Telegram Web Link
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የረቀቀው የአጠቃላይ ትምህርት ህግ የህፃናት የመማር መብትን የሚያረጋግጥ ነው፡- ትምህርት ሚኒስቴር፡፡
------------------------------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን የመማር መብትና ትምህርት የመከታተል ግዴታን ያካተተ ረቂቅ ህግ አዘጋጅቷል፡፡

የትምህርት ረቂቅ ህጉ የአጠቃላይ ትምህርት ተሳትፎን በማሳደግ ተማሪዎች አስፈላጊውን መሠረታዊ ዕውቀት፤ ክህሎትና አመለካከት ጨብጠው መልካም ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡

በረቂቅ ህጉ ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ህጻን በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ትምህርትን በነፃ የመማር መብት እንዳለውና ትምህርቱንም የመከታተል ግዴታ ያለበት ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ደግሞ በነፃ እንዲማር ይደነግጋል፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጁ ወይም የሚያስተዳድረው ልጅ ወደ ትምህርት ቤት የመላክና ትምህርቱን እንዲከታተል የማድረግ ግዴታ እንዳለበት በረቂቅ ህጉ ተመላክቷል፡፡

ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያለማቋረጥ መከታተላቸውን ማረጋገጥ ደግሞ የትምህርት ቤቱ ግዴታ ነው፡፡

የህፃናትን የመማር መብት የሚያረጋግጠው ይህ ረቂቅ ህግ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን በሚመለከተው አካል ሲፀድቅ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የሸገር ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።
................................
የትምህርት ሚኒስቴራ አመራሮች እና ሰራተኞች በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል የሸገር ፕሮጀክትን እና የ እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጅ ) ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በጋራ በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የሸገር ፕሮጀክትንና እንጦጦ ፓርክን በተመለከቱበት ወቅት "በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት የተሰሩት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ግዙፍ ስራዎችን መስራት እንደሚቻል የሚያሳይ ነው" ብለዋል።

የዚህ ዓይነቱ ፕሮጀክት ሰው "ማድረግ እችላለሁ" የሚል ብሩህ ራዕይ እንዲኖረው ያደርጋል ነው ያሉት።

አዲስ አበባ ውስጥ የታየው ይህው ስራ በ45ሺህ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ እናደርጋለን ያሉት ሚኒስትሩ ትምህርት ቤቶቹ በራስ አቅምና በውስን ወጪ ንፁህና ውብ ስራዎችን መስራት እንደሚችሉ ማወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።

"ሁሉም ነገር የሚቻል እንደሆነ ከፕሮጀክቶቹ ተምረናል፤ የ12ኛ ክፍል ፈተናም በኦንላይን ማከናወን እንደሚቻል ማሳያዎች ሆነዋል እኛም ዝግጁ ነን" ሲሉ ተደምጠዋል።

በኢትዮጵያ 3ሺህ 5መቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጅነር ጌታሁን ተማሪዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የሚማሩና ሙያዊ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆ እየተሰራ ነው ብለዋል።
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,326 የላብራቶሪ ምርመራ 1,336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 370 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 34,058 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 600 ደርሷል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13,308 ደርሷል። በፅኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 255 ደርሷል፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,456 የላብራቶሪ ምርመራ 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 228 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 35,836 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 620 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 13,536 ደርሷል።
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 23,035 የላብራቶሪ ምርመራ 1,829 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተጨማሪም 337 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 37,665 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 637 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13,913 ደርሷል።
የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም ከአዲሱ ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጋር በትላንትናው ዕለት የስራ ርክክብ አድርገዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነው መሾማቸውና በምትካቸው የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ መሾማቸው ይታወሳል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 118 ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃና በቅድመ መደበኛ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

ከተመራቂዎች መካከል 56ቱ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ 23 ተማሪዎች ደግሞ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሰለጠኑ የህክምና ዶክተሮች እንዲሁም በቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት 39 ተማሪዎች በኪነ ህንፃ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸው ናቸው፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተመራቂዎች ሃገራችን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ውስጥ ሆና የተመረቁ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በተለይም የህክምና ተመራቂዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በተጀመረው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ሎችም በተመረቁበት ሙያ የሃገሪቱን ብልፅግና በማረጋገጥ ረገድ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በመሰማራት በ2012 በጀት ዓመት 38 የምርምር ስራዎች ፀድቀው ወደ ስራ መግባታቸውንና ሃያ ሰባቱ መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 20,153 የላብራቶሪ ምርመራ 1,638 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 515 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 40,671 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 678 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14,995 ደርሷል።
#የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና እና የቀጣይ አመት የትምህርት ዘመንን በተመለከተ ለትምህርት ሚኒስቴር ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች በቅርቡ መልስ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ሚሊስቴሩ በይፋዊ ድህረገጹ ላይ እንዳስታወቀው ተማሪዎችና ወላጆች በተደጋጋሚ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ እና የቀጣይ አመት የትምህርት ዘመን የሚጀመርበትን የጊዜ ሰሌዳ በተመለከተ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን እየቀረቡለት እንደሆነ ገልጿል።

ተማሪዎችና ወላጆችም የጠየቁትን ጥያቄዎችንም በቅርቡ መልስ የሚሰጥ ስለመሆኑንና እስከዚያው ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ነው ያስገነዘበው።
በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለኢቲቪ ገልጸዋል።
-----------------------------------
የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል።

የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ሆኑ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጸው፣ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል።
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶችን ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች በየደረጃው በትምህርት ዘርፉ የ 10 አመት እቅድ ላይ ውይይት ጀምረዋል።
የትምህርት ዘርፉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አለመደገፍ፣ ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት አለመኖር፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት አለመስፈን በትምህርት ጥራቱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተንስቷል።
በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት በመስጠት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ለማፍራት የሚያስችሉ አሰራሮች በእቅዱ ውስጥ በዋናነት ተካቷል።
ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶች ከወረቀት ነፃ በማድረግ በዲጂታል መልክ መሰጠት የእቅዱ አንዱ አካል ነው።
ይህም መንግስት ለወረቀትና ህትመት የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከማስቀረት በተጨማሪ ተማሪዎች የዲጂታል አለሙን በቀላሉ እንዲቀላቀሉ ያግዛቸዋል ተብሏል።
ወደ ዲጂታል ስርዓቱ ለመግባት ለተማሪዎች ታብሌቶችን ለማሟላት የተለያዩ አማራጮች እየተፈለጉ ነው።
የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎም ይጠበቃል።
#ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ዓመት 2013 #ትምህርት #ቤቶች እንደሚከፈቱ እየተነገረ ነው

በመማር ማስተማሩ ሂደትም ተማሪዎች ራሳቸውን ከኮቪድ 19 ለመከላከል #የአፍና #አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲያደርጉ ከሌሎች ጋር ያላቸውን አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁ እንዲሁም እጃቸውን በአግባቡ መታጠብ ይጠበቅባቸዋል።

ከኮቪድ 19 መከላከል እንዲቻልም የፊትና አፍ መሸፈኛ ጭንብል እንዲሁም ፀረ ተሐዋሲ የሆኑ የእጅ ማጽጃዎችን በተባባሪ አካላት አማካኝነት ለትምህርት ቤቶች ይቀርባልም ተብሏል።
◉ የስፖርት መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት
➮የሀገር ውስጥ የስፖርት መረጃዎች
➮የውጪ ሃገር የስፖርት መረጃዎች
➮የዝውውር ዜናዎች በፍጥነት
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታድየሞቹ
➮የተለያዩ ስፖርታዊ ታሪኮች
ለማግኘት ይቀላቀሉን👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAExxeYlnFADso8ddVw
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ በኢትዮጵያ የጀርመን መንግስት አምባሳደርን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ በ ኢትዮጵያ አዲስ የተሸሙትን የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውርንን በ ቢሯቸው ተቀብለው በተለያዩ ትምህርት ነክ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

በ ኢትዮጵያ የጀርመን መንግስት አምባሳደር ሆነው የመጡት ስቴፈን አውርን በ ትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ የ ጀርመን መንግስት ሲያደርገው የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በ አጠቃላይ የ ትምህርት ዘርፍ በተለይም በ ትምህርት ፍኖተ ካርታው ላይ የተቀመጠውን የ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ላይ ሰርዕተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ለማጠናከር በ ሚያስችል ቀጣይ ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ላይ የ ሁለትዪሽ ውይይትም አካሂደዋል፡፡

የ ጀርመኑ አምባሳደር በቀጣይ የስራ ዘመናቸው ከ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር የተሻሉ ስራዋችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፡፡

የ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከ ጀርመን ብዙ ልምዶችን እና ድጋፎችን እንደምትፈልግ በመግለፅ ለ አምባሳደሩ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል፡፡
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን ሲጨርሱ የሙያ ባለቤት ይሆናሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ውይይት እያካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ አጠቃላይ ትምህርት አንዱ የሙያ መማሪያ ዘርፍ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) በ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሙያ ትምህርቶችን በሁሉም የሙያ ዘርፎች በመስጠት የተማረ እና በዘርፉ እውቀት ያለው ባለሙያ እንዲፈጠር ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ሙያ ያለው ተማሪን ለመፍጠር በቀጣይ የሙያ ትምህርቶች ከመደበኛ ትምህርት ጋር በተጣጣመ መልኩ ጎን ለጎን እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዋች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ የሙያ ባለቤት ይሆናሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆኑ ትምህርቶች በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተገለፀ ሲሆን ይህን ለማስፈፀም የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ የትምህርት ዘርፍ ተቋቁሟል።

እውቀትን ወደ ታች በማውረድ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ የ10 አመቱ አንዱ የእቅድ አካል መሆኑንም በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በ2013 የትምህርት ዘመን የገዳ ስረዓትን በስረዓተ ትምህርቱ ውስጥ በማካተት ለማስተማር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ እንዳሉት ቢሯቸዉ የገዳ ስረዓትን በክልሉ በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች (1-8) ከአዲሱ የኢትዮጵያውያን አመት ጀምሮ ያስተምራል።

ቢሮዉ ትምህርቱን በሁሉም ትምሕርት ቤቶች ለመስጠት ቢያቅድም ከትምህርት ቁሳቁስ ዝግጅት እና አቅርቦት አንጻር በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር መወሰኑን ገልጸዋል።

አዲሱ ትውልድ የገዳ ስረዓት መማሩ የሚያጋጥሙትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችለዋል ማለታቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮን ዋቢ አድርጎ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል የገዳ ስርዓት ትምህርት በአዲስ አበባ ከተማ ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግረዋል።

ሀላፊው እንደተናገሩት የገዳ ሥርዓት ስርዓተ ትምህርቱ ተጠናቆ የመፅሐፍ ዝግጅት ላይ ተደርሷል፡፡

የመፅሐፍ ዝግጀቱም በ2 እና 3 ሳምንታት ያልቃል በአዲሱ የትምህርት ዘመን የገዳ ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት መሰጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡

ትምህርቱን የሚሰጠው በአዲስ አበባ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በሚሰጥባቸው 7 ትምህርት ቤቶች ናቸው ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡
የግል ምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ ማድረግ አይችሉም ተባለ።

የ 2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከ ነሃሴ 20 ጀምሮ እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ተከትሎ ከተማሪዎች ምዝገባ እና ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ወላጆች ቅሬታን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍያ መመሪያን ተላልፈው ምዝገባ እያከናወኑ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጆች ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስተር ዴኤታዋ የ2013 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ላይም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል እና እንደሚያስጠይቅም ተናግረዋል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ በምትባለው ዉሀን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ቢጀምሩም ወላጆችና መምህራን ግን አሁንም ያላቸውን ስጋት እየገለጹ ነው፡፡

በማዕከላዊ ቻይና በምትገኘው የዉሀን ከተማ ከሰባት ወራት በኋላ ትምህርት ቤቶች ዳግም ተከፍተው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ተመልሰዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙት ከ2800 በላይ የትምህርት ተቋማት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ያህል ተማሪዎችን ቢቀበሉም የአንዳንድ ተማሪዎች ወላጆች ግን ልጆቻቸው ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ሲሰማቸው የነበረው ስሜት አሁንም ሙሉ በሙሉ እንዳልለቀቃቸው መገለጻቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል፡፡
በቀጣይ ተማሪዎች በመልካም ስነ-ምግባር የታነፁ ሆነው እንዲወጡ በትኩረት ይሰራል፡- ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች በስነ ምግባር የታነፁ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ በከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰራ በ 10 አመቱ እቅድ ውይይት ላይ አስታውቋል፡፡

በውይይቱ ወጣቶች አሁን እየታዩ ባሉ አላስፈላጊ ድርጊቶች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ገብተው መገኘታው በተማሪዎች የ ስነ ምግባር ግንባታ ላይ በትኩረት ያለመስራት አንዱ ምክንያት መሆኑ ተነስቷል፡፡

በእቅዱ ውስጥ ተማሪዎች ከመማር ማስተማር ባሻገር በመልካም ስነ-ምግባር የታነፁ ብቁ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮች እንደሚዘረጋ ተጠቁሟል፡፡

ሀገራቸውን የሚወዱ፣ ብዝሃነትን የሚያስተናግዱ፣ ለወንድማማችነት ትኩረት የሚሰጡ በመልካም ስነ ምግባር የታነፁ ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮች በ10 ዓመቱ እቅድ ውስጥ ተካትተዋል፡፡

ለማህበረሰቡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰጡ፣ የትምህርት ቤቶችን ህግና ደንብ የሚያከብሩ፣ በበጎ ምግባራቸው ማህበረሰቡ የሚረካባቸው ተማሪዎችን መፍጠር በ10 አመቱ እቅድ ውስጥ በትኩረት ይሰራባቸዋል ተብሏል።

በሚከተሉት አድራሻዎች አዳዲስ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ። የሚያዘወትሩትን መርጠው ይጠቀሙ።
በኢትዮጵያ ትምህርት ለማስጀመር ጥናት ተደረገ!

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያጋልጥ በማይችል እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲሱ ዓመት ለማስጀመር ጥናት መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። 

ሚኒስቴሩ እንዳለው በአንድ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ቁጥር በመመጠንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ትምህርት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ላይ ጥናት ተደርጓል። 

የትምህርይ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ባለፈው የመማር ማስተማር ሂደት በአማካይ ከ60 እስከ 80 ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ይማሩ የነበረበት ሁኔታ አስታውሰዋል።

በቀጣይ ትምህርት ሲከፈት በቅድመ መደበኛ 14 በመቶ የሚሆኑትን ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ብቻ በአንድ ክፍል እንዲያስተምሩና አንድ ተማሪ በአንድ ዴስክ ብቻ እንዲቀመጥ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል።

አቶ ሚሊዮን እንዳሉት ቀሪዎቹ 80 በመቶ ተማሪዎች በፈረቃ እንዲማሩና 6 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤት በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር ታቅዷል።

በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 24 በመቶ ወይም ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች በአንድ ከፍል ውስጥ እንዲማሩ ፣ 56 በመቶ በፈረቃ እንዲሁም 20 በመቶ ተጨማሪ ክፍል በመገንባት እንዲማሩ ተወስኗል።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 19 በመቶ ተማሪዎች ወይም ከ20 እስከ 25 የሚሆኑት በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲማሩ እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በፈረቃ የሚማሩ ይሆናል።

ሌሎች 31 በመቶ ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር መታቀዱንም አመልክተዋል፡፡
2024/05/12 08:34:54
Back to Top
HTML Embed Code: