በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫

//ጥያቄና መልስ//

1️⃣ በመፅሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ግዜ የምስጋና መሳሪያ  የሆነው በገና ነው

//መልስ//// እውነት

2️⃣በአድስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ዉዳሴ ማርያምን ደረሲ  ማን ይባላል

//መልስ//// ቅዱስ ብሩታዎስ ይባላል።=

3️⃣የእመቤታችን ጠባቂ የሆነው የአረጋዊ ቅዱስ ዩሴፍ እናትና አባት ማን ይባላሉ

//መልስ//// አባት  ያዕቆብ እናቱ ዩሐዳ ይባላሉ።=

4️⃣የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ እናትና አባቷ ማን ይባላሉ

/መልስ////  አባቷ   ድርሳኒ  እናቷ እሌኒ  ይባላሉ

5️⃣ በኢየሩስአሌምና በደብረ ዘይት ተራራ መካከል ዳሽ የምትባል  ለምለም ስፍራ አለች

/መልስ////  ጌቴሴማኔ

6️⃣ ዘጠኙ ቅዱሳት ወደ ሐገራችን ኢትዮጵያ የገቡት  በአፄ ዘርአ ያዕቆብ  ዘመን ነው

/መልስ//// ሐሰት ፦ ምክንያቱም  በንጉስ በአላሜዳ  ዘመነ መንግስት ነው።

7️⃣ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ታላቅ  ወንድም ማን ይባላል
      
             //ምርጫ//

ሀ// ቅዱስ ዩሐንስ
ለ// ቅዱስ ማርቆስ
ሐ//ቅዱስ ጎርጎርዮስ
መ//ቅዱስ ሳቢሮስ

8️⃣በመጸሐፈ ምሳሌ  'ምዕራፍ' 9 'ከቁጥር' 1  ላይ  "ጥበብ ቤቷን ሰራች ሰባቱንም ምሰሷዋን አቆመች ይላል" ጥበብ የተባለው ማነው?  ቤቷን የተባለውስ ምንድን ነው?ሰባቱ ምሰሶዎች  ምንድን  ናቸው

//መልስ///  'ጥበብ'  የተባለው ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ቤት' የተባለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት።

,,7ቱ ምሰሶዎች' የተባሉት  7ቱ  ሚሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ናቸው።

9️⃣ ለጊዮን/ለአባይ  ወንዝ ዳዊታቸውን አደራ የሰጡ  ከ 5  አመት እስር በኋላ ሲመለሱ ዳዊታቸውን ከወንዙ የተረከቡ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ አባት ማን ይባላሉ

        //ምርጫ//
ሀ//አቡነ ተክለ ሐይማኖት
ለ//አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሐ// አቡነ ዘርአ ቡሩክ
መ//አቡነ ሃፍተ ማርያም

🔟 በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18-2  ላይ ጌታችን በምሃላቸው አቁሞ በምሳሌ ሐዋርያትን ያስተማረበትና አቅፎ የሳመው ይህ ህፃን ማነው

//መልስ///ቅዱስ አግናጢዎስ


1️⃣1️⃣ መርቆሪዎስ ማለት ምን ማለት ነው

//መልስ//// የአብ ወዳጅ የክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።

1️⃣2️⃣  ነብዩ ነህሚያ የማን ቤት ጠጅ አሳላፊ ነበር

          //ምርጫ//
ሀ//የንጉስ አርጤክስስ=
ለ//የንጉስ ድርጣድስ
ሐ//የንጉስ ህዝቂያስ
መ//የንጉስ ዳዊት

1️⃣3️⃣ የአምስቱ ብሔረ ኦሪት ጸሐፊ ነብዩ ሙሴ ነው

መልስ ////  እውነት=

1️⃣4️⃣ የእመቤታችንን ሰኔ ጎለጎታን  የፃፈው አባት ማነው

            //ምርጫ//
ሀ//አባ ህሪያቆስ
ለ//ቅዱስ ዩሐንስ ወንጌላዊ =
ሐ//ቅዱስ ኤፍሬም
መ//አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ


1️⃣5️⃣ የሐዋርያው የቅዱስ ማቴዎስ  የቀድሞው ስሙ ማን ይባላል

          //ምርጫ//
ሀ//ስምኦን
ለ//ዲዲሞስ
ሐ//ሌዊ=
መ//ሳኦል

1️⃣6️⃣ ቅጣትን ሳይሆን የቅጣት እናት የሆነውን /ኃጢአያትን እንፍራ ይህን ያለው አባት ማነው

       //ምርጫ//
ሀ//አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ
ለ//ማር ይስሃቅ
ሐ//ቅዱስ ዩሐንስ አፈ ወርቅ
መ//አረጋዊ መንፈሳዊ

17/ አባታችን ኖህ ስንት ልጆች አሉት? ስማቸውስ

   መልስ///  3 ልጆች
ካም ፣ያፌት ፣ ሴም ይባላሉ።
https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫

//ጥያቄ እና መልስ

1️⃣ ነብዩ ኤልሳዕ በርግማኑ በድብ ያስበልስቸው ህጻናት ቁጥራቸው ስንት ነው ?

ሀ/ 15
ለ/ 50
ሐ/ 42  (2ኛ ነገ2÷24
መ/ 24

2️⃣ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ከእኔ ወጥቷል ያለው?

ሀ/ ለምፃሙን ሲፈውስ
ለ/ መቅደላዊት ማርያምን
ሐ/ ለ12 ዓመት ደም ይፈሳት የነበረችው ሴት ስትነካው (ማር 5-30
መ/5ሺውን ህዝብ አበርክቶ ሲመግብ

3️⃣ ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም እንደሚታሰር የተነበየው ነብይ ማን ይባላል?

ሀ/ ማርቆስ
ለ/ አጋቦስ (  ግብ.ሃዋ 20-10
ሐ/ ኤርሚያስ
መ/ ዳንኤል

4️⃣ የቅድስት አስቴር አጎት ማን ይብሃል ??

ሀ/ አርጤክስስ
ለ/ ሃማ
ሐ/ መርዶክዮስ
መ/ ሳሙኤል

5️⃣ከአሴር ወገን የምትሆን የፋኑኤል ልብ ሀና የምትባል ነብይት ነበረች ?

እውነት (ሉቃ 23/6)

6️⃣ የአባታችን አብርሃም እናት እና አባቱ ማን ይባላሉ ?

አባቱ ታራ
እናቱ እድና

7️⃣ የአዲስ ኪዳን የትእዛዝ መጽሀፍት የሚባሉት ?
ስምንት ነው

1/ መ. ትእዛዝ
2/ መ.ግፅው
3/ መ.አቦጠሊስ
4/ መ.ስረአተ ጺዮን
5/ መ. ኪዳን ቀዳማዊ
6/ መ. ኪዳን ካልእ
7/ መ.ዲድስቅልያ
8/ መ. ቀለመንጦስ

8️⃣ የ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ስም ዝርዝራቸውን ጥቀሱ ?

1/ ጴጥሮስ (ስምዖን
2/ እንድርያስ
3/ ያዕቆብ /የዘብድዮስ ልጅ
4/ ዮሃንስ
5/ ፊልጶስ
6/ በርተለሜዎስ
7/ዲዲሞስ ቶማስ
8/ ማቴዎስ /ሌዊ
9/ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ
10/ ታዴዎስ /ልብድዮስ
11/ ቀናተኛው ስምኦን /ናትናኤል
12/ ማትያስ /ማቴ 10-2-4)

9️⃣ በቅዱስ ወንጌል 120 ቤተሰብ እነማናቸው ?

12 ሐዋርያት
36 ቅዱሳን አንስት
72 አርድዕት

🔟 የጌታችን ዘጠኙ ዓብይት በዓላት የሚባሉትን ዘርዝሩ?

ብስራት
ልደት
ጥምቀት
ደብረታቦር
ሆሳዕና
ስቅለት
ትንሳኤ
እርገት
ጵራቅሊጦስ

1️⃣1️⃣ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል ከሰዱቃውያን ወገን የሆነው ቶማስ ነው ?

እውነት

1️⃣2️⃣ ካልባረከኝ አለቅህም በማለት ከእግዚአብሔር ጋር ሲታገል ያደረው አባት ነብዩ ሙሴ ነው ?

ሀሰት ዘፍ 32+26

1️⃣3️⃣ ቅዱስ አብሮኮሮስ የቅዱስ ዮሐንስ ወንግልላዊው ደቀ መዝሙር ነው ?
እውነት

1️⃣4️⃣ ከአራቱ ወንጌል መካከል ቴዎፍሎስ ለተባለ የግሪክ ባለስልጣን የተፃፈው የትኛው ወንጌል ነው?

ሀ/ የማቴዎስ
ለ/ የሉቃስ
ሐ/ የማርቆስ
መ/ የዮሃንስ


1️⃣5️⃣ ነብዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሳው የሰራፕታዋ ልጅ ስሙ ማን ይብላል ?

ሀ/ እለስክንድሮስ
ለ/ አግናጢዎስ
ሐ/ ነብዩ ዮናስ
መ/ መልስ የለም


1️⃣6️⃣ በመጸሀፍ ቅዱስ ረጅም እድሜ ኖሮ ያረፈው አባት ማነው ?

ሀ/ አዳም
ለ/ ኖህ
ሐ/ ማቱሳላ 969 (ዘፍ5+27
መ/ ሄኖክ


1️⃣7️⃣ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል  ግመል በመርፌ ቀዳዳ ያሳለፈው ማነው?

ሀ/ ጴጥሮስ
ለ/ቶማስ
ሐ/ ፊልጶስ
መ/  ታዴዎስ


1️⃣8️⃣ ከዳዊት ኃያላን መካከል ጦሩን አንስት 800 ሰው በአንዴ የገደለው ሰው ስሙ ማን ይባላል?

ሀ/ ዮናታን
ለ/ አሳፍ
ሐ/ ኢያቡስቴ 2ሳሙ2/38
መ/ አቢሳን


1️⃣9️⃣ ይውድስዋ መላእክት የተሰኘውን  የእመቤታችን የምስጋና ጸሎት የደረሰልን አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው

እውነት

2️⃣0️⃣ ቅዱስ ጴጥሮስ የፈወሰው የስምንት አመት  የአልጋ ቁራኛ የነበረው ሰው ?

ሀ/ አናንያ
ለ/ ጣቢታ
ሐ/ኤንያ ( ግብ ሐዋ 9-33
መ/ በርናባስ

ወስበሀት ለእግዚአብሔር
https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ እነሆ ጥያቄ እና መልስ


1️⃣ አባታችን ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ሲታገል ያደረበት ስፍራ

ሀ/ከነአን
ለ/ኡር
ሐ/ጵንኤል (ዘፍ32-30
መ/ ዮርዳኖስ

2️⃣ በመጸሀፍ ቅዱስ የመጀመርያው የብሉይ ኪዳን ሰአሊ ማነው ?

ሀ/ አዳም
ለ/ሙሴ
ሐ/አሮን
መ/ ኢያሱ

3️⃣ በጸሎቱ ለሶስት አመት ተኩል ሰማይ ዝናብ እንዳያዘንብ የዘጋው የእግዚአብሔር ነብይ ማነው?

ሀ/ ኤልሳ
ለ/ ኤልያስ
ሐ/ ዳንኤል
መ/ ኤርሚያስ

4️⃣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል ሰማይ ለስንት ሰአት ጨለመ ??

ሀ/ ከ3--9 ሰአት
ለ/ ከ6--12 ሰአት
ሐ/ ከ6--9 (ማቴ  27-45
መ/ ከ3--6 ሰአት


5️⃣ ነብዩ ከሰፒራ የወለደው የመጀመርያ ወንድ ልጅ ስሙ ምን ይባላል ??

ሀ/ ቢንያም
ለ/ ጌርሳህ ዘፀ 2-22
ሐ/ ሮቤል
መ/ ባኮስ

6️⃣ ሰባቱ ሊቃነ መላዕክት የሚባሉት ዘርዝሪ?

ቅዱስ ሚካኤል
ቅዱስ ገብርኤል
ቅዱስ ሩፋኤል
ቅዱስ ዑራኤል
ቅዱስ ራጉኤል
ቅዱስ ፋኑኤል
ቅዱስ ሳቁኤል

7️⃣ በእለተ ረቡዕ የተፈጠሩ ፍጥረታት  ስንት ናቸው ስማቸውስ ??

ሶስት ናቸ
-- ፀሀይ
--ጨረቃ
-- ከዋክብት

8️⃣በቅዳሴ ጊዜ አምስት መስዋዕቶች አሉ ምን ምን ??

ቁርባን መስዋዕት
የመብራት መስዋዕት
የከንፈር መስዋት
የእጣን መስዋዕት
የሰውነት መስዋዕት

9️⃣ አምስቱ ፍኖተ ጽድቅ የሚባሉትን ዘርዝሪ?

ፍቅር ትህትና ፆም ጸሎት ምፅዋት

🔟 ቤተክርስቲያን ሶስት መቅደሶች አሏት ምን ምን ይባላሉ ??

ቤተ መቅደስ
ቤተ ቅድስት
ቤተሌሔም

1️⃣1️⃣ በገዛ ወንድሟ የተደፈረችው የዳዊት ልጅ ስሟ ደሊላ ይባላል ?

2ሳሙ 13÷1 ሀሰት

1️⃣2️⃣ በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሊቀጳጰጳስ አቡነ ተክለሀይማኖት ይባላሉ??

ሀሰት  ፍሬምናጦስ (አባሰላማ

1️⃣3️⃣ ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው አባት  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው??

ሀሰት አባ ህርያቆስ ነው

1️⃣4️⃣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከእርሱ የሚበልጥ የለም ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረለት ለማነው??

ሀ/ ለቅዱስ ዳዊት
ለ/ለመጥምቁ ዮሃንስ (ሉቃ 7-28)
ሐ/ ለነብዩ ዳንኤል
መ/ለነብዩ ሙሴ

1️⃣5️⃣ የኢያሪኮን መራራ ውሃ ያጣፈጠው ነብይ ማን ይባላል

ሀ/ነብዩ ኤልያስ
ለ/ነብዩ  ሙሴ
ሐ/ ነብዩ ኤልሳዕ
መ/ነብዩ ዳንኤል


1️⃣6️⃣ በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ዕርስቲቱን ትወርሳላችሁ ያለው አባት ማነው ??

ሀ/ አቡነ ሺኖዳ
ለ/ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሐ/ አባ መቃርስ
መ/ አባ ይስሀቅ

1️⃣7️⃣ሰባቱ ሰማያት የሚባሉትን ዘርዝሩ?

ሰማየ ሰማያ
መንበረ መንግስት
ሰማይ ውዱድ
ኢየሩሳሌም  ሰማያዊት
ኢዮር
ራማ
ኤረር


1️⃣8️⃣የነብዩ ሙሴ ሚስት የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ሴት ማን ትባላለች ?

ሀ/ ቤርሳቤህ
ለ/ ሩት
ሐ/ሰፒራ (ዘፀ 2-21)
መ/ማርያም

1️⃣9️⃣ አንቀፀ ብርሀን የተሰኘውን የእመቤታችን የምስጋና ፀ
ጸሎት የደረሰው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬው ነው ??

እውነት

2️⃣0️⃣ በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያዎቹ ሰባቱ ዲያቆናት የሚባሉትን ዘርዝሩ ??

   ሐዋ. ሥራ 6
5፤ ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው _እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
6፤ በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።
ወስበሀት ለእግዚአብሔር https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
#ስለ #አዳምና #ሄዋን #ጥያቄ #ከነ #መልሱ
1/ እግዚአብሔር አዳምን ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ፈጠረው?
2/ እግዚአብሔር ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን አቅንቶ
ለምን ፈጠረው?
3/ እግዚአብሔር አዳምን ለሚቆም ፣የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው?
4/ እግዚአብሔር ለአዳም ስንት ሀብታትን ሰጠው? ምንምን ናቸው?
5/ እግዚአብሔር ሄዋንን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ለምን ፈጠራት ? ከግንባር
ወይም ከ እግር ለምን አልፈጠራትም?
6/ በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ?
7/አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል
ጊዜ ቆዩ?
8/ አዳምና ሄዋንን በእባቢቱ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል?
9/አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበራቸው ?
10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ?
አዳም ማለት ከመሬት የተፈጠረ ያማረ መልከ መልካም ማለት ሲሆን
የተፈጠረው ከአራት ባህርያተ ስጋ ማለትም ከነፋስ፣ከእሳት ፣ከውሀ፣ከመሬት
እንድሁም ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ማለትም ከልብ ፣ከቃል፣ከእስትፋስ
የስነ ፍጥረት መካተቻ በሆነች በእለተ አርብ በ3 ስዓተከህቱም ምድር ሚያዝያ
4 ቀን በምድር መካከል በምትገኘው <ኤልዳ> በተባለች ስፍራ የ30 አመት
ጎልማሳ ሁኖ በእግዚአብሔር አርአያነት መልክ ተፈጠረ፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት 1፣27 ፣ኩፉሌ 5፣6
መልስ ፡-
1/አዳም ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ተፈጠረ?
☞መጨረሻ የተፈጠረበት ምክንያት እግዚአብሔር አምላካችን "በጎ አምላክ"
ስለሆነ በጎ አባት ለልጁ አብሮት ከብት ያረባለታል ፣ጥማጅ ያጠምድለታል፣
የኑሮ ጓደኛ ያመጣለታል አስቀድሞየሚበላው፣የሚጠጣው፣የሚገዛውና
የሚነዳውን ፈጥሮለት በመጨረሻም በሁሉ ላይ ሊያሰለጥነው አዳምን
ፈጠረው፡፡
2/ ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቅንቶ
ፈጠረው?
☞ እሱ ገዥ እናተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነወ፣እንድሁም እናተ ፈርሳችሁ
በሰብሳላችሁ ትቀራላችሁ እሱ ግን" ትንሳኤ ሙታን " አለው ሲል አቅንቶ
ፈጠረው፡፡
3/ አዳምን የሚቆም የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው?
☞ መቆሙ- ሰማያዊ ፣
☞መቀመጡ- ምድራዊ ነህ ሲለው ነው፣
☞የሚተኛ ፣ የሚነሳ አድርጎ መፍጠሩ ደግሞ ☞መተኛቱ- ሞቱን
☞መነሳቱ - ትንሳኤውን ሲነግረው ነው፡፡
4/ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ስንት ሀብታት ሰጠው? ምን ምን?
☞ሰባት ሀብታትን የሰጠው ሲሆን እነሱም፡-
➊ሀብተ መንግስት (የማስተዳደር ሀብት
➋ሀብተ ክህነት ( የመቀደስ፣የመባረክ፣መስዋዕት የማቅረብ
➌ ሀብተ ትንቢት (የመጣውን የመናገር
➍ሀብተ መዋኢ (የማሸነፍ
➎ሀብተ ሀይል (የጥንካሬ
➏ሀብተ ፈውስ ( የመዳን ፣የመፈወስ
➐ሀብተ ዝምሬ (የመዝሙር
5/ ሄዋን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ወስዶ ለምን ተሰራች?ከግንባር ወይም
ከእግር ለምን አልሰራትም?
☞ አዳም ለእንሰሳት፣ለሰማይ ወፎች ና ለምድር አራዊቶች ሁሉ ተባእትና
እንስት ሁነው ሲመጡ ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡ነገር ግን ለአዳም እንደ ራሱ
ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር ፡፡
"እግዚአብሔርም " ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም
የሚመቸውን ረዳት ልፍጥርለት አለ ፡፡ኦዘፍ 2፣18
ከዚያም በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበትና ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ
ከጎኑ አጥንት አንስት አንስቶ ያችን ስጋ አልብሶ የ15 አመት ቆንጆ አድርጎ
ፈጠራት ፣ኦዘፍ 2፣18
አዳምም ስሟንም "ሄዋን" አላት ፣ሄዋን ማለት "ሀይው" ከሚለው የግዕዝ ቃል
የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም" የህያዋን ሁሉ እናት "ማለት ነው፡፡
ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ሄዋንን መፍጠሩ
☞ፈፅሞ ተኝቶ ቢሆን ኑሮ ምትሀት መስሎት ከየት መጣች ብሎ ይፈራታል
☞ፈፅሞ ነቅቶ ቢሆን ኑሮ ከአካሉ አጥንት ሲነሳለት ያመው ነበርና ይጠላት
ነበር ፡፡
☞ከፍ አድርጎ ከግባር ዝቅ አድርጎ ከእግር ያልሰራት ግባርና እግር በልብስ
አይሸፈንም ጎኑ ግን በልብስ ይሸፈናልና ተሰውራ ወይም ተሸፍና መኖር
ይገባታል ሲል ነው፡፡
በሌላ በኩል ግንባር የባለቤት እግር፣ የቤተሰብ ምሳሌ ነው ፡እሷም ከባለቤቷ
በስተታች ከቤተሰብ በላይ ሁና ትኑር ሲል ነው ፡፡ 1ኛ ቆሮ 12፣19-22
እንድህ አድርጎ አዳምና ሄዋንን እስከ 40 ቀን ድረስ በተፈጠሩበት በማዕለ
ምድር በቀራንዮ አስናበታቸው
ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበት ቦታ ነውና
ከዛም በ40ኛው ቀን አዳምን ብርሃን አልብሰው ፣ብርሀን አጎናፅፈው፣የብርሀን
ዘውድ አቀናጅተው በብርሃን ሰረገላ አስቀምጠው ወደ ገነት አስገቡት፡፡
ሄዋንንም በ80 ቀኗ እንደ አዳም ባለ ክብር ወደ ገነት አስገቧት ፡፡ኩፉሌ ፈ
4፣12-15
አዳምና ሄዋን ከእግዚአብሔር የባህሪ ደግነት የተነሳ እርሱን ለማመስገንና
ክብሩን ለመውረስ ተፈጠሩ፡፡ ኩፋሌ 4 ፣3-5
እግዚአብሔር ለአዳም ረዳት የፈጠረለት ስለ ሶስት ነገሮች ሲል ነው፡፡
➊ዘርን ለማብዛት
➋ ከዝሙት እንድፀዳና
➌ረዳት እንድትሆነው ነው
6/ በገነት ውስጥ 3 አይነት ዛፎች ነበሩ
➊ ዕፀ መብል -እንድበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ ነው
➋ዕፀ በለስ-እንዳይበሉ የታዘዙት ነው
➌ዕፀ ህይወት - እንደ <እግዚአብሔር > ፈቃድ የሚመገቡት የዘለዓለም
ህይወት የሚሰጥ ምግብ ነው፡፡
ህግን ጠብቀው በገነት ውስጥ 1000 አመት ከኖሩ ብኀላ እፀ ህይወት
በልተው ከገነት ወደ ሰማያዊ እየሩሳሌም (መንግስተ ሰማይ ) እንድገቡ
ለበለጠ ክብርና ፀጋ ሽልማት እንድሎናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ያለ ጊዜው ሳቱ
እንጅ
'እፀ በለስ ' እንዳይበሉ የታዘዙበት ህግ አዳም ፈጣሪ እንዳለው ፣ለፈጣሪው
ያለውን ፍቅር የሚገልፅበትና ተገዥነቱን የሚያሳይበት ነው፡፡
7/ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል
ጊዜ ቆዩ?
☞አዳምና ሄዋን ይህን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ለ7 አመት ከ 2ወር ከ
17 ቀን ኖሩ፡፡
8/ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል ?
☞አዳም በሳጥናኤል ተተክቶ መቶኛ ሁኖ ከመላእክት ጋር ተቆጥሮ ነበር
ሰይጣንም በእባብ አድሮ አሳቻቸው ጽድቃቸውም ተገፈፈ አዳምና ሄዋንን
በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ' ጋርድኤል ይባላል፡፡
በመሆኑም አትብሉ የተባሉትን እፀ በለስ ህጉን አፈረሱ ከገነት ተባረሩ ፡ኦዘፍ
3፣1 ኦዘፍ 3 ፣22-24
9/ አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበሯቸው?
☞ ከገነት ከተባረሩ ብኀላ በደብረ ቅድስት ይኖሩ ነበር፡
አዳምና ሄዋን በሰሩት ሀጢያት በመፀፀታቸውና በንሰሀ በመመለሳቸው
"እግዚአብሔር" መሀሪ ነውና 5 ቀን ተኩል ወይም 5500 ዘመን ሲፈፀም ሰው
ሁኖ በመወለድ እንደሚያድናቸው ቃል ኪዳን ገባላቻው ፡፡ኦዘፍ 3፣15-22
አዳም ግን የራሱን ደም በስንደ ለውሶ ሲሰዋ ጌታችን በአንተ ደም አይደለም
አለም የሚድነው በእኔ ነው ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡
አዳምና ሄዋንም በምድር ላይ ዘርን ተክተዋል ገብርኤል ፣ሚካኤል ፣ሩፋኤል
ወርቅ ,እጣን,ከርቤ አምጥተው ለአዳም ሲሰጡት ወርቁን ማጫ ይሁንሽ ብሎ
ሰጣት ከዛም አዳምና ሄዋን በ 30 ሩካቤ 60 ልጆችን ወልደዋል
10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ?
https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
☞ አዳም በተፈጠረ በ930 አመቱ አረፋ ፡አዳም ለሄዋን የሰጣት ወርቅ ለሴት
ሰጠችው ሴትም ለኖህ አስተላለፈው እጣኑንም ኖህ አፅመ አዳም እያጠነ
ድኖበታል ፡፡
በአዳም ስም በሀገራችን የተሰሩ ቤተክርስቲያኖች ብዛታቸው 5 ናቸው
በአዳም ስም የተቀረፀው ታቦት ከሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያመጣው ፃድቅ
አባት 'መልከአ እግዚአብሔር ' ይባላል፡፡እንድከበር ያደረገው ቅዱስና ሊቁ
ያሬድ ማህሌት ነው፡፡
----------ምንጭ----------
መፅሀፈ ኩፉሌ
ኦሪት ዘፍጥረት
ዜና አዳም
ገድለ አዳም
ዜና አበው
ቅዱሳን ታሪክ
---------------------------------
ለአባ ህርያቆብ ፣ለቅዱስ ኤፍሬም ፣ለቅዱስ ያሬድ፣ለአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ
የተገለፀች እመቤታችን እኛንም በበረከትና በረድኤት ተጎብኘን ከልጇ ከወዳጇ
ከመድሀኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ታማልደን አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላድቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር
አሜን
https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫

መንፈሳዊ ጥያቄ ና መልስ 
     //ስለ ዘመነ ፅጌ// 💠

1️⃣ ዘመነ ፅጌ ማለት ምን ማለት ነው ?

መልስ => የአበባ ዘመን ማለት ነው

2️⃣ ዘመነ ፅጌ እሚባለው ከምን ቀን እስከ ስንት ቀን ነው ?

መልስ => ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 6

3️⃣ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች የሚለውን ትንቢት ለመተርጎም በመጠራጠሩ ይህ ትንቢት እስኪፈፀም ሞትን ያላየው አባት ማን ይባላል ?

አረጋዊ ስምዖን

4️⃣ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ፡ ይህ ቃል የት ይገኛል ?

ማቴዎስ 2-20

5️⃣ ጾመ ፅጌ ከሰባቱ አጹአማት መካከል ይመደባል  እውነት ሀሰት?

ሀሰት

6️⃣ አረጋዊ ስምዖን ና 71ሊቃውንት አባቶችን መፅሐፈ ብሉያትን እንዲተረጎሙ ያደረገው ንጉስ ማነው ?

ሀ/ ንጉስ ሄሮድስ
ለ/  ንጉስ በጥሊሞስ
ሐ/ ንጉስ ፈርዖን
መ/ ንጉስ ዳዊት

7️⃣ በዚህ በፆመ ፅጌ በተለየ ሁኔታ የሚዘወተረው ማህሌተ ፅጌ የተሰኘውን ድርሰት የደረሱት አባት ማን ይባላሉ ?

ሀ/  ቅዱስ ያሬድ
ለ/ ቅዱስ ኤፍሬም
ሐ/አባ ጊዮርጊስ
መ/ አባፅጌ ድንግል

8️⃣ ከመጽሀፈ ብሉያት መካከል ለአረጋዊ ስምዖን እንዲተረጎም የደረሰው  የትኛው የትንቢተ መጽሀፍ ነው ?

ሀ/ ትንቢተ ኤርምያስ
ለ/ ትንቢተ ሕዝቅኤል
ሐ/ ትንቢተ ኢሳይያስ
መ/ ትንቢተ ሆሴዕ

9️⃣ የእመቤታችን ስደት ስቃይ እንግልት አስቀድሞ ታይቶት  በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል፡ ብሎ ትንቢት የተናገረው አባት ማነው?

አረጋዊ ስምዖን ሉቃስ 2
34-35፤

🔟 በተአምር ማርያም እና በማህሌተ ፅጌ ተፅፎ እንደሚገኘው ጌታችን በምድረ ግብፅ በስደት ሳለ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል ከእነዚህም መካከል እናቱን እመቤታችንን የዘለፏትን ሁለት ሴቶች ከሰውነት ወደውሻነት ተቀይረዋል የሴቶች ስም ማን ና ማን ይባላል ?

መልስ => ትእማን እና ኮቲባ

1️⃣1️⃣ የጌታችን እና የእመቤታችን ጥንተ ስደት የሆነው በምን ወር ነበር ?

መልስ => በግንቦት ወር ነው

1️⃣2️⃣ ስልጣንን ሊቀማኝ ነው በማለት የአይሁድ ንጉስ ወዴት ነው ብሎ ጌታችን በመፈለግ ምክንያት 144ሺ የቤተልሔም ህፃናት ያስፈጀው እንዲሁም እመቤታችን ክፉኛ ያሳደዳት ንጉስ ማነው ?

ሀ/ ንጉስ አንጢያኮስ
ለ/  ንጉስ በጥሊሞስ
ሐ/ ንጉስ ናቡከደነጾር
መ/  ንጉስ ሄሮድስ

1️⃣3️⃣ ጌታችን በምድረ ግብፅ በስደት ከአደረጋቸው ተአምራትን አ
እንደ አንዱ የሚጠቀስ ሲሆን ይኽውም  የሄሮድስ ጭፍሮች ደርሰው ልጅሽን ሊገድሉብሽ ነው ብሎ እመቤታችን በማስደንገጡ እስከ እለት ምፅአትት ድረስ ድንጋይ ሆኖ እንዲቆይ የተደረገው የዮሴፍ ልጅ ስሙ ማን ይባል ?

መልስ => ዮሳ

1️⃣4️⃣ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የሚለውን ትንቢት የተናገረው ነብይ ማነው ቃሉስ የት ይገኛል ?

=> የተናገረው ነብዩ ሆሴዕ ነው ቃሉ ትንቢተ ሆሴዕ 11-1 ላይ ይገኛል

1️⃣5️⃣ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፡— ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ፡ ይህ ቃል የት ይገኛል ??

መልስ => ማቴዎስ 2 ÷13
ወስበኃት ለእግዚአብሔር
https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
#እንኳን #አደረሳችሁ #በዓለ_ደብረ_ቁስቋም_ማርያም

©አስምኪ ቦቱ

አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር /፪/
ተፈጸመ /፭/ ማኅሌተ ጽጌ/፪/

ትርጉም:- የሰማይና የምድር ንግሥት ሆይ እነሆ ጽጌ ማኅሌት ተፈጸመ። ውድ ልጅሽ በእቅፍሽ አንደሚያርፍ አንቺም በዚህ ማኅሌት እረፊበት። ደስ ተሰኝበት።በመካከሉ ተገኝ አሳርፊው።

©ኀብረ ሐመልሚል

ኀብረ ሐመልሚል ቀይህ ወጸአድኢድ/፪/
ተፈጸመ/፭/ ማኀሌተ ጽጌ/፪/ እኽ

ትርጉም:- ቀይ እና ነጭ የሆነ የልምላሜ ምስጋናሽ ድንግል ሆይ ተፈጸመ።

©ዮም ጸለሉ መላእክት


ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም/፪/
እንዘ ይብሉ ስብሐት ስብሐት በአርያም ስብሐት በአርያም /፪/

ትርጉም፡- መላእክት በደብረ ቁስቋም ምስጋና በአርያም ይሁን እያሉ ማርያምንና ልጇን ከበቡ፡፡
የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮

©ብርሃነ ሕይወት

ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም ኀደረ ደብረ ቁስቋም /፪/
ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም /፬/ ኧኸ

ትርጉም፡- የማይጠፋው የሕይወት ብርሃን የአርያም
ኃይል በደብረ ቁስቋም አደረ ።
የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮

©አብርሂ

አብርሂ /፪/ ኢየሩሳሌም /፪/
በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም እግዚአብሔር /፪/

ትርጉም፡- ኢየሩሳሌም ሆይ ብርሃንሽ እግዚአብሔር ስለደረሰ አሁን አብሪ፡፡

የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮

©ወተመይጠት

ወተመይጠት ማርያም ሀገረ እስራኤል አቡሃ /፪/
ነቢራ በግብጽ /፬/ አርብዓ ወክልኤተ አውራኀ /፪/

ትርጉም፡- ማርያም አርባ ኹለት ወራት በግብጽ ተቀምጣ ወደ አባቷ ሃገር ኢየሩሳሌም ተመለሰች፡፡

የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮
©አልቦ እንበለ ሰሎሜ

አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ /፪/
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይጸውር ስንቀኪ /፬/ ኧኸ

ትርጉም ፡- ከሰሎሜ ውጪ የሚያግዝሽ ከቅዱስ ዮሴፍም ውጪ ስንቅሽን የሚሸከምልሽ የለም።

©ውድስት አንቲ

ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት/፪/
አክሊለ በረከቱ ለዮሐንስ ወትምክሕተ ቤቱ ለእስራኤል/፪/

ትርጉም፡- የዮሐንስ አክሊለ በረከት የእሥራኤል ቤት መመኪያው የሆነሽ እመቤታችን በነቢያት
አንደበትና በሐዋርያት የተመሰገንሽ ነሽ፡፡https://www.tg-me.com/yaradawyimezmuroch
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫
ጥያቄ እና መልስ

1️⃣ አኬልዳማ ማለት የደም መሬት ማለት ነው

እውነት

2️⃣ የነብዩ ሳሙኤል እናት አባቱ ማን ይባላሉ

አባቱ ሕርቃል እናቱ ሀና

3️⃣ የገነትን በር ይጠብቁ የነበሩት ሁለቱ መላእክት ማን እና ማን ናቸው

ዙጡኤል ሰራቅኤል

4️⃣ አርከ እግዚአብሔር በመባል የሚታወቀው አባታችን ዳዊት ነው

ሀሰት አባታችን አብርሃም ነው

5️⃣ ሃይማኖት ማለት ማመን መታመን ማለት ነው
እውነት

6️⃣ እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ አሸተተ እንደአንቺ ያለ አላገኘም እና የሚወደው ወደ አንቺ ላከ ያለው


ሀ/ አባ ጊዮርጊስ
ለ/ አባ ህርያቆስ
ሐ/ ቅዱስ ያሬድ
መ/ ቅዱስ ኤፍሬም

7️⃣ በቤተክርስቲያናች ስርዓት መሰረት በዓመት ውስጥ ስንት ቅዳሴአት አሉ

ሀ/ 10
ለ/ 16
ሐ/ 14
መ/ 15

8️⃣ በቤተክርስቲያን ስርዓት  በዓመት ውስጥ ሰባት አጽዋማት አሉ ምን ምን

ፆመ ፍልሰታ
ፆመ ገና
ፆመ ድህነት
ፆመ ገሀድ
ፆመ ነነዌ
የሐዋርያት/ሴኔ ፆም
የዓብይ ፆም ነው

9️⃣ የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛባታል ስለዚህ ከግል ህይወታችን ይልቅ የቤተክርስቲያን አቋም አጠንክሩ ያለው አባት

ሀ/ አትናቴዎስ
ለ/ ብፁእ አቡነ ጎርጎርዮስ
ሐ/ ዮሃንስ አፈወርቅ
መ/ አረጋዊ መንፈሳዊ


🔟 ቤተክርስቲያን የሰማይ ስርዓት አላት ያለው አላት ያለው

ሀ/ ቅዱስ ያሬድ
ለ/ አባ ህርያቆስ
ሐ/ አባ ጊዮርጊስ
መ/ ቅዱስ ቄርሎስ

1️⃣1️⃣ መጸሐፈ መነኮሳት በስንት ይከፈላል

በሦስት👍

ፊልክሱስ
አረጋዊ መንፈሳዊ
ማርይስሀቅ

1️⃣2️⃣ አማኑኤል ማለት ምን ማለት ነው

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው

1️⃣3️⃣ በብሉይ ኪዳን  ዘመን ለመጀመርያ ካህን ሆኖ የተመረጠው ና ለአገልግሎት  የተጠራው ሰው ስሙ ማን ይላል

መልኬ ጼዴቅ

1️⃣4️⃣ አባታችን ኖህ ለስንት ዓመት በድንግልና ኖረ

500 አመት

1️⃣5️⃣ ነገረ ማርያምን የፃፈልን አባት ማነው

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

1⃣6️⃣ የጦቢትን አይን ያበራው መልአክ ማነው

ቅዱስ ሩፋኤል

1️⃣7⃣ ቀውስጦስ የሚባለው መክዓክ ከእግዚአብሔር ማልዶ  ያስታረቀው ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ነው

ሀሰት አባ ሳሙኤል ዘቀልሞን ነው.

1️⃣8⃣ ዳዊት ማለት ህሩይ ማለት ነው

እውነት

1⃣9⃣ የቅዱስ ያሬድ ወላጆቹ  ማን ማን ይባላሉ

ክርስቲና ታውክልያ/ይስሐቅ አብድዩ
ወስበሀት ለእግዚአብሔር
https://www.tg-me.com/Teyakaenamels
#ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል?
ለምንስ_እንፆማለን?

ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም #__ሐሙስ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 በዕለተ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ፆም ቅበላ እስከ ማክሰኞነው ከረቡዕ ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም።

ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

=> ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።

#ፆመ_ድህነት የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።

#ፆመ_ማርያም የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

#ፆመ_አዳም የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡

#ፆመ_ፊሊጶስ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ፆመ_ስብከት የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡

ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።

ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል
ወለመስቀሉ_ክቡር !!!!!
ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሃን በእላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍፁም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያፅናናኝ

እንኳን አደረሳችሁ
Watch "የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አከባበር በዱባይ ልዑል እግዚአብሔር የዓመት ሰው ይበለን" on YouTube
https://youtu.be/ygGh_bgZ_oI
Audio
*ከምዕመናን ለመጡ ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ (፰ ዓመት ጠበኩት..)*
በመጋቤ ሐዲስ አእምሮ ደምሴ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*
          ደቂቃው *// 23:04//*
*Ke M'emenan Lemetu Tyakewoch Yetesete Mels(8 Amet Tebekhut..)*
Be Megabe Hedis A'emro Demse
Lememhrachn Kale Hiywet Yasemaln
*MAHBERE TEWAHDO ZE ORTHODOX*
         👆👂👂👈
https://youtube.com/channel/UCSzRc-X36uAdN5vIJ6MPwlQ
*የዩቲዩብ ቻናል👆*
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEbd5IkdiManf9kEuQ
*የቴሌግራም ቻናል👆*
🕊               🔔                🕊


ድምፀ ተዋህዶ 

----------------------------------------

[ '' ስለ ጽዮን ዝም አልልም ! '' ]    


[ በአባታችን በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ]

----------------------------------------

ልባችንን አረጋግተን በማስተዋል እናዳምጥ !

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
----------------------------------------

                  👇
Forwarded from ®Fenote birhan(የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት የመረጃ ገጽ) (ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ (1ኛ ጢሞ 1፤15))
ስለ ከራድዮን ወፍ ምን ያክል እናውቃለን
"ከራድዮን ወፍ ይባላል
ከራድዮን ነጭ ወፍ ሲሆን በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው። ጠቢባን በድካም ፈልገው አድነው ይይዙታል፣ የታመመ ሰው ቢኖር ያቀርቡታል ፤ እሱም በሽተኛውን ትኩር ብሎ ያየዋል የማይድን ለሞት የቀረበ ከሆነ ፊቱን አዙሮ ይመለሳል፣ ቀኑ ገና ከሆነ ግን አፉን ከፍቶ ከበሽተኛው አፍ እስትንፋሱን ይወስዳል፣ በልዑል እግዚአብሔር ኃይል የሰውየው ደዌ ሙሉ ለሙሉ ወደ ወፉ በእስትንፋሱ ይተላለፋል። ሰውየው ይድናል ወፉ ይታመማል።
ፊት ነጭ የነበረው እንደ ከሰል ይጠቁራል፣ ህመም ሲሰማው ወደ አየር ይነጠቃል ሲብስበት ወደ ባህር ራሱን ይወረውራል። በባህር 3 መዓልት 3 ሌሊት ቆይቶ ጽጉሩን መልጦ አዲስ ተክቶ፣ድኖ፣ታድሶ፣ኃያል ሆኖ ይወጣል።
ይህ ፍጥረት በዕለተ። ሃሙስ እግዚአብሔር ፈጥሮታል።
ስለምን ፈጠርው ቢሉ የወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ለማያምኑ ትምህርት ምሳሌ አብነት ይሆን ዘንድ ሥላሴ ይህን ወፍ የማዳን ኃይል ሰተው ፈጥረውታል።
ትንታኔ፦
ከራድዮን ወፍ ---- የክርስቶስ ምሳሌ
የታመመው ሰው --- የአዳም ዘር ምሳሌ ሲሆን
ወፉ በዐይኑ መመልከቱ --- በክርስቶስ ላመነ ሁሉ ድኅነት ምህረት ማግኘቱ ምሳሌ
ወፉ መታመሙ---- ክርስቶስ ስለ እኛ በደል መታመሙ ምሳሌ።
መጥቆሩ ---- ስለእኛ ቤዛ ከኀጢአተኛ የመቆጠሩ ምሳሌ
ወፉ ወደ ላይ መውጣቱ---- ክርስቶስ ከፍ ብሎ መሰቀሉ ምሳሌ
ወፉ በባህር 3ቀን 3ሌሊት መኖሩ ----ክርስቶስ በከርሰ መቃብር 3ቀን 3 ሌሊት መቆየቱ ምሳሌ
ከራድዮን ወፍ ታድሶ ኃያል ሆኖ ከባህር መውጣቱ ---ክርስቶስ በሲዖል የነበሩ ነፍሳትን አድሶ አንጽቶ ገነት አስገብቶ፤ እርሱም ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በለበሰው ሥጋ ወደ ቀደሞ መለኮታዊ ሥልጣኑ ኃይሉ መቀመጡ ምሳሌ ነው።
  24ቱ ካህናተ ሰማይ ስም 
            -------------------

       1.አካኤል
       2.ፋኑኤል
       3.ጋኑኤል
       4.ጋድኤል
       5.አፋድኤል
       6.ዘራኤል
       7.ተዳኤል
       8.ኤልኤል
       9.ዮአኬል
       10.ጋርድኤል
       11.ልፋድኤል
       12.መርዋኤል
       13.ኑራኤል
       14.ክሥልቱኤል
       15.ኡራኤል
       16.ባቱኤል
       17.ሩአኤል
       18.ሠላትኤል
       19.ጣዉርኤል
        20.እምኑኤል
        21.ፔላልኤል
        22.ታልዲኤል
        23.ፐርሠዱኤል
       24.አልቲኤል   ናቸው ፡፡

በዚህ ዕለት ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ተነጥቀው 25 በመሆን ማዕጠንት ያጠኑበት ድንቅ ዕለት ነው ፡፡ ይህ ለማንም የማይቻል ለቅዱሳን ግን ተችሏል ምን የሚሳነው ነገር አለ  ፈጣሪ፡፡

አቡቀለምሲስ ዮሐንስም፦

1. " አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።

2. እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ።

3. ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ፡፡" በማለት ግልጽ አድርጎታል
(ራእይ 4 : 8-11፡፡)

ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም፦

☞"ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዓውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ፤ ካህናት የዓጥኑ በማዕጠንት ዘወርቅ" ( የሰማይ ካህናት በዙሪያው ይቆማሉ ፤ በዙፋኑ ፊት ሲሰግዱ ዘውዳቸውን ያወልቁ ነበር፤ በወርቅ ማዕጠንትም ያጥናሉ) በማለት ተናግረዋል፡፡

           በረከታቸዉ ይደርብን
አሜን፫
†       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


ንስሐ !

🕊


" የነበረውን ጦርነትና ድል ፤ የዲያብሎስን ድል መነሣትና የክርስቶስን ድል መንሣት ተመለከታችሁን? ንስሐ ምን ያህል እንደ ገነነችስ ተገነዘባችሁን? ዲያብሎስ ያን ቁስል መቋቋም እንዳቃተው እንዲያውም እጅግ እንደ ራደ እንደ ተንቀጠቀጠም አስተዋላችሁን?

ዲያብሎስ ሆይ ! ንስሐ እንደዚያ ስም አጠራሯ ከፍ ከፍ ሲል የምትፈራው  ለምንድን ነው? ነገረ ንስሓን ስትሰማ የምታዝነው የምትቆረቆረው ለምንድን ነው? በረዓድ በመንቀጥቀጥ የምትርበደበደው ለምንድን ነው?

“ይህቺ ንስሓ የሚሏት ብዙ ሀብት ንብሮቶቼን ቀምታ ወስዳብኛለቻ ! እንደዚህ ነዳይ ስታደርገኝ ታዲያ እንዴት አልዘን? እንዴትስ አልቆርቆር?” ይላል።

“ማንን ወሰደችብህ?”

“ዘማይቱን ሴት! ቀራጩን ሰው! ፈያታዪ ዘየማንን ! ተሳዳቢውን ጳውሎስ! ሌላም ብዙ ንብረቶቼን ቀምታ ወስዳብኛለች!"

በርግጥም ንስሐ ብዙ ንብሮቶቹን ወርሳበታለች፡ አምባውን አፍርሳበታለች፡፡ እስኪሞት ድረስም መትታዋለች፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! እናንተም ንስሐን ብታፈቅሯት ከላይ በተነገሩት ታሪኮች ላይ እንደ ተመለከትከው በርግጥ ታውቋታላችሁ፡ ለምን ታዲያ በንስሐ ቃላት ተድላ ደስታ አናደርግም? ለምን ታዲያ ዕለት ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመኼድ ንስሐ አንገባም?

ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፡፡ ጻድቅም ከኾንህ ከፍኖተ ጽድቅ እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፡፡ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና ና !"

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

  †       †       †

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

💖                🕊                   💖
2024/05/16 07:31:35
Back to Top
HTML Embed Code: