Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🛑 #ማስጠንቀቂያ - ለወላጆች በሙሉ
••
👉 ሕፃናት ልጆቻችሁን በሰንበትም ይሁን በሌላ ቀን ለምታስቆርበለ ወላጆች ቅዳሴ አሃዱ ብሎ ሲጀመር ጀምሮ በቅዳሴው መሳተፍ ይገባችኋል። ከአቅም በላይ ከሆነ ቅዱስ ወንጌል ከመነበቡ በፊት ድረሱ አለዚያ ከእግዚኦታ በኃላ እየመጣችሁ አታስቆርቧቸው። በተለይ ቤተሠችሁ ከቤተክርስቲያን ቅርብ የሆነ።
••
👉 ለማስቆረብ ስትመጡ  ረዥም ቀሚስ ፣ ከሰውነት ጋር ያልተጣበቀ ልብስ ፣ ሻሽ ፣ ረዥም ነጠላ መልበስ ግዴታ ነው ሲሆን ጠፍር ቀለምና ከንፈር ማቅለሚያ ብ፣ ብልጭልጭ ነገሮችን አለመጠቀም።
••
📎 ክርስቲያናዊ አለባበስና ክርስቲያናዊ ስርዓት ሊኖራችሁ ይገባል።
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
  ግንቦት  26 || አቡነ ሀብተማርያም
••
በገድል የተጠመዱ ኮከብ ገዳማዊ  የጽድቅ የትሩፋት  ሕይወታቸው እንደ ባሕር አሸዋ የበዛላቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም ልደታቸው ነው።
••
የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በስጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር
••
ለዮስቲና አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም
••
ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የገድሉና የትሩፋቱ ዜና እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል በህይወተ ስጋ ሳለ በፈጣሪው እግዚአብሔር ፍቃድ የብዙዎችን ሰዎች ነፍሳት ከሲኦል ያወጣል እንደ መላእክትም ክንፈ ፀጋ ተሰጥቶታል፤ በሰው አካል ከስጋ ሆኖ ሳለ በተመስጦ ወደ ሰማይ የሥላሴን የአንድነትን የሦስትነትን ምስጢር ያያል አላት የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሃሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡
ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እጅግ
ያመረ ጻዲቅ ወለደች።
••
በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ...
በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር።
••
ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡
••
ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።
••
👉 አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንት አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡
••
👉 አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡
👉 በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ በየቀኑ 150 መዝሙረ ዳዊት፣ 4ቱአራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር፡፡
••
👉  ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸው
👉 ከገድላቸው ከትሩፋታቸው ብዛት የእሳት የብርሃን ሰረገላ የተሰጣቸው።
••••
👉 7 አክሊላት  የተሰጡት ቅዱስ አባት ናቸው
❤️ ስለ ንፅሕ ክህነትና ማዕጠንት
❤️ ስለምናኔ
❤️ ስለ ድንግልና     
❤️ ስለ ወንጌል ፍቅር
❤️ ስለ ቂምና በቀል ስላለመያዝ 
❤️ ስለ ተባረከ ምንኩስና
•••
👉በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ።
•••
በዓለ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሰባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል።
•••
ህዳር 26 ቀን ዐርፈዋል በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን  ይገኛልን ። የአባታችን አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት በረከት በሁላችንም ይደርብን።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
••
እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም {ማቴ፣11÷11}
•••
መጥምቁ ዮሐንስ በያለንበት ከክፉ ነገር ይጠብቀን! አሜን፫
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ #እግዚአብሔር_ዐረገ
❤️እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁአደረሰን 🙏
••
የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡
••
ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡    
••
እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡
ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
••
እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር  የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡
••
ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡
••
ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡
••
አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። መዝ ፵፮ ፡ ፭
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ሰኔ 12  ||  #ቅዱስ_ሚካኤል
••
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ  በዓል  አደረሳችሁ አደረሰን‼️
••
ታሪኩ እንዲህ ነውቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ እርሷም በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ደገኛ ሴት ናት፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደ ደረሰባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ ባሏም ታሞ ሞቶ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡
••
እርሷም "ከቤትገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም "እኛማ በነግህ ጸልየናል?" አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን."... እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ" አላት፡፡
••
ቅድስት አፎምያም "አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ አትጸልዩ ያልከኝ ጌታ ምጽዋት አበድር እመስዋዕት ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? እርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?" ብላ ሞገተችው፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ከላይ እንዳየነው ..በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
••
በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድር ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን ፣ ያዕቆብን ፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡
••
ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታበቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና "የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?" በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው " በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም" ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ። ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡
••
ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደ የመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
••••
#ቅዱስ_ሚካኤል  ከክፉ  ሁሉ ይጠብቀን 🙏
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ!
••
" ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል" (ዮሐ.፲፬፥፲፮)
••
ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡
••
120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት ፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡
••
ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው ፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡
••
በዚያም ዕለት  በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡
••
“ እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ ፣ ኀጢአትን አታድርጉ ፣ በቅድስና ኑሩ ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት ፣ አንገላታችሁት ፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡ ” በማለት አስተማራቸው፡፡
••
የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡
••
ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡
••
በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት ፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Photo
ጾመ ሐዋርያት ( የሰኔ ጾም ) መቼ ይገባል
              ለምንስ ይጾማል ⁉️
•••   
👉 ጾመ ሐዋርያት ወይም ሰኔ ጾም ሰኔ 17 ይገባል ( ይጀምራል ) ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል።
••
ይህ ጾም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ጾም ነው።
••
❤️ የሰኔ ጾም ይህ ጾም የሐዋርያት ጾም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ጾም ተባለ ቢሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት ጾም ስለሆነ ነው።

❤️ የሰኔ ጾም የሚጾምበት ጊዜያት
•••
👉  የሰኔ ጾም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይጾማል
👉  የሰኔ ጾምን እስከ 9 ሰአት እንድንጾም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
👉  ጾሙ የሚገባበት ቀን በየዓመቱ የተለያየ ቢሆንም የጾሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ።
••
ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡
••
ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው ( ተከፈፍለው ) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያ ጾምን አድርገዋል፡፡
••
ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡
••
‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት
••
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ ›› ማቴ 9፥15-16
••
እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹ መሣሪያ ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው፤ አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
••
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን
••
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያበመልጣል " ምሳ 1፥33
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መጠፋፋት ይብቃ ይብዛ ሠላማችን
#ገብርኤል አትለይ ቁም ከመሀላችን
                 💚💛❤️
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ ( የምሥራች ) ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ላዘንን ለእኛ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታ ቃል አሰማን።
••
ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን።
••
አለም! የጥፋት ፣ የሞት ፣ የክስረት ፣ የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምጽን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ፣ ስብራታችን የሚጠግን እንባችን የሚያብስልን የብስራት ድምጽህን አሰማን እንድንጽናናም አድርገን::
•••
ጠበቃችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሰለስቱን ደቂቅን ከእቶን እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው፣ ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢአት እሳትም አጥፋልን አሜን::
••
የመላከ ብስራት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው አይለየን::
••••
👉 የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉 የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉 የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 21 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሰኔ ጎልጎታ የጸለየችበት ዓመታዊ ክብረ በዓሏ ነው እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ።

ጥበቃዋ አይለየን🙏
••••
👉 የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
👉 የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉 የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ጠባቂዬ አባቴ ቸሩ መድኃኔዓለም
••
መድኃኔዓለም የህይወት እስትንፋሴ ፣ ለመኖሬ ምክንያት ነህ ፤ እንደ አባቶቻችን አበርታን እነሱ ከያዙት ጦር ይልቅ አንተ ትበልጣለህ ፤ ህዝብህን ጠብቅ ለጠላቶቻችን አሳልፈህ አትስጠን። አቤቱ አቤቱ ስንልህ በከንቱ እንዳንጠፋ ጠብቀን 🙏🏻🙏🏻🙏🏻
••••
ትክክለኛና ለወቅታዊ የቤ/ክ መረጃዎችና መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለማግኘት፥ ለአስተያየትና ጥቆማ
••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አማኑኤል ሆይ - በክንፍህ መዘርጋት ይህን ትውልድ አንተ ጋርድ። በዚህ ዓለም ሹሞች ሳይሆን ማመኔን በአንተ አድርግልኝ። ልቤን በአንተ አሳርፍልኝ!! ለተጨነቁ መጽናናትን ፣ ለተረበሹ ሰላምን ፣ ላጡት ማግኘትን ፣ ለታመሙት ምህረትን ይስጥልን አሜን!
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ሰኔ 30 || #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ
••
ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።
••
በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።
••
ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።
••
ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።
••
የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።
••
ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።
••
ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡
••
የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
••
👉 ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ
••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን -  https://www.facebook.com/terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
••
የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከታቸው ይደርብን ፤በቃልኪዳናቸው ይጠብቁን አሜን!
•••••
👉🏼 የፌስቡኩ ገፃችን -  https://www.facebook.com/terbinos
👉🏼 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
👉🏼 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://www.tg-me.com/Terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
••
❤️ #ቅድስት_ሥላሴ
••
ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡
••
2025/06/28 20:38:40
Back to Top
HTML Embed Code: