Telegram Web Link
የእግዚአብሔር_ፈቃድ_እንዴት_ይታወቃል.pdf
275.1 KB
1. የእግዚአብሔር ፈቃድ (ፈቃደ እግዚአብሔር) ምንድን ነው?

2. የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምናውቀው እንዴት ነው?

3. በፈቃደ እግዚአብሔር ውስጥ የእግዚአብሔርንና የእኛን ድርሻ እንዴት መለየት እንችላለን?

4. በሕይወታችን የሚገጥመንን ማንኛውንም ነገር፤ መልካምም ሆነ ክፉ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ማለት እንችላለን ወይ?

5. በፈቃደ እግዚአብሔር ዙሪያ ሊስተዋሉ የሚገባቸው አንዳንድ መሠረታዊ ነጥቦች

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
የክርስቶስ ማዳን እና የቅዱሳን ምልጃ

ሰው መድኅን ክርስቶስ ላይ ያለው መረዳት እምነቱን እና በዓለም ላይ ያለውን አኗኗር ይወስነዋል፡፡ የክርስቶስም ማዳን ዓለም ሳይፈጠር በልበ ሥላሴ የታሰበ እና የተመከረ የዘለዓለማዊ ፍቅር አምላካዊ ሥራ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረውም በእግዚአብሔር ምሳሌ በመሆኑ፤ በዚህ አምላካዊ የማዳን ሥራ ላይም በጸጋ በመሳተፍ አምላኩን እየመሰለ ይኖራል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን እንደሚወድ (እንደሚፈቅድ)፤ በእርሱ አምሳል የተፈጠረውም ሰው እንዲሁ ሌላው እንዲድን ይወዳል (ይጓጓል)፡፡ በቅድስና ከእግዚአብሔር ይሳተፋል፡፡ ያለ ፍቅር ቅድስና የለምና፡፡ በዚያውም ሰው መሆኑን አጽንቶ በጸጋ እግዚአብሔር ይጠብቃል፡፡ አሁን እያሰብን ያለነው ቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚናገሩለት ህያው ሰው (ማቴ 8፡ 22)፡፡ አሁን እያሰብን ያለነው ስለ እውነተኞቹ ሰዎች፤ ስለ ቅዱሳን ነው፡፡ ሰው መሆን እግዚእብሔርን መምሰል ነው ያልነው፤ በእርሱ የማዳን ሥራ ውስጥም በጸጋ መሳተፍን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የድኅነት ምክንያት መሆን፤ ፍቅርና ትሕትናን በዓለም ላይ ማስፋት፤ ክፋትን መታገል እና ሌሎችም ተሳትፎው ምን እንደሆነ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ እኒህ ሁሉ ሰው ብቻውን የሚያደርጋቸው አይደሉም፤ በእግዚአብሔር ጸጋ እና ረድኤት ያደርጋቸዋል እንጂ፡፡ ሰው መውደድን ይወዳል፤ መፍቀድን ይፈቅዳል፤ እግዚአብሔር ማዳኑን ያደርጋል፡፡

የቅዱሳን ምልጃ በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚደረግ የአባላት (የብልቶች) ትክክለኛ ሥራ ነው፡፡ የአካል ክፍሎች በትክክል ለተፈጠሩበት ዓላማ ሲሠሩ ማለታችን ነው፡፡ ብልቶች ሳይነጣጠሉ በሚሠሩት ሥራ አንዱ አካል በትክክል ይኖራል፡፡ እኒህን ጉዳዮች ማስተዋል የክርስቶስን ማዳን እና የቅዱሳንን ምልጃ ግንኙነት ለመረዳት ይጠቅማል፡፡ የክርስቶስ ማዳን እና የቅዱሳን ምልጃ ከሁለት አንዱን እንድንመርጥ የሚያስገድዱን፡ እንደ ሁለት ትይዩ መስመሮች (መንገዶች) አይደሉም፡፡ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎች ይህን "የትይዩ መስመር አስተሳሰብ ሞዴል" ጥቂት ለማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን ያጋቡ ይመስላል፡፡ በዚህ ምክንያት “ስለ ቅዱሳን ማስተማር ክርስቶስን ማደብዘዝ አይሆንም ወይ?”፤ “ሰው የሚድነው በክርስቶስ ቤዛነት ነው ወይስ በቅዱሳን ምልጃ?” … እና የመሳሰሉት ለሰዎች መልስ የሚሹ ዋና ጥያቄዎች ሆኑ፡፡ ነገር ግን “የአስተሳሰቡን መንገድ” ጥቂት እንመርምረው፡፡ የመድኅን ክርስቶስ ማዳን እና እርሱን የሚመስሉት ቅዱሳን ምልጃ “ወይስ” በሚል በትይዩ እና በአማራጭ የሚታሰብ ጉዳይ ነውን? ቅዱስ ወንጌል ከዚህ የተለየ እሳቤ አለው፡፡ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን ሲሰበስብ እያንዳንዱን “ተከተለኝ” እያለ ወደ መንግሥቱ ወንጌል ጠርቷቸዋል (ዮሐ 1፡ 44)(ዮሐ 21፡ 19)(ማር 2፡ 14)(ማር 10፡ 21)፡፡ ለጊዜው በእግር ተከተለኝ ማለቱ ሲሆን፤ ፍጻሜው ደግሞ በግብር (በሥራ) ምሰለኝ ማለቱ ነው፡፡ መንገዱ እርሱ ነው፤ መንገዱንም የሚመራ መርቶም ወደ አባቱም መንግሥት የሚያስገባም እርሱ ነው፡፡ እርሱን የተከተሉ ቅዱሳን ከእርሱ ኋላ ናቸው እንጂ ከእርሱ ትይዩ አይደሉም፡፡ እርሱ በአምላካዊ ሥልጣኑ የሚሠራውን እነርሱ በጸጋ እየሰሩ፤ እርሱን በሥራቸው እየመሰሉት ከኋለው እስከማታልፍ መንግሥቱ ይከተሉታል (ፍጻሜ የሌለው እስከ እንደሆነ ልብ ይሏል)፡፡ እርሱን እየተከተሉት የሚፈጽሙት ምልጃ በመንገዱ (በሃይማኖት) ውስጥ ላሉ ለንስሐ እና ቅድሳቱ ሁሉ መቀበያ ምክንያት ነው፡፡ ከክርስቶስ ማዳን ጋር የሚተባበር ነው፡፡ ጌታ ተከተሉኝ ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ካስከተለባት ከአንዲቱ መንገድ በበደል የወጣውን በምልጃ ምክንያት ወደ ራሱ ማዳን ይመልሰዋል፡፡ ለዚህም በቸርነቱ ብዛት ቃልኪዳንን ወደ እርሱ ለቀረቡት (ለቅዱሳን) ቃል ኪዳንን ይሰጣል፡፡ በበደል የራቀው በቅዱሳን ምልጃ ሲመለስ፤ ዐመጸኛው ዲያብሎስ ያፍራል፤ በቅዱሳን ዘንድ ደስታ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለፈቀደ (በቸርነቱ) ስላደረገ ይመሰገናል፤ በዚህም ሕይወት ይበዛል፤ ሞት ይሰደዳል (ይጠፋል)፡፡

ምኵራብ፡- የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት
 
“ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት፤ ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት፤ አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት፤ እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም
የሰንበት ጌታዋ ነው።” (ጾመ ድጓ)
 
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስተኛውን የዐቢይ ጾም ሳምንት “ምኵራብ” ይባላል። ቀጥተኛ ፍቺው “ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ፣ ሰቀላ መሰል አዳራሽ” ሲሆን፣ የአይሁድ መካነ ጸሎት ወይም ቤተ መቅደስ በመሆን ያገለግል ነበር። በብሉይ ኪዳን አይሁድ ቤተ መቅደስ ነበራቸው፡፡
 
ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተ መቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤(፪ኛነገ.፳፬-፳፭፣ኤር.፬፥፯:፣፴፱፥፩-፲፣፶፪፥፩-፴) ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ በዚያን ዘመን ቢያንስ ዐሥር አባ ወራዎች/የቤተ ሰብ ኃላፊዎች/ በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመሥራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ (Talmud Mishnah, Responsa literature, Jewish Encyclopedia, Academic Scholarly Works.)  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ግን ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ለሐዋርያት በብዛት የስብከት ዓውደ ምሕረቶች ሆነው አገልግለዋል።
 
ምኵራበ አይሁድ በውስጡ የብራና የሕግ እና የነቢያት መጻሐፍት ይገኛሉ፡፡ ምእመኑ እንዲሰማቸው ከፍ ባለ መድረክ ላይ በመሆን መምህራንና ካህናት ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም  ያስተምሩ ነበር። የምኵራብ ሹማምንት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሊቀጡ ሥልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር፣ በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትእዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡
 
በሰንበት ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስቦ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፣ ስብከትና ቡራኬ በመቀበል አምልኮታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምኵራብ ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ”ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን  ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሣ” እንዳለ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ፣ መማር፣ መመርመር፣መተርጎም፣ጉባኤ መሥራት አዘውትረው የሚፈጽሙት ተግባር እንደነበር ያስረዳል።(ሉቃ.፬፡፥፲፮)
 
ነገር ግን በምኵራብ ሰዎች ለተለያየ ዓላማ ይሰበሰቡ ነበር፡፡
 
፩. አማናዊ እረኛ ነው ብለው፦
ወልድ ዋሕድ ብለው ሲጠብቁት የነበረው ተስፋ “ደረሰልን፤ ወረደ፤ ተወለደ፤ የዓለም መድኃኒት እርሱ ነው” ብለው አዳኝነቱን አምነው ይከተሉታል። “ነዋ በግዑ ለእግዚብሔር ዘያአትት ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፤ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስተሰርይ የእግዚብሔር በግ መሆኑን አውቀው የሚከተሉት አሉ። ”በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል” እንዲል። (ዮሐ.፲፥፬)
 
፪. የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ሽተው፦ ከደዌ ለመፈወስ ይሰበሰባሉ፤ ልብሱን ዳሰው፣ ወድቀው ሰግደው፣ ጥላውን ተጋርደው፣ በእጁ ተዳሰው የሚፈወሱ ነበሩ። (ማር. ፭፥፳፪ እስከ ፍጻሜ)። ጌታችን በዕለተ ሰንበት ሕዝብ በተሰበሰበበት በምኵራብ እንደሚያስተምር ያስረዳናል፤ ”ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤…ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ፡፡”  (ማር.፮፥፩) “ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር።” (ማቴ.፲፫፥፶፬)
 
፫. ምግበ-ሥጋ ፈልገው ደም ግባቱን አይተው:- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከምኵራብ ጉባኤ ትምህርት በኋላ ጥቂቱን አበርክቶ እልፉን ይመግብ ስለነበር ጉባኤውን ይታደማሉ። ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን የምናመልከው ምግበ ሥጋ ስለሰጠን አይደለም። እርሱንማ ለሕዝብም ለአሕዛብም ሳይሰስት የሚመግብ መጋቤ ዓለማት ነው። ክርስቲያን በመብል አይገመትም። “እንግዲህ በመብልም ቢሆን÷ በመጠጥም ቢሆን÷ በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን÷ በመባቻም ቢሆን÷ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡” እንዲል፡፡ (ቆላ. ፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ)
 
፬. ለክስ የሚቀርቡ አሉ፦ ከቃሉ ግድፈት ከትምህርቱ ስሕተት የሚፈልጉ ሰቃለያን አይሁድ፣ ሊቃነ ካህናት አምላክነቱን የሚጠራጠሩ አይሁድ የሸንጎውን ጌታ ለሸንጎ ፍርድ ሊያቀርቡት ከግር በግር ይከተሉት ነበር። “ወጸቢሖ ተጋብኡ ሊቃነ ካህናት ወጸሐፍት ወሊቃናተ ሕዝብ ወወሰድዎ ውስተ ዐውዶሙ። ወይቤልዎ እመ አንተሁ ክርስቶስ ንግረነ ገሃደ ወይቤሎሙ እመኒ አይዳእኩክሙ ኢተአምኑኒ፡፡ በነጋም ጊዜ፥ የካህናት አለቆች፥ ጻፎችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ ሸንጎአቸው ወሰዱት፡፡ “አንተ ክርስቶስ እንደ ሆንህ በግልጥ ንገረን” አሉት፡፡እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ብነግራችሁም አታምኑኝም” እንዲል፡፡ (ሉቃ. ፳፪፥፷፮፣ ማቴ.፳፮፥፶፱)
 
ዛሬም በአማናዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥጋዊ ነገር ብቻ ገዝፎባቸው ቤተ መቅደሱን ለንግድ፣ ንዋያተ ቅድሳትን ለትርፍ ብቻ አሳልፈው የሚሸጡ፣ የሚለውጡ፣ ለክስ የሚፋጠኑ ከምኵራብ ያልወጡ የበጎችን እረኛ አሳልፈው የሚሰጡ አዋልደ ይሁዳ እንዳሉ ግልጽ ነው። “ወረከበ በምኵራብ እለ ይሠይጡ አልህምተ ወአባግዐ ወአርጋበ …፤ በመቅደስም በሬዎችን፣ ላሞችን፣ በጎችን፣ ርግቦችን፣ የሚሸጡትን አገኘ …፤ “ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል” እያለም የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ.፪፥፲፮፣ማቴ.፳፩፥፲፫)
 
በምኵራብ ይሸጡ፣ ይለውጡ የነበሩትን የገሠፀበት፣ ቤተ መቅደስን የከብት መንጃ የወርቅ መነገጃ ያደረጉ ሰዎችን ከእነ ሸቀጣቸው ከቤተ መቅደስ ያስወጣበት፣ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ የመሥዋዕቱ መክበሪያ፣ የጸሎት ሥፍራ ምስካበ ቅዱሳን መሆኗን ያስተማረበት ዕለት ነው። ቃሉ በዚያን ዘመን ተነግሮ ብቻ ያለፈ አይደለም፤ ለእኛ የተነገረን መሆኑን አውቀን የባለቤቱ ጅራፍ ሳይገርፈን ልንመለስ ይገባል። “የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፡፡” (ዮሐ.፪፥፲፬)
 
ከሚመጣው ጅራፍ ለመዳን እምነት ከተግባር ይዞ መገኘት ያስፈልጋል።” ወንድሞቻችን ሆይ÷ እምነት አለኝ፤ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር÷ ምን ይጠቅመዋል? በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን? ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ …እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።” እንዳለ። (ያዕ.፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ)
 
የዕለቱ መዝሙር (ከጾመ ድጓ)፦ ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት፤ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤
 
መልእክታት፦(ቆላ.፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ) (ያዕ.፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ)
ወንጌል፦ (ዮሐ.፪፥፲፪-እስከ ፍጻሜ)
(የሐዋ.፲፥፩-፰)
 
ምስባክ፦ “እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ፡፡ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ፡፡ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡” ትርጉም “የቤትህ ቅንዓት በልቶኛልና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በለዬ ወድቆአልና፡፡ ሰውነቴን በጾም አደከምኋት፡፡  (መዝ.፷፰፥፱)     
 
በምሕረቱ ይታደገን፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15
------------------------------------------
ቁጥር 578፡ በሊህ በስድስቱ ቀኖች ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡
ቁጥር 588፡ አንድ ሰው በባሕር ቢኖር ሰሙነ ሕማማትን ባያውቅ ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ይጹም፡፡ ይኸውም ሰሙነ ሕማማትን የሚጠብቅ አይደለም፡፡ ምሳሌውን ብቻ ነው እንጅ ስለእርሱ መጾም ይገባዋል፡፡
ቁጥር 590፡ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡
ቁጥር 596፡ ክብርት በምትሆን በአርባ ጾም በመጀመሪያው ሱባዔ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ይጹሙ፡፡ የመጀመሪያው ሱባዔ ካለፈ በኋላ እስከ 11 ሰዓት ድረስ ይጹሙ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ድረስ ይጹሙ፡፡ በእነዚህም ወራቶች አያጊጡ፡፡
ቁጥር 597፡ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተዉ፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ?
ቁጥር 600፡ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ፡፡
ቁጥር 601፡ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን
ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል፡፡
Forwarded from 🄱~𝕃Ⓘ🅾🄽
ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/

ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ «ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ ...»፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡ በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡
2024/05/15 10:49:58
Back to Top
HTML Embed Code: