TIKVAH-ETHIOPIA
#መሰቦ ፋብሪካው ጥሬ እቃ ከሚያገኝባቸው አከባቢ ማህበረሰብ በተከሰተው ችግር ምክንያት ስሚንቶ ማምረት ማቆሙ አስታወቀ። ፋብሪካው ተከሰተ ያለውን ችግር ከማብራራት ተቆጥበዋል። የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ በሰጠው መረጃ ፥ በኳሪ ሳይቱ ባጋጠመው ጊዚያዊ ችግር " ማምረት አቁሚያለሁ " ብሏል። ፋብሪካው ችግሩ መቼና ? እንዴት ? እንደሚፈታ አስመልክቶ ያለው ነገር የለም። …
#Mesebo
የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሁለት ወራት በላይ ከስራ ገበታ ውጪ ሆኗል። ስራ ባቆመባቸው ቀናት 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ሳያመርት ቀርቷል።
ፋብሪካው ከማምረት ውጪ ሊሆን የቻለው ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር በተፈጠረ አለመስማማት ነው።
የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ክብረኣብ ተወልደ ምን አሉ ?
" የላይምስቶን ጥሬ እቃ የሚያገኝበት አከባቢ የሚኖረው ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳው ጥያቄ በጊዜ ባለመመለሱ የተነሳ ፋብሪካው ላለፉት 65 ቀናት አላመረተም።
ባለፉት 65 ቀናት ውስጥ 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ማምረት ይችል ነበር በመጋዘን የነበረው ክምችት ባለፉት 30 ቀናት ተሽጦ አልቋል።
ፋብሪካው ማምረት በማቆሙ የስሚንቶ መወደድ አስከትሏል። ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር ህዝብ የተፈጠረው አለመግባባት ተፈትቶ ፋብሪካው በቅርቡ ወደ ስራ ይመለሳል። " #DemtsiWeyane
@tikvahethiopia

❤230🕊24🙏14😭14🤔9💔9😡6😱3👏1
#ለጥንቃቄ
#ጥቆማ_ለሚመለከተው_አካል!
አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የኢሚግሬሽ እና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ ከሰሞኑን የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል የዘረፋ ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎች የተሞከረባትን የዘረፋ ሙከራ አንድ የቤተሰባችን አባል ለጥንቃቄ አጋርታለች።
የጎተራው አገልግሎት መ/ቤት የውጭ ዜጎች አገልግሎት ፣ የቪዛም አገልግሎት የሚገኝበት በመሆኑ ብዙ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለአገልግሎት ይሄዳሉ።
በባለፈው ሳምንት ለዚሁ የውጭ አገልግሎት የሄደች አንዲት ከአሜሪካ የመጣች የቤተሰባችን አባል የዘረፉ ሙከራ ተፈጽሞባታል።
ነገሩ እንዲህ ነው ...
ቦታው እንደልብ ትራንስፖርት የማይገኝበት እና ጭር ያለ ነው።
ልክ ከአገልግሎቱ መ/ቤቱ ስትወጣ በቦታው ቀድሞውንም የነበሩ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የሚመስሉ ሰዎች " ይኸው ነይ የሜትር ታክሲ አገልግሎት " ይሏት።
እሷም ወደ መኪናው ትገባለች።
ብዙ ሳይጓዙ መኪናውን የሚያሽከረክረው ሰው መኪናውን ያቆመውና አንድ ሰው ገቢና ይጨምራል።
" ለምን ሰው ትጨምራለህ ? " ብትለውም " ምን አገባሽ ዝም ብለሽ ቁጭበይ " የሚል መልስ ይሰጣታል።
ነገሩ ያላማራት ይህች እህታችን ሁኔታውን በንቃት መከታተል ትጀምራለች።
አሁንም ትንሽ ከተጓዙ በኃላ መኪናውን አንድ ግብረአበራቸው ጋር ያቆሙና እሷ በተቀመጠችበት በር በኩል እንዲገባ ይነግሩታል።
በዚህ ወቅት እሷ " እኔ አልከፍትም በዛኛው ተቃራኒ በኩል ከፍቶ ይግባ " የሚል ምላሽ ትሰጣለች። ልክ ሰውየው በዛኛው በር ለመግባት ሲሄድ የነበረችበትን በር በመክፈት ወርዳ ወደ ኃሏ ሩጣ ማምለጥ ችላለች።
ሰዎቹ መንገዱ ወደፊት እንጂ ወደኃላ መመለስ የማያስችል በመሆኑ ሊከተሏት አልቻሉም።
በኃላም አካባቢው ግር ስላለባት በጎተራ ድልድይ አድርጋ ወደ ሳሪስ አቅጣጫ በእግር እየሮጠች ራሷን አትርፋለች።
በሩጫ በምታመልጥበት ወቅት ሰዎቹ " ነቃሽብን አይደል " እንዳሏት ታስታውሳለች።
ታርጋውን ለማየት ባትችልም የመኪናው ቀለም ' ብሉብላክ ' ቶዮታ ቪትዝ እንደነበር አስተውላለች።
አካባቢው ጭር ያለም ስለሆነ ብዙ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የሚስተናገዱበት በመሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ መከታተል ይገባል።
የሜትር ታክሲ አገልግሎት የምትጠቀሙም " ኑ ታክሲ ይኸው " ብትባሉ እንዳትገቡ። ይልቁም ወደ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶቹ ስልክ በመወደል እና የተመዘገበ ህጋዊ መኪና ወደእናተ እንዲመጣ ማስደረግ አለባችሁ።
በማንኛውም ሁኔታ ስልካችሁ ባልተመዘገበበት እና ባለመኪናውም በድርጅት በህጋዊነት የተመዘገበ መሆኑን ሳታረጋግጡ ትራንስፖርት ለመጠቀም አትሞክሩ።
መንገድ ላይ የምትገቡም ከሆነ ስልካችሁን የግድ አስመስግባችሁ መልዕክት ሲመጣላችሁ ብቻ ተንቀሳቀሱ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

❤1.3K🙏325👏93🤔15🥰12😢12😭5😡5😱4
ከ3 ጊዜያት በላይ ሲራዘም የቆየዉ ቶምቦላ ሎቶሪ ዛሬ ይወጣል ተባለ።
የሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን ለማጠናቀቅ ታስቦ ለሽያጭ የቀረበዉ ቶምቦላ ሎተሪ ከሶስት ጊዜያት በላይ ሲራዘም ቆይቶ ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አደራሽ እንደሚወጣ የሀዋሳ ከተማ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ፈንድ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
አስቀድሞ ጥር 20/2017 ዓ/ም ከዚያም ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ዕጣዉ እንደሚወጣ ተገልፆ ሲራዘም የቆየዉ ሎተሪ 500 ሺህ ትኬቶች ለገበያ የቀረቡ ሲሆን 1 መቶ ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብም ዕቅድ ተይዞበት ነበር።
" ሶስቱንም ዙሮች ትኬቶቹ በበቂ ሁኔታ ስላልተሸጡና በተለያዩ አከባቢዎች የተሰራጩ የቲኬት ወረቀቶችም ተሰብስበዉ ስላላለቁ " በሚል መውጫው ሲራዘም ነበር ተብሏል።
250 ካ.ሜ ለንግድ እና 200 ካ.ሜ ለመኖሪያ የሚሆን መሬትን ጨምሮ ኩዊት ባጃጅ፣ ሞተር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ ዕጣ የሚወጣባቸው ሲሆኑ 14 ዕድለኞች ይታወቃሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

❤218😡30🙏13😭4🥰2😢2
ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተነገረ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ወንጀል ምርመራ በማጣራት ለፌደራል ዐቃቤ ህግ በማስተላለፍ ክስ እንዲመሰረት ማድረጉን አመልክቷል።
ተከሳሾቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሌሎች የግል ባንኮች የሚደውሉ በማስመሰል እንዲሁም የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀሉን እንደፈጸሙ ፖሊስ ገልጿል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያብራራው፣ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመሰወር፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን እና መታወቂያዎችን በማዘጋጀት እና በመጠቀም የተበዳዮችን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረበው ክስ በዋናነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን እንዲሁም የብሄራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003ን የተላለፉ መሆናቸውን ይገልጻል።
ለወንጀል ድርጊቱ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ፦
- በርካታ የባንክ አካውንቶች፣
- የሞባይል ቀፎዎች፣
- ሲም ካርዶች እና ኮምፒውተሮች የተያዙ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ ፥ ህብረተሰቡ ከማያውቋቸውና አጠራጣሪ ከሆኑ የስልክ ጥሪዎችና መልዕክቶች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
(በክሱ ከተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች መካከል የተወሰኑት ስም ዝርዝራቸው ከላይ ተያይዟል)

❤586👏272🤔15😭13😡5😱4🕊4💔4😢2🥰1🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 " አሁን የ2,000 ብር ደሞዝ የለም በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም ! " - የምክር ቤት አባል በገቢ ግብር ማሻሽያ አዋጅ ላይ ዝቅተኛ የግብር ከፋይ መነሻ ደመወዝ 5,000 ብር እንዲሆን በምክር ቤት ተጠየቀ፡፡ ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ ከሰዓት በጠራው ልዩ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ አሁን በስራ ላይ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹
የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ከ2,000 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጠንካራ ጥያቄ ቀርቧል።
ጥያቄው የቀረበው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገዉ ዉይይት ላይ ነው።
በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፣ ከ2,000 ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር እንዲከፈል የሚለው ሀሳብ ቀርቧል።
ይህ የገቢ ግብር አዋጅ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ስራ ላይ መዋሉ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን በማሻሻያው ከግብር ነፃ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ በ300% በማሳደግ ወደ 2,000 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።
በተጨማሪም፣ ከፍተኛው የማስከፈያ መጣኔ የሆነው 35% ግብር የሚያርፍበት ገቢ ደግሞ ወደ 14,000 ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፣ የአዋጁ መሻሻል መንግስት ግብር በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚረዳ ገልጸዋል።
ከግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የሚነሱ " ግብር በዝቷል ይቀነስ " የሚሉ ሀሳቦች ሚዛናዊ በሆነ መልኩ እንደሚታዩም አክለዋል።
በውይይት መድረኩ ከተነሱት አስተያየቶች መካከል፣፦
- የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺህ ብር ጀምሮ እንዲሆን፣
- ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መልኩ ግብር እንዲቀነስ፣
- በተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንፃር በደንብ እንዲታይ የሚሉ ሀሳቦች ቀርበዋል።
የመረጃው ባለቤት የካፒታል ጋዜጣ ነው።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤695👏92😭67😡57🕊25🙏14😢6🤔5
በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ።
ትላንት ምሽት በአሜርካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ " ለቡ " አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በዲኤስቲቪ እየተመለከቱ በነበሩ ተመልካቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ለጋ ወጣት ህይወት አልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በለቡ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኘት የሟቹ ወጣት የቀብር ስነስርዓት ሲፈፀም ተመልክቷል።
በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የሟቹ ወዳጆች ፣ ጓደኞች " አሟሟቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው " ያሉ ሲሆን " ግለሰቡም ተይዟል " ብለዋል።
" እስከ ምሽት 3:00 ሰአት ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር ካመሸ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ትንሽ ልዝናና ብሎ ሆቴሉ እንደገባ ነው ክስተቱ የተፈጠረው " ሲሉ ተናግረዋል።
በአሟሟቱ ቤተሰቦቹ እጅግ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኙ ለመመልከት ችለናል።
" ወጣቱ ከኳስ ስሜታዊነት መቆጠብ ወይም የእግር ኳስ ጨዎታዎችን ተሰባስቦ ከማየት መቆጠብ አለበት ካልሆነ ግን የቤተሰብን ሀዘን ማብዛት ነው " ሲሉ ያነጋገርናቸው ለቀስተኞች ተናግረዋል።
" ወጣቶች እባካችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ሀዘን አታብዙ፣ ሁሉን በማስተዋል አድርጉ፣ ማታ ማታ አታምሹ፣ በአጭሩ እየተቀጫችሁ ሃዘናችንን አታብዙት " የሚሉ እና ሌሎች ልብ የሚነኩ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ቃላቸውን የሰጡ አንድ እናት ሟቹን ወጣት እንደሚያውቁት ገና በ22 ዓመቱ በተፈጠረው ፀብ እንደተቀጠፈ ገልጸዋል።
" በውጭ ኳስ ምክንያት የለጋ ወጣት ህይወት መጥፋቱ እጅግ ያሳዝናል። ሁሉም ወጣቱ ከስሜታዊነት መራቅ አለበት፣ የሚመለከታቸው አካላትም እንዲህ ያለው ነገር እንዳይፈጠር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው " ሲሉ እናታዊ መልዕክታቸውን በሀዘን ስሜት አስተላልፈዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

😭883❤445😡79😢53💔36🕊31🤔28🙏15😱13🥰10👏1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ከ2,000 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጠንካራ ጥያቄ ቀርቧል። ጥያቄው የቀረበው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገዉ ዉይይት ላይ ነው። በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ…
" ተቀጣሪው ሰራተኛ በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ምክንያቱም በርካታ ወጪዎች አሉበት ፤ ... ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል !! " - ኢሰማኮ
➡️ " ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም !! "
🔴 " የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው የሚለምኑ ሰራተኞችን አብረን ማየት እንችላለን !! "
የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡
ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ/በህ/ም/ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ?
" ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት ነው።
ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው።
ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል። እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል ? ፣ ልብስ ይለብሳል ? ፣ ህክምና ይሄዳል ?
ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ ?
አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ፤ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ?
ነጋዴውም፣ ድርጅቱም ከትርፉ ነው እኮ 35 በመቶ የሚከፍለው ሰራተኛው ግን ከትርፉ ሳይሆን ከሚበላው ላይ ነው የሚከፍለው ይህ እንዴት ነው ? እኩል የሚሆነው።
ስለሰዎች ስናስብ ልማት ለማስቀጠል ነው ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም።
ስለዚህም የሰራተኛውንም ጫና የመንግስትን ዓላማ ታሳቢ ያደረገ የግብር ምጣኔ መጣል አለበት።
አሁን በማሻሻያው የግብር መነሻ 2000 ሺ ብር ሲሆን ምን ታሳቢ ተደርጎ ነው ? አንድ ስልት ሲሰራ ሰውን ማኖር አለበት ይህ መነሻ ግን ታሳቢ አልተደረገም።
ቋሚ ኮሚቴው እንደገና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር ቢመካከር ይሻላል።
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው ሲለምኑ አብረን ማየት እንችላለን። "
የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍቃዱ ሆረታ ምን አሉ ?
" አዋጁ በይድረስ ይድረስ የተዘጋጀ ሳይሆን ሁለት ዓመት ጥናት ተሰርቶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው።
2000 ብር መነሻ የተደረገበት ምክንያት የመክፈል አቅማችን ዝቅተኛ ስለሆነ ነው።
መነሻን ከዚህ ከፍ ለማድረግ ቢፈለግ አገሪቱ ያላት ገቢ አይፈቅድም ወደፊት ገቢው እያደገ ሲሄድ ግን መነሻን ከፍ ማድረግ ይቻላል።
የኑሮ ውድነቱ ግብር በመክፍል ብቻ የመጣ አይደለም። በኢትዮጵያ ብቻም ያለ ችግር አይደለም።
ከውጭ የምናስገባቸውን መዳበሪያ ፣ ነዳጅ እና መሰል ግብዓቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሰዎች ላይ ጫና ይፍጥራል።
ይህን ችግር ለመፍታት ደግሞ መንግስት ደሞዝ ጨምሯል። መንግስት አቅም በፈቀደ መሰረት ድጋፍ አድርጓል።
በገቢ ግብር ላይ ያለውም ጫናውን መቀነስ ነው እንጂ ማጥፋት አይደለም። በነባሩ አዋጅ ላይ መነሳት ብናመለከት 600 ነው ወደ 2000 ያደገው በውይይት ተደርጎበት ነው።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የሞያ ማህበራት ተሳትፎ የተደረገ ማሻሻያ እንጂ ዝም ብሎ የመጣ ቁጥር አይደለም።
የግብር መነሻው ከተቀጣሪ ሰራተኛ አሁን ካቀረብነው ከፍ ካለ መንግስት ከፍተኛ ገቢ ያጣል። በተለይ በክልሎች ገቢ ላይ የበረታ ጫና ያሳድራል። "
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።

❤1.52K😭697👏101😡97🙏55💔37😢33🕊26🤔14🥰12😱5