Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም #የአረንጓዴ_አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡416334😭23🤔16🕊14👏11😱10💔7🙏5🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም #የአረንጓዴ_አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
#Ethiopia🌱

የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ።

በአጠቃላይ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል  ዕቅድ ተይዟል።

በዛሬው ዕለት በወንዝ ዳርቻ ልማት አንዱ ክፍል በሆነው በእንጦጦ ዙሪያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕረዚዳንት ካቲም ሼቲማን ጨምሮ የክልል አመራሮችና ሚኒስትሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ የሚስማማውን ችግኝ በሚስማማው ቦታ እንዲተከል ጥሪ አቅርበዋል።

የአረንጓዴ አሻራ በቀጣይ አመት ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በስምንት ዙር የችግኝ ተከላ መርኃግብር (የአረንጓዴ አሻራ ሲጠናቀቀ) የተከለቻቸውና የምትተክላቸው ችግኞች አጠቃላይ ብዛት 50 ቢሊዮን እንደሚደርሱ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
650😡396👏21😭19🕊15🤔14😱13🙏13💔6🥰3😢2
#Tigray

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ኣለም  ገ/ዋህድን በምክትል መአርግ የፕሬዜዳንት የፓለቲካዊ  ጉዳዮች አማካሪ አድርጎ ሾመ።

ሹመቱ በምርጫ ቦርድ የተሻረው ህወሓት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለውን ቦታ እጅግ ከፍ አድርጎታል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለው የተፎኳኳሪ ፓርቲዎች ቦታ ከ3 አይበልጥም።

ከሰኔ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) በምክትል ፕሬዜዳንት መአርግ የፓለቲካዊ ጉዳዮች አማካሪ ተደርገው የተሾሙት ኣለም  ገ/ዋህድ ፥ ከጦርነቱ በፊት እስከ አምና 2016 ዓ.ም ነሀሴ ተካሂዶ ህገ-ወጥ ነው የተባለው የህወሓት ጉባኤ ድረስ የድርጅቱ የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።

በተጨማሪ ከጦርነቱ በፊትና በኋላ ከ5ቱ የህወሓት የፓሊት ቢሮ አባላት አንዱ በመሆን ሰርተዋል።

በተካሄደው ጉባኤ ደግሞ ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ ወርደው የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ 'የተገፉ' ናቸው ተብሎ ሲነገርባቸው ቆይተዋል።

ከያዝነው ወር ጀምሮ ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ማግኘታቸውን ተከትሎ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት በሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በሚመራው ካቢኔ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ እንዲሆን አስችሎታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
556😡104🕊36😭16👏14🤔12🙏7🥰6😢5😱3
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃ. የተ. የግ. ማኅበር

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃ. የተ. የግ. ማኅበር፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው ሽልማቶች ውስጥ ስድስተኛ የሆነው ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በጅማ ከተማ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡

በጅማ ቆጬ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት ዕድለኛው አሸናፊ አቶ ዮሐንስ ካሳ፣ ሽልማታቸውን ሰኔ 21 ቀን 2017ዓ.ም. በጅማ ከተማ በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ ኃ. የተ. የግ. ማኅበር፣ የፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕ ምርቶቹን በድጋሚ ለገበያ ካቀረበ በኋላ የተለያዩ እና በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን ለደንበኞቹ አዘጋጅቶ ዕድለኛ አሸናፊዎችን በአስገራሚና አጓጊ ሽልማቶች በማንበሽበሽ ላይ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

#ሞሐ
421👏48😡12😢11🕊10🙏7🤔5😱1
2025/07/14 06:49:45
Back to Top
HTML Embed Code: