"ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የጥላቻ ንግግር የተሰራጨው በታዋቂ ሰዎች/በፐብሊክ ፊገርስ መሆኑን ጥናቱ ያረጋግጣል”- ጥናት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ስለመድረሱ በጥናት ማረጋገጡን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
"በሀገራችን የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱ በጥናት ተረጋግጧል” ሲልም ተናግሯል።
በጥናቱ ግኝት መሠረት፣ “አብዛኛው የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ የተሰራጨው ባብዛኛው በጽሑፍ እና በተንቀሳቃሽ ምስል፤ በአብዛኛው የተሰራጨውም በፌስቡክ፣ ቲክቲቶክና በቴሌግራም እንደሆነ ጥናቱ ያመለክታል” ብሏል።
ባለስልጣኑ በመግለጫው፣ ተጠቃሚዎቹ የተሳሳተ መረጃ ሲያገኙ ሪፖርት እንደሚያደርጉና ለማን ሪፖርት እንደሚደረግ እንደማያውቁ ተናግሯል።
ይህን ሁሉ ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ታምራት ደጀኔ፣ “ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆኑ የጥላቻ ንግግር የተሰራጨው በታዋቂ ሰዎች/ፐብሊክ ፊገርስ በሚባሉት መሆኑን ጥናቱ ያረጋግጣል” ብለዋል።
በግኝቱ መሠረት፣ “የጥላቻ ንግግር ያነጣጠረው የፖለቲካ አመለካካት ላይ ነው፡፡ ቀሪዎቹ በብሔርና ሃይማኖት ናቸው፤ (ብሔር 15%፣ ሃይማት 6%”) ብለው፣ “ሀሰተኛ መረጃው የተሰራጨባቸው ዋና ዋና መንገዶች በግኝቱ መሠረት የሐሰት አውድ በመጠቀም፣ በተሳሳቱ መረጃዎች (በእንዝላልነት)፣ አሳሳች በሆኑ ይዘቶች..." መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ለማሰራጨት የተፈለገው፣ “ማሕበራዊ አለመረጋጋት እንዲፈጠር፣ በማህበረሰብ መካከል ግጭት የመቀስቀስ አላማ፤ የመግስት ተቋማትና መንግስት ሥራቸውን ተረግተው እንዳያከናውኑ ለማድረግና የማስተባበል፣ የግለሰብና የቡድኖችን ሥም ለማጠልሸት..” መሆኑን የጥናቱ ዳሰሳ እንደሚያስረዳ ገልጸዋል።
"ዜጎችን ለአመጽና ለጥቃት እንዲነሳሱ መቀስቀም 15% ይዟል፣ የማህበረሰቡን አብሮ የመኖር እሴት በመሸርሸርም ወደ 11% ታርጌት እንደተደረገ መረጃው ያመለክታል" ነው ያሉት።
“እንደ ኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚዩኒኬሽን መረጃ በአገራችን ከ44 ሚሊዮን በላይ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ይገኛሉ፡፡ ለብቻው የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ ወደ 4 ሚሊዮን ይጠጋሉ፡፡ ይህ ቀላል ቁጥር አይደለም” ሲሉም ተናግረዋል።
ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር፣ “የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በአንጀንዳ ሴቲንግ ከፍተኛ ሚና አላቸው፣ ኮንተንት እስከመወሰን ራሱ የሚደርስ አቅም እንዳላቻው”ም የጥናቱ ግኝት እንደሚያስረዳ አብራርተዋል።
የጥናቱ መረጃ ምንጭ በአምስት ዋና ዋና ማለትም ሜታ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክና ቲዊተር ማህበራዊ ሚዲያዎችን መሠረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም፣ ከ500 ሺሕ ባላይ ተከታዮች ያላቸው ተጸዕኖ ፈጣሪ፣ ግለሰቦችን መሠረት ያደረገ እንደሆነ እና ወደ 1700 ከሚሆኑ ተጽዕኖ ፈታጣሪ ግለሰቦችም በጉዳዩ ዙሪያ የህዝብ አስተያየት እንደተሰበሰበ ገልጸው፣ “ከ2000 በላይ ይዘቶች በባለሙያዎቻችን ሞኒተር ተደርገዋል” ተብሏል።
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ለሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት ምክንያት እንደሆነ፣ በዚህም ታዋቂ ሰዎች 56%፣ መገናኛ ብዙኃን 26%፣ ግለሰቦች 17% አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤595😡56🕊19🤔16😱11💔9😭9😢6🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከማረሚያ ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ ገብተዋል " - ቤተሰቦች
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና አብሯቸዉ ታስረዉ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታርኩ ታመነ ከማረሚያ ተለቀዉ ወደ ቤታቸው መግባታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩትና ከሁለት ወራት በፊትም የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለት የክስ 13 ዓመት ፅኑ እስራት ዉሳኔ አስተላልፎባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ይግባኝ ጠይቀዉ ዛሬ በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነፃ መሰናበታቸውን ተከትሎ ከሀዋሳ ከተማ ማረሚያ ቤት ወጥተው ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቅለዋል።
ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ከማረሚያ ቤት ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ ሲሄዱ በርከት ሰዎች በሞተር ሳይክሎችና በመኪና አጅቧቸዉ ደስታቸዉን ሲገልፁ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

❤922🤔98🙏58🕊44😡38😭26🥰6😢6😱3
“ ካሜራ ይዛ አንገቷን በመስኮት አውጥታ ነበር ”- የኮንታ ዞን ጸጥታ መምሪያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንታ ዞን ዛሬ በደረሰ የመኪና አደጋ የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን የካሜራ ባለሙያ ሕይወት መቀጠፉን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
አንድ ዞኑ ጸጥታ መምሪያ አካል በሰጡን ቃል፣ “ አንዲት ካሜራ ማን ለመግስታዊ የሥራ ጉዳይ ከዞን ወደ ወረዳ እየሄደች በአጋጣሚ ቀረጻ ላይ እያለች መኪና ተገልብጦ ነው የሞተችው ” ብለዋል።
የአደጋው ምክንያት ምን እንደሆነና ከሟቿ ባሻገር ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱ ሲጠየቁ፣ “ የቴክኒክ ችግር ይመስለኛል። የመንገድ፣ የቦታ ችግር አይደለም። የቴክኒክ ችግር ሳይሆን አይቀርም የሚል ስጋት አለ። ሌላ ሰው ብዙ የተጎዳ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ካሜራ ይዛ አንገቷን በመስኮት አውጥታ ነበር ” ብለው፣ አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ እንደደረሰም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ “ዛሬ ረፋድ እህታችን ወ/ሮ ቃልኪዳን መለሰ የኮንታ ዞን የመንግስት ኮሚኒዩኬሽን የሚዲያ ባለሙያ ለመንግስት ሥራ በሚታደርገው ጉዞ በደረሳት ድንገተኛ የመኪና እደጋ ሕይወቷ አልፏል ” ሲሉ አስታውቀዋል።
“ አደጋው ሲያጋጥም በቅርብ ርቀት ለነበርን ሐዘኑ በጣም ጥልቅ ነው። ፈጣሪ ነፍሷን በአፀደ ገነት ያኑርልን ” ብለው ለሟች ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል። “ በአደጋው የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የሥራ ባልደርቦቻችንም ፈጣሪ ፈጥንነው እንዲያገግሙ ብርታቱን ይስጣችው ”ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

😢1.36K❤849😭300💔110🕊63😱16🥰13🙏12😡12👏11🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የ2017 ዓ/ም የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየተላከ ይገኛል። ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየላከ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋማቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው ውጤታቸውን በሬጅስትራር በኩል እንዲያዩ መልዕክት እያስተላለፉ ናቸው። ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከልም ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን…
#ExitExamResult
“ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” - ኤባ መጂና (ዶ/ር)
በዘንድሮው መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ መጂና (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽም “ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስንት ተማሪዎች አለፉ ? ስንት ተማሪዎች ወደቁ ? የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አናላይሲሱ እየተሰራ እንደሆነ፣ ነገ ማብራሪያ እንደሚሰጡን መሪ ሥራ አስፈጻሚው የገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ውጤቱ ስለተለቀቀ ተማሪዎች ማየት እንደሚችሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ከዚህ ቀደም ውጤት በሚለቀቅበት በተለመደው ድረ ገጽ ውጤት ማየት እንደሚቻል መሆኑን ጠቁመዋል። “ ውጤት የሚታየው ያው ከዚህ በፊት በነበረው ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት በበኩሉ፣ ተማሪዎች እያዩ መሆኑን፣ ማለፊያው 50% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።
https://result.ethernet.edu.et

❤1.4K😭179🙏91😡63🤔47🕊39🥰30😢30👏29😱28💔5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በነፃ ይመዝገቡ !
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo
ከመስመር እስከ ከባድ መሳሪያ፣ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ እስከ የስልጣን መፍትሄዎች፣ ለየትኛውም የኮንስትራክሽን እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችዎ የሚፈልጉትን ሁሉ በአንድ ቦታ ያግኙ። Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo የሚያስተናግዱት እዚህ ነው።ከየትኛውም ዓለም አቀፍ አገር የመጡ 180+ ባለስልጣን ብራንዶችን በአንድ ጣቢያ ይያዙ፤ ፕሮጀክቶችዎን ለማንቃት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችንና መፍትሄዎችን ያግኙ።አሁኑኑ በነፃ ይመዝገቡ:👉 https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia📅 ሰኔ 19–21፣ 2017 ዓ.ም (26–28 June 2025)📍 ሚሊኒየም አዳራሽ፣ አዲስ አበባ

❤240🤔9🙏8🕊5😢4😡4😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም፤ የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው ነው " - የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዑሽ (ዶ/ር) የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ሙሉ ሆኖ ባለመተግበሩ 1.2 ሚሊዮን ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳልተመለሱ ገልጹ። " የጦርነቱ ጦስ ዛሬያችን ብቻ ሳይሆን ነገያችንም እያጨለመው…
#Tigray
" የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " - አቶ አማኒኤል አሰፋ
በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙበት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።
ዛሬ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም ለሦስተኛ ቀን የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ መሰረት የመንግስት ሠራተኞች ስራቸውን በማቆም የታደሙበት ነው።
በሰልፉ ማጠቃለያ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቁ በርካታ መልእክቶች ተደምጠውበታል።
በሰልፉ መልእክት ያስተላለፉት የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አማኒኤል አሰፋ " የተደፈረው ግዛትና ተፈናቃዮች በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የሚደረገው ሁሉን አይነት ጥረት ካልተሳካ ዝም ብሎ የሚተው እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ብለዋል።
" ከተፈረመ ሦስት ዓመት ሊሞላ ወራት የቀሩት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተኩስ ከማቆም በዘለለ የተፈናቃዮች ደህንነት ማረጋገጥ አቅቶታል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" የትግራይ ህዝብ ሉአላዊ ግዛቱ ተቀምቶ ፣ ከቄዩ ተፈናቅሎ ተሰዶ በማያቋርጥ መከራ ተዘፍቆ ይገኛል " ያሉት ምክትል ፕሬዜዳንቱ " የፌደራል መንግስት በጦርነት ያላሳካው ድል በፕሪቶሪያ ውል ስምምነት ስም የተከፋፈለች ትግራይ እንድትኖር የዲሞግራፊ ለውጥ ለመቀየር እየተጠቀመበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
" የፌደራል መንግስት ለሰላም ዋጋ ሰጥቶ እንዲሰራ ደጋሜ ጥሪ እናቀርባለን " ያሉት አቶ አማኒኤል " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች የኩርድ ህዝቦች ዕጣ ፈንታ እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር መቆም አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ የሦስት ቀናት ማጠቃለያ ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት
- የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አመራርና ምእመናንና ምእመናት
- የሚድያ ባለሙያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች
- ተማሪዎች
- መምህራንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸው ተነግሯል።
የፌዴራል መንግሥት ሁሉም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፅና ፍላጎ እንዳለው በተደጋጋሚ መግለጹ አይዘነጋም።
የቀድሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም አሁን ላይ በትግራይ ትርምስ እንዲፈጠር እየሰራ ያለው የህወሓት አንጃ ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ ፍጆታ በመጠቀም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዳይመለሱ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበው ነበር።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትላንት በስቲያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትግራይ ተፈናቃዮችን ጉዳይ አንስተው ነበር።
" የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ በሚመለከት 100% ዝግጁ ነን እኛ 100% ፤ ነበርን ነን ፤ ራያ እኮ መልሰናል ፤ ራያ ተመልሰዋል የተፈናቀሉ ሰዎች ወልቃይትም እንደዛ አይነት ፍላጎት ነው ያለን። ከጊዜያዊ መንግሥቱ ጋር እየተነጋገርን ነው በእኛ በኩል እነኚያ ዜጎች ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ሳይሆኑ ቦታቸው ቢመለሱ ከማንም በላይ ኢትዮጵያ ታተርፋለች " ብለዋል።
" በእኛ በኩል አንዴ አይደለም 10 ጊዜ እቅድ ያወጣነው ፤ የትግራይ ጉዳይ ብዙ የማይገደን ፣ የማያሳስበን አይመሳላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።
" ያስጨነቀንን ጉዳይ በግልጽ እንድታውቁት ግን ትንሽ ዘመን ተቀይሯል የዛሬ 4 አመት 5 አመት የነበረን የውጊያ አቅም የነበረን ቴክኖሎጂ እና ዛሬ ትንሽ ይለያያል። በተቻለ መጠን maximum ውጊያ ብናስቀር ይሻላል ለምን ? እንደምታውቁት በባለፈው ውጊያ ያኔም ተናግሪያለሁ ከትግራይ ወጣቶች ከትግራይ እናቶች በላይ የተጎዳ ሰው የለም ፤ የሚያስገድሉ ሰዎች ይፎክራሉ አስገዳዮች ይፎክራሉ ሟቾች ግን ጉዳዩን ሳያውቁ ይጠፋሉ ያ እንዳይፈጠር ነው maximum ትዕግስት የምናደርገው " ብለዋል።
" ትግራይ ውስጥ ሊመጣ የሚገባው ልማት ፤ ሊሰራ የሚገባው ስራ በበቂ ተሰርቷል ብለን አናምንም እንጂ የሚደረጉ ሙከራዎች unconstitutional ልምምዶች እንዳሉ ስለማናውቅ አይደለም በደምብ ነው የምናየው " ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

❤991😡103🕊64🤔30😭25😢12🥰10🙏9😱6👏5💔4
" የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል ! "
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የ8 ዓመቷ ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በመፈጸምና በመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የግብረስጋ ድፍረት ወእና ግድያ ወንጀል መዝገብ ተከፍቶባቸዉ በሰውና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ የቅጣት ዉሳኔ እንደተላለፈባቸው የሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰረድተዋል።
ዳዊት ሻንቆ እና ታምራት ኦሳ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በሶዶ ከተማ ' ፋና ዎንባ ' ተብሎ ከሚጠራዉ አከባቢ ሰኔ 16/ 2016 ዓ/ም የ8 ዓመት ልጅን ከቤት አታለው ወደ ጫካ በመውሰድ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ከፈጸሙ በኋላ ወዲያዉኑ ሕይወቷ ያልፋል።
በዚህም ጊዜ እራሷን ያጠፋች ለማስመሰል በአከባቢዉ በሚገኝ አንድ ኦና ቤት በማስገባት አስክሬኗን በማንጠልጠል ከአከባቢው መሠወራቸው በፖሊስ ምርመራ መረጋገጡን አዛዡ ገልፀዋል።
የወንጀል ድርጊቱ ጥቆማ የደረሰዉ የሶዶ ከተማ ፖሊስ ግለሰቦቹን በጠንካራ ክትትል ይይዛቸዋል።
የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለዐቃቤ ሕግ ያቀርባል።
ጉዳያን የተከታተለው የወላይታ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ግለሰቦቹን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ም/ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahEthiopia

❤872😭443👏122😡112🙏46🕊22🥰7🤔7😱7💔7😢4