Telegram Web Link
"የሴት ልጅህን ብልት ተልትለሃል" አሉት።

"ወላሂ አላደርኩትም" ቢልም አልታመነም። ምስክሮች ቢደረድርም ተቀባይነት አላገኘም። "ስለት ተጠቅመህ የገዛ ልጅህን ብልት የተለተልክ አ ረ መ ኔ ነህ" አሉት።

ካሊድ ይባላል። ኢትዮጵያዊ ነው። ውልደት እና እድገቱ መርካቶ ነበር። በትምህርቱ ሰቃይ፥ በባህሪው ምስጉን ሆኖ አደገ። ካደገ በኋላ ለብዙ ሰዎች "የተስፋይቱ ምድር" ወደ ሆነችው አሜሪካ አቀና። በአሜሪካ ኑሮውን ቀጠለ።

በአሜሪካ ሳለ ከደቡብ አፍሪካ ከሆነች ሴት ጋር ተዋውቆ ትዳር መሰረተ። በፍቅር የተሟሟቀ የትዳር ቆይታ ነበራቸው። በትዳራቸው ሴት ልጅ አፍርተዋል።

ከእለታት በአንዱ ጎጇቸው ዘመመ። ትዳራቸው ተነቃነቀ። ፍቅራቸው ደፈረሰ።
የደፈሰው አልጠራም። የዘመመው አልተቀናም። ትዳራቸው ፈረሰ።

ከትዳራቸው መፍረስ በኋላ "ክፉኛ እጎዳሃለሁ" ብላ የቀድሞ ሚስት ዛተች።..
አንድ እለት ለካሊድ መጥሪያ ደረሰው። በቀድሞ ባለቤቱ ክስ እንደተመሰረበት ተነገረው። ክሱ "ሴት ልጅህን ገርዘሃታል" የሚል ነበር። ካሊድ የተባለው አስገርዘሃታል አይደለም። ገርዘሃታል ነው።ክሱ በገዛ እጅህ ሴት ልጅህን ገርዘሃታል የሚል ነው።

ካሊድ ክሱን ሊያስተባብል ፍርድ ቤት ቀረበ። "አላደረግኩትም" አለ። "በሃይማኖቴም በባህሌም የሴት ልጄን መራቢያ መመልከት ፥ መነካካት አይፈቀድልኝም። እንዴት አድርጌ እገርዛታለሁ?" አለ። ሰሚ አላገኘም። "አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ፥ ሐገርህ ኋላቀር ናት። ጎጂ ልማዶች ካሉባት ሐገር መምጣትህ ብቻውን ያስጠረጥርሃል" አሉት።

ማስረጃዎችን ደረደረ።

ልጅቷ ተገረዘች በተባለችበት ወቅት ካሊድ ስራ ላይ ነበር። ስራ ገበታው ላይ ለመሆኑ ማስረጃ አቅርቧል። ከሳሽ "ከስራው ቀርቶ ነው የገረዛት" ነበር ያለችው። በተባለበት ወቅት በስራ ገበታው ላይ ለመገኘቱ ማስረጃ አቀረበ።

የውሸት ፈተና በሚፈትን ማሽን ፊት ተቀምጦ ያለምንም ችግር አልፏል። ማሽኑ "እየዋሸ አይደለም" ብሎ መስክሮለታል። በተቃራኒው ከሳሽ በማሽኑ ፊት ቀርባ ለመፈተን ፈቃደኛ አልነበረችም። ፍርድ ቤት ከሳሽን በውሸት መፈተኛው እንዳትፈተን ፈቀደላት። ይህ ግራ አጋቢ ውሳኔ ነበር።

ከሳሽ ካሊድ ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ ታደርስበት ነበር። "ልጅህን ለዘላለም እንዳታገኛት አድርግሃለሁ" ብለዋለች። መኪናው ላይ ጉዳት አድርሳለች። እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ካሊድ ለፍርድ ቤት አቀረበ። "ሆነ ብላ እየጎዳችኝ ለመሆኑ ማስረጃ ይሆነኛል" ቢልም ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገበት።

ካሊድ ሴት ልጁን በገዛ እጁ እንደገረዛት ነበር የተነገረው። በኢትዮጵያ ግርዛትን ማንኛውም ሰው እንደማይፈፅም ፥ ለመግረዝ ልምድ እንደሚያስፈለግ ለፍርድ ቤት ቢያስረዳም ማብራሪያው ውድቅ ተደረገበት።

"የተገረዘች ሴት ቁስለት ስለሚኖርባት መገረዟ ወዲያው ይታወቃል። ልጄ ላይ ደግሞ ይህ አልታየም" አለ። ይህም ውድቅ ተደረገበት።

የህፃናት ስነልቦና ባለሞያዎች ተገረዘች የተባለችውን ልጅ አጥንተዋት ነበር። "ልጅቷ እየተናገረች ያለችው ትልቅ ሰው ያሰለጠናትን ነው" አሉ። የባለሞያዎችም ሃሳብ ውድቅ ተደረገ።

ካሊድ ማለ። "ወላሂ አላደርግኩትም" አለ። ተሰሚ አልሆነም።
ፍርድ ቤት ካሊድን በአስራአምስት አመት እስራት ቀጣው። አስራ አመስት አመታት ሊታሰር ወደወህኒ ወረ።
ካሊድ የተፈረደበት ቀን የካሊድ ጠበቃ አለቀሰ። "ካሊድ ሐቀኛ ነው። ማስረጃዎች ነበሩት" ብሎ አለቀሰ። ጠበቃው ነፃ ሊያወጣው ስላልቻለ አነባ።

ካሊድ ወሂኒ ሆኖ ይግባኝ አለ። ታዋቂ ጠበቆች ይግባኝ ጠየቁለት ፥ ነገር ግን ፍትህ ተነፈገ። ይግባኙን ፍርድ ቤት ጣለበት።

ካሊድ እስር ቤት ዘጠኝ አመት ከቆየ በኋላ አመክሮ ተፈቀደለት። ስነስርዓት ያለው ታራሚ ስለሆነ በአምክሮ ይለቀቅ ተባለ። ከዛስ... ሳይለቀቅ ቀረ።

ካሊድ "ፍትህ ያጣ እንባ" በሚል ርዕስ ህይወት ታሪኩን ፅፎታል። እርሱ ፍትህ የተነፈገ ሰው ነው። ለምን ፍትህ ተነፈገ? አጭሩ መልስ በሚዲያ የተነሳ ነው።

ካሊድ እንደተከሰሰ ሚዲያ አጀንዳውን አጮኸው። "በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የገረዘ ሰው ለፍትህ ሊቀርብ ነው" የሚል ዜና ተቀባበሉ። ጋዜጠኞች ካሊድን ተቀባበሉት። "የመጀመሪያው የሴት ገራዥ ሊቀጣ ነው" አሉ።

ካሊድ በመፅሐፉ ላይ "የሚዲያ ተፅዕኖ ፍትህ እንዳጣ አድርጎኛል" ይላል።

በእርግጥ የህዝብ ጩኸት ፍትህ ያዛባል።

የህዝብ ጩኸት እውነታቸውን የቀበረባቸው ፥ የሚዲያ ዘመቻ ፍትህን የቀማባቸው ብዙ ናቸው።

ይህ ምን ያስተምረን ይሆን?

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
😢22👏2
ሁለቱ መምህራን
* * *
አንዳንድ ሰው ስራው ገናና ነው። ታሪኩ በብዙ የሚተረክ ፥ ተግባሩ የሚወደስ ፥ ገናናነቱ የሚዘከር ነው። ልክ እንደ ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሔር

ስለ ዶክተር ተወልደ ምን እንላለን? በእርግጥ ብዙ ማለት እንችላለን። ደግሞም በጥቂት ቃላት መገለፅም እንችላለን። "የምድራችን ጀግና" በሚል የከበረ ስምም ልንጠራውም እንችላለን።

ስለ የምድራችን ጀግና ማብራራት አይደለም ሃሳቤ። የምድራችንን ጀግና ዶክተር ተወልደን ያስተማሩ ሁለት መምህራንን ላስታውሳችሁ

1፥ ዶክተር ተወልደ አንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበረበት ወቅት ከአንድ መምህሩጋ መግባባት አቃተው። (ባልሳሳት የ5ኛ ክፍል ተማሪ ነበር) ቀለሜው ተማሪ ከአስተማሪው መግባባት አለመቻሉ በአጭር አልተቋጨም። ለቤተሰብ ስሞታ ቀረበ።

"ተወልደ ብርሃንን ተው በሉት" ተባለ።
"ምንድነው ጥፋቱ?" አሉ አክስቱ።
"ይፈጥናል፥ ይንቀለቀላል"
"እኮ እንዴት?"
"በዚህ አመሉ ከቀጠለ ያ ብ ዳ ል"
"እንዴት ሆኖ?"
"መጠየቅ ያበዛል፥ ጥያቄዎቹ ለሱ እድሜ የሚሆኑ አይደሉም። የአስራሁለተኛ ክፍሎችን ጥያቄ ይጠይቃል"

(ውይይቱ ቃል በቃል እንዲህ አይደለም። ሃሳቡ ግን የተፃፈው ነው)

ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሔር በልጅነቱ አእምሮው ፈጣን ነበር። ለመምህሩ ፈታኝ ጥያቄ ያቀርባል። በሚያሳስዝን ሁኔታ መምህሩ የአእምሮውን ፍጥነት ጠላ። አስተማሪውን ጠጣር ጥያቄ መጠየቁ እንደ ጥፋት ቆጥሮ ስሞታ አቀረበ።

2

ሁለተኛው መምህር ልዩ ሰው ነው። ጌታቸው ቦሎዲያ ይባላል። አዎን ታላቁ ጌታቸው ቦሎዲያ!
ተወልደ ብርሃን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለ ጌታቸው የነ ተወልደ መምህር ነበር። ከእለታት በአንዱ ጌታቸው ለተማሪዎች ማብራሪያ አቀረበ። የመምህሩ ማብራሪያ ከተማሪዎች መካከል ለአንዱ አልተዋጠም። ተወልደብርሃን ቅር ተሰኘ።

"መምህር የተሳሳቱ ይመስለኛል" አለ ተወልደ
"የቱጋ?"
ተወልደ አብራራ።
ጌታቸው ቦሎዲያ የላቀ ሰው መሆኑን የሚያሳይ ምላሽ ለተወልደ መለሰ። "ልክ ልትሆን ትችላለህ፥ ስለዚህ እኔም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ነገር ላጥና። መፅሓፍ ላገላብጥ። አንተም ተጨማሪ ነገር አንብብ። ከሁለታችን የማናችን ልክ እንደሆነ እናመሳክራለን" አለ። (ቃል በቃል አይደለም)

ጌታቸው እንዴት ያለ ታላቅ መምህር ነው? በተማሪዎች ፊት ተሳስቼ ይሆናል ለማለት የሚያስደፍር የሞራል ልዕልና ነበረው። ከተማሪዎቹ መካከል በአንዱ "ሳይሳሳቱ አይቀርም" ሲባል ለማድመጥ ፈቃደኛ ሆነ።

ብዙ መምህራን በሁለቱ የተወልደ መምህራን የሚወከሉ ይመስለኛል

ስለ ዶክተር ተወልደ ሌላ ጊዜ በሰፊው እንጨዋወታለን

Via ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
7
"እ ብ ድ ነኝ" ፥ የአንዳርጋቸው ፅጌ ድራማ
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
በዘመነ ደርግ ለእድገት በህብረት ዘመቻ ከተመረጡ ወጣቶች መካከል አንዱ አንዳርጋቸው ፅጌ ነበር። አንዳርጋቸው በዘመቻው ደስታ አጣ፥ ከዘመቻው ለማምለጥ ወጠነ።

በወቅቱ ወጣት የነበረው አንዳርጋቸው ያኔ የኢህአፓ አባል ብቻ ሳይሆን ዋና አመራሮችን ከቦታ ቦታ የሚውስድ ሹፌራቸው ጭምር ነበር። እናም 'ከዘመቻው አምልጬ የኢህአፓን ስራ ልከውን' ብሎ ወጠነ፥ ውጥኑም እንዲሰምር ድራማን ፈጠረ።

ከእለታት በአንዱ እንዲህ ሆነ። ለሊት ነው፥ አብዛኛው ሰው እንቅልፍ ላይ ሳለ ያልተኙቱ ተተራመሱ። በኡኡታ እንቅልፍ ላይ ያሉትን አነቁ፥ ጠባቂዎች ተጣድፈው ወደ ስፍራው ደረሱ።

የመተራመሱ ሰበብ አንዳርጋቸው ነበር። ጨርቅ ቀዶ ራሱን ሰቆሎ ሊ ገ ድ ል ሲል ደረሱበትና አተረፉት። ግራ መጋባትና ውክቢያ በቤቱ ተፈጠረ።
'ምን ነክቶት ሊሞት አሰበ' ተብሎ ሲጠየቅ ከወዳጆቹ "አልፎ አልፎ የሚነሳ የአእምሮ ህመም አለበት፥ ይህን ያደረገው እብደቱ ተቀስቅሶ ነው" የሚል መልስ ተሰጠ።
የነገሩን ልክነት ለማጥራት ወደ ምርመራ ክፍል ተወሰደ። በምርመራ ቦታ አንዳርጋቸው ግድግዳው ላይ እያፈጠጠ መዛበረቅ ጀመረ። ለሚቀርብለት ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ ሁሉ አራምባና ቆቦ ሆነ። ይሄኔ መርማሪዎች 'ይህ ወጣት የአእምሮ መታወክ አለበት' ብለው ደመደሙ። አብሯቸው ቢቆይ ድንገት ህይወቱን በገዛ እጁ ሊያጠፋ እንደሚችል ጠረጠሩ። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ እሱን ማሰናበት ሆነ።

አንዳርጋቸው ፅጌ ያኔ እንደ እብድ ሆኖ የታየው ድራማ ሲሰራ ነበር። ከዘመቻው የማምለጫ እቅድ ማዘጋጀት ሲጀምር አልፎ አልፎ የሚነሳ 'የአእምሮ መታወክ' እንዳለበት ውስጥ ውስጡን አስወራ። ቀጥሎ ገመድ ይዞ ራሱን ሊ ገ ድ ል እንዳሰበ አስመስሎ ተወነ። ይሃኔ እብደቱን ያመኑቱ በድንጋጤ በገጠር ያለውን ዘመቻ አቋርጦ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ወሰኑ።


@Tfanos
9
'አማራ በትግራዩ ጦርነት'
* * *

በቁጥር ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የትግራዩ ጦርነት ዋና አክተሮች የአማራ ኤሊት ይመስላቸዋል፥ ወይንም አስመስለው ያቀርባሉ።
የትግራዩ ጦርነት ተዋናዮችን ማንነት በብሔር መመደብ ፥ በነገድ ኮታ መስጠቱ አስፈላጊ ባይሆንም አማራን ለሚወቅሱቱ አግባባዊ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።

ከልደቱ አያሌው እስከ ኢንጂነር ይልቃል ፥ ከቴዎድሮስ አስፋ ወሰን እስከ ያየሰው ሽመልስ ጦርነቱን ተቃውመዋል፤ የኤርትራን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል፣ ለህዝቡ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። እውነት ለመናገር የትግራዩን ጦርነት ያወገዙ የአማራ ተወላጆች ቁጥር ብዙ ነው። ምናልባት ከጦርነቱ አውጋዦች መሓከል ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው።
ይሄን እውነት ቸል ብሎ አማራን መኮነን ጥፋት ነው።

ምናልባት 'ብዙ አማራዎች ጦርነቱን ደግፈዋል' የሚል ክርክር ይመጣ ይሆናል፤ ይህ ከፊል እውነት ነው። ጦርነቱን የደገፉት ከአማራ የተወለዱት ብቻ አይደሉም። ከሁሉም ብሔር የተውጣጡ ሰዎች ለጦርነቱ ድጋፍ ሰጥተዋል፥ ዘመቻውን መርተዋል። ጦርነቱ ላይ በፕሮፖጋንዳ ፥ በፖለቲካ አመራር ፥ በጦር ተሳትፎ የነበራቸውን የሌላውን ብሔር ተወላጆች በብዛት መቁጠር ይቻላል።

አለማዬ ፥ ጦርነቱን በብሔር ኮታ መከፋፈል አይደለም። ነገር ግን አግባብነት በጎደለው እና ከአውድ በወጣ መንገድ አማራን መውቀስ ህዝብን ለጥቃት የሚያመቻች በትር ማቀበል እንዳይሆን ማሰብ ያስፈልጋል !

@Tfanos
12👏1😁1
የመፅሐፍ ምርቃት

"የዙፋን ልፊያ" ነሐሴ 23 ይመረቃል።

አድራሻ ፥ አራት ኪሎ ዋሊያ መፅሐፍት

10 ሰአት ተኩል።
🔥95
አብይ አህመድን መናቅ ማንን ጠቀመ?
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
"አብይ አህመድ የክፋቱን ያህል እውቀት ቢኖረው...."
ከላይ ያለው አገላለፅ የቴዎድሮስ ፀጋዬ ነው። ቴዲ አብይ አህመድ ክፉ እንደሆነ ደጋግሞ ተናግሯል፥ አስረድቷል። አብይን "ክፉ" ከማለቱ መሳ-ለመሳ አብይ አላዋቂ ስለመሆኑ አብራርቷል። "አብይ አህመድ ደ ደ ብ ነው" ይላል። አብይ በዚህ ክፋቱ እውቀት ቢኖረው ከአሁኑ የከፋ ጥፋት እንደሚፈፅም አስረድቶ ያውቃል።

አብይ ደ ደ ብ ነው?
በእርግጥ አብይ አህመድ ደ ደ ብ ነው? በእውነቱ አብይ ደ ደ ብ ነው?

ብዙ ሰው፥ ጠቅላይ ሚኒስተሩ እውቀት የለሽ፥ ልፍስፍስ ፥ ንክ ፥ ወዘተ እንደሆነ ያምናል። አብይ መራሹ ብልፅግና መንግስትም ፍፁም ደካማ ፥ ለመውደቅም አንድ ሃሙስ የቀረው ይመስለዋል።

በእርግጥ፥ እውነታው እንደዛ ነው?

አብይ እየተናቀ ሰባት አመት ገዝቷል። ቀጣይ ብዙ የስልጣን አመታት ከፊቱ እንዳሉት በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።

አብይንና ብልፅግናን በስልጣን ካቆዩት አስቻይ ሁኔታዎች መካከል አንዱ እንደደካማ መቆጠሩ ይመስለኛል። ብዙ ሰው የአብይን የማድረግ አቅም ዝቅ አድርጎ ይገምታል። ብልፅግና በአንድ ግፊ የሚወድቅ ልፍስፍስ ፓርቲ ይመስለዋል።

አንዳንዴ ዝቅ ተደርጎ መቆጠር ድል ማድረጊያ መሳሪያ ይሆናል። ባለጋራውን ደካማ እና ምንም አቅም የሌለው አድርጎ የሚያስብ ተፋላሚ አያሸንፍም። ተፎካካሪውን በቀላሉ እንደሚረታ ገምቶ ወደ መፋለሚያ ቦታ የሚወርድ ፥ በቂ ዝግጅት አያደርግም። የቤት ስራውን አይሰራም። በተቃራኒው እንደደካማው የሚቆጠረው አቅሙን አሟጦ ይጠቀማል። እስከመጨረሻው ጠብታ ይፋለማል።

"አብይ ደ ደ ብ ነው" ብሎ የሚያስብ ፖለቲከኛ በቂ የእውቀት ትጥቅ ታጥቆ እየተፋለመ ነው? አይመስለኝም።
ብልፅግና ለመውደቅ አንድ ሀሙስ የቀረው ልፍስፍስ እንደሆነ የሚያምኑ የቤት ስራቸውን እየሰሩ ነው? አይደለም።

ተቃዋሚዎች አብይን እያናናቁት ፥ አብይ ሰባት አመት በመንበር ቆይቷል። ተቃዋሚዎች ንቀታቸውን እስኪያቆሙ ድረስ አብይ በመንበር ይቀጥላል።

በግጥም እንዝጋው። (2013 ዓ.ም የፃፍኩት ግጥም ነው። በእርግጥ ግጥሙ መስመር በመስመር አብይን ይወክላል ማለት ላይሆን ይችላል)
የድል መንገድ
* * *
ለተጋጣሚ አይን ፥ አንሶ የቀረበ
ለፍልሚያ አውድማ ፥ አሻግሮ ያሰበ
ትምክህትን የቀጣ፥ ራሱን ያልካበ
አቅመቢስ በመምሰል፥ ጠላት አሰነፈ
ባለጋራ ሲሞኝ፥ እርሱ አሸነፈ

ቂ ሎ ች ለመሸነፍ ፥ጠላትን ሲንቁ
ደካማ በመምሰል፥ ድልን መቀናጀት፥ ጠቢባን አወቁ


@Tfanos
8
የሴቶች ዘመን ከደጅ ነው!
(ተስፋኣብ ተሾመ)
***
ጥንት ጉልበት የብዙ ነገር ምንጭ ነበር። ውትድርናው ጉልበትን ይሻል፥ መብልና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ያለ ጉልበት ማሟላት አይቻልም፥ ለመኖር ጉልበት ወሳኝ ነበር። አያቶቻችን ያድናሉ ፥ ይለቅማሉ። ይፈለማሉ። ይህን ለማድረግ ጉልበት የሌላቸው ይሸነፋሉ። ሲስተሙ ገፍቶ ይጥላቸዋል።

ዘመን ተለወጠ።

ልዩ እና ታላቅ አብዮት ተከስተ። የአንዲስቱሪ አብዮት ፈነዳ። የኢንደለስትሪ መስፋፋት የሰውን አኗኗር ለወጠ።
የኢንዱስትሪ አብዮት ጉልበትን በእውቀት የሚተካ መደላድልን ፈጠረ። ከዘመን ዘመን ሳይንስ ደረጀ፥ ቴክኖሎጂ ፈረጠመ። የጉልበት አቅም ኮስሶ የእውቀት ተመን ይጨምር ዘንድ የግድ ሆነ።

ይህ ለሴቶች ታላቅ የምስራች ነው!

ሁላችንም እንደምናውቀው ሴቶች በጉልበት ከወንድ ያነሱ ናቸው። በዚህ የተነሳ ሃይል የሁሉም ነገር ምንጭ በነበረበት ዘመን ወንዶች ቁንጮ ሊሆኑ ችለዋል። ይህ ግን የሚያበቃበት ዘመን ተቃርቧል።

ውትድርናን ጨምሮ ትልልቅ ጉዳዮች ለሳይንስ የሚገብሩበት ዘመን እየመጣ ነው። ትላንት ግብርና ያለ ጉልበት አይታሰብም። ዛሬ ግን ሳይንስ ምስጋና ይግባውና አእምሮ ጉልበትን እየተካ ነው። ትላንት ውትድርና ያለ ጉልበት አይታሰብም። ነገ ግን ይህ ይቀየራል። ሳይንስና ቴክንሎጂ ውትድርናን ከጉልበት ወደ አእምሮ ይወስደዋል። ከዚህ ቀደም ጉልበት ብዙ ተፅዕኖ ነበሰው። ነገ ግን አእምሮ ዋና ይሆናል። ያኔ መወዳደሪያው ጉልበት ሳይሆን እውቀት ይሆናል።

ትላንት ሃይል ዋና ነገር ሳለ ሴቶች በጉልበት ከወንድ ያንሱ ነበር። ነገ እውቀት ዋና ነገር ሲሆን ግን ሴቶች በአእምሮ ያነሱ አይደሉምና መወዳደሪያው ላይ አቻ ይሆናሉ።

ተራ ነገር ቢመስልም ሴቶች ውበት የሚባል ተጨማሪ ሃይል አላቸው። ይህ ተራ አባባል ይመስል ይሆናል። እውነታው ግን ውበት በሰዎች ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አድራሽ ነው።
ሰዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጥቂት ነገሮች አሉ። አንዱ ውበት ነው። ሌሎቹ ደግሞ ፣ ስልጣን ፥ ሀብት ፥ እውቀት እና ዝና ናቸው።

ሴት ውበት አላት። ይህ ተጨማሪ እድል ነው።

የሴቶች ዘመን በደጅ ነው።

ነገ ሴቶችን "ከናንተ እኩል እንድንወዳደር ውበታችሁን ቀንሱልን" ለማለት እንገደድ ይሆናል።

ሴቶች ፥ ከፊታችሁ ላለው ዘመን በሚገባው ልክ ተዘጋጁና ዘመናችሁን ውረሱት !


@Tfanos
👍4
"ልጅነት የሚያደርሰውን ጉዳት ጠላት አያደርሰውም"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
ሰሞኑን የዘሪቱ ከበደን መፅሐፍ ሳነብ ነበር። "ከልጅነት እስከልጁነት" ን ጓግቼ ነው የገዛሁት። ፈጥኜም አነበብሁት።
መፅሐፏን ሳነብ የተለያዩ ስሜቶች ተሰምተውኛል። ቅሬታ ፥ ግርታ ፥ ፈገግታ ፥ መደነቅ ተፈራርቀውብኛል። በተለይ ልጇ ክርስቲያን ላቀው በሆስፒታል ፅኑ ህሙማን ክፍል ሳለ የነበራት ስሜት ሃዘን ውስጥ ከቶኛል። በበገና ስቱዲዮ የነበራቸው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት እና መፅሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ትኩረቴን ስቦታል።ዘሪቱ እና ጓደኞቿ መፅሐፍ ቅዱስን የተረዱበት መንገድ ፥ ፀጋና ሕግን የበየኑበት አግባብ ፥ ለሃይማኖቶች ያላቸው ምልከታ ብዙ ያወያያል።

ከዘሪቱ መፅሐፍ ትኩረታችሁን የሳበው የቱ ነው?

ከንባባችን በኋላ ወደ ልባችን የሚቀረው ልዩ ልዩ ነው። አንዳችን ልብ ውስጥ የቀረ በሌላው ያልታየ ይሆናል።

"ልጅነት የሚያደርሰው ጉዳት ጠላት ከሚያደርሰው የከፋ ነው" ይህን አባባል ያገኘሁት ከዘሪቱ መፅሐፍ ነው። (አባባሉ ቃል በቃል አይደለም) የዘሪቱ ከበደ እናት ልጅነት ከባለጋራ በላይ ጉዳትን እንደሚያደርስ ትናገር ነበር። የእናቷን አባባል ዘሪቱ የተረዳችው ዘግይታ ነው።

ልጅነት ልዩ ልዩ ነው። በአካል ልጅ መሆን አለ። ደግሞ የአእምሮ ልጅነት አለ። አንዳንዱ በስነልቦና ያልበሰለ ልጅ ነው። አንዳንዱ በመንፈሳዊ ነገር ልጅነት ያጠቃዋል። ከልጅነት እውነተኛ ገፅታዎች መካከል አንዱ አለመብሰል ነው። (ሌላው ደግሞ ንፅህና)

ዘሪቱ በይፋ እንደነገረችን ከሆነ ማመፅ ያስደስታት ነበር። እርሷና ባሏ ትዳርን በሚያስቡበት ወቅት ባህላዊ ሰዎችን እንደ ኋላ ቀር ቆጥረው ይንቁ ነበር። ሰርጋቸው ላይ ጭምር ባህል ላይ ያላቸውን አመፅ አሳይተዋል።

ልጅነት ያሳምፃል። ልጅነት ነገሮችን በእኛ አቅጣጫ ብቻ እንድናይ ይገፋናል። በልጅነት ስሜት ይገናል። የቀደመውን ልማድ እንደ አሮጌ ቆጥረን እንድንንቀው ያደርጋል።

ዘሪቱ "ምናልባት ባህልን እና ትልልቅ ሰዎችን በጭፍን ከማናናቅ ይልቅ፥ የሚናገሩትን ብሰማቸው አንዳንድ ጉዳቶችን ማስቀረት እችል ይሆናል" ትላለች።

ልጅነት ልዩ ልዩ ነው ብለን አይደል?

አንዳንዴ ባለመብሰላችን የተነሳ ያመፅንባቸው ልማዶች አሉ። ልጅነት ገፋፍቶን ከእኛ አንፃር ብቻ የተመለከትናቸው ነገሮች አሉ። ስሜታችንን መከተል ዋና ነገር መስሎን ያውቃል። ታላላቆቻችንን ማድመጥ አስፈላጊነቱ ይጠፋብን ይሆናል። ይህ ሁሉ ልጅነት ነው።

በህይወታችን ትልልቅ ተግዳሮቶች ይገጥሙናል። አንዳንዴ ባለጋራ ከፈጠረብን መከራ በላይ አለመብሰላችን የፈጠረው መከራ ይገዝፋል።

በእርግጥ ልጅነት የሚያመጣው ችግር ፥ ጠላት ከሚያመጠው የከፋ ይሆናል። ከሌላ የሚወረወርን ፍላፃ መመከት ወይም መሸሽ ይቻል ይሆናል። ከራስ አለመብሰል የሚመዘዝን ሰ ይ ፍ እንዴት ማስቆም ይቻላል?

በእርግጥም በስሜት ፥ በእውቀት ፥ በመንፈሳዊ ነገር አለማደግ ታላቅ ፈተና ነው።


@Tfanos
@Tfanos
2
የመፅሐፍ ምርቃቱ ተሰርዟል!

"የዙፋን ልፊያ" የተሰኘች መፅሐፌን የፊታችን አርብ እንደማስመርቅ አስተዋውቄ ነበር። ነገር ግን ከአቅም በላይ በሆነ ምክኒያት የመፅሐፉ ምርቃት ተሰርዟል።

ስለሆነም ፥ "የዙፋን ልፊያ" ያለ ምርቃት ሰሞኑን ለገበያ ትቀርባለች።

ይህን ላልሰሙ አሰሙ።
🤔5👍4
ህዳሴ ግድብ ማለቁ ደስ ይላል። ግን ደስታዬ ከፊል ነው።

ኢትዮጵያ የግድቡ የተረጋገጠ የባለቤትነት ዋስትና የላትም። ነገ ጠዋት ቤንሻንጉል ክልል ልገንጠል ቢል አስቻይ ሁኔታ አለው። ዜጎች መቀነታቸውን ፈተው የገነቡት ግድብ ቋሚ ሀብት ለመሆኑ ሽራፊ ማረጋገጫ የለም።

ክልሎች እጩ ሐገር ናቸው። ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ሉኣላዊ ሐገር እንዲሆኑ ሕገመንግስታዊ ድጋፍ አላቸው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደገፍ እንዲሉ የፖለቲካ ልዩነታችን ከእለት እለት እየሰፋ ይገኛል።
እርስ በእርስ እየተገፋፋን ፥ እየተቃቃርን ፥ እየተዋጋንና እየተቆራረጥን ነው።

ለምሳሌ ግድቡ የሚገኝበት ቤንሻንጉል ክልል ባለፉት አመታት ችግር ውስጥ ነበር። የየብስ ትራንስፖርት ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ግጭትም ነበር። ይህ ወዴት ይወስዳል?

አንድ ዜጋ ለዳር ድንበር ህይወቱን ከከፈለ በኋላ ፥ ያ ቦታ ሊገነጠል ይችላል። ታዲያ ለሐገር ደም ማፍሰስ ለምን?

ትግራይ ፥ ቤንሻንጉል፥ አማራ ፥ ኦሮሚያ ፥ ሶማሌ ወዘተ እጩ ሐገራት ናቸው።

የመገንጠል ስጋት እያለ ፥ የሆነ ክልል ላይ የተገነባ ሐብት ሐገራዊ ሊሆን ይችላል? አይመስለኝም!

@Tfanos
🔥116👍5😢3
"የዙፋን ልፊያ" ገበያ ላይ ቀርቧል።

መፅሐፌ ገበያ ላይ ውሏል። ይህን በ2 ምክኒያቶች እንድታስተዋውቁ እፈልጋለሁ።

ምክንያት አንድ ፥ መፅሐፌ አልተመረቀም። የምርቃት ፕሮግራም ለማስታወቂያ ቀጥተኛ ጥቅም አለው። ለኔ ግን አልሆነልኝም። ስለዚህ የእናንተን ማስታወቂያ እፈልጋለሁ

ምክንያት ሁለት ፥ ፌስቡክ ሊገባኝ ባልቻለ ሰበብ ቀጥቶኛል። ተደራሽነቴ ላይ ገደብ አድርጓል። ስለዚህ ይህን ለማካካስ የናንተ ማስታወቂያ ያስፈገኛል።

ይህን ስለምታደርጉ አመሰግናለሁ

አሳታሚና አከፋፋይ ጃፋር መፃሕፍት
11👍3🔥1
የዙፋን ልፊያ ልብወለድ ነው።

ከዚህ ቀደም እንዳልኩት ፥ ስነ-ፅሑፍ ለፖለቲካ ጉዳይ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። ስነ-ፅሁፍ ከሰው ለሰው በሰው ነው። ሰው ይፅፋል ፥ በሰው በኩል ለሰው ይቀርባል። በአንድም በሌላም ትኩረቱ ስለ ሰው ነው።
ፖለቲካ ደግሞ በእያንዳንዱ ሰው ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያሳደራል። ብንወድም ባንወድም በፖለቲካ ተፅዕኖ ስር ነን።

"ነገን ፍለጋ" በሚለው መፅሐፌ ያልኩትን እዚህ ልድገም። ፖለቲካ የማግባት ወይም ያለመግባባት ሁኔታችንን ይወስናል። እውነት መስሎ ባይታይም ፖለቲካ የዜጎችን ትዳር እስመወሰን ድረስ ጉልበት አለው።

"ፖለቲካ በሩቁ" ባዮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ መሆን አይችሉም። ሰው ፖለቲካን ይሸሽ ይሆናል። ፖለቲካ ግን ሰውን አይሸሽም። ስለዚህ ለፖለቲካ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።

የዙፋን ልፊያ ልብወለድ ነው። ፖለቲካ የተርታ ሰዎች ህይወት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የሚያሳይ የልብወለድ...

በመፅሐፌ ከመንግሥት ወይም ከተቃዋሚዎች ጋር ቃላት መወራወር አልፈለግኩም። መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎች ትኩረቴ አይደሉም። ትኩረቴ ፖለቲካ ግለሰብ ህይወት ላይ ያለው ቀጥተኛ ተፅዕኖ ነው።

የዙፋን ልፊያ ሁነኛ ትከረቱ ቀጣይ ነጥቦች ናቸው

ፖለቲካ በተርታ ሰው ህይወት ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድነው?
ጦርነት እና የግለሰብ ህይወት ምን አገናኘው?
የፖለቲከኞች ግላዊ ባህሪ እና የዜጎች የእለት ተዕለት ህይወት እንዴት ይገናኛል?
ከላይ ያነሳኋቸው ጥያቄዎች "የዙፋን ልፊያ" መፅሐፌ ትኩረት ናቸው።

በተቻለኝ መጠን ከቀደመው ስራዬ የተሻለ ስራ ለማምጣት የሞከርኩ ይመስለኛል።

መፅሐፌ ገበያ ላይ ውሏል። ይህን በ2 ምክኒያቶች እንድታስተዋውቁ እፈልጋለሁ።

ምክንያት አንድ ፥ መፅሐፌ አልተመረቀም። የምርቃት ፕሮግራም ለማስታወቂያ ቀጥተኛ ጥቅም አለው። ለኔ ግን አልሆነልኝም። ስለዚህ የእናንተን ማስታወቂያ እፈልጋለሁ

ምክንያት ሁለት ፥ ፌስቡክ ሊገባኝ ባልቻለ ሰበብ ቀጥቶኛል። ተደራሽነቴ ላይ ገደብ አድርጓል። ስለዚህ ይህን ለማካካስ የናንተ ማስታወቂያ ያስፈገኛል።

ይህን ስለምታደርጉ አመሰግናለሁ

@Tfanos
5👏2👍1
በዚህ ምሽት ይህን መፃፌ ትክክል ይሆን? እንጃ!

ከምሽቱ 3 ተኩል አከባቢ ልብሴን እንድታጥብልኝ የሰጠኋት ሴትጋ ሄድኩ። ተቀብያት በመውጣት ፋንታ ቤቷ ገባሁ። አንዳንድ ጉዳዮችን አወራን።

ታሪኳን በአጭሩ።

ከጅማ ወደ አዲስ አበባ ከመጣች 11 አመት ሆኗታል። አዲሳባ የፍቅር ህይወት ጀመረች።
ግኑኝነት ከጀመረች በኋላ ፀነሰች። እርግዝና ተፈጠረ። ከእርግዝናው በኋላ በየኋህነት ተስፋ ያደረገችው የፍቅር ግኑኝነት አልቀጠለም። በአጭሩ ተቀጨ። ፅንስ ማቋረጥ ስላልፈለገች ልጅ ወለደች። ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ!

አራስ ሆና ጡቷ ወተት አልነበረውም። ምግብ ስለማትበላ ጡቷ ወተት ማምረት አልቻለም ነበር። ወልዳ ሳምንት ሳይሞላት የሰው ልብስ ለማጠብ ተገደደች። የሰው ልብስ አጥባ ገንዘብ ካላገኘች በረሃብ መሞቷ ስለሆነ ገና የሳምንት አራስ ሳለች የጉልበት ስራ ጀመረች። ጠያቂ የላትም። አልባሽ አጉራሽ የላትም። እሷ እና ልጇ ብቻ ናቸው።

መገናኛ አከባቢ በጠባብ የቆርቆሮ ቤት እየኖረች ጎመን ትሸጥ ነበር። ጎመንና መሰል ነገሮች መገናኛ ሰፈር ስትሸጥ ደንቦች አስቸገሯት። የምትሸጠውን ይበትኑባታል ፥ ይደበድቧታል ፥ ይነጥቋታል። መገናኛ ለሽያጭ አስቸጋሪ ሲሆንባት በአንፃራዊነት የተሻለ ሰፈር ፈለገች። ጎሮ ድረስ ሄዳ ሸጣ ሲመሽ ወደ መገናኛ ቤቷ ትመለሳለች።

ከእለታት በአንዱ አምሽታ ወደ ሰፈሯ ተመለሰች። ለመሸጥ የወሰደችው ንብረት አልተሸጠላትም። ልጇንና ያልተሸጠ ንብረቷን በጀርባ አዝላ ወደ ሰፈሯ ብትደርስ ቤቷ ፈርሷል። የቆርቆሮ ቤቷ ለልማት ፈርሷል....

ቤቷ ሲፈርስ የት አረፈች? ጎዳና! ልጇን ይዛ ጎዳና ወጣች!

አሁን ከልጇጋ የምትኖረው ተጀምሮ ባላለቀ ኮንዶሚኒየም ነው። ከጎዳና ወጥታ ባላለቀ እና አስተማማኝ ባልሆነ ኮንዶሚኒየም እየኖረች "ተመስገን" ትላለች። ልብስ ታጥባለች ፥ ፅዳት ትሰራለች። በምታገኘው ገንዘብ ልጇን ትመግባለች።

ልጇ 5 አመት ሞልቶታል። ነገ ልደቱ ነው።

ይህን መፃፍ ምንም ትርጉም ላይኖረው ይችላል። ከእናትና ልጅ የተለየሁት ከደቂቃዎች በፊት ነው። ስለነሱ እኔ አቅመቢስነት ተሰማኝ።

@Tfanos
😢227
አጋን ንት በሰው ጭካኔ ተገርመው እጃቸውን በአፋቸው አኖሩ፡፡ ሰው ከሰ ይጣን ሊስተካከል ጥረት የሚያደርግ መሰለ፡፡ የሞት መልዓክ ፋታ አጣ፣ ዲ ያ ቢ ሎስ ስራ በዛበት፡፡
ሐገር ሞት የሚታጨድባት ማሳ ሆነች፡፡
መሽቶ ፀሐይ ወደ ዘወትር ማደሪያዋ ስትከተት የሐገሪቱ ጨለማ ጀመረ፡፡ ጨረቃ የጠለቀችውን ፀሐይ ለመተካት አልወደደችም፡፡

‹‹ጧ…ጧ… ጧ›› የተኩስ ድምፅ በየአቅጣጫው ተሰማ፡፡

ጥይት በየሰው ገላ ተሰነቀረ፣ ወጣቶች እየተገነደሱ ወደቁ፣ ቤቶች በእሳት ጋዩ፣ እንስሳት በየአቅጣጫው ተሯሯጡ፣ ወፎች የጥይት ሲሳይ ሆኑ፡፡፡

‹‹ጧ ጧ ጧ››

ውሾች ያላዝናሉ፣ ጅቦች ከጎሬያቸው የሚሻል መሸሸጊያ ፈለጉ፡፡ የሌሊት ወፎች ሐገር ጥለው ለመሰደድ መብረር ጀመሩ፡፡ ሐገር ተተራመሰ፡፡
መሽቶ ፀሐይ ስትጠልቅ ብሄራዊ ጨለማ ተፈጠረ

‹‹ብወልድህ አደርስሃለሁ፣ እናትህ ነኝ›

የተዳፈነ እሳት ከማጀት እየቆሰቆሱ ሳለ ብሄራዊ እሳት ነደደ፡፡ ከአምስት ዓስርት ዓመታት በፊት የሰሙትን ታላቁን መከራ ተጋፈጡት፡፡
‹‹መብራታዊያን ታላቁ መከራን የሚጋፈጡበት ዘመን ይመጣል፡፡ የደም ጎርፍ ወደ መብራት ሐይቅ ይፈሳል፣ የመብራት ጎዳናዎች በሬሳ ይሞላሉ፣ የመብራት ተራራ ግርማውን ያጣል›› ተብሎ ነበር፡፡

‹‹ልጄ አታዋርደኝ››

ፀጉራቸው በሽበት የተወረሰ ነው። በእድሜ የልጅ ልጃቸው የሚሆን ጎረምሳ እግር ስር ተደፍተው ይለምኑታል።

‹‹እባክህን ልጄ››

በደፈረሰ ዐይኑ ሲያፈጥባቸው የሚናገሩት ቸገራቸው፤ ልባቸው ራደ።
እድሜያቸው ምሕረት አላስገኘላቸውም፣ እናትነታቸው ከጭካኔ አላዳናቸውም፣ ልመናቸው ከጎረምሳ ጥፊ አልታደጋቸውም። በጠንካራ መዳፉ በጥፊ ሲመታቸው በጀርባቸው ወደቁ፡፡
ጊዜ አላጠፋም። ተስገብግቦ ቀሚሳቸውን ለመግለብ ታገለ፡፡

‹‹ልጄ እናትህ ነኝ። ፈጣሪን አታሳዝነው››
በእንባ የራሰ ፊታቸው ሌላ ጥፊ ተቀበለ።

‹‹ፈጣሪህን አትፈራም?››

ከዐይናቸው የሚፈሰው እንባ በጆሮ ግንዳቸው በኩል ወረደ፡፡ ለዓመታት ተከብረው በኖሩበት፣ ልጆቻቸውን ወልደው ባሳደጉበት፣ ያሳደጓቸውን በዳሩበት ፣ እንግዶች በተቀበሉበት መኖሪያ ቤታቸው የልጅ ልጃቸው እኩያ አጎደፋቸው።
የዘመናት ፀሎታቸው ሳይሰማ ቀረ፡፡ ‹‹ታላቁን መከራ ሳላየው ልሙት›› የሚል ፀሎት ነበራቸው፡፡ ያልተሰማ ፀሎት…

#የዙፋን_ልፊያ ገፅ 1
😢3
3🔥2
‹‹ዲ ቃ ላ፣ የሰይጣን ልጅ››

ጦርነቱ የተጀመረባትን የተረገመች ቀን እያሰበች የአብራኳን ክፋይ ትሰድበዋለች።
‹‹አታልቅስ!... ዲ ቃ ላ››

ጦርነቱ የጀመረ ምሽት ባሏ ተባራሪ ጥይት በላው። ለታሪኩ ማንም ግድ ባይሰጠውም ባሏ በእርስ በእርስ ጦርነቱ የሞተ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ሲቪል ሆነ። አባቷ በወጣበት ሲቀር ወንድሟ አካሉ ጎደለ።

‹‹ዲ ቃ ላ››
ባሏ በሞተበት ምሽት፣ ወንድሟ አካሉ በጎደለበት ምሽት፣ አባቷ በወጣበት በቀረበት ምሽት እርሷ ለጥቃት ተላልፋ ተሰጠች። በወታደር ተደፈረች።
ደፋሪዋ ከማን ወገን እንደሆነ አታውቅም። ከጀነራሉ አሊያም ከፕሬዝዳንቱ ወገን ቢሆን ግድ አይሰጣትም፡፡ የምታውቀው በወታደር መደፈሯን ነው።
በሰደፍ ሲመታት ተዘለፍልፋ ወደቀች። የለበሰችውን ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ ለመቅደድ ሲታገል ‹‹በሕግ አምላክ›› አለች።

የሐገሪቱ አድራጊ ፈጣሪ የሆኑ ሁለት ሹማምንት ከተጣሉ በኋላ ሕገ-አራዊት እንደሰፈነ ስላላወቀች ‹‹በሕግ አምላክ›› በማለት ራሷን ለመታደግ ፈለገች።
ከምንም ሳይቆጥራት ሱሪዋን ለማውለቅ ሲታገል ‹‹መለዮህን አታከብርም?›› አለችው።
ስለመለዮ ክብር እየሰማች ስላደገች የፈጣሪን ስም ጠርቶ ከመማፀን ይልቅ ለአንደበቷ የቀረበው መለዮ ነበር፡፡

ለጥያቄዋ ቡጢ መለሰላት። ሁሉም ነገር ብዥ አለባት… እይታዋ ተጋረደ… አፏ በደም ተሞላ.. አፍንጫዋ እንደ አንዳች ባዕድ ነገር ከበዳት… ከአፏ ውስጥ ጠጣር ነገር አገኘች… ጥርሷን ተፋችው፡፡
‹በሕግ አምላክ› የሚል ተማፅእኖ ለማሰማት ጉልበት አጣች፡፡ አቅም ከዳት፡፡

ቆንጆ ነበረች፡፡ በአጭር የምትቆረጠው ፀጉሯ ከክብ ፊቷ ጋር የውበት ኪዳን ፈፅመዋል፡፡ የጥቁር ቆዳዋ ልስላሴ ድህነቷን መሰወር ተችሎታል፡፡ ጥርሶቿ፣ የጥርስ ውበት ማነፃፀረሪያ ናቸው፡፡ የረጃጅም እጅ ጣቶችዋ ከፊል በረጃጅም ጥፍር ያጌጣሉ፡፡ ከቀኝ ጣቶችዋ የቀለበት ጣትዋን እና የትንሽ ጣትዋን ጥፍሮች ታሳድጋለች፡፡ ከግራ እጇ ጣቶች መካከል ከአውራ ጣቷ እና የመሃል ጣቷ በቀር የሦስቱ ጣቶችዋ ጥፍሮች ሁሌም እንዳደጉ ናቸው፡፡

ቆንጆ ነበረች፡፡ በአንድ ቦክስ ውበቷ ከዳት፡፡
‹‹በሕግ አምላክ›› ብላ እየለመነች ውበትዋን በተነጠቀች አፍታ ክብሯንም ተቀማች፡፡
‹‹መለዮህን አክብር›› የሚለው ማሳሰቢያዋ ረብ እንደሌለው ሲገባት አቅሟን አስተባብራ ልታጠቃው ፈለገች፡፡ በደህናው ጊዜ ለውበት ዓላማ ያሳደገቻቸውን ጥፍሮች የአደጋ ጊዜ መከላከያ ልታደርግ ሞከረች፡፡ በጥፍሮቿ ልታጠቃው ታገለች፡፡ ጉልበተኛውን በጥፍሯ ልትቧጭረው መሞከሩ ከጥፍር መሰበር ውጭ ምንም አልፈየደላትም፡፡

‹‹በሕግ አምላክ›› በተሸነፈ ድምፅ ለመጨረሻ ጊዜ ተለማመጠችው፡፡
በጉልበት ተገናኛት፤ ተደፈረች። የመጀመሪያም የመጨረሻዋም ከሆነው ባሏ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንድ ገባባት፡፡
ማሕጸኗ ባዕድ ነገር የገባበት ይመስል አመማት። እላይዋ ላይ ተከምሮ የቆየበት ጥቂት ደቂቃ የዘላለም ያህል ረዘመባት።
‹‹በሕግ አምላክ›› እያለች መደፈሯ እንደ እግር እሳት ለበለባት፤ ‹መለዮ አክብር› የተባለ ወታደር የጀመረውን ክፋት ሁሉ እርግፍ አድርጎ እንደሚተው እየሰማች አድጋ ተቃራኒው ቢገጥማት ሃዘን ሰረሰራት፡፡
ከራሷ ተጣልታ ፣ የገዛ እሷነቷን ተፀይፋ መኖር ጀመረች።

‹‹ሁለት ባለሥልጣናት ለመንበር ሲሉ በመጣላታቸው የተነሳ የእኔ ማሕጸን ጦር ሜዳ ሆነ›› ትላለች ሆድ እየባሳት።

የወር አበባዋ እንደቀረ ያወቀች ሰሞን፣ ፅንስ የማቋረጥ ሃሳብ አልተፈጠረባትም ነበር።
የመጀመሪያውን ስድስት ወር ያሳለፈችው የተደፈረችበትን ቅፅበት በማሰብ እያለቀሰች ነው። ግማሽ ዓመት ያለ እረፍት አነባች።አዛኝ የለሽ ለቅሶ …

በሆዷ የተሸከመችው ፅንስ ስድስት ወር ሲሞላው በረገገች። ‹‹የጠላቴን ልጅ አልወልድም›› ብላ ወደ ሆስፒታል ሄደች።
‹‹ማስወረድ አትችይም›› አላት ዶክተሩ
‹‹ለምን ሲባል?››
‹‹ለሕይወትሽ አደገኛ ነው››
‹‹ይሁና››
‹‹ገብቶሻል? ልትሞቺ ትችያለሽ››
ልቧ በጦር የተወጋ መሰላት። ደነገጠች።
መሞት አትፈልግም። ሕይወቷ ባያጓጓትም አለመኖርን አትመኝም። መኖሯን የጠላች ሆና ሳለ መሻቷ በህይወት መቆየት ነው።
ደመ-ከልብ ሆኖ የቀረ ሟች ባሏ መታሰቢያ የሆነውን የበኩር ልጇን ትታ መሞት አትፈልግም።

#የዙፋን_ልፊያ መጻሕፍ የተወሰደ

@Tfanos
🔥5
ስለዙፋን ልፊያ የመጀመሪያ የአንባቢ አስተያየት
(አስተያየት ሰጭ ፥ የስነልቦና ባለሞያ በሀሴት የማማከር አገልግሎት አማካሪ ረድኤት ዳዲ)

ከረጅም ጊዜ በኋላ ልብ ወለድ መፅሀፍ አነበብኩ።

አሹ ደግ አረኩ ብያለሁ!

ገና የመጀመሪያዋቹን ገፅ ማንብብ እንደጀመርኩ ነው ሳላስበው ብዙ ደቂቃዋች ያለፉት።

በመፅሀፉ ላይ ያሉት አብዛኞቹ ታሪኮች ልብ ወለድ ከመሆናቸው በላይ በተላያየ ጊዜ በማማክርበት ወቅት ቢሮዬን ያንኳኩ፤ ዕንባዬን ከዓይኔ ያፈሰሱ ታሪኮች ጋር የተዛመዱ ታሪኮቸ‍ መሆናቸው ተስፋኣብ ተሾመ ፀሀፊ ብቻ ሳይሆን ጥሩ የስነልቦና ባለሙያ ሊሆን እንደሚችል የታዘብኩበት ነው።

የተለያዩ የግለሰቦች ታሪክ እና ስሜትን በጥልቀት የሚተርክ፤ የተለያዩ ስነልቦናዊ ጉዳዮችን በይበልጥ እንድናስተውል በተለይም “The child is a father of the man” የሚለውን ትልቅ ስነልቦና ሀሳብ በእያንዳንዱ በዙፋን ልፊያ ታሪኮች ውስጥ የሚያስኮመኩም ነው።

ራሳችንን እና ልባዊ መሻቶችን ከልጅነት ታሪካችን ጋር ያለውን ዝምድና እንድንመረምር ፍንጭ የሚሰጥ ነው።

የግለሰቦች ፀብም የህዝብን ዕጣ ፈንታ እንደሚወስን አስተውዬበታለሁ።

ሁላችሁም እየገዛችሁ አንብቡት ታተርፋበታላችሁ።

ተስፍሽ እጆችክ ከፅሁፍ አይንጠፋ ብያለሁ🙌

@Tfanos
🔥10
"ሁላችንም ራሳችንን ማሰልጠን አለብን! ሳይቋሰሉ መለያየትን ራሳችንን ማሰልጠን አለብን! ሳይጎዳዱ ግኑኝነታትን ማቋረጥን ራሳችንን ማሰልጠን አለብን! እንደ አ ው ሬ ሳይነካከሱ መሰነባበትን ራሳችንን ማሰልጠን አለብን!"

#የዙፋን_ልፊያ ገፅ 163
👍6🔥41
2025/10/31 15:15:52
Back to Top
HTML Embed Code: