‹‹የ ቆ ማ ጣ ልጅ››
‹‹የ ለ ማ ኝ ልጅ››
‹‹ቡ ዳ››
‹‹ዘረ-ቢስ››
‹‹ወፍ ዘራሽ››
‹‹ዲ ቃ ላ››
ጀነራሉ ልጅነታቸው በስድብ ተዋቅሮ በውርደት የታነፀ ነው፡፡ ‹‹የዚህ ሁሉ ስድብ ምንጭ እናቴ ናት›› ይላሉ ልጅነታቸውን ባስታወሱ ቁጥር

በለጋነታቸው "የ ቆ ማ ጣ ልጅ" የሚል ተቀፅላ የተጣበቀባቸው እናታቸው የስጋ ደዌ ህመም ተጠቂ በመሆናቸው ነው፡፡ የእናታቸው ሁለቱ እጆች እና ሁለቱ እግሮች ጣት አልባ ናቸው፣ አፍንጫቸው ከፊሉ የተጎመደ ይመስላል፣ ከጥርሶቻቸው መካከል ገሚሱ የለም፣ ቅንድባቸው በምላጭ የተወገደ ይመስል ባዶ ነው፣ አጭሩ ፀጉራቸው ቅጫም አልባ ሆኖ አያውቅም፣ አንዱ ዓይናቸው ፈሷል፣ ጥቁረታቸው አስፈሪ ገፅታ ፈጥሮባቸዋል፡፡

ጀነራሉ የምድራችን መልከ-ጥፉ ሴት እናቱ እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን ‹‹እንደእናቴ ያለች ቆንጆ ሴት አይቼ አላውቅም›› ብሎ ማውራት ይወዳሉ፡፡ እናታቸው ከዓይናቸው ብሌን በቀር አንዳች ውብ ነገር እንደሌላቸው እያወቁ ‹የእናቴ ውበት እንከን የለሽ ነው› ይላሉ፡፡

በልጅነታቸው ‹‹የ ለ ማ ኝ ልጅ›› የተባሉት በእናታቸው የተነሳ ነው፡፡
እናታቸው ማልደው ለልመና ስራ ይሰማራሉ፡፡ ጣት አልባ እጃቸውን ለልመና ይዘረጋሉ፡፡ በምግብ ቤቶች በራፍ ላይ ተገኝተው የሚበላ ይጠይቃሉ፡፡

የጀነራሉ እናት ምግብ ቤት የሚሄዱት የሚበላ ለመለመን ብቻ አይደለም፡፡ ተመጋቢዎች መልካቸውን ሲመለከቱ የምግብ ፍላጎታቸው እንደሚጠፋ ያውቃሉ፡፡ ሰው ሁሉ እንደሚፀየፋቸው ስለሚያስቡ የተመጋቢውን የመመገብ ፍላጎት በመዝጋት ይበቀላሉ፡፡
ጀነራሉ በእናታቸው የተነሳ ‹‹የ ቆ ማ ጣ ልጅ›› እና ‹‹የ ለ ማ ኝ ልጅ›› የሚል ስድብን ተቀብለዋል፡፡

በልጅነታቸው የትምህርት ቤት ክፍያ እና የህክምና ወጪ ይሸፍንላቸው የነበረው የእርዳታ ድርጅት መኖሪያቸውን የሚጎበኙ ሁለት ሰራተኞችን ላከባቸው፡፡ ፈንጠር ብለው ኳስ የሚጫወቱ እኩዮቻቸውን ቆመው ሲታዘቡ የእርዳታ ድርጅቱ ተወካዮች ጋር ተገጣጠሙ፡፡
በዛን ወቅት ‹‹ቤታችንን ማንም እንዲያይብን አልፈልግም›› የሚል ድፍረት ስላልነበራቸው ቅሬታ እየሸነታተራቸው ወደ ቤታቸው አዘገሙ፡፡

የቤታቸው ጣሪያው ጥቁር ላሰቲክ ለብሷል፡፡ ግድግዳቸው በወዳደቁ እንጨቶች ፣ በጥቂት አፈር፣ ባረጀ ቆርቆሮ፣ የአገልግሎት ዘመኑን በጨረሰ ቅርጮ የተዋቀረ ነው፡፡ ሶስት ሜትር በሶስት ሜትር የሆነው ቤታቸው ውስጥ የአፈር መደብ የወንበርን ሚና ይጫወታል፡፡ መኝታቸው ጭድ የተጠቀጠቀበት ማዳበሪያ ነው፡፡ ጎበኚዎች ወደቤቱ ከመግባታቸው ፈጥነው ወጡ፡፡
የዛሬው ጀነራል ዓይኑን ወደ ጎብኚዎች ሲወረውሩ አፍንጫቸውን ሲይዙ እና ምራቃቸውን ሲተፉ ተመለከቱ፡፡

ያቺን ቀን እያሰቡ እናታቸውን ‹‹ግ ማ ታ ም›› ይላሉ፡፡
ብቻቸውን ሲሆኑ ሲጃራቸውን እየማጉ ‹‹ቆ ማ ጣ›› ይላሉ እናታቸውን፡፡
‹‹ዲ ቃ ላ›› ይባሉ እንደነበር ሲያስታውሱ ‹‹ሸ ር ሙ ጣ ፣ የቆ ማጣ ሸ ር ሙጣ›› ይላሉ፡፡

የአባታቸውን ማንነት የማያውቁበት ዘመን ነበራቸው፡፡ የማወቅ ፍላጎትም አልነበራቸውም፡፡ ሲጎረምሱ ግን ‹‹ወፍ ዘራሽ፣ ዲ ቃ ላ›› መባል ታከታቸው፡፡

‹‹አባቴ ማነው?›› ድንገተኛ ጥያቄ ለእናት ተወረወረ
‹‹ዛሬ እንዴት ጠየቅኸኝ?››
‹‹አባቴ ማነው?››
‹‹አትጩህብኝ››
‹‹አባቴ ማነው?››
‹‹ና ምታኛ››
‹‹ስለአባቴ ማንነት ካልነገርሽኝ እ ገ ድ ል ሻ ለሁ››
‹‹እስከዛሬ ጠይቀህ የማታውቀውን ጥያቄ ዛሬ እንዴት ጠየቅከኝ?››
‹‹አባቴ ማን እንደሆነ ንገሪኝ››
‹‹ገድለከዋል፡፡ አባትህን በ ቡ ዳ በላኝ ብለህ የገደልከው አንተ ነህ››

ዝምታ መንበሩን ተቆጣጠረ፡፡ የዝንብን ኮቴ የሚያሰማ ዝምታ ተፈጠረ፡፡ እናት ልቧ መታ፣ ልጅን ግራ መጋባት ናጠው፡፡
ጀነራሉ ከዛች ምሽት በኋላ ወደ ቀያቸው አልተመለሱም፡፡ ሰፈራቸውን ትተው ሸሹ፡፡ ያደጉበትን መንድር ትተውት ኮበለሉ፡፡ በሸሹበት ሁለተኛ ዓመት ለውትድርና ተመዘገቡ፡፡

#የዙፋን_ልፊያ

መጽሐፉን ያላነበባችሁ አንብቡ፥ ያነበባችሁ ሃሳባችሁን አጋሩ

@Tfanos
2
‹‹ልብስሽን አውልቂ›› አዛውንቱ በለሆሳስ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡

‹‹የምትባይውን ሁሉ አድርጊ›› አያት ልጅት የመቃወም መብት እንደሌላት አስወታሱ፡፡

‹‹የእኔ ልጅ አውልቂው›› እናትም አዘዘች፡፡

መለመላዋን ከሆነች በኋላ ፋኖስ የያዘ ወጣት ቀረባት፡፡ ወጣቱ እጆቿን ከሀፍረተ ስጋዋ አንስቶ ዐይኖቹን ወደ ሴትነቷ ሰደደ፡፡ ቀጥሎ መላ አካሏን በጥንቃቄ መረመረ፡፡ ሰውነቷ ላይ አንዳች ጠባሳ እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ ‹‹ጌታዬ ንፁሕ ናት›› አለ፡፡

አዛውንቱ ሲያፏጩ በአከባቢው የነበሩ ሁሉ በርከክ አሉ፡፡ ነገሩ ግራ ሲያጋባት ብላቴናዋም ተንበረከከች፡፡

‹‹አንቺ አትንበርከኪ››

ሀፍረተ-ሥጋዋን በእጆቿ ሸፍና ቆመች፡፡
አዛውንቱ በድጋሚ አፋጩ
ከደቂቃዎች በኋላ ብላቴናዋ ጩኸት አቀለጠች፡፡ ፈርጣማ ወጣት እጇን ይዞ ‹‹እንዳትፈሪ፣ የእናታችን መብራት መንፈስ ይጠብቅሻል›› አላት

ጅብ እየተንጎራደደ መጣ፡፡ አዛውንቱ ወደ ጅቡ አቅጣጫ ሲራመዱ ጅቡ ባለበት ቆመ፡፡ በስፍራው የነበሩት እልልታ አሰሙ፡፡ ባለፋኖሱ ወጣት ብላቴናዋን ደግፎ ያዛት፡፡ ጅቡ ከአዛውንቱ እግር ሥር ተጋደመ፡፡

‹‹ነይ ወዲህ››

ብላቴናዋ በፍርሃት ባለችበት ደርቃ ቀረች፡፡

‹‹ነይ ወዲህ›› ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጠሯት፡፡
‹‹ጅቡ የእምዬ መብራት አገልጋይ ነው፡፡ ምንም አያደርግሽም›› ባለፋኖሱ ወጣት እየተናገረ እጇን ሲይዘው ተጎተተችለት፡፡
አዛውንቱ ሁለት እጃቸውን ግራ እና ቀኝ ዘርግተውት አጉተመተሙ፡፡ ጅቡ ከእግራቸው በታች ያንቀላፋ መሰለ፡፡

‹‹ይህን ያዢ››
ቀስት አቀበሏት፣ እንደታዘዘችው አደረገች፡፡

‹‹ጅቡን ውጊው››

በድንጋጤ ዐይኗ ፈጠጠ፡፡
‹‹ምንም አያደርግሽም፡፡ ደፍረሽ ውጊው፡፡ ካልወጋሽው ግን ይገድልሻል፡፡ ያኔ ማንም አያስጥልሽም››
እየፈራች ጅቡ ጉሮሮ ላይ ጦሩን በሰካችበት ቅፅበት እልልታ ተሰማ፡፡
አዛውንቱ ምንም እንዳልተፈጠረ ጉዳያቸው ላይ አተኮሩ፡፡ ከወጣቱ ስለት ተቀብለው ጅቡን ማ ረ ድ ሲጀምሩ፣ ወጣቶች ተረባርበው ከጅቡ የፈሰሰውን ደም በገንቦ ቀዱት፡፡

‹‹ተከተዪኝ››

አማራጭ ስላልነበራት ወደ ሐይቁ ተከተለቻቸው፡፡ የጅብ ፈርስ በተሞላበት ጨርቅ እርቃን ገላዋን ካሹት በኋላ ፣ በጅብ ደም ሰውነቷን ቀቡት፡፡ በደም የተቀባ ሰውነቷን ደግሞ በሐይቁ ውሃ አጠቡላት፡፡

ይህ ከሆነ ስድሳ ዓመታት ያለፉ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል፡፡
ብላቴናዋ መንፈስ የመዋረስ ስርዓት ከፈፀመች በኋላ ኪዳን አሰረች፡፡

‹‹የብልትሽን ፀጉር እንዳትላጪ፣ ሰውነትሽን ከመብራት ሐይቅ በተወሰደ ውሃ ብቻ ታጠቢ፣ የእናታችን መንፈስ ባል እስኪመርጥልሽ ድረስ እንዳታገቢ፣ ድንግልናሽን ጠብቂ›› ተባለች፡፡ የታዘዘችውን ለማድረግ መሓላ ፈፀመች፡፡

ኪዳኗን ለማፍረስ አምስት ዓመት ብቻ በቃት፡፡ ድንግልናዋን አሳልፋ ሰጠች፡፡ ኪዳን ማፍረሷ ከተረጋገጠ በኋላ የጅብ አንጀት እየተነበበ የወደፊት እጣ-ፈንታዋ ተነገራት፡፡
‹‹የእናታችንን መንፈስ ስላዋረድሽ ትዋረጂያለሽ፡፡ ምሕረትን አታገኚም፡፡ እርቃን ገላሽን ልጅሽ ያዋል፡፡ የእርጅና ዘመንሽ በውደርት ይገባደዳል፣ ሽበትሽ ይናቃል›› ተባለች፡፡ ‹ታላቁ መከራ› የሚባል ዘመን እንደሚመጣ እና ዘመኑ እርሷን በማዋረድ እንደሚጀምር ተነጋራት፡፡

..
.
አዛውንቷ እናት እርቃናቸውን በጀርባቸው እንደተጋደሙ ከስድሳ ዓመታት በፊት የገቡትን ኪዳን አሰቡ፡፡ የደፈራቸው ጎረምሳ እርቃናቸውን ትቷቸው ሄዷል፡፡ ከወደቁበት ለመነሳት አቅም አንሷቸው በጀርባቸው ተንጋለዋል፡፡
በተኙበት የበኩር ልጃቸው ተንደርድሮ ገባ፡፡ የእርስ በእርስ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ እናቱን ለመውሰድ ነበር ወደ ወላጁ ቤት ያቀናው፡፡
እናት እርቃናቸውን በጀርባቸው ተጋድመዋል . . .

#የዙፋን_ልፊያ

መጽሐፉን ያላነበባችሁ አንብቡ፥ ያነበባችሁ ሃሳባችሁን አጋሩ

@Tfanos
🤔3😢1
መስፍን እና መልኬ...

ጓደኝነት ምንድነው? ጓደኝነት እንዲህና እንዲያ ነው ብዬ መተርጎም ይከብደኝ ይሆናል። ነገር ግን የልብ ጓደኞች እንዳሉኝ ደረቴን ነፍቼ እናገራለሁ።

መስፍን ስልሺ እና መልካሙ ለብሶ ጓደኞቼ ናቸው። ጓደኛ የሚለው ቃል ሊገልፀው ከሚችለው በላይ ጓደኞቼ ናቸው!
አስረዳለሁ...

ከመስፍን ጋር የተዋወቅነው በቃለህይወት ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት (ሰንደይ ስኩል) ነው። ያን'ዜ እድሜያችን ቢበዛ አስር ቢሆን ነው። ያን ሰሞን የተጀመረ ትውውቅ ከፍ ስንል ወደ ልብ ወዳጅነት ተቀየረ።
መስፍን "እንደ ተስፋአብ አይነት ጠማማ ሰው አይቼ አላውቅም። ግትር ነህ" እያለ ስሜን ያጠፋዋል ግን ጓደኛዬ ነው።

ከመልካሙ ጋር ጓደኝነት የመሰረትነው በ2001 አ.ም ነው። አስራ ሰባት አመት ሆነው ማለት ነው። ያኔ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ነበርን። ሁልጊዜ "ጭ ገ ራ ም ሙድ ነው የምታራምደው" ይለኛል በብስጭት።

ከተለያዩ ሰዎችጋ በተለያየ ወቅት ጓደኝነት መስርቼ አውቃለሁ። ከአንዳንዶቹ ጋር ያለን ጓደኝነት በአንዲት መቀያየም ላይጠገን ተቋርጧል። ደግሞ እንዲህ ያለ ገጠመኝ ያላቸውን ብዙ ሰዎች አውቃለሁ። ጥሩ ጓደኛሞች ሆነው ይቆዩና አንድ አጋጣሚ ያቀያይማቸዋል። ከመቀያየሙ በኋላ እርቅ ቢፈጥሩ እንኳን ጓደኝነታቸው እንደቀደመው አይሆንም።

ከመስፍንና መልካሙጋ በተደጋጋሚ ተቀያይመናል። እርስ በእርስ መነጋገር አቁመን እናውቃለን። ነገር ግን በተራ አጋጣሚ ፀባችን ተረስቶ የቀደመው ጓደኝነት ይቀጥላል። ፀባችንን መዘርዘሩ አያስፈልግም። ነገር ግን ፀብ ጓደኝነታችንን አላደበዘዘውም።
ሌሎች ጥሩ ጓደኞች አሉኝ። ከአንዳንዶቹጋ አንዴ ከተጣላን ጓደኝነታች ላይጠገን እንደሚበላሽ አሳምሬ አውቃለሁ።

አንዳንድ ጓደኝነትን የቦታ ርቀት ይገድበዋል። ሶስታችን ተራርቀን ነው ያለነው። እኔ አዲሳባ ፥ መስፍን አዳማ ፥ መልካሙ ሻሸመኔ። ነገር ግን ጓደኝነታችን እንደ ጥንቱ ነው።
እኔም መስፍንም በየሰበቡ ሻሸመኔ ደጋግመን እንሄዳለን። ሻሸመኔ ስንሄድ አዳራችን መልካሙ ቤት እንደሚሆን የኔም የመስፍንም ቤተሰቦች ያውቃሉ።

ሶስታችንን ከድሮም የሚያውቀን ሰው አለ። አንድ ቀን "ምንድነው ጓደኛሞች ያደረጋችሁ?" አለኝ። በሀይማኖታዊ አስተሳሰባችን ሶስታችንም እንለያያለን። ዝንባሌያችን ለየቅል ነው። ስራችን ይራራቃል። በየግል ያለን ሰርክል አይገጥምም። የምንጋራው ለእግርኳስ ያለንን መውደድ ነው። (በምንወዳቸው ቡድኖች ፥ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች ብንለያይም)

የምንድነው ጓደኛ ያደረገን?

የሁለቱም ልብ ይገርመኛል። ሰው ይረዳሉ። ድንበር ያውቃሉ። ለሰው ስኬት ይመኛሉ። ቅን ናቸው። አያስመስሉም። ቂም አያውቁም።

መልካሙ ሲናደድ "ብ ዳ ታ ም አትሁን። ጭ ገ ራ ም ሙድ አታራምድ" ማለት ይቀለዋል።
መስፍን ሲበሳጭ "ጠማማ" ይላል።

ይህን ለምን ፃፍኩ? እንጃ!
በእርግጥ ከእናንተ ህይወት ጋር አይገናኝም።

ይህን ሁሉ አመት በቆየ ጓደኝነታችን መካከል የጋራ ፎቶ ኖሮን አያውቅም።

መስፍን ስለሺ አሳሮ አዴቶ ገለቶ
መልካሙ ለቢሶ ለማ ላንጋኖ
🤝
1
የማህበራዊ ሚዲያ ሰው አይደሉም። ፂማሙ እና ሲታይ ሀይማኖተኛ የሚመስለው መስፍን ነው። (ሀይማኖተኛ ይመስላል እንጂ የበግ ለምድ የለበሰ ተ ኩ ላ ነው)
ሲታይ ወመኔ እንደሆነ የሚያስታውቀው ደግሞ መልካሙ ነው።
😁4🔥3👍2👎1
‹‹ዲ ቃ ላ፣ የሰይጣን ልጅ››
ጦርነቱ የተጀመረባትን የተረገመች ቀን እያሰበች የአብራኳን ክፋይ ትሰድበዋለች።

‹‹አታልቅስ!... ዲ ቃ ላ››

ጦርነቱ የጀመረ ምሽት ባሏ ተባራሪ ጥይት በላው። ለታሪኩ ማንም ግድ ባይሰጠውም ባሏ በእርስ በእርስ ጦርነቱ የሞተ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ሲቪል ሆነ። አባቷ በወጣበት ሲቀር ወንድሟ አካሉ ጎደለ።

‹‹ዲ ቃ ላ››

ባሏ በሞተበት ምሽት፣ ወንድሟ አካሉ በጎደለበት ምሽት፣ አባቷ በወጣበት በቀረበት ምሽት እርሷ ለጥቃት ተላልፋ ተሰጠች። በወታደር ተ ደ ፈ ረ ች።
ደፋሪዋ ከማን ወገን እንደሆነ አታውቅም። ከጀነራሉ አሊያም ከፕሬዝዳንቱ ወገን ቢሆን ግድ አይሰጣትም፡፡ የምታውቀው በወታደር መደፈሯን ነው።

በሰደፍ ሲመታት ተዘለፍልፋ ወደቀች። የለበሰችውን ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ ለመቅደድ ሲታገል ‹‹በሕግ አምላክ›› አለች።
የሐገሪቱ አድራጊ ፈጣሪ የሆኑ ሁለት ሹማምንት ከተጣሉ በኋላ ሕገ-አራዊት እንደሰፈነ ስላላወቀች ‹‹በሕግ አምላክ›› በማለት ራሷን ለመታደግ ፈለገች።

ከምንም ሳይቆጥራት ሱሪዋን ለማውለቅ ሲታገል ‹‹መለዮህን አታከብርም?›› አለችው።
ስለመለዮ ክብር እየሰማች ስላደገች የፈጣሪን ስም ጠርቶ ከመማፀን ይልቅ ለአንደበቷ የቀረበው መለዮ ነበር፡፡

ለጥያቄዋ ቡጢ መለሰላት። ሁሉም ነገር ብዥ አለባት… እይታዋ ተጋረደ… አፏ በደም ተሞላ.. አፍንጫዋ እንደ አንዳች ባዕድ ነገር ከበዳት… ከአፏ ውስጥ ጠጣር ነገር አገኘች… ጥርሷን ተፋችው፡፡
‹በሕግ አምላክ› የሚል ተማፅእኖ ለማሰማት ጉልበት አጣች፡፡ አቅም ከዳት፡፡

ቆንጆ ነበረች፡፡ በአጭር የምትቆረጠው ፀጉሯ ከክብ ፊቷ ጋር የውበት ኪዳን ፈፅመዋል፡፡ የጥቁር ቆዳዋ ልስላሴ ድህነቷን መሰወር ተችሎታል፡፡ ጥርሶቿ፣ የጥርስ ውበት ማነፃፀረሪያ ናቸው፡፡ የረጃጅም እጅ ጣቶችዋ ከፊል በረጃጅም ጥፍር ያጌጣሉ፡፡ ከቀኝ ጣቶችዋ የቀለበት ጣትዋን እና የትንሽ ጣትዋን ጥፍሮች ታሳድጋለች፡፡ ከግራ እጇ ጣቶች መካከል ከአውራ ጣቷ እና የመሃል ጣቷ በቀር የሦስቱ ጣቶችዋ ጥፍሮች ሁሌም እንዳደጉ ናቸው፡፡

ቆንጆ ነበረች፡፡ በአንድ ቦክስ ውበቷ ከዳት፡፡
‹‹በሕግ አምላክ›› ብላ እየለመነች ውበትዋን በተነጠቀች አፍታ ክብሯንም ተቀማች፡፡
‹‹መለዮህን አክብር›› የሚለው ማሳሰቢያዋ ረብ እንደሌለው ሲገባት አቅሟን አስተባብራ ልታጠቃው ፈለገች፡፡ በደህናው ጊዜ ለውበት ዓላማ ያሳደገቻቸውን ጥፍሮች የአደጋ ጊዜ መከላከያ ልታደርግ ሞከረች፡፡ በጥፍሮቿ ልታጠቃው ታገለች፡፡ ጉልበተኛውን በጥፍሯ ልትቧጭረው መሞከሩ ከጥፍር መሰበር ውጭ ምንም አልፈየደላትም፡፡

‹‹በሕግ አምላክ›› በተሸነፈ ድምፅ ለመጨረሻ ጊዜ ተለማመጠችው፡፡
በጉልበት ተገናኛት፤ ተ ደ ፈ ረ ች። የመጀመሪያም የመጨረሻዋም ከሆነው ባሏ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንድ ገባባት፡፡
ማሕጸኗ ባዕድ ነገር የገባበት ይመስል አመማት። እላይዋ ላይ ተከምሮ የቆየበት ጥቂት ደቂቃ የዘላለም ያህል ረዘመባት።

‹‹በሕግ አምላክ›› እያለች መደፈሯ እንደ እግር እሳት ለበለባት፤ ‹መለዮ አክብር› የተባለ ወታደር የጀመረውን ክፋት ሁሉ እርግፍ አድርጎ እንደሚተው እየሰማች አድጋ ተቃራኒው ቢገጥማት ሃዘን ሰረሰራት፡፡
ከራሷ ተጣልታ ፣ የገዛ እሷነቷን ተፀይፋ መኖር ጀመረች።

‹‹ሁለት ባለሥልጣናት ለመንበር ሲሉ በመጣላታቸው የተነሳ የእኔ ማሕጸን ጦር ሜዳ ሆነ›› ትላለች ሆድ እየባሳት።
የወር አበባዋ እንደቀረ ያወቀች ሰሞን፣ ፅንስ የማቋረጥ ሃሳብ አልተፈጠረባትም ነበር።
የመጀመሪያውን ስድስት ወር ያሳለፈችው የተደፈረችበትን ቅፅበት በማሰብ እያለቀሰች ነው። ግማሽ ዓመት ያለ እረፍት አነባች።አዛኝ የለሽ ለቅሶ …

በሆዷ የተሸከመችው ፅንስ ስድስት ወር ሲሞላው በረገገች። ‹‹የ ጠ ላ ቴ ን ልጅ አልወልድም›› ብላ ወደ ሆስፒታል ሄደች።

‹‹ማስወረድ አትችይም›› አላት ዶክተሩ
‹‹ለምን ሲባል?››
‹‹ለሕይወትሽ አደገኛ ነው››
‹‹ይሁና››
‹‹ገብቶሻል? ልትሞቺ ትችያለሽ››

ልቧ በጦር የተወጋ መሰላት። ደነገጠች።
መሞት አትፈልግም። ሕይወቷ ባያጓጓትም አለመኖርን አትመኝም። መኖሯን የጠላች ሆና ሳለ መሻቷ በህይወት መቆየት ነው።
ደመ-ከልብ ሆኖ የቀረ ሟች ባሏ መታሰቢያ የሆነውን የበኩር ልጇን ትታ መሞት አትፈልግም።

ፕሬዝዳንቱ እና ጀነራሉ ተጣልተው የእርስ በእርስ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት፣ ከባሏ እና ከሁለት ዓመት ልጇ ጋር በደስታ ይኖሩ ነበር። የድሃ ቤታቸው ተስፋ እና ፍስሐ ነበረው። ጦርነቱ የተጀመረ ምሽት ባሏ በወጣበት ቀረ። ከዚያን ጊዜ በኋላ ልጇ ድንጉጥ እና ህመምተኛ መሆኑን አይታለች።
ፅንስ ለማቋረጥ ስትሞክር ብትሞት ከአፍቃሪ ባሏ ያገኘችው ልጇ ሊገጥመው የሚችለውን ክፉ እጣ አስባ የጠላቷን ልጅ ለመውለድ ወሰነች።

ተደፍራ የወለደችው ልጅ ስድስት ወር ሆኖታል። ልጇን ስታየው ሆድ ይብሳታል፣ መጠቃት ይሰማታል።
ልጇን ስታቅፈው አካላዊ ህመም የሚሰማት ጊዜ አለ።
የገዛ ልጇን አቅፋው ከእንብርቷ በታች ውጋት ይሰማታል። ራሷን ከፍሎ ያማታል፣ ከመቀመጫዋ ጀምሮ እስከታፋዋ ድረስ ይደነዝዛታል፣ ልቧን ያፍናታል፣ ዐይኗን ይቆጠቁጣታል። የሰውነቷ ሙቀት ይጨምራል።

አንዳንዴ ልጇን አቅፋው ትታመማለች፡፡
ለምን እንደሚያማት አታውቅም። ሃኪም ዘንድ ሄዳ ምንም ዐይነት ህመም እንደሌለባት ነግረዋታል።
‹‹ዲ ቃ ላ የሰይጣን ቁራጭ››
ህመሟን የምታስታግሰው ከጠላቷ የወለደችውን የአብራኳን ክፋይ በመስደብ ነው።
‹‹ሰ ይ ጣን፣ ዘረ-ሰ ይ ጣን፣ ዲ ቃ ላ››


#የዙፋን_ልፊያ

መጽሐፉን ያላነበባችሁ አንብቡ፥ ያነበባችሁ ሃሳባችሁን አጋሩ
3
ለታክሲ ተሰልፈናል። የጋምቤላ ልጆች ሰብሰብ ብለው ከፊታችን ተደርድረዋል። ከአንድ ፕሮግራም እየተመለሱ ይመስላል። ዘንጠዋል፥ ፊታቸው ደስታቸውን ይመሰክራል። በጣም ብዙ ናቸው። እየተሳሳቁ በቋንቋቸው ያወራሉ።

አጠገቤ የነበረው እንደዋዛ "እነሱ እኮ ራሳቸውን እንደ ኢትዮጵያዊ አይቆጥሩም" አለኝ። እንዲህ አይነት ወሬ ብዙ ጊዜ ሰምቼ ባውቅም ቅሬታ ሸነታተረኝ...

በእርግጥ ራሳቸውን እንደ ኢትዮጵያዊ አይቆጥሩም?

ለዳር አገር ዜጎች ያለን የተዛባ አሰተሳብ ያሳፍራል። አንዳንዶቻችን ራሳችንን እንደተዋጣለት ኢትዮጵያዊ መቁጠር ላይ ጎበዝ ነን። ለሌሎች ደግሞ የዜግነት ደረጃ ማውጣት ያምረናል።

ከተወሰነ አመታት በፊት ጋምቤላን ጎብኝቼ ነበር። ጋምቤላ ውብ ክልል ናት። የክልሉ መቀመጫ የሆነችው ከተማም ከሙቀቷ በቀር ወድጃታለሁ። ጋምቤላ እጅግ ለም አካባቢ ነው። ባሮ ወንዝ ይማርካል። ባሮ ወንዝ ከጋምቤላ ወደ ሱዳን የሚፈስ ወንዝ ሲሆን የጋምቤላ ከተማን ያቋርጣል። ግዙፉ ባሮ ዳር ተቀምጠን አሳ እየበላን ስለ ጋምቤላ ተጨዋውተናል። የባሮ አሳ እጅግ ግዙፍ ነው። በአንድ አጋጣሚ 150 ኪሎ የሚመዝን አሳ ተገኝቶ ጉድ እንደተባለ ሰምተናል።

ጀጀቤ ተራራ ደግሞ ከከተማው ብዙ ሳይርቅ የሚገኝ ሲሆን፥ ከሩቁ ደቡብ ሱዳንን ያሳያል።
ጋምቤላ ብዙ መስህብ አለው።

እንደ ሕዝብ ለዳር አገር ዜጎች የተዛባ አመለካከት አለን ተባባልን አይደል?

ከበዙ የተዛቡ አመለካከቶች መካከል አንዱ "አገር አይወዱም" የሚል አሳፋሪ ፕሮፖጋንዳ ነው። ጋምቤላ በነበረኝ ቆይታ ያየሁት ሐቅ ሕዝቡ ለአገሩ ያለውን ቀና አመለካከት ነው። ከተማው መሐል ባለ የመዝናኛ ቦታ የኢትዮጵያ ካርታ በግዙፉ ተሰርቷል። ስለዛ ካርታ የሚያወሩት በኩራት ነው። ያገኘኋቸውን ሰዎች ስለ ኢትዮጵያ ስጠይቃቸው የሚመልሱልኝ በጣም ቀና በሆነ እና ደስ በሚል መልኩ ነው።

አገር መውደድ እንዴት ይገለፃል? አንዳንዱ ባንዲራ ሲያይ በማልቀስ የአገር ፍቅሩን ይገልፃል። ስለ አገሩ ታሪክ በኩራት ይተርካል። ይህ ጥሩ ነው። ነገር ግን አገር መውደድ በዚህ መንገድ ብቻ አይገለፅም።... ስህተታችን የዳር አገር ሰዎች በዚህ መንገድ ብቻ ፍቅራቸውን ካልገለጡ የአገር ፍቅር የላቸውም የሚለው አስተሳሰብ ነው።

ሌላ መራራ እውነት...

አገር ለምን ይወደዳል?

አገር ጣዖት አይደለችም። አገር አንዳች አይነት መለኮታዊ ነገርም አይደለችም። ከአገር ተጨባጭ ፋይዳ ሊገኝ ይገባል።

ዜጎች ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ያገኙት ተጨባጭ ፋይዳ ምንድነው? ይህ ጥያቄ በጣም የቅንጦት ጥያቄ ነው። በኛ አገር ሁኔታ ዜጎች ከአገራቸው ተጨባጭ ፋይዳ ማግኘትን ሊመኙ የሚችሉበት ሁኔታ የለም። ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጉዳቶችን እየተመለከትን ነው።

የዳር አገር ዜጎችን እንደ ኢትዮጵያዊ አናያቸውም። ነገር ግን አገር ውደዱልን እንላለን። ይህ ቤት አይመታም።

ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ፥ መልካም አስተዳደር ፥ ፖለቲካዊ ውክልና ወዘተ አላገኙም። በቆዳ ቀለማቸው የተነሳ ይሰደባሉ። በባህላቸው እንሳለቃለን። ስለ ታሪካቸው እና አኗኗራቸው ግድ አይሰጠንም። ግን ደግሞ አገር ውደዱ እንላለን። ይህ ቤት አይመታም።

በቅርቡ ጋንቤላ ላይ ሲቪሎች የሞቱበት ግጭት ተከስቶ ነበር። ለነሱ ማን ድምፅ ሆነ? ሚዲያው ፥ አክቲቪስቱ ፥ ፖለቲከኛው ወዘተ ዝም አላላቸውም? ሀዘናቸውን ሳንጋራ ሌላ ነገር ማውራት እንችላለን?

አገር የሚወደደው በምክኒያት ነው። ምናልባት አንዳንድ ሰዎች አገር መለኮታዊ ግኝት ይመስላቸዋል። ከነሱ መከራከር አልፈልግም። ነገር ግን አገር በተጨባጭ ፋይዳ ያልሰጠችው ማህበረሰብ በአገር ፍቅር ስሜት እንዲንገበገብ አይጠበቅም።

ይህ ፅሁፍ ረዘመ መሰለኝ

VIA ተስፋኣብ ተሾመ

@Tfanos
10
ጥቂት የጋምቤላ ቃላት ልንገራችሁ

ውነ ሪዮንደ ፥ እንደምን አላችሁ ማለት ነው

አሜሪኪኒ ኬልካሃ ለዘላለም እወድሻለሁ /እወድሃለሁ/ ማለት ነው።

ያኔ ጋምቤላን ስጎበኝ የ ቃረም ኳቸው ናቸው። የማስታውሰው እኒህን ብቻ ነው
👍4
"ውልደ ብርሃን በክስቶስ" ቤተክርስቲያን በተለምዶ ቃለ አዋዲ ተብላ ትጠራለች። ትክክለኛው የቤተክርስቲያኗ መጠሪያ ስም ውሉደ ብርሃን በክርስቶስ ነው።

ከተወሰነ አመታት በፊት በጓደኛዬ ግብዣ ሄድኩ። ብዙ የእምነት ተቋማት እየተገኘሁ ትምህርታቸውን ተካፍዬ አውቃለሁ። ነገር ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ውሉደ ብርሃን የሄድኩበትን ቀን ያህል ከአእምሮዬ የማይጠፋ ቀን የለም።

በእለቱ ሁለት ጊዜ ተሰበከ። ስሙን የረሰሁት ሰባኪ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 3ን አስተማረ። መምህር አሰግድ ደግሞ እንደ ሁልጊዜው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አስተማረ። አሰግድ ሳህሉ ሲያስተምር በእንባ ጭምር ነበር። ምሳሌዎቹ ፥ ትምህርቱ ወዘተ ዛሬም ድረስ ትዝ ይለኛል።

ግጥም ተነበበ፥ ተፀለየ ፥ ተዘመረ።

ፕሮግራሙ ረጅም ነው። ሰአታት የፈጀ፥ ነገር ግን ፍፁም የማይሰለች ነበር።

የፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ ሁለት ሰዎች ሊዘምሩ ተነሱ። ዘመናይ ጎሳዬ እና ላዕከ ይባላሉ። በኪራር ታጅበው ዘመሩ። "በሰማይ ታላቅ ምስጋና ይሰማል" የሚለውን መዝሙር ነበር የዘመሩት። መዝሙሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የሰማሁት።

ጉባኤው የዘመረበት መንገድ ፥ የህዝቡ መነካት ፥ የነዘመናይ መሰጠት ከአእምሮ አይጠፋም።... ድንገት ራሴን ከታዛቢነት ወደ ተሳታፊነት ተቀይሬ አገኘሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁትን መዝሙር በእንባ ጭምር አብሬያቸው ዘመርኩ።

"በሰማይ ታላቅ ምስጋና ይሰማል
የእልልታ ወጀብ መድረኩን ይንጣል
ሺ ጊዜ ሺ የሚሆኑ ባንድነት
ይሰግዱለታል በበጉ ዙፋን ፊት"

ከጉባኤው በኋላ መዝሙሩ የዘማሪ ሀብታሙ እንደሆነ አወቅሁ። እስከዛሬ ድረስ መዝሙሩን ደጋግሜ እሰማዋለሁ። መዝሙሩን ስሰማው ትዝ የምትለኝ ዘመናይ ናት።

"በደ ም ህ ከነገድ ሁሉ
ሰወችን ዋጀህ እያሉ
ኢየሱስ ታ ር ደ ሀ ልና
ያበዙልሀል ምስጋና

ዐዕላፋት ጊዜ ዐዕላፋት
ከቁጥር በላይ መላዕክት
አዲሱን ቅኔ ሊ ዘ ር ፉ
ይታደማሉ ከሰልፉ"

ዘመናይ የምትዘምርበት መንገድ ይገርመኛል። ሻሸመኔ ጉባኤ ባዘጋጁ ቁጥር ቋሚ ታዳሚያቸው ሆኛለሁ። ዘመናይ በጉባኤ መሐል ስትዘምር ጉባኤው በሙሉ ትኩረቱ ክርስቶስ ይሆናል።...

ለዘማሪ ጓደኞቼ ስለ ዘመናይ ነግሬያቸው አውቃለሁ። እወዳታለሁ!

ዘመናይ አዲስ አልበም ልትለቅ እንደሆነ ሰማሁ።

እወዳታለሁ!

እንደተለመደው ይህ ጽሁፍ ከናንተ ህይወት ጋር አይገናኝም

@Tfanos
5
በዚሁ አመት "ኮርደር ልማት" የሚባለው የኮስሞቲክስ ስራ አይኖርም። ለምን?

ሀ፥ IMF መንግስታችንን ስለተቆጣ

ለ፥ ምርጫ ስለደረሰ የህዝብን ልብ ለማግኘት

ሐ፥ በጀቱን ድ ሮ ን መግዣ ላይ ለማዋል

መ፥ መንግሥት በኮሪደር ሰበብ ለሚፈናቀሉ ራርቶ

ሠ፥ ከ "መ" በቀር ሁሉም መልስ ነው

ተማሪዎች ፥መሳሳት ካልፈለጋችሁ ምርጫ "ሠ" ን አክብቡ

@Tfanos
😁20
ቴዎድሮስ ፀጋዬ መጽሐፌን አንብቦ ወዶታል። ደግሞም በቲክቶክም ሆነ በዩቲዩብም ሰዎችን "የዙፋን ልፊያን አንብቡ" እያለ ነው።

ሰሞኑን በልደቱ መጽሐፍ ምርቃት ላይ የተናገረውን ላጋራ

"እዚህ መጥቀሱ ተገቢ ነው ብዬ የማስበው መጽሐፍ አለ። የሐገሩን አደጋ ለማሳሰብ የተፃፈ... ፈልጋችሁ እንድታነቡት የምለው መጽሐፍ የዙፋን ልፊያ የተሰኘው መጽሐፍ ነው። በተስፋኣብ ተሾመ የተፃፈ ነው።... ሐገሩ የዘቀጠበትን ሁኔታ ለማሳሰብ የሚሞክር ደራሲ ነው ተስፋኣብ።... ስለዚህ የተስፋኣብ ተሾመን የዙፋን ልፊያ መጽሐፍ ፈልጋችሁ አንብቡ።... በመጽሐፉ ዙሪያ ተነጋገሩ ተከራከሩ።... /የዙፋን ልፊያ/ በኢትዮጵያ የታተመ እና የሚገባውን ያህል ሽፋን ያላገኘ መጽሐፍ ነው"

ቴዲ ይህን የተናገረው በልደቱ መጽሐፍ ምርቃት ላይ ነው
2
ቴዲ ከላይ የተገለፀውን የተናገረው የልደቱ መጽሐፍ ሲመረቅ ነው። በፕሮግራሙ ልደቱ አያሌው ፥ አንዳርጋቸው ፅጌ ፥ ያሬድ ሀይለማርያም ፥ ርዕዮት አለሙ ፥ በቃሉ አለምረው ፥ ጋዜጠኛ ጴጥሮስ ፥ ዶክተር ኤርሲዶ ወዘተ ተገኝተዋል።

ቴዲ የዙፋን ልፊያ አንደርሬትድ መሆኑን መስክሯል 😎😎😎

ከቴዲ ምስክርነት በኋላ እኔ ለራሴ እየዘፈንኩ ነው።

"ይችላል ፥ ተስፋ ይችላል
ይችላል ፥ ተስፋ ይችላል"

እያልኩ ነው 😀😀😀
👍112😁1
ይህ ማማረር ሳይሆን ትዝብት ነው...

በአገራችን ካሉ ግዙፍ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መካከል ከአንዱጋ ስለ የዙፋን ልፊያ የቃለመጠይቅ ቀጠሮ ነበረን። እንዳላረፍድ ስላስጠነቀቁኝ በጊዜ ከቤቴ ወጣሁ። የቀጠሮችን እለት "በጊዜ ተገኝልኝ" ብሎኝ ነበር አስተባባሪው።... በጊዜ ተገኝ ካለኝ ከ30 ደቂቃ በኋላ ቀጠሮ መሰረዙን ነገረኝ።
የሚጠበቅ ነው!

ሰሞኑን ስለዙፋን ልፊያ ልናወራ ከአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ቀጠሮ ነበረን። እሱም ተሰረዘ። አልገረመኝም።

የኛ አገር ሚዲያ ባህሪ አስቸጋሪ ነው። ሎቢ ማድረግ ይፈልጋል። "መጽሐፍ ፅፌያለሁና እንግዳ አድርጉኝ" እንድትሏቸው ይፈልጋሉ። ራስን ማሻሻጥ ላይ ጎበዝ ያልሆነ ስለስራው አይወራለትም።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ስለ ዙፋን ልፊያ ለማውራት ቀጠሮ ከሰጡኝ በኋላ ቀጠሯቸውን የሰረዙ የዩቲዩብ ፥ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ሚዲያዎች አሉ።... የጠበቅኩት ነው። ገና የመጽሐፉን ርዕስ ሲያዩ "ይሄ ነገር..." ያሉኝ ብዙ ናቸው። አልፈርድባቸውም።

ማማረር አልፈልግም። ግን ደግሞ የተጋነነ ፍርሃት ትክክል አይመስለኝም።

ለማንኛውም ከዚህ በኋላ የዙፋን ልፊያን ለማስተዋወቅ የተሻለው ቦታ ማህበራዊ ገፅ ይመስለኛል።

መጽሐፉን ያነበባችሁ ሰዎች ሪቪው ብትፅፉ ደስ ይለኛል።

አቅም ያላችሁ ደግሞ መጽሐፉን ለሰዎች በስጦታ ብትሰጡ ሸጋ ነው።

ለምሳሌ ወንድማችን ቢላል ከዚህ ለ35 ሰዎች ዮሴፍ ኢየሱስ ወርቅ ደግሞ ለ10 ሰዎች የዙፋን ልፊያን ስጦታ ሰጥተዋል።

መጽሐፉን አምስትም አስርም እየገዙ ስጦታ መስጠት እኔን ማበረታታት ነው። ደግሞ ማንበብ የሚፈልጉ እንዲያነቡት ማገዝ ነው።
👍6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቴዎድሮስ ፀጋዬ 🤝 የዙፋን ልፊያ

"ለሌሎችም አረአያ እንዲሆን ብዬ ነው የዙፋን ልፊያን የማነሳው"
👍2
‹‹... ‹ተደፈርኩኝ› ብዬ ለማዘን አቅም የለኝም፡፡ የመጣሁት ስለልጄ ወደፊት በመጨነቄ ነው››

‹‹ልጅሽን ምን አገኘው?››

‹‹የአራት ዓመት ልጅ አለኝ፡፡ ስለ እርሱ ተጨንቄ መ ሞ ቴ ነው፡፡ ጦርነቱ ሲጀምር ሕግ ጠፍቶ ስርዓት አልበኝነት ነገሠ››

አዛውንቱ የሚያውቁትን እውነት ደግመው እየሰሙ ነው፡፡ የእርስ በእርሰ ጦርነቱ ከጀመረ በኋላ የሐገሪቱ ሕግ ሕገ-ወጥነት እንደሆነ አስተውለዋል፡፡ የሐይማኖት አባቶች ጆሮ ሲነፈጉ፣ የእምነት ተቋማት አቅም ሲያጡ፣ የመብራት ከተማ አባቶች መደመጥ የማይችሉ ሲሆኑ፣ ሸንጎው መዘባበቻ ሲደረግ፣ ሥነ-ምግባር ለጉልበት ሲገብር፣ ሕግ ለአመፅ ሲሰግድ አይተዋል፡፡

‹‹ጉልበተኞች ባሌን አገቱት›› አለች ሕይወት

‹‹ጉልበተኞች ባሌን ካገቱተ በኋላ ማስለቀቂያ ገንዘብ ጠየቁኝ፡፡ የጠየቁኝን ያህል ገንዘብ ዘር ማንዘሮቼ ኖሯቸው አያውቅም፡፡ የማደርገው ግራ ቢገባኝ የልጄን አባት ለማስለቀቅ ለልመና ወጣሁ፡፡ የሆነብኝን እየተናገርኹ የመብራትን ሕዝብ ለመንኹ፡፡ህዝቡ አላሳፈረኝም ነበር፤ አጋቾቹ ግን አሳፈሩኝ፡፡ ገንዘቡን ከተቀበሉኝ በኋላ ባሌን ይለቁልኛል ብዬ ብጠብቅም እነርሱ ግን ‹ገንዘቡን የከፈልሽው የሰጠንሽን ቀነ ገደብ አሳልፈሽ ነው› ብለው ባሌን ገ ደ ሉ ት››

አዛውንቱ ‹የመብራታዊያን አባት› በመሆናቸው ሲደሰቱ ኖረዋል፡፡ ‹‹ፈጣሪ ስለወደደኝ መረጠኝ›› ይሉ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ግን ደስታቸው በምሬት ተተክቷል፡፡ ‹ምነው ባልተመረጥኩ› ማለት ጀምረዋል፡፡ የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከጀመረ በኋላ በየዕለቱ ብዙ ሀዘን ይሰማሉ፡፡ ጫንቃቸው መቋቋም ከሚችለው የበለጠ የመከራ ታሪክ ያደምጣሉ፡፡

‹‹አባቴ ፈርቻለሁ›› አለች ሕይወት

‹‹እንደምሞት ታውቆኛል፡፡ ባሌ ከሞተ በኋላ ልጄን ለማሳደግ ብዙ ለፋሁ፡፡ እድሜ ለዐጦ ርነ ቱ ስራ ማግኘት በባዶ ሆድ ወደተራራ መሮጥ ሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ልመና ጀመርኩ፡፡ ጦ ር ነ ቱ ኩራቴን ወስዶብኛል፣ ክብሬን ቀምቶኛል፡፡ ልመናን ብቻ ሳይሆን ተገዶ መደፈርን በፀጋ መቀበል ቻልኩበት፡፡ ከአንድም ሦስቴ ተደፈርኩ፡፡ በህብረት ተፈራረቁብኝ፡፡ መደፈርን ይሄ ጦርነት ለሁሉም ሴቶች ያመጣው መርገም እንደሆነ ስላመንኩ ህመሜን ቻልኩት››

ህይወት እየተናገረች አዛውንቱ ወደ ውስጥ አለቀሱ፡፡

የጦርነት እሳት ከተለኮሰበት ቀን ጀምሮ የሴቶች ማሕጸን ጦር ሜዳ መሆኑ ያንገበግባቸዋል፡፡ ‹ሴት ስትጠቃ ሐገር ትጠቃለች› ይላሉ አዛውንቱ፡፡

‹ሴት የቤተሰብ ማገር ናት፡፡ የተጠቃች ሴት ለመንፈስ ህመም ተጋላጭ ትሆናለች፡፡ ሥነ-ልነቦናዋ ይታመማል፣ የአዕምሮ ጠባሳ ይፈጠርባታል፡፡ ሥነ-ልቦናዋ የተጎዳ ሴት ቤተሰብ ስትመሠርት ቤተሰብዋ ለህመም ተጋላጭ ይሆናል፣ የታመመ ቤተሰብ የታመመ ልጅ ይፈጥራል፣ መንፈሱ የታመመ ልጅ የሐገር ስጋት ነው› ይላሉ አዛውንቱ፡፡
‹የሰለጠነ ሕዝብ ለደካሞች ይሟገታል፡፡ ጉልበተኛ ወንድ ደካመዋን ሴት ሲያጠቃ ጠበቃ መሆን ማህበረሰባዊ ግዴታ ነው› ይላሉ አዛውንቱ፡፡

‹ጉልበተኞች ደካሞችን ሲያጠቁ ዝም ማለት ሐገር እንድትፈርስ መፍቀድ ነው፡፡ ወንድ ሴትን ሲያጠቃ ዝም የሚል ሰው ጉልበተኛው ደካማን እንዲያጠቃ ፈቅዷል፡፡ ይህ ማለት ሀብታም ድሃን እንዲበድል፣ በቁጥር ብዙ የሆነ ጥቂት የሆኑትን እንዲያጠቃ፣ ስልጣን ያለው ስልጣን አልባው ላይ እንዲሰለጥን መፍቀድ ነው፡፡ ጉልበተኛ ጉልበት የለሽን ሲያጠቃ ስርዓት አልበኝነት ይፈጠራል፡፡ ስርዓት አልበኝነት ደግሞ ሐገር ያፈርሳል› ይላሉ አዛውንቱ፡፡

‹አስገድዶ የሚደፍር ወንድ ማህበራዊ ግኑኝነት ላይ ጥቃትን ይፈፅማል፡፡ እርስ በእርስ እንዳንተማመን የሚያደርግ መርዝን ይረጫል፡፡ ማህበራዊ ግኑኝነትን ያላላዋል› ይላሉ አዛውንቱ

‹አስገድዶ ደፋሪ፣ ወንድነት ላይ ጭምር ጥቃት አድራሽ ነው፡፡ ደፋሪዎች ሌሎች ወንዶች እንደ አውሬ እንዲታዩ ያደርጋሉ፡፡ ወንዶች ጠባቂዎች ተደርገው መቆጠር ሲገባቸው እንደስጋት እንዲታሰቡ ሰበብ ይሆናሉ› ይላሉ አዛውንቱ፡፡

‹‹አባቴ›› አለች ሕይወት እንባዋን እየጠረገች

‹‹እያደመጥኩሽ ነው፤ ቀጥይ ልጄ››

‹‹በልመናው ብዙ አልቆየሁኝም፡፡ ሁሉም ህዝብ ለማኝ ሆኗል፡፡ ትላንት ለተቸገሩት ይረዱ የነበሩ ዛሬ እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል፡፡ ቸርነትን ለማድረግ ይዘረጋ የነበር እጅ ለእርዳታ ፍለጋ ሲዘረጋ አየን፡፡ ለማኙ ሲበዛ ልጄን ለምኜ ማብላት ቸገረኝ፡፡ ያኔ ገላ ሽያጭ መፍትሄ መሰለኝ፡፡ ከልመና ወደ ሽርመጥና ገባሁ፡፡ … እድሜ ለጦርነቱ አቻዎቼ በመደዳ ሴተኛ አዳሪ እየሆኑ ነው፡፡ ስህተት እና ትክክሉ ድንበሩ ጠፍቶብናል፡፡ ለእኔና ቢጤዎቼ ትክክል ማለት ራስን በሕይወት ማቆየት ሆኗል››

አዛውንቱ ጦርነቱ የተጀመረበትን ቀን ረገሙ፡፡ በሐገሪቱ ምን እየተደረገ እንዳለ የማያውቁ ሚስኪኖች በጦርነቱ የተነሳ የተጫነባቸውን የመከራ ቀንበር አስበው ጦርነቱ የጀመረበትን ቀን ረገሙት፡፡

‹‹አባቴ ሰሞኑን የምሞት ይመስለኛል፡፡ የስኳር ህመም እያሰቃየኝ ነው፡፡ መድሀኒት የለኝም፡፡ መድሀኒት መግዣ አላጣሁም፤ ያጣሁት መድሀኒት ነው፡፡ ሁለቱ ተዋጊዎች በዙሪያችን መፋለም ከጀመሩ በኋላ ወደ ከተማችን መሠረታዊ ነገሮችን ማስገባት ከባድ ሆኖብን መክረሙን ያውቁታል፡፡በዚህ የተነሳ በከተማችን መድሀኒት ጠፍቷል፡፡ የምሞት እየመሰለኝ ስለልጄ ፈራሁኝ አባቴ››

አዛውንቱ እንባቸውን ለመገደብ ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸው ቆይተው የነበረ ቢሆንም ተሸነፉ፣ ለእንባቸው ተረቱ፡፡ አንገታቸውን አቀርቅረው አለቀሱ፡፡

የለቅሷቸው ሰበብ ጉዳቷ ብቻ አልነበረም፡፡ በየዕለቱ ብዙ ሰቆቃ ያደምጣሉ፣ ችግር ሲያደምጡ ነግቶ ይመሻል...

ያስለቀሳቸው የሕይወት ስሜት ነው፡፡

በፊታቸው ሆና ብሶቷን የምትናገርው ምስኪን ሴት ገፅታ ላይ የተመለከቱት ስሜት አስነባቸው፡፡ ‹‹ሀዘኗ ከህመሟ አይነፃፀርም፡፡ ማዘን በሚገባት መጠን እንዳታዝን ያደረጋት መከራን መለማመዷ ነው›› ብለው ሲያስቡ አለቀሱ፡፡

‹‹መከራን እንደመልመድ ያለ መከራ ከወዴት ይገኛል?››

#የዙፋን_ልፊያ

መጽሐፉን ያላነበባችሁ አንብቡ፥ ያነበባችሁ ሃሳባችሁን አጋሩ።


@Tfanos
4
የአንባቢ አስተያየት

መጽሐፍህን አንብቤ ጨረስኩት። በስራ መደራረብ ምክንያት ለንባብ ጊዜ አላገኘሁም ነበርና፡ ትላንት ነው የጀመርኩት። ጀምሮ ለማቆም ይከብዳል። እያንዳንዱ ገፀ ባህሪ የሚወክለው ስብእና (ፖለቲካችን፥ ኋላ ቀር እምነታችን፥ የስነ አይምሮ በሽታ/ጠባሳ፥ ..) መማር ለሚፈልግ ብዙ ዕውቀት ይሰጣል።

በውስን ገፆች ብዙ subject ያካተተ ድንቅ መጽሐፍ ነው የጻፍከው፡ ጥልቅ አንባቢ መሆንክን ተረድቻለሁ ("አንተ ከተረዳኸኝማ ምኑን አንባቢ ሆንኩት" እንዳትለኝ አደራ 😊)።

ወቅታዊ ሁኔታ ስጋት ጥሎብን ለመናገር ምንፈራቸውን አሁናዊ እውነታዎችና የወደ ፊት ስጋቶች poetic በኾነ መንገድ ከትበህ voice of the voiceless ስለሆንከን ከልብ አመሰግናለሁ። የጻፍክበት ዓላማ ከግብ እንዲደርስ እመኛለሁ።

በርታ!

አስተያየቱን ያጋራን Henisha Henishom ነው።

#የዙፋን_ልፊያ

መጽሐፉን ያላነበባችሁ አንብቡ፥ ያነበባችሁ ሃሳባቾሁን አጋሩ
3
ለልደቱ አያሌው

ከአክብሮት ጋር

#የዙፋን_ልፊያ 🤝
"ወንድ ልጅ ከሃያዎቹ በኋላ ያለው ህይወት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር መጫወትን ይመስላል?"

... አትሌቲኮ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ከነሱጋ መጋጠም...


@Tfanos
አትሌቲኮ ተከላካይ ቡድን ነው። አንዴ ግብ ቀድሞ ካስቆጠረ በኋላ ፈፅሞ ይከላከላል። አትሌቲኮ ላይ ግብ ማስቆጠር ከባዱ ስራ ነው
👏3
የአንባቢ አስተያየት

ትዝታን ማን ፈጠረዉ?

የተሰበረ ልብ ያላቸዉ ሰዎች በጥሩም ይሁን በመጥፎ ጊዜ ፥ ትዝታቸውን ማን ፈጠረው?

መጥፎ ትዝታ በሰዉ ልጅ ላይ አሳርፎ ከሚያልፍ ነገር መካከል ዋነኛው ጦርነት ነው። ጦርነት ብዙ ሊባልለት የሚገባ ቢሆንም ዝምታን መርጠናል። ስለ ጉዳዮ በምሬት የያነሱትም ይፈረጃሉ። እንደ ፓለቲካኛ እና የአንድ ወገን ደጋፊ ተድርገው ይቆጠራሉ።

የጦርነት አጀንዳ በፅንፈኝነት ሰበብ ተደባብሶ ያልፋል። አንዳንዴ ደግሞ "ጦርነት ዛሬ ነዉ ወይ የተጀመረዉ? ምነዉ አዲስ ሆነባችሁ?" አይነት የስላቅ ጥያቄ ይነሳል።
እይታችን ምንም ሆነ ምን ጦርነት disaster ነዉ።

የዙፋን ልፊያ የጦርነትን ጅራፍ በmass ሳይሆን በነጠላ ያስቃኛል። እያንዳንዳችን ልብ ላይ ያረፈዉን ጅራፍ ያስታዉሰናል።

የዙፋን ልፊያን ሳነብ ጦርነቶ እንዴት ሰባሪ እንደሆነ ተረድቻለሁ። መጽሐፉን እያነበብኩት ከ 2 ገፅ ማለፍ ያቅተኝ ነበር። ብዙ ጊዜ ሰዉነቴ ሲቆጣ ፥ ሲከፋኝ ፥ ግፋ ሲልም ጉሮሮዬ ላይ ማላቀዉ ነገር ሲመረኝ እና ሳለቅስ እራሴን አግኝቼዋለሁ።

ለእኔ ለአንዲት ድሃ ሴት ጦርነት የሚያመጣዉን ዉድመት ተስፋአብ ብዙ ቃላት ሳያባክን ገልፆልኛል። የጦርነትን ግፍ፣ የግብዝነትን ጥግ ማወቅ እና መጠንቀቅ ከፈለጋችሁ የዙፋን ልፊያን አንብቡት

አስተያየቷን ያጋራችን አርሴማ ረታ ናት

የዙፋን ልፊያን ያላነበባቾሁ አንብቡ ፥ ያነበባችሁ ሃሳባችሁን አካፍሉ

@Tfanos
2
2025/10/19 01:18:02
Back to Top
HTML Embed Code: