ያየ ሰው ሽመልስ ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪ ደራሲ ነው። 'ጎቲም ሲሞን' የሚል የልብ ወለድ መፅሐፍ አለው። የዛሬ 10 አመት አከባቢ ነው ያነበብኩት። በዛ መፅሐፍ ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ያለውን ፍላጎት በደንብ አሳይቷል።
ከፋና ሬዲዮ ጀምሮ እከታተለው ነበር። ትንታኔዎችን የሚያቀርብበት መንገድ ደስ ይለኛል። ENN ሲገባ ቋሚ ተከታታዩ ሆንኩ። አብይ ወደ ስልንጣን ሲመጣ ከመንጋው ጋር አልተነዳም። ነገሮችን በጥንቃቄ ለመከታተል ሞክሯል። ሊፈጠር የሚችለውን ቀውስ ቀድሞ ተገንዝቧል።
ENN ሲዘጋ ወደ ናሁ ቴሌቪዥን ገባ። እዛም እከታተለው ነበር።
ኢትዮ ፎረም ገና ጥቂት ተከታይ እያለው ጀምሮ እከታተላለሁ። (ኢትዮ ፎረም ላይ ከአበበ ባዩ ይልቅ በብዛት የምሰማው የያሰውን ነው)
በነገራችን ላይ በሐገራችን ያሉትን የሁሉንም ፅንፍ ሚዲያዎች በተቻለኝ መጠን እከታተላለሁ።
Omn፥ ርዕዮት ፥ ኢትዮ ፎረም ፥ ኢቲቪ ፥ ኢትዮ 360 ፥ የሃሳብ ገበታ ፥ ኩሽ ማዲያ፥ ምንግዜም ሚዲያ... ወዘተ። ሁሉንም እሰማለሁ። ከሁሉም የምቀበለው ደግሞም የማልቀበለው አለ።
ያየሰው ሽመልስ መፅሔት ላይ ሲፅፍ ብዕር ይታዘዝለታል። ቴድሮስ ፀጋዬ እና ያየሰው ሽመልስ ከሚጋሩት ፀጋዮች መካከል አንዱ የፅሐፍ ችሎታ ይመስለኛል። ሁለቱም ጥሩ ፀሐፊ ፥ ጥሩ ተናገሪ ፥ ጥሩ ጠያቂ ናቸው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሩ የህዝብ ግኑኝነት ባለሞያ ያስፈልጋቸዋል። እንደ ያየሰው አይነቱ ሰው ለእንዲህ አይነት ስራ የሚመች ይመስለኛል።
ብልፅግና ፓርቲ በማህበራዊ ሚዲያ ፥ በሜይንስትሪም ሚዲያ ወዘተ ብዙ ፕሮፖጋንዲስቶች አሉት። እኒያ ሁሉ ቢጨመቁ የያየሰውን ሩብ ያህል ተፅዕኖ አይፈጥሩም። በእሱ ፊት ሁሉም ደካማ ናቸው። ምክኒያቱም እሱ በማንበብ አቅም ፥ በፅሉፍ ችሎታ ፥ በስል አንደበት ፥ ሃሳቡን በማደራጀት አቅም ይበልጣቸዋል።
አንዳንድ ሰዎች ያየ ሰውን በወገንተኝነት ይከሱታል። ለምን እንደሚከሰስ ይገባኛል። ግን ያየሰውን በወገንተኝነት የሚከሱ ሰዎች ከእሱ መማር ያለባቸው ቁም ነገር አለ። እሱ በሚሰራበት አቅም ልክ እነሱ ለሚወግኑለት አካል ለመስራት ይጣሩ።
መውጫ ፥
ያየሰው ፈገግ የሚያሰኙኝ አገላለፆች አሉት።
1፥ አብይ አህመድ በሙስሊሙ ኢድ ጊዜ እንደ ሙስሊም በክርስቲያኑ በዓል ጊዜ እንደ ክርስቲያን መሆን መለያው ነው። ይሄን አይቶ ያየሰው "ለፋሲካ ጊዜ የኢየሱስ ወታደር ፥ ለአረፋ ጊዜ የአሏህ ወዛደር" ብሎታል።
2፥ አብይ ወደ ስልጣን የመጣ ጊዜ ከእግሩ ስር መነጠፍ የፈለጉ የአማራ ኤሊቶች ነበሩ። የአብን ሰዎች ፥ የብአዴን ሰዎች ፥ ዛሬ ተቃዋሚ የሆኑ አክቲቪስቶች ወዘተ። እኚህ ሰዎች ያኔ አብይ ሲጋራ ሲያጬስ ቢመለከቱ 'የኔን መዳፍ መተርኮሻ አድርገው' ይሉት ነበር። ያየሰው እኚህን አደር ባዮች "የአብይ አማራ" ብሎ ይጠራቸዋል።
3፥ ተማሪዎች 12ኛ ክፍል ላይ በብዛት ይወድቃሉ። ለወደቁ ተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ ማንም ግድ አይሰጠውም። ይሄን የታዘበው ያየ ሰው "ብርሃኑ ነጋ ሲጥላቸው ብርሃኑ ጁላ ያነሳቸዋል" አለ።
ዞሮ ዞሮ ፥ ፕሮፖጋንዳ መስራት የምትፈልጉ ፥ ዜና መስራት የምትወዱ ወዘተ ከያየሰው ተማሩ።
@Tfanos

👍14❤5👎1😁1
ፍልስፍና ምንድነው?
አንዳንዶች ፍልስፍና ፀረ ሐይማኖት እና ፀረ ባህል ይመስላቸዋል። በእርግጥ ፍልስፍና ምንድነው? ፍልስፍና ምን ይጠቅማል?
የዛሬው ደርዘን ጥያቄዎች አጀንዳ ፍልስፍና ነው። እንግዳዬ Yonas Tadesse Berhe ነው።
አድምጡት። ብትችሉ ለሌሎችም አጋሩ። አስተያየታችሁን በቻናሌ ስር ብትሰጡም እወዳለሁ
https://youtu.be/j_-sAO2DwYc

YouTube
ፍልስፍና ምንድነው? ፍልስፍና እና ሐይማኖት አብረው ይሄዳሉ? ቆይታ ከዮናስ ታደሰ በርሄ ጋር #philosophy #ethiopia #books #ebs
በሐገራችን ፍልስፍና እና ሐይማኖት አብረው የማይሄዱ ተደርገው ይቆጠራሉ። በእርግጥ ፍልስፍና ምንድነው? በዚህ ፕሮግራም ስለ ፍልስፍና ምንነት እንወያያለን #ethiopia #books #habesha
👍4
እንቁ ግርማ የተወደደ የመዝሙር አቀናባሪ ነው። ብዙ ተወዳጅ መዝሙሮችን ሰርቷል።
ብዙ ጊዜ "ምናለ እንቁ የተወሰኑ ዘፈኖችን አቀናብሮ በነበር?" ብዬ ተመኝቼ አውቃለሁ። በእርግጥ ይሄ ለአንድ ክርስቲያን ስነ ምግባር የጎደለው ምኞት ይሆናል።
ለ ቀድሞዋ ጋዜጠኛ ለአሁኗ ፖለቲከኛ፥ ሚስጥረ ስላሴ ታምራት 'እንቁ ዘፈን አቀናብሮ ቢሆን ኖሮ ኤሊያስ መልካ አይገንም ነበር። እንቁ ኤሊያስን ይበልጣል' ብዬ አናድጃት አውቃለሁ።
መዝሙር ለመንፈሳዊ ዋጋው እንጂ ለሙዚቃ ቅንብሩ መደመጥ የለበትም የሚል ሰው ቢገጥመኝ ልክ ነህ እለዋለሁ። ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ አንዳንድ የመዝሙር ቅንብሮች ይገርሙኛል።
የተስፋዬ ጫላ "ኢየሱስ" የሚለውን ቅንብር የሚያህል የለም። በጣም የተለየ ስራ ነው። በተለይ ኢንትሮው ይገርመኛል። የዮሴፍ በቀለ "መስቀልህ ስር" የሶፊያ "በምህረቱ ባለጠጋ" የአውታሩ "ይቅርታ" እያልን ብዙ ገራሚ ቅንብሮች ማንሳት እንችላለን። የእንቁ ስራዎች ናቸው።
ብቻ እንቁ ግርማ ዘፈን አቀናብሮ ቢሆን ኖሮ እያልኩ መመኘት ማቆም አልቻልኩም። እኔ ሃጢያተኛ ሰው ስለሆንኩ ዘፈን እወዳለሁ። ሀጢያተኛ ሰው ስለሆንኩ እንቁ ዘፈን ቢያቀናብር እላለሁ።
ጌታ ልብ ይስጠኝ

👍5😁2👎1
የብልፅግና ሰዎች "Tplf በንፋስ የተበተነ ዱቄት ነው" ሲሉን ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ "ስልጣን ቢየዙ እንኳ በምን ሞራል ህዝብ እንመራለን ይላሉ" እያለ ነበር።
የህወሓት ሰዎች "ከዚህ በኋላ አብይን የሚያድነው የለም" ሲሉ ነበር። "ጦርነቱን ጨርሰናል" ብለው ሲፎክሩ ነበር።
ህወሃት "የትግራይን ህዝብ ከጥፋት ለማዳን ነው የምዋጋው" ብሎ ነበር። ፌደራል መንግስት "ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለማዳን ነው የምዋጋው" ብሎ ነበር። ከሁለቱም ወገን የተነገረውን አምነው ህይወታቸውን የገበሩ ብዙ ናቸው።
አሁን ሂሳብ ማወራረድ ያስፈልጋል። ለህወሓት ሰዎች "እኛ ልጆቻችንን ሰጠናችሁ። እናንተስ የትግራይን ህዝብ ከጥፋት አዳናች ወይ?" መባል አለባቸው። ቢያንስ መጠየቅ አለባቸው።
ለብልፅግና ሰዎች "እኛ ልጆቻችንን ገበረን። እናንተስ ኢትዮጵያን ከመፍረስ አዳናችሁ? አሁን ሐገራችን ወዴት እየተንደረደረች ነው?" ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።
ለሁለቱም ሀይሎች "የነገራችሁንና የሆነው አንድ ነው ወይ?" የሚል ጥያቄ ማቅረብ ያስፈልጋል።
መታረቃቸው ፥ መሿሿማቸው ጥሩ ነው። ግን ደግሞ ትላንት የተናገሩትን እያስታወሱ መገማገም ጥሩ ነው።

👍8❤3😢2🤔1
ድሮ ቸርች የማልቀር ሰው ነበርኩ። 10ኛ ክፍል ሳለሁ የስነፅሁፍ ቡድን መሪ ነበርኩ።
በዛን ወቅት በተለምዶ "ተካፋች" የሚባለው ስልክ የነበረኝ ሲሆን ማንንም ሰው በተለይ የቸርች ሰው ማስነካት አልፈልግም ነበር። ስልኬን በሆነ ምክኒያት ለቸርች ሰው ፥ ለቤተሰብ አባል... ብሰጥ እጃቸው ላይ እንዳይቆይ ጥረት አደርጋለሁ። በሆነ አጋጣሚ ሰዎች ስልኬን ቢበረብሩት ሃጢያተኛ ሰው መሆኔን ስለሚያውቁ ስልኬን ከሰው አርቃለሁ።
ከእለታት በአንዱ Nehemiah Byn ስልኬን ሲጎረጉር ጉዴን አገኘው። በሰአቱ ቆሌዬ ነበር የተገፈፈው። "እንዴት ያለኸው ሃጢያተኛ ነህ?" እንደሚለኝ አስቤ ተሳቀቅኩ።
ነህሚያ ፈገግ ብሎ "ለካ ዘፈን ትሰማለህ" አለኝ። እየተቅለሰለስኩ "ደካማ ነኝ። በዘፈን ሃጢያት እፈተናለሁ። ብቻ እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ" አልኩት።
"እኔም ዘፈን እሰማለሁ" አለኝ። እሱ በወቅቱ ላፕቶፕ ነበረው። በድብቅ ዘፈን ይሰማ ነበር። (ነህሚያ ገመናዬን አወጣህ ብሎ እንደማይወቅሰኝ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ንስሃ ገብቶ ዘፈን መስማት አቁሟል😎) ነህሚያ የሃጢያት ጉዳይ ባልደረባዬ የሆነ መሰለኝና ደስ አለኝ። ከዚያ በኋላ በጣም የልብ ጓደኛሞች ሆንን። (ሀጢያተኞች ጓደኛሞች ይሆናሉ😂
አንድ እለት የስነፅሁፍ ፕሮግራም አዘጋጀን። ቸርች ነው ፕሮግራሙ። የቡድኑ መሪ እንደመሆኔ ብዙ ስራ ነበረብኝ። ሃሳቤን ለመሰብሰብ የሆነ ጥግ ላይ ተነጥዬ ተቀምጬ ኤርፎን ጆሮዬ ላይ ሰካሁ። ቤቲ የምትባል የቡናችን ልጅ ድንገት ከጆሮዬ ኤርፎኑን ነቅላ ጆሮዋ ላይ ሰካችው። ያኔ ቆሌዋ ተገፈፈ።
"ዘፈን ትሰማለህ?" አለችኝ። የምለው ግራ ሲገባኝ ዝም አልኩ። "እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ" ብላኝ ሄደች። ቸርችው ውስጥ ዘፈን በመስማቴ ንስሃ ገባው። ንሰሃ ከገባሁ በኋላ ዘፈን መስማቴን ቀጠልሁ
አንድ እለት ከቃለህይወት ተመልሼ ቤት ተመስጬ ዘፈን ስሰማ እናቴ ደረሰች።
"እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ። ያውም ከቸርች መጥተህ ዘፈን ትሰማለህ?" አለችኝ። ድንጋጤዋን አልረሳውም።
የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ፈራ ተባ እያልኩ ጥያቄ ሰንዝሬ ነበር። "ፓስተር ዘፈን ሃጢያት መባሉ ትክክል ይሆን?" ብዬ ጠይቄቅኹ። ፓስተራችን በጣም ገሰፀኝ። ከዚያን በኋላ በድብቅ ዘፈን መስማቴን ቀጠልኹ። ዘፈን ስሰማ ሃጢያተኝነት ይሰማኛል። ቢሆንም እሰማለሁ።
አሁን ከ Elroe Fida ጋር ስልክ እያወራን ነበር። ከድሮ ጀምሮ ታውቀኛለች። "አንተ እኮ ከጥንት ሃጢያተኛ ነህ። በዛች ተካፋች ስልክ ዘፈን እንደምትሰማ አውቅ ነበር" አለችኝ።
አንድ እለት ጓደኛዬ Yitagesu Amare መፅሐፍ አዋሰኝ። የዮናስ ጎርፌ መፅሐፍ ነው። ቤት ያጣው ቤተኛ ይላል ርዕሱ። በእርግአኝነት ትወደዋለህ አለኝ። ይዘቱን ጠየቅኩት። "ዘፈን ሃጢያት እንዳልሆነ ያብራራል" አለኝ። በጣም ደስ አለኝ። መፅሐፉን ሳላነበው በመፅሐፉ ሃሳቦች ለመስማማት ወሰንኩ።
የዮናስ ጎርፌን መፅሐፍ ያነበብኩ ጊዜ "ዘፈን ሃጢያት አይደለም ብዬ ለመከራከር ሰበብ አገኘሁ" አልኩ።
ብቻ ጌታ ልብ ይስጠኝ

😁8👍4🔥1
ማድሪድ አርሰናል ላይ ሁለት ጎል ካገባ በኋላ እስከ 94ኛው ደቂቃ ምንም ሳያገባ ቆይቶ በ94ኛው ደቂቄ ቢያገባ ደስ ይለኛል።
አርሰናሎች ጭንቀት እና ተስፋ መሓከል ቆይቶ ባለቀ ሰአት ሲገባባቸው የሚፈጠርባቸው ድንጋጤ 👌
ከዛ ጨዋታው ወደ ፍፁም ቅጣት ምት አምርቶ ማድሪዶች የመጀመሪያውን ቢስቱ... ከዛ እንደሚያሸንፉ ካመኑ በኋላ የመጨረሻውን ሁለቱን ቢስቱ 👌
አርሰናሎች ተስፋ እያደጉ ተስፋቸው ሲከዳቸው ደስ ይለኛል።
ከዛ ደግሞ ማድሪድ ቀጣይ ጨዋታውን በቀላሉ ቢሸነፍና አርሰናሎች በማድሪድ መሸነፍ አልነበረብንም እያሉ ቢንገበገቡ
ይቅናን

ቀደም ሲል ማንነታቸው ያልታወቀ አካላት ገፄን ጠልፈውት ነበር።
ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ስለማድሪድ ሲፅፉ ነበር።
ማድሪድ ማን ነው? ቡድን ነው? ሰንሰል ነው? ብረት አስተኔ ነው?
ድል ለታላቁ አርሰናል

😁14👍1👎1🥰1
ከዛሬው ጨዋታ በፊት ማድሪዶች "ውጤት እንቀለብሳለን" ሲሉ ነበር። ከዛሬው ጨዋታ በኋላ "15 ዋንጫ አለን" የሚል ፕሮፖጋንዳ ይነዛሉ።
አሴ ማነው አርሴ ግን ሞያ በልብ ነው። አርሰናል ከፈለገ የአለም ዋንጫ ሁላ ይበላል።
እንደውም ማድሪድ እስከዛሬ 15Ucl የበላው ታላቁን መድፈኛ ስላልገጠመ ነው።
ለማንኛውም የሀሙስ ከነማ ደጋፊዎች እኛ እንዲህ ነነ
(ሁላችሁም 'አለቀ ፥ ተጠናቀቀ' በሚለው የአብነት አጎናፍር ዘፈን ተባረኩበት

🔥7❤1👍1👎1🥰1
መሰረት ሚዲያ የፖስታ አገልግሎት ድርጅትን የሚመለከት ዜና አጋርቶ ነበር። የድርጅቱ ምክትል ስራ አስፈፃሚ የሆነው ጋሻው መርሻ ለዜናው ምላሽ ይሆን ዘንድ ተሳድቧል። (ዜናውን ከመሰረት ሚዲያ መመልከት ትችላላችሁ። የዜናው ጥቅል ጭብጥ ድርጅቱ ለማኔጅመንት አባላት ብነስ ስለመስጠቱ ነው)
ጋሻው መርሻ በሰጠው ምላሽ ምን ያህል ስርኣት አልበኛ እና ሃላፊነት የማይሰማው ሰው መሆኑን አሳይቷል። " ደ ደ ብ ፥ ደን ቆ ሮ..
" የሚል የስድብ ቃል ተጠቅሟል።
እሱ ፖለቲከኛ ፥ የህዝብ ተወካይ ፥ የተቋም መሪ ነው። ከተርታ ሰው የመሻል ግዴታ አለበት። ግዳታ!
ስሜትን መግዛት ፥ በጨዋነት ማስረዳት ወዘተ ግዴታው ነው። በዚህ ደረጃ ስሜቱን የማይገዛ ሰው ሆኖ ትልቅ ተቋም የሚመራው እንዴት ነው? ህዝብን የሚወክለው በየትኛው ስነምግባር ነው? የህዝብ ችግር መፍቻ ትዕግሥት ከየት ያመጣል? ዛሬ ስለሚራው ተቋም ትችት ሲሰነዘር ስድብ ያዘነበ ሰው ነገ ከፍ ያለ ስልጣን ቢኖረው ተቃዋሚዎችን ምን ያደርጋል?
መሰረት ሚዲያ ያጋራው መረጃ ሃሰት ቢሆን እንኳን የጋሻው ምላሽ ለሃላፊነት ብቁ አለመሆኑን አሳይቷል!
መፅሐፍ ቅዱስ ከተማ ከሚገዛ ራሱን የሚገዛ ይበልጣል ይላል። እንደ ጋሻው ያሉ ፖለቲከኞች ተቋምን ከማስተዳደር በፊት ስሜታቸውን ማስተዳደር ቢማሩ ጥሩ ነበር

👍11
"ፌሚኒስት ሴቶች አስቀያሚ ናቸው"
* * *
"ፌሚኒስት ሴቶች ሁሉ መልከ-ጥፉ ናቸው" ይባላል።
ፌሚኒስት ሴቶች ወደ አደባባይ የወጡት ለቁንጅና ውድድር አይደለም። ስለዚህ ስለ መልካቸው አስተያየት መስጠት አስተዛዛቢ ነገር ነው።
አጀንዳቸው 'የሴቶች መብት ይከበር' የሚል ነው። አቀራረባቸውን መተቸት ፥ ሃሳባቸውን መሞገት ፥ አጀኝዳቸው ላይ መወያየት ፥ ነጥባቸውን አለመቀበል ይቻላል። ነገር ግን 'መልከ-ጥፉ ናቸው' ማለት ትዝብት ላይ ይጥላል።
እንደተባለው ፌሚኒስቶች ሁሉ መልከ-ጥፉ ናቸው ብለን እንመን። ታዲያ ምን ይጠበስ?
1ኛ ፥ ሰውን በመልኩ ለማሸማቀቅ መሞከር በጣም አሳዛኝ አለመሰልጠን ነው። በሰው መልክ መሳለቅ ነውር ነው።
2ኛ ፥ ሰዎች አንድ ሃሳብ ሲያነሱ ከቻሉ መወያየት ፥ መሞገት እና መከራከር መሰልጠን ነው። ልዩነትን ለማጥበብ አልያም የተለየ መንገድን ለማየት ይረዳል። ይህ ካልሆነ ከነ ልዩነት ዝም ብሎ መተውም ሌላ አማራጭ ነው። ነገር ግን ሃሳቡን በመሞገት ፋንታ በሰው መልክ መሳለቅ የተሸናፊ ሰው ባህሪ ነው። ያለ አዋቂ ሰው መገለጫ ነው።
ፌሚኒስቶች ሃሳብ በሰነዘሩ ቁጥር "እነሱ መልከ-ጥፉ ናቸው" ማለት የለየለት ሃሳብ አጠርነት ነው።
3ኛ ፥ ፌሚኒስት ሴቶች መልከ-ጥፉ ቢሆኑ እንኳን የመብት ጥያቄ ለማንሳት መብት አላቸው። "መብታችን ይከበር" የማለት መብት ያላቸው መልከኛ ሴቶች ብቻ አይደሉም። "መልክ የለሽም" እያሉ ለማሸማቀቅ መሞከር "መብት የሚገባው ለቆንጆ ብቻ ነው" የማለት ያህል ነው። ነውር ነው!
በአጭሩ "ፌሚኒስት ሴት መልከ-ጥፉ ናት" እያሉ ማላዘን ነውር እና ሃሳብ አጥርነት ነው።

👍7🥰1
ካቶሊካዊያን "እንዲህ እና እንዲያ አደረግን" ብለው ሲመፃደቁ አንሰማም። ነገር ግን ለሐገራችን ያደረጉት የሚቆጠር በጎ ነገር አለ። በተለይ ዘመናዊ ትምህርት ማስፋፋት እና ጤና ላይ የሰሩት ስራ በጣም የሚመሰገን ነው።
ለምሳሌ በከተማዬ ሻሸመኔ ከድሮ ካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት የሚባል አለ። እኛ ከልጅነታችን ጀምሮ "ሚሽን ትምህርት ቤት በስነምግባር የታወቀ ፥ ጎበዝ መምህራን ያሉት" ሲባል እንሰማ ነበር።
መክፈል የማችይሉ በነፃ የሚማሩበት ፥ መክፈል የሚችሉ ተመጣጣኝ ክፍያ ከፍለው የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው።
ካቶሊክ ሚሽን ክሊኒክም በጣም የተመሰገነ ነው። ዋጋቸው ርካሽ ፥ ህክምናቸው ጥሩ እንደሆነ እሰማ ነበር። (እናቴ ጥሩ እና ርካሽ ክሊኒክ መሆኑን ስታወራ ሰምቻለሁ)
ካቶሊኮች በመላው ሐገሪቱ ውስጥ አሻራቸውን አኑረዋል። ለዚህ ምስጋና አልጠየቁም። እወቁልን አላሉም።
ዛሬ ፖፑ መሞታቸውን ስንሰማ እንዲህ ያሉ ውለታቸውን አስታውሰን ከካቶሊካዊያን ጋር በጋራ ማዘን ይኖርብናል።

👍13❤3
የመፅሐፍ ቀን ነው። ይህን ምክኒያት በማድረግ የምንወዳቸውን መፅሐፍት ብንጠቁምስ?
እኔ ግለ ታሪክ ማንበብ እወዳላሁ። የሰዎችን ህይወት ታሪክ ማንበብ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ እንዳለው አምናለሁ። በተለይ የኢትዮጵያዊያንን ታሪክ ማንበብ ከምንጋራው የጋራ ስነልቦና እና የጋራ ተግዳሮት አንፃር ብዙ ትምህርት ይሰጡናል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ የምወዳቸውን ልጋብዝ
(ቅደም ተከተሉ በዘፈቀደ ነው
1፥ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ "ህብር ህይወቴ"
2፥ ፓስተር ታምራት ሀይሌ "የታምራት አምላክ ታምረኛ"
3፥ ዶክተር ጥላዬ ታደሰ "ጥላዬን ቀደምኩት"
4፥ ተመስገን ገብሬ "ህይወቴ"
5፥ ስዩም ወልዴ ራምሴ "ኩርፊያ የሸነፈነው ፈገግታ"
6፥ አምባሳደር ብርሃኑ ድንቁ "ብቻዬን ቆሜያለሁ"
7፥ ፊት አውራሪ ተክለሃዋሪያት "ኦቶ ባዮግራፊ፥ የህይወቴ ታሪክ"
8፥ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ "ህይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ"
9፥ ደጃዝማች ወልደሰማዕት "ህይወቴ" (ይህ መፅሐፍ ተራ ቁጥር አራት ላይ ከተጠቀሰውጋ በርዕስ ይመሳሰላል)
10፥ ፋሲካ ሲደልል "የሻሞላው ትውልድ"
11፥ ህይወት ተፈራ "ማማ በሰማይ"
12፥ አምባሳደር ታደለች "ዳኛው ማነው"

👍10
መለስ ዜናዊ ደራሲ ጭምር እንደሆነ ታውቃላችሁ?
በዛሬው ዳሳሽ ወግ ስለ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር አንዳንድ ጉዳዮችን እናወጋለን።
በዛውም ዩቲዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ አድርጉ ፥ ሃሳብ አስታያየትም አጋሩ
https://youtu.be/_Xb0Mnn44aY?si=g-F3UcYZzUrBWZEL

ስለ መለስ ዜናዊ ያልተሰሙ ሚስጥሮች፤ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ደራሲ እና ጋዜጠኛ ጭምር ነበር። #ethiopia #books #motivation
#ethiopia #habesha #podcast #books #ebs #abelbirhanuየወይኗ
ጆርዲ በዛብህ የምትባል ፌሚኒስት አለች። ቲክቶክ ላይ ትታወቃለች።
ሰሞኑን አንድ ሰው "የጆርዲ የራቁት ቪዲዮ" በሚል ለቀበባት። ራሷ እንደተናገረችው ከሆነ ልጁ በቴሌግራም ጭምር ሲያስፈራራት ነበር።
ቀጥሎ ጆርዲ የተባለው ቪዲዮ የሷ እንዳልሆነ አስረዳች። የሌላ ሴት ቪዲዮን ኤዲት በማድረግ የሷ አስመስለው እንደሰሩባት አብራራች። ነገር ግን ብዙ ሰው አላመናትም። ሰዎች ተሳለቁባት።
ቲክቶክ ላይ ስሟ ሰርች ሲደረግ "የራቁት ቪዲዮ" የሚል ፅሁፍ ተያይዞ ይመጣል። የስብዕና ግድ*ያ ነው የተፈፀመባት።
ልጅቷ የሴቶች መብት ነው ትኩረቷ። ለሰዎች መብት የሚከራከርን ሰው ያለ ቅደመ ሁኔታ አከብራለሁ። ለደካሞች ድምፅ የሚሆን ሰው ክብር ይገባዋል።
በአቀራረቧ ፥ በአንዳንድ ነጥቦቿ ላይ አልስማማም። ይህ የሚከበር ልዩነት ነው። የሷን ነጥቦች አለመቀበል መብት ነው። ነገር ግን እሷን በግል ማጥቃት የለየለት ነውር ነው። የሃሳብ የለሾች ባህሪ ነው። ያልወደድነው ሃሳብ ሲኖር ሃሳቡን በመሞገት ፋንታ አሳቢውን ማጥቃት ሲበዛ ኋላቀርነት ነው።
ጆርዲ ራሷን ነፃ ማድረግ ስለነበረባት እውነታውን ልታጋልጥ ወሰነች። ቪዲዮው የሷ እንዳልሆነ በማስረጃ አቀረበች። የቪዲዮው ባለቤት ማን እንደሆነች የሚያሳይ ቪዲዮ ሰራች።
ይሄኔ ሰዎች ይቆጧት ጀመር። "የብልግና ምስሉን ባለቤት ለምን አጋለጥሻት" አሉ።
ጆርዲ ምን ማድረግ ነበረባት? ያቺ ሴት ራሷን ለችግር የሚዳርግ የብልግና ቪዲዮ ሰርታ ለቃለች። ለገዛ ጥፋቷ ራሷ ሃላፊነት ትውሰድ።
ጆርዲስ? ያለ ስሟ ስም ሲሰጣት ዝም ትበል? የስብዕና ግ ዲ ያ ሲፈፀምባት በፀጋ ትቀበል? "እኔ አይደለሁም" ብላ ስታብራራ ላላመኗት ሰዎች እውነተኛዋን ሴት ከማጋለጥ ውጭ ምን ምርጫ ነበራት?
ከሳሾቿ በሷ ቦታ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ? አንዳንዴ ግብዞች መሆን አያስፈልግም። እኛ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ብንገኝ ለሌላ ሰው ስንል ራሳችንን አንሰዋም። እንደዛ ማድረግም አይጠበቅብንም።
በዚህ ታሪክ ጆርዲ ተጠቂ ናት። ራሷን ነው የተከላከችው። ተጠቂን መውቀስ አግባብ አይደለም።
ለማንኛውም የጆርዲ ታሪክ ሁለት ጠቃሚ ትምህርት ሊሰጠን ይገባል።
1ኛ ፥ ማንኛውም ሰው የፖለቲካ አቋሙ ፥ ግላዊ አስተሳሰቡ ፥ ዝንባሌው ፥ የሚያራምደው አቋም ወዘተ ስህተት ቢሆን እንኳን በግል ለማጥቃት መሞከር እና ስም ማጥፋት ነውር ነው። ያለማሰብ ምልክት ነው።
2ኛ ፥ ተጠቂዎችን መልሶ መውቀስ ጭካኔ ነው። ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ መረዳት አስፈላጊ ነው። ማንም ሰው ራሱን ለመከላከል ሲሞክር ሰውዬው ላይ ድንጋይ መወርወር ነውር ነው።
Via ተስፋኣብ ተሾመ

👍12👏3
መብት የሚገባው ለማን ነው?
ይኸን ፅሁፍ መፃፍ ያሳፍረኛል። የሰውን ንቃተ ህሊና የመናቅ ያህል መስሎ ይሰማኛል። ቢሆንም ግን ቀላል ቁጥር የሌላቸው ሰዎች መሰረታዊ ነገርን ስለሚስቱ ማስተማር ያስፈልግ ይሆናል።
መብቱ ሊከበርለት የሚገባው ማነው? ሰብአዊ ክብሩ ሊጠበቅለት የሚገባው ማነው? ድንበሩ መነካት የሌለበት ማነው?
አንድ እጅ ላይ አምስት ጣቶች እንደሚኖሩ ማስተማር ያሳፍር ይሆናል። ይኸን የሚስት ሲኖር ግን የግድ መናገር ያስፈልጋል። ሰዎች ሁሉ መብታቸው ሊከበርላቸው እንደሚገባ ሁሉም ሰው ሊያውቅ ይገባ ነበር።
አንዳንድ ሰዎች አስተሳሰባቸውን አንወደውም ፥ የአንዳንድ ሰዎች አቋም አያስደስተንም ፥ አንዳንዶች አለአዋቂ ናቸው ፥ አንዳንዶች ሃሳባቸው አይረባም። ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን መብታቸው ሊከበር ፥ ሰብአዊ ክብራቸው ሊጠበቅ ፥ ድንበራቸው ሊከበር ይገባል።
እኛ የማንወደውን አቋም የሚያራምድን ሰው ለማዋረድ መሞከር ፥ ሲጠቃ ጥቃቱን መደገፍ ፥ ሰብአዊ ክብሩን መግፈፍ የበዛ ኋላቀርነት ነው።
ሰዎች የሚያራምዱት የፖለቲካ አቋም ፥ የፆታ አስተሳሰባቸው ፥ ሃይማኖታዊ መረዳታቸው ፥ ለነገሮች ያላቸው ብያኔ ከእኛ ተፃራሪ ሲሆን የጥቃታቸው ተባባሪ መሆን አሳፋሪ ኋላ ቀርነት ነው። "እሱ እኮ እንዲህና እንዲያ ያስባል" በሚል ሰበብ የሰዎችን ክብር ማዋረድ ነውር ነው።
በእርግጥ እንዲህ ያለ ነገር መፃፍ አስፈላጊ አልነበረም። ይኸን ሁሉም ሰው ሊያውቀው የሚገባ መሰረታዊ ነገር ነበር። ነገር ግን ብዙዎች መሰረታዊ ነገርን ይስታሉ።
ሃሳብን ትቶ አሳቢውን ማጥቃት የሃሳብ የለሾች ባህሪ ነው። ሰዎች የማትወዱትን ሃሳብ ሲያራምዱ ሃሳባቸውን በምክኒያት መዶሻ አፈራርሱት ፥ በማስረጃ ተሟገቱ ፥ አሳምኑ ፥ እመኑ ፥ ወደ አማካይ ነጥብ ተጓዙ። ይህን ማድረግ ካልወደዳቸው በዝምታ እለፉ። በዚህ ፋንታ ሰውዬውን ማጥቃት ፥ መሳደብ ፥ መሳለቅ የኋላቀርነት ደ ዌ ነው።
በእርግጥ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ለመጠቀም ለበቃ ሰው እንዲህ ያለ መሰረታዊ ነገር ለማስረዳት መገደድ ያሳዝናል!

ፌሚኒዝምን እንርሳው።
በሐገራችን ያለው መሰረታዊ የሆነ የመብት ጥሰት ነው። ሴቶች በጣም መሰረታዊ መብታቸው ይጣሳል።
በባላቸው ይደበደባሉ ፥ አፈቀርኩ ባይ ነሆለል አሲድ ይደፋባቸዋል ፥ ይደፈራሉ ፥ ገላቸው የጦር ሜዳ ይሆናል ፥ ከገዛ ቤተሰብ ጥቃት ይሰነርባቸዋ፥ ይገደ*ላሉ... ወዘተ።
ፌሚኒዝም ምናምኒዝም የሚለውን እንርሳው። እዚህ ሐገር ሴቶች መሰረታዊ የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል።
ለሴቶች ድምፅ መሆን የህሊና ግዴታ ነው።
አሳዛኙ ነገር አንድ ሰው ስለሴቶች መብት በለሆሳስ ሲያወራ እልፍ ፍረጃዎች ይለጠፋሉ። ሴቶችን "አጉል ፌሚኒስት አትሁኚ" ከሚል ጀምሮ "ሌዝ ቢያን ፥ ወንድ ጠል" ማለት የሚቀላቸው አሉ። ወንዶችን ደግሞ "አሽቃባ*ጭ ፥ የፌሚኒስት ትኩረት ፈላጊ ወዘተ" ማለት..
እንደው ሰው መሰረታዊ ነገር መረዳት ያቅተዋል?
ፌሚኒዝምን እርሱት። እዚህ ሐገር ሴቶች የተጫነባቸው የመከራ ቀንበር ሊያሳስበን ይገባ ነበር እኮ።

👍5❤1
ምዕራባውያንን በተመለከተ አሉታዊ አስተሳሰብ ያላቸው ብዙ ናቸው። ነገር ግን ዮናስ ታደሰ "ምዕራባውያን ይመስገኑ" ይላል።
ምዕራባውያን እነማን ናቸው? መሰረታዊ ፍልስፍናቸው ምንድነው? ለምን ሲባል ይመስገኑ? ደርዘን ጥያቄዎች ላይ ያደረግነውን ቆይታ ይከታተሉ።
https://youtu.be/yXD-RldqjfM

ወደ ምዕራባዊያን እንመልከት ፥ ምዕራባዊያን ይመስገኑ። ፍልስፍና ምንድነው? ከዮናስ ታደሰ ጋር የተደረገ ክፍል ቆይታ ክፍል ሁለት #ደርዘን_ጥያቄዎች
ኢትዮጵያ ከፌልስፍና ማግኘት ያለባትን እውነተኛ ጥቅም ሳታገኝ የቆየችበት ምክኒያት ምን ይሆን? #ethiopia #books #habesha