Telegram Web Link
" የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ መቀበል ማቆሟን በይፋ ታበስራለች " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

የ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገራት ባለሥልጣናት በተገኙበት መጀመሩን በልዩ መርሐግብር ይፋ ተደርጓል።

ባለፉት 6 አመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች 40 ቢሊየን በላይ መድረሳቸውን በመድረኩ ተገልጿል።

በዘንድሮ ክረምት የሚተከለውን ጨምሮ እስከሚቀጥለው አመት የአረንጓዴ አሻራ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ድረስ ከ53 ቢሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ ተብሏል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጀመሩን ያበሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) " በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያሳተፈ በአለም ትልቁ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ (ዶ/ር) ፥ " የአረንጓዴ አሻራ በሚቀጥለው ዓመት 50 ቢሊየን በላይ ችግኞችን በመትከል የሚጠናቀቅ ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።

"በ2011 ዓም የጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የዘንድሮውን ጨምሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን በሚቀጥለው የስምንተኛው ዙር መርሃ ግብር ይጠናቀቃል " ነው ያሉት።

" የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ መቀበል ማቆሟን በይፋ ታበስራለች " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የመክፈቻ መርሐግብር ላይ በይፋ ተናግረዋል።

በ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ነገ ችግኞችን መትከል በይፋ የሚጀመር ሲሆን በዘንድሮው ዓመት ከ7.5 ቢለየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ ተብሏል።።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሁሉም ዜጋ ከነገ ጀምሮ ወጥቶ ችግኝ እንዲተክል ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ባለፉት 6 ዓመታት ከተተከሉ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ውስጥ ከ 10 ቢሊየን በላይ (27.5 በመቶ) የሚሆኑት በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የተተከሉ ናቸው " - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትርና የአረንጓዴ አሻራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተገኙ ውጤቶችን ይፋ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያዊ በአፈር መሸርሸር ምክንያት ወንዞች በየአመቱ 1.9 ቢሊየን ቶን አፈር ወደ ጎረቤት ሃገራት ይወስዱ ነበር ያሉ ሲሆን ባለፉት ስድስት አመታት ቁጥሩን ወደ 208 ሚሊየን ቶን አፈር ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ከእርሻ መሬቶች በየዓመቱ 130 ቶን ሄክታር በዓመት ይሸረሸር የነበረውም በተመሳሳይ ወደ 54 ቶን ሄክታር በዓመት ዝቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

የደን ሽፋንን በሚመለከትም በ 2011 ዓም ከነበረበት 17.2 በመቶ በ 2016 ዓ.ም ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት። የችግኝ ጣቢያዎችም በ2011 ዓ.ም ከነበሩበት 45 ሺ ወደ 130 ሺህ በላይ ማደጉን ተመላክቷል።

የግብርና ሚኒስትሩ፥ " ባለፉት ስድስት አመታት ከተተከሉ ከ 40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ውስጥ ከ 10 ቢሊየን በላይ ይህም 27.5 በመቶ የሚሆነው በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የተተከሉ ናቸው " ብለዋል።

በዚህም በአባይ ተፋሰስ አከባቢዎች የነበረውን የደን ሽፋን ከ19 በመቶ በ2024 እ.ኤ.አ ወደ 25 በመቶ ማሳደግ መቻሉን አንስተዋል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የከርሰ ምድር ውሃ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጸዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩም ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው የተናገሩ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 63 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ 40 ቢሊዮን ችግኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል 40 ቢሊዮን ዶላር የአየር ንብረት ፋይናንስ ከሀገር ቤት (Public Finance / Domestic Climate Finance) አዋጥታለች።

ነገ በሚጀመረው የ 2017 ዓም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 7.5 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#መሰቦ

ፋብሪካው ጥሬ እቃ ከሚያገኝባቸው አከባቢ ማህበረሰብ በተከሰተው ችግር ምክንያት ስሚንቶ ማምረት ማቆሙ አስታወቀ። 

ፋብሪካው ተከሰተ ያለውን ችግር ከማብራራት ተቆጥበዋል።  

የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ በሰጠው መረጃ ፥ በኳሪ ሳይቱ ባጋጠመው ጊዚያዊ ችግር " ማምረት አቁሚያለሁ " ብሏል።

ፋብሪካው ችግሩ መቼና ? እንዴት ? እንደሚፈታ አስመልክቶ ያለው ነገር የለም።

" የፋብሪካው ምክንያት አሳማኝ አይደለም " በሚል የተቋወሙ አስተያየት ሰጪዎች " ማምረት አቁሚያለሁ የሚለው ከነጋዴዎች በመመሳጠር ገበያ ለማስወደድ ነው " ብለዋል።

የፋብሪካው ኮሙኒኬሽን ኮርፓሬት በሰጠው አስተያየት " ይህ ከእውነት የራቀ ውሸት ነው " ብሎታል።

" ፈጠራ " ሲል ያጣጣለው አስተያየቱን ፋብሪካውን ጥላሸት የሚቀቡ ያላቸውን ግለሰቦችና አካላት በህግ እንደሚጠይቅ አሳስቧል።

የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ጥሬ እቃ ከሚያገኝባቸው አከባቢ ማህበረሰብ ከሚያጋጥም ችግር ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ማምረት እንደሚያቆም ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
🔈#የአሽከርካሪዎችድምጽ

" በአንድ ሳምንት ሦስት አሽከርካሪዎች በሙቀት ሳቢያ ሞተዋል። ' ጂቡቲ ገብታችሁ ነው የምትመዘገቡት ' ስለሚባሉ ቀድመው ሂደው እስከ 40 ቀናት የሚቆዩበት አጋጣሚ አለ " - ማኀበሩ

የከባድ ተሽከርካሪ ሾፌሮች ግብዓት ጭነው የመመለሻ ጊዚያቸው ሲቃረብ ወደ ጅቡቲ ሊላኩ ቢገባም ቀድመው እንዲሄዱ ስለሚገደዱ ከ10 እስከ 40 ቀናት ሙቀት ላይ ስለሚቆዩ መኪናቸው ውስጥ በተኙበት በሙቀት ሳቢያ ሞተው እየተገኙ መሆኑን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በሳምንት ሦስት አሽከርካሪዎች በፀሐይ ሙቀት በጅቡቲ እንደሞቱ፣ አንዱ ሟች የኢንሹራንሳቸው አባል በመሆኑ የኢንሹራንስ ፕሮሰስ ሲያልቅ የሚገባውን እንደሚያገኝ ገልጾ፣ " አዋሽ ላይ ነው መኪናው ውስጥ ተኝቶ ጠዋት ሞቶ የተገኘው " ነው ያለው።

" ሁለቱ አሽከርካሪዎችም በአንድ ቀን ነው በመንገድ እያሉ መኪናቸው ላይ ተኝተው አድረው በሙቀት የሞቱት " ያለው ማኀበሩ፣ " በሳምንት ሦስት አሽከርካሪዎች በሙቀት ሳቢያ ሞተዋል " ብሏል።

" ' ጂቡቲ ገብታችሁ ነው የምትመዘገቡት' ስለሚባሉ ቀድመው ሄደው እስከ 40 ቀናት የሚቆዩበት አጋጣሚ አለ " ያለው ማኅበሩ " አንድ አሽከርካሪ ወረፋ ደርሶት ለመጫን ሦስት አራት፤ ቀናት ሲቀሩት ወደ መጫኛ ስፍራው ቢሄድ ቶሎ ጭኖ ሙቀቱ ሳይበላው ይመጣል " ሲልም አስገንዝቧል።

ማኀበሩ፣ የችግሩ መንስኤ ሹፌሮች ከመነሻቸው (አዲስ አበባ) እያሉ ከጂቡቲ የሚጭኑበትን ቀን (ወረፋቸውን) እንዲያውቁ ሳይደረግ እንዲሄዱ መገደዳቸው መሆኑን አስረድቷል።

መፍትሄው ምንድን ነው ?

ቅድሚያ ግብዓት የሚጭኑበት ቀን ለሾፌሮች ቢነገራቸውና የተወሰኑ ቀናት (የጂቡቲ መንገድ ሁለት ቀናት ነው ጉዞው) ቀደም ብሎ ተነግሯቸው በቶሎ ጭነው እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባ ማኅበሩ አስረድቷል።

" ነዳጅ በኢትዮጵያ በቀን ከ250 እስከ 270 ቦቴዎች ናቸው የሚጫኑት። ግን በአሁኑ ወቅት ከ2000 በላይ ቦቴዎች ቆመው ነው የሚታዩት። ባለሃብቶቹም፣ ካምፓኒዎቹም ሹፌሮቹን ቀድማችሁ ግቡ ነው የሚሏቸው። ጁቡቲ ሲገቡ ነው ለወረፋ የሚመዘግቧቸው " ብሏል።

ጂቡቲ ከሄዱ በኋላ ለመጫን እስከ 40 ቀናት ስለሚቆዩ ከሞቱ ባሻገር እስከ 40 ሺሕ ላላስፈላጊ ወጪ እየተዳረጉ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል።

በሌላ በኩል፣ ከወራት በፊት በአማራ ክልል ነዳጅ የጫነ ቦቴ በታጣቂዎች ተመትቶ ነዳጁ እንዲፈስ በተደረገበት ወቅት በጥይት የተመቱ ሾፌር ጥይቱ ከእግራቸው እንዳልወጣ ማኀበሩ ገልጿል።

በወቅቱ ታጣቂዎቹ፣ " ከመኪና አውርደው ነው በጥይት እግራቸውን የመቷቸው እግራቸው ውስጥ ጥይቶቹ አሉ " ሲልም ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahEthiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Big 5 Construct Ethiopia እና East Africa Infrastructure & Water Expo፣ ሌላ ስኬታማ የንግድ፣ የፈጠራ እና የልዩ ልዩ ምቹ ዕድሎች ቀንን በአዲስ አበባው ሚሊኒየም አዳራሽ አሳልፈዋል።
20+ ሀገራት የተውጣጡ ኢግዚቢሽን አቅራቢዎች፣ ዘመን አፈራሽ የሆኑ ምርቶቻቸውን፣ የቀጥታ የምርት ስኬታማነት ሙከራዎቻቸውን እና ሁነኛ የግንባታው ዘርፍ አማራጮቻቸውን ሲያስጎበኙ ውለዋል።
🚨በነገው የመጨረሻ የንግድ ትርዒቱ ቀን፣ እንኳን መቅረት - ማርፈድ ያስቆጫል!

በነጻ ይመዝገቡ : https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia
ዋሪት ፈርኒቸር

የቢን ባግ መቀመጫ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ያውቁ ኖሯል?
🛋 ሰውነትዎን በትክክል በመደገፍ ምቹ አቀማመጥን ይሰጣል
💪 የጡንቻ ህመምን ይቀንሳል
😴 ለመዝናናት፣ መጽሐፍ ለማንበብ አልያም ፊልም ለማየት ምርጥ ናቸው !

ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22 - ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* አዳማ - ሶረቲ ሞል * ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት * ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
*ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07
2025/07/06 08:03:23
Back to Top
HTML Embed Code: