እንደምን አየሽኝ?
* * *
አንቺዬ . . .
ከጨረቃ በቀር ፥የአይንሽን ፀዳል ፥ ማን ተገዳደረ
ከፀሐይዋ ሌላ ፥ የአይንሽን ብርሃን ፥ ማን ተወዳደረ
አንቺዬ
አምላክ ይታረቀው ፥ በአይኖችሽ ለታየ
አለት ጠጣር ልቤን ፥ እይታሽ አጋየ
@Tfanos
* * *
አንቺዬ . . .
ከጨረቃ በቀር ፥የአይንሽን ፀዳል ፥ ማን ተገዳደረ
ከፀሐይዋ ሌላ ፥ የአይንሽን ብርሃን ፥ ማን ተወዳደረ
አንቺዬ
አምላክ ይታረቀው ፥ በአይኖችሽ ለታየ
አለት ጠጣር ልቤን ፥ እይታሽ አጋየ
@Tfanos
❤4🥰1
"የዝሆኖች ፀብ ሳሩን ይጎዳል፡፡ አሳዛኙ እውነት የዝሆኖች ፍቅርም ሳሩን መጉዳቱ ነው፡፡ ዝሆኖች በፀብ ሲፋለሙም ሆነ በፍቅር ሲላፉ ሳሩ መከራ ይወርድበታል፡፡ ከታችኛው መደብ ያለ ዘወትር ይረገጣል"
"የዝሆኖች የፀብ ፍልሚያም ሆነ የፍቅር ልፊያ ሳሩን ያደቃል፡፡ መላው ገደል መሆን ነው፡፡ ሳር ከመሆን ይልቅ ገደል መሆንን የሚመርጥ ብልህ ነው፡፡ ገደሉ በልፊያ እና በፍልሚያ ደካመውን የሚረግጡትን ያስውግዳል፡፡ አክሳሚውን ያከስማል"
#የዙፋን_ልፊያ

👍5
ሱሪ ለባሽ ሴቶች
* * *
ፓስተር ሀብቴ አሰፋ የምወደው የቤተክርስቲያን መጋቢ ነው። የደቀመዝሙርነት ትምህርት እና የአገልግሎት ትምህርት የተማርኩት በእርሱ ነው። በሚያስተምረን ጊዜ በተቻለ መጠን ጥያቄ እንድንጠይቀው ያበረታታን ነበር። ያኔ እኔ እድሜዬ 14 ነበር።
ድንገት ስለ ሱሪ ለባሽ ሴቶች ጠየቅነው። ከመካከላችን አንዱ ሱሪ ለባሽ ሴቶች ላይ ቁጣ አወረደ። በመንፈሳዊ ቅናት ተሞልቶ "አ ሰ ና ካ ይ ናቸው" አለ።
ፓስተር ሀብቴ በጣም ትሁት ሰው ነው። ከማውቃቸው ትሁት ሰዎች መካከል አንዱ እርሱ ነው። የግራ ቀኙን ንግግር ሲሰማ ከቆየ በኋላ ጉዳዩን በአጭር ቋጨው።
"ወንድ ለዝሙት እንዳይነሳሳ የሴቷን አለባበስ ከመቀየር ይልቅ የወንዱን ልብ መቀየር ይሻላል" አለን።
ሴ ሰ ኛን ሰው ልብስ አያስቆመውም። አ መ ን ዝ ራ ወንድ፥ ሴቷ ሱሪ ስለታጠቀች አልያም ቡቱቶ ስለለበሰች ስሜቱ ላይ የሚፈጠር መሰረታዊ ለውጥ የለም። ሀቅ ሀቁን ከተነጋገረን የሴቷን ልብስ ከመቀየር በላይ የወንዱን ልብ መቀየር ዋጋ አለው።
ህፃናትን ለወሲብ የሚመኙ ፥ ውብ ሚስታቸውን ትተው ከጎስቋላ ሰራተኛቸው የሚተኙ ፥ ከአእምሮ ህሙማን ጋር የሚዋሰቡ ፥ አዛውንቶችን የሚያስገድዱ ፥ አካል ጉዳተኞችን የሚ ደ ፍ ሩ ስንት ናቸው? ጉዳዩ የልብሰ ሳይሆን የልብ ነው!
ወንዱ እንዳይወሰወስ ተብሎ ሴቶች ልብሳቸው ላይ ገደብ ብናደርግ መንገዱ የት ድረስ ይወስደናል? የትም አያደርሰንም!
አንደኛ የሰውን ፍላጎት አስገድዶ መገደብ ሌላ ያልተጠበቀ አፈንጋጭነትን ይወልዳል። ሌላው መዘንጋት የሌለበት እውነት ሁሉንም መቆጣጠር አለመቻላችን ነው።
በዙሪያችን ያሉ ሴቶችን ፥ ልንቆጣጠራቸው የምንችላቸውን እንስቶች በማስገድድ የምንወደውን አይነት አለባበስ ልናስለብሳቸው እንችላለን። ነገር ግን የማንቆጣጠራቸው ሚሊዮን ሴቶች አሉ። በፊልም ፥ በቴሌቪዥን ፥ በመዝናኛው ስፍራ ወዘተ ለእርቃን ሩብ ቀረሽ የሚለብሱ ሴቶች አሉ። እነሱንስ ምን እናድርግ? እነሱን አይቶ የተወሰወሰ ወንድ...
ቀላሉ ነገር ወንዱ ራሱን እንዲገዛ ማሰልጠን ነው። ራሱን የሚገዛ ወንድ እንደ እንስሳ ያየውን ሁሉ አይመኝም። ገደቡን ያውቃል። አጥር አያልፍም።
ይህን ያፃፋኝ ዛሬ በሲዳማ ክልል ወንዶ ወረዳ የሆነው ነው። ሴቶች ሱሪ አይልበሱ በማለት የአካባቢው ሽማግሌዎች መወሰናቸውን ተከትሎ ሴቶችን ወንዶች ሱሪያቸውን እየተረተሩት ነው። ይህ ክስተት ስለ ሴቶች አለባበስ የምናደርገውን ክርክር ስላስታወሰኝ ከላይ ያለውን ፃፍኩት።
(በነገራችን ላይ የሴት ሱሪን ኢ ሞራላዊ ከሚያስመስሉ እንስቶች መካከል አንዳንዶቹ ወሲብ ቀስቃሽ ቀሚስና ጉርድ በመልበስ የሚታወቁ ናቸው። ከአንዳንድ ቀሚሶች ይልቅ የሴት ሱሪ እንደሚሻል እናውቃለን። ጉዳዩ ተራ ግብዝነት ካልሆነ በቀር...)
ከዚህ በፊት እንዳልኩት ባሕል ስታንዳርድ አይደለም። ባሕል በባሕሪው ተለዋዋጭ ነው። ይዳብራል ፥ ይኮሰምናል። ሌላው መራራ ሐቅ ደግሞ በባሕል ሰበብ የግለሰቦች መብት ይደፈጠጣል። በባሕል ካባ የተሸሸጉ ያልተገሩ እና አውዳሚ ልማዶችንም መዘንጋት የለብንም።
አንድን ጉዳይ "ባሕላችን ስላልሆነ አታድርጉት" ማለት ወንዝ አያሻግርም። መሰረታዊ የሰው ባህሪ ፥ ፋይዳው ፥ የግለሰብ መብት ወዘተ ሁሌም ከግምት መግባት አለባቸው።
ፅሁፉ ረዘመብኝ...
ለማንኛውም የሴትን ልብስ ለመቀየር ከመታገል ይልቅ የወንድን ልብ መለወጥ እውነተኛ ፋይዳ አለው።
Via ተስፋኣብ ተሾመ

❤9👎2🔥1🥰1
የዙፋን ልፊያ ምን ነገረን?
በደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ
አንዳንድ ድምፅ ወደ ጆሯችን ጠልቆ የሚገባው ንቁ! የእንቅልፍ ሰዓት አብቅቷል ለማለት ነው። አንዳንዱም ሥሪቱ እያባበለ እንዲያስተኛ ይሆናል። ሁለቱም ያስፈልገናል። የዙፋን ልፊያ እኔ እንደገባኝ ንቁም፣ ተኙም የሚል መልእክት የለውም። ችላ ወዳላችሁት ድምፅ ጆሯችሁን አዘንብሉ ዐይነት ነው።
ምን ችላ አልን?
አይገባኝም፣ አያገባኝም፣ ድምፄ ለውጥ አያመጣም፣ አላይም አልሰማም ... ላልን ችላ ማለት አያዋጣም የሚል ድምፅ ነው።
ታዲያ ድምፁ ችላ ወዳልነው የሚመልስ ነው?
ለጆሮ የማይደላ፣ በሰቆቃ የተሞላ፣ ከመጽሐፉ መነሻ እስከ መድረሻ እፎይ የሚባልበት ማረፊያ ቦታ የሌለው ነው። ችላ ላለ አማራጩ መንገድ ይኽ ይኾን? ቢኾንም፣ እንዲህ ዐይነት ድምፅ ይሰማል ወይ? እንደ ሰሚው ነው ሊባል ይችላል። የድምፁ ዐይነት ወይም የወጣበት መንገድ "ቶኑ" ወሳኝ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ። ገፋ እናድርገው ከተባለ የተናጋሪው ሰው የልብ ዝንባሌም ይለካ ልንል እንችላለን። ሚዛኑ በሰው እጅ እንዳልኾነ ብናውቅም። የተጮኸበት ጊዜም እጅግ ወሳኝ ነው።
ወዳጄ ተስፋአብ ድምፅህ ምን ዐይነት መልክ እንዳለው ከአንተ በላይ አድማጮችህ እንዲናገሩ እንደምትፈቅድ አስባለሁ። ስለ ድምፅህ ቶን ልታስረዳን እንደማትነሣም እምነት አለኝ። አንዷ አድማጭህ አይደለሁ? መልሴን ልንገርህማ ... ደግሞ ንግግር በተራ ሲኾን ያምር የለ!
ከድምፅህ የተነሣ ታምሜያለሁ። ግን ሕመሜን ሳስታምም አልገኝም፤ አላቃስትም። ለሕመም ክብር አልሰጥም። ያንተም ደስታ ቀና፣ ቀና ማለቴ ነው።
ቢኾን የምመኘው ...
ከመከራቸው የተነሣ ያነባህላቸው፣ "መብራታውያን" የእንባ ጩኸታቸው አንተ ጋ በመድረሱ፣ ስሟቸው በማለትህም እፎይ ማለት እንዲኾንላቸው። ደግሞም ለካ እንዲህ ነበር የተጎዳሁት ከሚሉ ይልቅ ትናንትናን አልፈው ዛሬ የዝማሬ ቀን ነው ብለው ለምስጋና የሚነሡ እንዲበዙ። የሀዘን ሸማቸውን ወደ ኋላ ጥለው በሚታየው የብርሃን ጭላንጭል ተስፋን የሚሰንቁ እንዲበረክቱልን ነው።

❤6
ፓስተር እና ዘማሪ መሆን እመኝ ነበር።
"ዘማሪ እና መጋቢ ተስፋኣብ ተሾመ" ተብዬ ስለመጠራት አስብ ነበር።
ልጅ ሳለሁ ህልሞቼ ብዙ ነበሩ። እግር ኳስ ተጫዋች መሆን ተመኝቼ አውቃለሁ። ከእግርኳሰኛም እንደ ሄነሪ መሆን ነበር ህልሜ። ጋዜጠኝነትንም ተመኝቻለሁ። በተለይ በምርጫ 97 ወቅት የቅንጅትን ፕሮግራም በሬዲዮ የሚያስተዋውቀው ደበበ እሸቱ ነበር። አባቴና ጓደኞቼ ደበበን በጉጉት እንደሚሰሙት ባወቅሁ ወቅት አድጌ በሬዲዮ መደመጥን ተመኘሁ።
ምኞቴ ብዙ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን ዘማሪ እና ፓስተር መሆንን የተመኘሁትን ያህል ምንም አልተመኘሁም።
ፓስተር ጌቱ ዱሬሳ ሻሸመኔዎች በፍቅር የምንወደው ሰባኪ ነው። በሻሸመኔ ሸዋበር ቃለህይወት ቤተክርቲያን በየሳምንቱ ማክሰኞ ያገለግላል። እርምጃው ፥ ድምፁ ፥ የአነጋገር ለዛው በልጅ አእምሮዬ በልዩነት ተሳለ።
ለማገልገል በወጣ ቁጥር የፓስተር ታምራት ሀይሌን መዝሙር ይዘምር ነበር።
"አለኝ ቀጠሮ፥ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ
እስቲ ልነሳ ፥ ቤቴን ላሰናዳ" እያለ ይዘምራል።
የፓስተር ጌቱ ድምፅ ለመዝሙር ባይሆንም ሲዘምር ደስ ይለኝ ነበር።
እኛ ቤት በየእለቱ ይፀለያል። እናቴ አሁንም ድረስ በየእለቱ ትፀልያለች። ልጆች ሳለን ቤታችን መለስተኛ ቸርች ይሆን ነበር። እኔ ለቤተሰቦቼ እሰብካለሁ። እነሱ ይሰሙኛል። ብዙ ጊዜ የምሰብከው ከፓስተር ጌቱ ዱሬሳ የሰማሁትን ነው። የምፀልየውም እንደ ጌቱ ዱሬሳ ነው።
ከእለታት በአንዱ ፥ አይኔን ጨፍኜ ድምፄን ከፍ አድርጌ እየፀለይኩ የከሰል ጭስ ረበሸኝ።ይሄኔ "በጌታ በኢየሱስ ስም ይህ ጭስ ይጥፋ" አልኩ። ይሄኔ እናቴ በቀስታ ጭሱን ወደ ውጭ አወጣች። ጭሱን ያወጣችው እናቴ መሆኗን ባለማወቄ ተአምር የሰራሁ መስሎኝ ደስ አለኝ።
ፓስተር መሆን እመኝ ነበር። ከፓስተርም እንደ ጌቱ ዱሬሳ አይነት ፓስተር ለመሆን እፈልግ ነበር...
ዘማሪ መሆንም እመኝ ነበር።ዘማሪ ተስፋዬ ጫላን መውደድ የጀመርኩት በጨቅላነት እድሜዬ ነበር። ድምፄን ከፍ አድርጌ የተስፋዬን መዝሙሮች ስዘምራቸው ደስ ይለኛል። አድጌ ልክ እንደሱ አይነት ዘማሪ ለመሆን ፈለግኹ።
በሻሸመኔ መሐል ከተማ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን የልጆች ኳየር ነበረን። የኳየሩ መሪ እኔ ነበርኩ። በዛን ወቅት ለኳዬራችን ልጆች መዝሙር አስጠናለሁ። በብዛት የማስጠናቸው የተስፋዬ ጫላን መዝሙር ነበር።
እድሜዬ ጥቂት ከፍ ሲል የራሴን መዝሙሮች መፃፍ ጀመርኩ። ገና የ 12 ወይ 13 አመቴ ሳለ የፃፍኳቸው መዝሙሮች አሁንም ድረስ ይገርሙኛል። መዝሙር መፃፍ ስጀምር ዘማሪ እንደምሆን እርግጠኛ ሆንኩ።
እኛ ቤት የቤተሰብ ፀሎት ፕሮግራም ሲደረግ እንደምሰብክ ገልጬ ነበር አይደል? ደግሞም በሳምንት አንዴ ትልልቅ ሰዎች በቤታችን ተሰብስበው ይፀልያሉ። ሳሎናችን ይሞላል። ያኔ እኔ ሰባተኛ ወይም ስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ቤታችን ለፀሎት በሚሰበሰቡ ሰዎች ፊት እዘምራለሁ። ብዙ ጊዜ የምዘምረው የተስፋዬ ጫላን መዝሙሮች ነው። አልፎ አልፎ የራሴን መዝሙር እዘምራለሁ።... እጅ ጭነው ይፀልዩልኛል።
ልጅ ሳለሁ ዘማሪና ፓስተር መሆን እመኝ ነበር...
ዛሬ ወረቀቶች ሳተራምስ ድሮ ከፃፍኳቸው መዝሙሮች መካከል ጥቂቱን አገኘሁ። ሳያቸው ገረመኝ። በዛ እድሜዬ ጥሩ መዝሙር እፅፍ እንደነበር ተሰማኝ።
በእርግጥ ይህ ፅሁፍ ከእናንተ ህይወት ጋር አይገናኝም።

❤10😁2🤔1
ቲክቶክን ረብ ላለው አላማ ማዋል ይገባል ደግሞም ይቻላል።... ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቲክቶክን ረብ ያላቸው ሰዎች እየተቀላቀሉ ነው። ይህ በጣም አስፈላጊ እና የሚበረታታ ነው።
ቴዎድሮስ ፀጋዬ ማለት... ስል አእምሮ የታደለ ፥ አሸናፊ አንደበት ያለው ፥ በተደራጀ መንገድ የሚያስብ ፥ ሲፅፍ የሚዋጣለት ፥ ሲናገር የሚሰምርለት ፥ አንብቦ የሚረዳ ፥ አድምጦ የሚገባው የሚዲያ ሰው ነው። ቴዲ ቲክቶክን ተቀላቅሏል። ከዛሬ ጀምሮ ርዕዮት ኪኒን በቀጥታ ስርጭት ያስተላልፋል።
ዛሬ የቴዲ ፀጋዬ የርዕዮት ኪን እንግዳ እኔ ነኝ። ስለ መጽሐፌ (ዙፋን ልፊያ) አንዳንድ ጉዳዮች እንወያያለን። በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ምሽት 12 ሰአት ሲሆ፥ በቀጥታ ስርጭት እንገናኝ።