Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የመምህራን ጥቅም ባልተከበረበት ሁኔታ ውስጥ ለዚህ በቅተናል። የመምህራን የ17 ወራት ደሞዝ ሳይከፈል ለዛሬዋ ቀን ደርሰናል " - መቐለ ዩኒቨርሲቲ

መቐለ ዩኒቨርስቲ 31ኛ ዙር የምረቃ ስነ ስርዓቱን ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ/ም በሰማዕታት ሀውልት አካሂዷል።

ዩኒቨርስቲው በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፋና ሀጎስ (ዶ/ር)፣ " የመምህራን ጥቅም ባልተከበረበት ሁኔታ ለዚህ በቅተናል " ብለዋል።

" የመምህራን የ17 ወራት ደሞዝ ሳይከፈል ለዛሬዋ ቀን ደርሰናል " ሲሉም አክለዋል።

በመክፈቻ ንግግራቸው፣ " መቐለ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ቢኖርበትም፤ ከመንግስት የተሰጠው ተልዕኮ በላቀ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በመፈፀም ላይ ይገኛል " ሲሉም ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንቷ፣ " ከጦርነት ወቅት ጠባሳ ያን ሁሉ ተግዳሮት አልፋችሁ ለዚህ የደስታችሁ ቀን ያደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

መቐለ ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች እና ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 2,385 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል በመጀመሪያ የዲግሪ መርሃ ግብር 1,859፣ በሁለተኛ ዲግሪ 509 ተማሪዎች፣ በሦስተኛ ድግሪ ደግሞ 17 ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ከተመራቂዎቹ ውስጥ 600 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው የተባለ ሲሆን፣ በምረቃ መርሃ ግብሩ ከፍተኛ የክልል ባለሥልጣናትና የዩኒቨርስቲው አመራሮች ተገኝተዋል።

በትግራይ ክልል መምህራን የ17 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው በተደጋጋሚ ሲገልጹ የነበረ ሲሆን፣ ይህንኑ ጉዳይ ዩኒቨርሲቲውም በዛሬው የምረቃ መርሃ ግብር ወቅት አንስቶታል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ከአንድ አመት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " በትግራይ ክልል የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ አልተከፈለም። የአምስት ወሩን ክልሉ እከፍላለሁ ብሎ ነበር እስካሁን አልከፈለም " ማለቱ አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
549😢90🕊22😱13🤔12👏4😭4🥰3🙏3😡1
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶናልድ ትራምፕ ? ፕሬዜዳንት ትራምፕ: "ስምምነት እንዲደርሱ አድርጌ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች። ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት። በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም። ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። እንዴት እየሆነ…
#GERD🇪🇹

ዶናልድ ትራምፕ ?

ከዚህ ቀደም በነበራቸው የፕሬዝዳንትነት ስልጣን ዘመን " ግብፅ ግድቡን (የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን) ልታፈነዳው ትችላለች ፤ ግብፅ ግድቡን ታፈነዳዋለች ፤ ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ እንድትደርስ ብሞክርም ጥላ ወጥታለች በዚህ ምክንያት ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል " ሲሉ የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሁን ደግሞ ግድቡ ሊመረቅ ሲቃረብ " ግድቡን ፋይናንስ ያደረግነው እኛ ነን " ማለት ጀምረዋል።

ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው አሜሪካን በመሩበት የስልጣን ጊዜ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ " ኢትዮጵያና ግብፅ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አድርጌ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች። ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት። በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም " ብለው ነበር።

" ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። ስምምቱን አፍርሰዋል (ኢትዮጵያን) ።ግብጽ በዚህ ሁኔታ መኖር አትችልም። ልታፈነዳው ግብጽ ትችላለች፤ ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች " የሚል ንግግርም ተናግረው ነበር።

እኚሁ እራሳቸው ፕሬዚዳንት አሁን ደግሞ " ግድቡን ፋይናንስ አድርገናል " የሚል ነገር ይዘው መጥተዋል።

ፕሬዝደንቱ ትላንት ለሊት በትሩዝ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አንድ ፅሁፍ አጋርተው ነበር።

አጠቃላይ ፅሁፉ በተለያዩ ሀገራት ሰላም ስለማስፈን ስለሰሯቸው ስራዎች የሚያትትና ለሰሯቸው ስራዎች ግን የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆን እንዳልቻሉ በመግለጽ የሚያማርር ነው።

በዚህ ፅሁፋቸው " በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም እንዲፀና አድርጊያለሁ ፤ ግን የኖቤል የሰላም ሽልማት አልተሰጠኝም " ብለዋል።

የግብፅ እና ኢትዮጵያን ጉዳይ ያነሱትም በቀጥታ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሲሆን ትራምፕ " ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ግዙፍ ግድብ በጅልነት በአሜሪካ ፋይናንስ የተደረገ ነው ፤ ይኸው ግድብ ወደ ናይል የሚፈሰው ውሀ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ የሚያደርግ ነው " ብለዋል።

አወዛጋቢው ፕሬዚዳንት በተለያየ ጊዜ ምንም ማስረጃ የሌላቸውና ተጨባጭ ያልሆኑ መረጃዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከመነሻው ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በኢትዮጵያውያን ላብና ሃብት የደም ዋጋ ተከፍሎበት ጭምር በህዝብ መዋጮ፣ መንግሥት በሚመድበው በጀት የተገነባ እንደሆነ የዓለም ህዝብ የሚያውቀው ነው።

ይልቅም ግብፅ ግድቡን ለማስቆም በኢትዮጵያ ሰላም እንዳይኖር በምትሰራው ስራ፣ በምትሸርበው ሴራና ሀሰተኛ ውንጀላ እንዲሁም በገንዘብ ጭምር የአሜሪካ ባለስልጣናትን በመደደል ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲፈጠር ስታደርግ ቆይቷል።

ለዚህም ዋና ማሳያ ከወራት በፊት የ11 ዓመታት እስር የተፈረደባቸው የዶናልድ ትራምፕ ሀገር ሰው የአሜሪካው ባለልስጣንና ተፅእኖ ፈጣሪው ሴናተር ቦብ ሜንዴዝ ናቸው።

ሰውየው ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብፅ ጉቦ ሲበሉ ፤ የግብፅን ጥቅም ለማስከበር ከግብፅ ብዙ ብር ሲቀበሉ እንደነበር ተረጋግጦና በሌሎችም የሙስና ወንጀሎች የ11 ዓመታት እስር በሀገራቸው ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው ነበር።

ሜኔንዴዝ የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት ውስጥ የሰሩ ፤ በፈረንጆቹ 2020 ላይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር (ኢትዮጵያ፣ ግብፅ ፣ ሱዳን) ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የተደረጉ ሰው ናቸው።

በወቅቱም ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና ሲያሳድሩ ነበር። ይህን ያደረጉትም ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነው።

የሶስትዮሽ ድርድሩ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን እንዲሄድ ያደረጉት ደግሞ በወቅቱ በመጀመሪያው የፕሬዝዳንት ስልጣን ዘመናቸው ላይ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

በዋሸንግተን በተደረጉት ተከታታይ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ በጫና ወደ ስምምነት እንድትመጣ ግፊት ሲደረግ እንደነበር እና ኢትዮጵያ ስምምነቱን " አልፈርምም " በሚል አቋም መጽናቷ የሚታወቅ ነው።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመስከረም ወር ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

NB. ከላይ የተያያዘው ቪድዮ ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ስለግድቡ ሲናገሩት የነበረ ነው ፤ " ግብፅ ግድቡን ታፈነዳዋለች " እያሉ። ቪድዮው ለታሪክ ጭምር ተሰንዶ የሚቀመጥ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12.94K😡513🤔123👏87🕊66😭48🙏40😱35🥰30💔30😢5
#SafaricomEthiopia

🌐 ቅመም ማይፋይ በአዲስ ዋጋ መጥቷል 🙌

💨 እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰  ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት

#SafaricomEthiopia
251😡22💔9🙏8😢4😭3👏1🕊1
" ሕጋዊ አካሄዱን ተከትለው አይደለም ያገዱን። ከጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ጋር የተያያዙ ድጋፎችን ስንሰጥ ስለቆየን ነው " - ማኀበሩ

ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መታገዱን የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገረ።

የማኀበሩ ም/ፕሬዚዳንት አቶ መለሰ ባታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" ማኀበሩ ታግዷል። ከመታገዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባለስልጣኑ ደውሎ ስለማኀበራችሁ እንድንወያይ ብሎን ነበር። ማኀበራችን ለጤና ባለሙያዎች ድምፅ በመሆኑ ሊያግዙንና እንዴት አብረን መስራት እንዳለብን ሊያናግሩን መስሎን ነበር።

ተቋሙ ማኀበሩን ለማገዝ ነው የተቋቋመው በሚል እምነት ነበረን ሄድን፤ ስንሄድ ግን የጠበቅነው አይደለም የጠበቀን።

ባለስልጣኑ የገለጸልን ' መግለጫ ማውጣት ማቆም ' አለባችሁ ብሎ ነው።

ማኀበሩን ለማገድ ባለስልጣኑ ያነሳውን የተወሰነ ነጥብ አለ። አንደኛው ‘የተሟላ ጠቅላላ ጉባኤ አላካሄዳችሁም የሚል ነው (ተጠርተን ስለነበር እሱን ማሟላታችንን የሚያሳይ ሰጥተናቸዋል ፋይሉ አለ)።

ሌላው  'ሐሰተኛ ማህተም ተጠቅማችኋል ፤ ሁለተኛ ማህተም አስቀርፃችኋል’ ነው የሚለው (ያስቀረጽነው ሁለተኛ ማህተም የለም)። ይሄም ክስ 2015 ዓ/ም የተነሳ ነበር። ምንም የተቀረጸ ሐሰተኛ ማህተም እምደሌለ ተማምነን የተዘጋ ፋይል ነበር።

ሌላው አንዳንድ ጉዳዮችን ጨምረው ነው እንደ አዲስ ያነሱት ተነጋግረን የቆዩ ጉዳዮችን እንጂ እንደ አዲስ ክስ አልነቀረበም፤ ማህበሩም ቀጥሎ ነበር።

ችግር ከነበረበት ሁለት ዓመት ሙሉ ጸጥ ማለት አልነበረባቸውም፤ ችግር ነው ብለው ካሰቡ ሁለት ዓመት ሙሉ እንዴት ዝም አሉ?

ከእገዳው በፊት በቃል ደረጃ ‘ የውስጥ ችግራችሁን ሳታስተካክሉ እንዴት መግለጫ ታወጣላችሁ ? ከጽንፈኛ ኃይል ጋር በመሆን ' በሚል ባለስልጣኑ አናግሮናል።

እኛም ፣ ከማንኛውን ጽንፈኛ ጋር ግንኙነት የለንም። ጤና ባለሙያዎችን ሰፓርት አድርገናል። ጥያቄው የባለሙያዎች ነው፤ እኛም እንደ ማህበር አንስተነዋል። ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያለሰለሰ ሚና ተጫውተናል የሚል ምላሽ ሰጥተን ነበር።

' መግለጫ እንዳታወጡ ' ብለውን ነገር ግን ማኀበሩ እንደማይታገድ ተነግሮን ነበር። በማግስቱ ደብዳቤ ውሰድ ተባልኩ። ደብዳቤውን ሳየው 'ታግዷል' የሚል ነው፤ አብሮ የተያያዘ ደብዳቤም ነበር ከዚያ በፊት ያልሰጡን። ማስጠንቀቂያ ቀደሞ ብሎ ነው የሚሰጠው ፋይል ላይ አይያያዝም። ከሰስፔንሽን በፊት ቀድመው ማስጠንቀቂያ ሊሰጡን ይገባል ነበር።

የእግዱን እንጂ ቀድሞ ያልተሰጠንን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደማንቀበል ሞግተናል ምክንያቱም '/ማስጠንቀቂያም ሰጥተናቸው ነበር ቀደም ብለን ' በማለት ይጠቀሙበት ነበር። ስለዚህ ሕጋዊ አካሄዱን ተከትለው አይደለም  ያገዱን። ከጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ጋር የተያያዙ ድጋፎችን ስንሰጥ ስለቆየን ነው። " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለሪፖርተር በሰጠው ቃል፣ " እገዳው ሕግን ተከትሎ የተፈጸመ መሆን አለመሆኑ ክትትል ይደረጋል " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የባለስልጣኑ ደብዳቤ በዝርዝር የተለያዩ ምክንያቶችን በማስቀመጥ ማኀበሩን እግድ እንደተጣለበት ያስረዳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ጋር ሲደውል ስልካቸው ባለመስራቱ፤ ከባለስልጣኑ አቶ ተሾመ የተባሉ አካል ጋርም ደውሎ ስልክ ባለመንሳታቸውና የፅሑፍ መልዕክት ቢላክላቸውም ባለመመለሳቸው የባስልጣኑን ምላሽ ማካተት አልተቻለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ 
#TikvahEthiopiaFamilyAA
 
@tikvahethiopia
616💔108😡95😭34🙏10😱6🕊5👏3🤔3🥰1😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የ2017 ዓ/ም የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየተላከ ይገኛል። ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየላከ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋማቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው ውጤታቸውን በሬጅስትራር በኩል እንዲያዩ መልዕክት እያስተላለፉ ናቸው። ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከልም ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን…
" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የፈተና አገልግሎት ክፍያ (Exam Service Payment) የከፈሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት ዛሬ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የተለቀቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

በዚህም የፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈሉ ተቋማት የተፈታኞቻቸውን ውጤት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን፤ የግል ተፈታኞች ወደ ተማሩበት ተቋም በመሔድ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ 

Via @tikvahuniversity
379🤔54🙏45💔29🕊23😢13😭12😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት የዋጋ ጭማሪ ፕሮፖዛል ላይከወላጆች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለ ባለሥልጣኑ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ 1,227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን እስከ 65 በመቶ ድረስ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ እንደተፈቀደለቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ጭማሪውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ዙሪያ ላይ የግል ትምህርት ቤቶች ወላጆችን ለማወያየት ሲጠሩ ወላጆች በመገኘት ሊወያዩ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሠራር ሥርዓት ደንብ ቁጥር 194/2017 በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀ መሆኑን አስታውሶ ደንቡን መሰረት በማድረግ መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት መደረጉን ገልጿል።

ደንቡ ያስቀመጣቸው የክፍያ ዋጋ ጭማሪ ጣሪያዎች መሰረት ትምህርት ቤቶች ወላጆችን በመጥራት ግልጽነት የመፍጠር ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋልም ብሏል፡፡

በውይይቱ መሰረትም የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ ወላጆችና ት/ቤቶች በጋራ በሀሳቡ ላይ በመወያየትና በመመካከር የሚወስኑ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት የዋጋ ጭማሪ ፕሮፖዛል ላይ ከወላጆች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለ ሪፖርቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የሚቀርብና በባለስልጣኑ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል ሲል ትምህርት ቢሮው አሳውቋል፡፡

(የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ጣሪያ ምስል ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
858😭184😡92👏35🙏25🤔17🕊15🥰10💔9
" በነዳጅ ማደያዎች ላይ ያልተገባ ወረፋ እየተስተዋለ ያለው በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ የተሳሳተ መረጃ ነው " - ሚኒስቴሩ

" የድጎማም ሆነ የታክስ ክፍያ አይኖም !! "


የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነዳጅ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚህም " መንግስት በሀገር ውስጥ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ያደርግ የነበረውን የጥቅል ድጎማ በሂደት በመቀነስ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም. መጨረሻ ከድጎማ ሥርዓት በመውጣት በዓለም ገበያ ልክ እንዲሆን አድርጎ ነበር " ብሏል።

" ሆኖም ግን መንግስት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ መጠን በማደጉ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል " ሲል ገልጿል።

" ይህ በመሆኑ መንግስት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ አንዳይጎዳ በማሰብ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የጥቅል ድጎማ አድርጎ በማቅረብ ላይ ነበር " ብሏል።

" ሆኖም ግን ከጎሮቤት ሃገራት ጋር ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ልዩነቱ ሰፊ ስለሆነ ለኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ግብይት እንዲጋለጥ ከማድረጉ በተጨማሪ በመንግስት ላይ ያለው ጫና በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ በሂደት ከድጎማ ለመውጣት ባለፉት 11 ወራት ሰፋፊ ስራዎች ተከናውነዋል " ሲል አስረድቷል።

" ይህን ተከትሎ ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ነጭ ናፍጣና ሌሎች የነዳጅ ውጤቶችን ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የጥቅል ድጎማውን በማስቀረት በዓለም የነዳጅ ዋጋ መሰረት እንዲሆን ተደርጓል " ሲል አሳውቋል።

ነዳጅ ከድጎማ መውጣቱንና በዓለም የነዳጅ ዋጋ መሰረትም እንደሚሆን ነው ያብራራው።

" ነገር ግን በያዝነው ሳምንት ውስጥ መንግስት ከድጎማው እንዳልወጣና ተጨማሪ የታክስ ክፍያዎችን አንደሚተገብር  በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳቱ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ በነዳጅ ማደያዎች ላይ ያልተገባ ወረፋ እየተስተዋለ ነው " ብሏል።

ሚኒስቴሩ " ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎቹ የሚናፈሰውን ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑን ይገንዘብ " ያለ ሲሆን " የድጎማም ሆነ የታክስ ክፍያ እንደማይኖርና ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን ተገንዝቦ ተረጋግቶ እንዲገበያይ " ሲል ገልጿል።

ከመጭው ሐምሌ ወር ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዓለም አቀፉ ዋጋ መሰረት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፤ ላለፉት ወራት ቀስ በቀስ የነዳጅ ድጎማን እያነሳ ያለው መንግስት ሙሉ በሙሉ ድጎማውን ከማቆም ባሻገር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስከፍል ማቀዱ ከሰሞኑን ተዘግቦ ነበር።

ይህ መረጃም ዋቢ የተደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ለተወካዮች ምክር ቤት ካቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ከሚያብራራ ሰነድ ላይ ነው።

መንግሥት ከነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 15 በመቶ ቫት በማስከፈል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱ ተዘግቧል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ግን በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን በመግለፅ የድጎማም ይሁን የታክስ ክፍያ እንደማይኖር አሳውቋል።

#ነዳጅ

@tikvahethiopia
1.47K😡333🤔68😢59🙏38😭34🕊19💔14😱10🥰9👏5
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

በዘንድሮው ቶምቦላ ሁሉ ሙሉ ነው።
ባለ 3 መኝታ በየወሩ ለ 3 ዓመት የሚቆይ 60ሺህ ብር ሽልማት ጋር እንድሁም ባለ 2 መኝታው ደግሞ ለ2 ዓመት የሚቆይ በየወሩ 40ሺህ ብር ሽልማት ጋር።

ቮልስዋገን ID-6 እና BYD SUV መኪና የግልዎ አድርገው ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ጋር ይንበሸበሻሉ።
ዕድልዎን ይሞክሩ!
ሰኔ 29 የሚወጣው  ቶምቦላ ሎተሪ በዲጂታል https://www.ethiolottery.et ላይ እና በቴሌ ብር ሱፐር አፕ አሁኑኑ ይግዙ!  

ለበለጠ መረጃ
​በ +251977717272፣
​+251950189808 እና
​ +251950199808 ይደውሉ!
241🙏26😭10😢5🥰3👏2
ሚዛን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት !

ክረምቱን በምን ለማሳለፍ አቅደዋል ?

የቴክኖሎጂ ኮርሶችንና የኮምፒዩተር ስልጠናዎችን ከፈለጉ፤ 9ኛ ዙር ምዝገባና የክረምት የቡትካምፕ ኮርሶች ምዝገባ ጀምረናል።

ተቋማችን አጫጭር ስልጠናዎችን በመረጡት ቀንና ሰአት በብቁ አሰልጣኞች በመስጠት ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ቋንቋና ቲቶሪያል ጀምረናል፤ ለጀማሪዎችና ለታዳጊዎች መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና (Basic Computer Skills) አለን።

የመክፈል አቅም ለሌላቸው በክሬዲት (ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር/ዱቤ) መማር የሚችሉበት እድል አመቻችተናል።

ስለ ፓኬጆቹ፣ እያንዳንዱ ኮርስ የስንት ወር እንደሆነና ስለ ኮርሱ ምንነት ማብራሪያ፣ ስለ ክፍያው እንድሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በቻነላችን ያግኙ https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/436

ለመመዝገብ፦ http://www.mizantechinstitute.com

ከግል የትምህርት ዝግጅታችሁ ጋር ምን መማር እንዳለባችሁ በነፃ እናማክራለን። በአካል ወይም በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio አግኙን።

🗺በአካል: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ፣ 0987143030

በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን አገኙን፦
🌐👍🌐📱▶️🌐📧 🗺
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
214🙏13😡5😭4👏2🥰1🕊1
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በቀጥታ ወደ ጦርነቱ ትገባ ይሁን ? እስራኤል በኢራን ላይ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ ስለምትሳተፍበት ሁኔታ ለመወያየት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር አድርገዋል። አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ በቆየው ስብሰባ ላይ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማዕከላት ላይ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ውስጥ አሜሪካ መሳትፍ እንዳለባት…
#Iran #USA

" ዛሬ ማለዳ የተከሰተው ጥቃት እጅግ አሳፋሪ እና ማቆሚያ የሌለው መዘዝ የሚያስከትል ነው " - የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

በእስራኤል እና ኢራን መካከል የተነሳው ጦርነት ተባብሶ አሜሪካም ተሳታፊ ሆናበታለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በጦርነቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ቢናገሩም ለሊቱን የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት በቦምብ ሲደበድቡ አንግተዋል።

አሜሪካ ኢራን ውስጥ በሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ተቋማት ፦
- ናታንዝ፣
- ኢስፋሃን
- እና ፎርዶ ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብላለች።

ፎርዶ በተራራዎች ውስጥ የሚገኝ እጅግ በጣም ለመድረስ አስቸጋሪ የሆነ ተቋም እንደሆነ ይታመናል።

ትራምፕ በቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር ዘመቻውን " አስደናቂ ወታደራዊ ስኬት " ሲሉ አሞካሽተው፣ ቴህራን በፍጥነት ሰላም እንድትፈጥር ወይም " ከዚህ የባሰ " ጥቃት እንደሚደርስባት አስጠንቅቀዋል።

አሜሪካ ቢ-2 አውሮፕላኖቿን በመጠቀም ወደ መሬት ሰርስረው የሚገቡ ቦምቦችን በመጠቀም ድብደባ መፈፀሟ የተገለፀ ሲሆን የአገሪቱ መከላከያ በጉዳዩ ላይ ዛሬ መግለጫ ሊሰጥ ይችላል።

የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ፎርዶ በከፊል " በጠላት ጥቃት ተፈጽሞበታል " ብለዋል። ያን ያህል የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ነው እየገለጹ ያሉት።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰይድ አባስ አራግቺ በበኩላቸው የአሜሪካን ጥቃት " አስከፊ " ሲሉ አውግዘዋል።

ኢራን " ሉዓላዊነቷን ለመጠበቅ ሁሉንም አማራጮች እንደምትመለከት " ተናግረዋል።

" ዛሬ ማለዳ የተከሰተው ጥቃት እጅግ አሳፋሪ እና ማቆሚያ የሌለው መዘዝ የሚያስከትል ነው። እያንዳንዱ እና ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት በዚህ እጅግ አደገኛ፣ ሕገወጥ እና የወንጀል ባህሪ ሊደናገጡ ይገባል " ብለዋል።

" አሜሪካ ከባድ ጥሰት ፈጽማለች " ሲሉ ኮንነዋል።

ቴህራን ቀደም ሲል አሜሪካ በሁለቱ አገራት ግጭት ውስጥ ጣልቃ የምትገባ ከሆነ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙየአሜሪካን ጦር ሠፈሮች ላይ ጥቃት እንደምታደርስ አስጠንቅቃለች።

እስራኤል በአሜሪካን ጥቃት መደሰቷን የገለፀች ሲሆን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ " ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ " እና " የታሪክን ሂደት የሚለውጥ " ሲሉ አወድሰዋል።

በአሜሪካ ሪፐብሊካኖች የትራምፕን እርምጃ ሲያወድሱ ዲሞክራቶች ደግሞ አሜሪካ ወደ ሌላ " ማብቅያ ወደሌለው " ጦርነት እየገባች ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል ኢራን እስራኤን በሚሳኤል የደበደበች ሲሆን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን 11 ሰዎች መጎዳታቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ገልጸዋል።

መረጃው የቢቢሲና ሲኤንኤን ነው።

@tikvahethiopia
1.76K😭311🕊176😡95👏39🤔33💔27😱16🙏13😢12🥰11
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ፤ ነዳጅ እያለ ዋጋ ይጨምራል በሚል እሳቤ ' የለም ' በሚሉ ማደያዎች ላይ  እርምጃ እንደሚወሰድ ገለጹ።

" አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ' ነዳጅ ይጨምራል ' በሚል አገልግሎት አቁመዋል። ነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል።

መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ ከነዳጅ ድጎማ መውጣቱን አመልክተዋል። የነዳጅ ዋጋም በዓለም የነዳጅ ገበያ እንደሚወሰን ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ተንቀሳቅሶ እንደተመለከተው በተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች " ቤንዚን የለም ፤ ናፍጣ የለም " የሚሉ ፅሁፎች በብዛት ተለጥፎ አስተውሏል።

ነዳጅ ባለባቸው ማደያዎች ደግሞ ከፍተኛ ሰልፍ ነው ያለው።

@tikvahethiopia
1.25K😭117🙏94🕊67😡37💔31🤔29👏25😢25🥰21
2025/07/13 13:32:55
Back to Top
HTML Embed Code: