናይጄሪያ ከፍተኛ ፉክክር ባለባት ሀገር ቡሃሪ የትውልድ አካባቢያቸውን ሰዎች እና ዘመድ አዝማዶቻቸውን ለከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን በመሾም አለመተማመን እና ጥርጣሬ እንዲነግስ አድርገዋል እየተባሉ ይተቻሉ።

Credit - DW

@tikvahethiopia
406😭151😢28🕊16💔14👏8🤔8🙏8😡4
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤት አንገባም ያሉ ነዋሪዎች ! " መንግስት መጥቶ ጥያቄያችንን ካለመለሰልን ወደ ቤት ላለመመለስ ወስነን ሜዳ ላይ ተሰብስበናል " - ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " ሰሚ እስክናገኝ ወደ ቤታችን አንመለስም ! " በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ አከባቢ ነዋሪዎች " በአዲስ የመዋቅር ጥናት እና ልማታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወረዳዉ…
" ሸዉደዉናል 5ዐ ሰዉ መርጣችሁ ስጡን ብለዉ ካስነሱን በኋላ የተወከሉትን ስብሰባ ጠርተዉ አስፈራርተዋል " - ነዋሪዎች

➡️ " የኛ ጥያቄ የወረዳውን የተወሰኑ ቀበሌያት ወደ ሀዋሳ ከተማ ክፍለ ከተማነት ለማጠቃለል መወሰኑ ተገቢነት የለዉም የሚል ነው ! "


የሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ  አከባቢ ነዋሪዎች ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዲስ ተዋቀረ በተባለው የክፍለ ከተማ አደረጃጀት ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ 5 ቀበሌያትን ብቻ ነጥሎ መወሰዱን በመግለፅ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵየ ገልጸው ነበር።

ነዋሪዎቹ የተመረጡት ቀበሌያት ምርታማና የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸዉ በመሆኑ የወረዳዉን የመልማት አቅም ያዳክመዋል፤ ከዚህ ቀደም የተገባልንም ቃል ተግባራዊ አልተደረገም ሲሉ አደባባይ በመዉጣት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ወደ ቤታችን አንመለስም " ማለታቸው አይዘነጋን።

" በዕለቱ ሕዝቡ ከሜዳ ላይ አልነሳ በማለቱ ምሽት ከ2 ሰዓት በኋላ የዞንና የወረዳ አመራሮች መጥተዉ 'ለነገ 50 ተወካዮችን መርጣችሁ ዉይይት እናድርግ' ብለዉ ሕዝቡ እንዲበተን ካደረጉ በኋላ በማግስቱ የተመረጡትን ተወካዮች ሰብስበዉ አስፈራርተዋቸው ስብሰባዉን ረግጠዉ ወጥተዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" አመራሮች ሸዉደዉናል 50 ሰዎችን መርጣችሁ ወክሉና እናንተ ወደ ቤት ተመለሱ እነሱ ነገ ከኛ ጋር ይወያዩ ብለው በሽማግሌዎች በኩል ሕዝቡ እንዲበተን ካደረጉ በኋላ በማግስቱ የተወከሉትን ሰዎች ' እናንተ ናችሁ ሕዝቡን የሚታሳምፁት ' ብለዉ በማስፈራራት ስብሰባዉን ጭምር ረግጠዉ ወጥተዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

ዶሬ ባፋናና አከባቢዉ ያሉ ሌሎች ቀበሌዎች ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ ስር ከመካለል ጋር ተያይዞ አንድ ላይ ዉሳኔው ያለ ልዩነት ተግባራዊ እንደሚደረግ እየተነገራቸዉ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ በወረዳው የተሻለ አቅም ያላቸው የተባሉ 5 ቀበሌያትን ብቻ ነጥሎ ' በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዋሳ ላንጋኖ ክፍለ ከተማ ' በሚል ሊደራጅ እንደሆነ መነገሩ ሕዝቡን ማስቆጣቱን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ የወረዳዉ አስተዳዳሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

@tikvahethiopia
504😢57🕊26😡24🤔16😭14💔9🥰8👏8😱6
2025/07/14 17:54:15
Back to Top
HTML Embed Code: