Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
“እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” - ባለስልጣኑ ➡️ከ2015 እስከ ሰኔ 24/2017 ዓ/ም በሥራ ላይ የ142 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል! የአዲስ አበባ ከተማ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2015 እስከ 24/10/2017 ዓ/ም ድረስ በመዲናዋ በ11ዱም…
ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።

እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።

ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።

ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።

ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡

እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡

(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
592😡113👏44🙏14😢13🤔10🕊10🥰8💔1
ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤት አንገባም ያሉ ነዋሪዎች !

" መንግስት መጥቶ ጥያቄያችንን ካለመለሰልን ወደ ቤት ላለመመለስ ወስነን ሜዳ ላይ ተሰብስበናል " - ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

" ሰሚ እስክናገኝ ወደ ቤታችን አንመለስም ! "


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ አከባቢ ነዋሪዎች " በአዲስ የመዋቅር ጥናት እና ልማታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወረዳዉ መንግስት እንዲያነጋግን ብንጠይቅም ተገቢዉን ምላሽ ባለማግኘታችን በአደባባይ ወጥተን ድምፃችንን ለማሰማት ተሰብስበናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የአከባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሀዋሳ ከተማ አዲስ የመዋቅር አደረጃጀት ጋር በተያያዘ የተናገሯቸው መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ሕዝቡ የወረዳው መንግስት ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ነገር ግን የሚያናግር አካል ባለመምጣቱ 18 የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ባለሃብቶችን ያካተተ የሕብረተሰቡ ተወካዮች ተሰይመዉ በየደረጃው የመንግስት አካላትን እንዲያነጋግሩ ቢላኩም ተገቢው ምላሽ ስላልተሰጣቸው ሕዝቡ ሜዳ ላይ ተሰብስቦ መዋሉን አስረድተዋል።

የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄ " ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ዶሬ ባፋኖ አከባቢ ያሉ አምስት ቀበሌያት በአዲስ መልክ ይዋቀራል በተባለዉ የሀዋሳ አንድ ክፍለ ከተማ ስር ተካተዋል " መባሉ ነዉ ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ " ይህ የወረዳዉን አቅም ያዳክመዋል የሚል ቅሬታ ሕዝቡ ዘንድ ፈጥሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዛሬዉ ዕለትም ' የሚያናግራችሁ የመንግስት አመራር ይመጣል ' ተብለን ቀኑን ሙሉ ብንጠበቅም እንደተባለው ባለመምጣቱ ሕዝቡ በነቅስ ወደ ወረዳ አስተዳዳሪዉ ቢሮ ሄዷል ' አመራሩ ተነጋግሮ ያነጋግራችኋል ' ተብለን ምላሽ ባለመምጣቱ ሕዝቡ ' የሚያነጋግረን የመንግስት አካል እስኪመጣ ወደ ቤታችን አንመለስም ' በማለት ምሽቱንም በአንድ ቦታ ላይ ተሰባስቦ ይገኛል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ባደረገዉ ሙከራ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊን በስልክ አግኝቷቸው ነበር። ግን " የወረዳ አስተዳዳሪ አነጋግሩ " በማለታቸዉ ወደ አስተዳዳሪዉ የእጅ ስልክ ደጋግመን ብንደዉልም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ምላሻቸው ሳይካተት ቀርቷል።

ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.03K👏124😭50😱43🕊30😢23🤔20🙏12🥰11😡10💔2
#SouthEthiopia

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የማሽንጋ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የወላይታ ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ወደ ገበያ እየሄዱ የነበሩ አራት አርሶአደሮችን የዉሃ ሙላቱ ወስዷቸዉ እንደነበር የገለፁት አቶ ዳዊት ሁለቱ በሕይወት መትረፋቸውን ሁለቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመሬት ናዳ ሰዎች እንደሞቱ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ከእዉነት የራቄ ነዉ ያሉት ኃላፊዉ ከሰሞኑ በዞኑ በየትኛውም ቦታ በመሬት ናዳ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በዛው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ አሪ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ዲሜገሮ ቀበሌ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ምሶሶ ለመትከል በቁፋሮ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ ሦስት ወጣቶች ወዲያውኑ መሞታቸውን የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዳጁ ጨነቀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የደረሰዉ በአከባቢው የከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ታዎር ለመትከል DCGG በተባለ ኮንትራክተር አማካኝነት በተቆፈሩ ጉድጓዶች የዝናብ ዉሃ መሙላቱን ተከትሎ ዉሃዉ በጄኔሬተር ፓንፕ እንዲወጣ ተደርጎ ሰራተኞች ግንባታ እየሰሩ በነበረበት የአፈር መደርመስ ተከስቶ እንደሆነ አስረድተዋል።

በአደጋው ሦስት ወጣቶች ሲሞቱ በሁለቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታዉቀዋል።

የሦስቱ ወጣቶች አስከሬን በእስካቫተር ተቆፍሮ መዉጣቱንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
😭625541💔44🕊30😢29🙏19👏13🤔12🥰10
#SafaricomEthiopia

በፈጣኑ እና በማይቆራረጠው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ BET-WiFi ከቤት እንስራ ውጤታማ እንሁን!
#SafaricomEthiopia
111🙏17😡13👏2😢1
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የጋዜጠኝነት የክረምት ስልጠና የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም ይጀመራል።    
በስልጠናው፦
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሖች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል፡፡

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram Tiktok Linkedin
124🙏4😭2
#Tinsae #IDEXX

ትንሳኤ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ከአይዴክስ (IDEXX) ላቦራቶሪስ ጋራ በጋራ በመሆን የውሃ ጥራት መመርመሪያ መሳሪያዎች ላይ ያተኮረ ዎርክሾፕ ከሰሞኑን አካሂዶ ነበር።

ወርክሾፑ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት ተሳታፊ እንደነበሩ ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" መሳሪያዎቹ እጅግ በጣም ቀላል፣ ጊዜ ቆጣቢና በቀላሉ በአጭር ጊዜ ስልጠና በቀላሉ ለመስራት የሚያስችሉ " ናቸው ያለ ሲሆን " በተለይ Tecta B4 እና Teta B6 የተባሉት መሳሪያዎች እጅግ ዘመናዊ ከእጅ ንኪኪ ውጪ የሆኑ፣ ባንድ ጊዜ አራት ወይም ስድስት ናሙናዎችን ለመመርመር የሚያስችሉና ውጤቱንም በኢሜል ለሚመለከተው አካል የመላክ አቅም ያላቸው " ናቸው ሲል ገልጧል።

" ይኼንን የመሳሰሉት መሳሪያዎች በስፋት ወደ ስራ በሚገቡበት ጊዜ የሀገሪቱን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና ተደራሽነት ከፍ በማድረግ በተለይም በውሃ ወለድ የሚመጡ በሽታዎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሱ ይሆናሉ " ብሏል።

ትንሳኤ ኢንተርናሽናል ከአይዴክስ (IDEXX) በተጨማሪ ሀክ (HACH) እና ሌሎች አለማቀፍ የውሃ መመርመሪያ አምራች ድርጂቶች ጋር ብቸኛ አቅራቢ በመሆን የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳለውና በዚህ ረገድ በሃገሪቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ያለ ተቋም መሆኑም አመልክቷል።

@tikvahethiopia
222🤔5🙏5🕊3🥰2😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ
(ለሚመለከተው አካል - አዲስ አበባ)

" በሰውና መኪና ላይ ወድቆ ጉዳት እንዳይደርስ መፍትሄ ይፈለግለት ! "

" ይህ በቪድዮው ላይ የምትመለከቱት የመብራት ኮንክሪት ፖል ታቹ ተበልቶ አልቆ ለመውደቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ከጎኑ ትራንስፎርመርንም አለ።

ቦታው ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር ነው ሲሆን ብዙ ሰው የሚመላለስበት መኪናም የሚንቀሳቀስበት ነው።

ፖሉ ወድቆ በሰው እና በመኪና ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት። ወቅቱም ክረምት በመሆኑ ዝናቡና ንፋሱ ኃይለኛነውና ፈጣን መፍትሄ ይፈለግለት። " - ዮሴፍ (ከአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
675🙏216👏40😭38🕊19😱14🤔3😡1
" ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል" - ፖሊስ

በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ የጅብ መንጋ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ስምዖን ለንበቦ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ገደማ የጅብ መንጋ በወረዳዉ ወይደ መላቶ ቀበሌ በሰዎች ላይ ጉዳት ሰንዝሮ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

በአከባቢው ከከተማ በቅርብ ርቀት ጥብቅ ደኖች መኖራቸውን የገለፁት ፖሊስ አዛዡ ጅቦች በጫካዉ ዉስጥ እንዳሉ ቢታወቅም እስካሁን በሰዉ ላይ ጉዳት አድርሰው እንደማያውቅና የትናንት ምሽቱ ጥቃት ድንገተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አዛዡ ገልጸው ማምሻዉን ጥንቃቄና ጥበቃ ሲደረግ ማደሩንና ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ የፀጥታ አባላት ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አሰሳ እያደረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
427😭151😢27😱24🙏23🤔11🕊10🥰8👏8
2025/07/13 20:44:56
Back to Top
HTML Embed Code: