Telegram Web Link
የ ZTE ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ!

የዜድ.ቲ.ኢ 5ጂ ብሌድ ኤ73 እና ዜድ.ቲ.ኢ ብሌድ ቪ40 ፕሮ ሲገዙ የአንድ አመት የ2 ጊ.ባ ወርሀዊ የዩትዩብ ጥቅልን ጨምሮ ለ3 ተከታታይ ወራት የዳታና ድምጽ ጥቅል በስጦታ ያገኛሉ!

በአቅራቢያዎ በሚገኙ የአገልግሎት ማዕከሎቻችን እንዲሁም የአዲስ አበባ ደንበኞቻችን በቴሌገበያ ድረገጽ ጭምር https://telegebeya.ethiotelecom.et/ ያገኟቸዋል!

የዜድ.ቲ.ኢ 5ጂ ብሌድ ኤ73 እና ዜድ.ቲ.ኢ ብሌድ ቪ40 ፕሮ ሲገዙ እስከ ግንቦት 23 ድረስ የኤርፖድ ስጦታ ያገኛሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ጥናት

" ሴቶችን በኢንተርኔት ላይ መሳደብ እና ማስፈራራት ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ የኢንተርኔት ላይ መግባቢያ መንገድ ሆኗል "

ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሬዚሊያንስ / #CIR / ጾታን መሰረት ያደረገ የኦንላይን ጥቃትና ትንኮሳ ተፅእኖዎች ላይ ያጠናውን ሰፊ ጥናት በቅርቡ ይፋ አድርጎ ነበር።

ጥናቱ ሁለት ክፍሎች ይዟል።

የመጀመሪያው የከዚህ ቀደም ጥናቶች ፤ በኢንተርኔት መድረኮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያላቸው / የነበራቸውንና ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ቃለ መጠይቅ የያዘ ነው።

ሁለተኛው በ3 (ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ X) የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ጥናት ያደረገ ነው።

በጥናቱ እንደተገለጸው ሴቶች ላይ የሚደርሱ የጥላቻ ንግግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተደረገው ጥናት ምን ተገኘ ?

ጥናቱ በ4 ቋንቋዎች (አማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ) የጥላቻ ንግግሮችን ከኢንተርኔት ላይ ለመለየት የሚያግዙ 2058 ጥቃት አዘል ቃላቶችን በመምረጥ ተደርጓል።

ቃላቶቹ በተከታታይ ውይይቶች እና ጥናቶች የተለዩ የ " ጥላቻ ንግግር " ን ይገልጻሉ የተባሉ ናቸው።

አጠቃላይ ከተሰበሰበው መረጃ 44.5 በመቶ የብሔር ጥላቻን ሲወክሉ ፤ 30.2 በመቶ ፆታን ኢላማ ያደረጉ ጥላቻ ንግግሮች ናቸው። ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ 17.5 ከመቶ ይይዛሉ።

ሴቶች (77.8 ከመቶ) ከወንዶች (22.2 ከመቶ) በላይ የጥላቻ ንግግር ይደረስባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ሴቶች (13.5 ከመቶ) ከወንዶች (9.2 ከመቶ) በለይ ‘#ዛቻ’ የያዙ ንግግሮችን ያስተናግዳሉ፡፡

#ስድቦች ’ ከአጠቃላይ ጥቃት 36.6 ከመቶ በመያዝ ዋና ድርሻ የሚይዙ ሲሆን ዛቻና ማስፈራሪያዎች ደግሞ 13.4 ከመቶ ይይዛል፡፡

በቃ ለመጠይቅ የተሳተፉ ሴቶች ምን አሉ?

" በኢንተርኔት ላይ ሴቶችን መሳደብ እና ማስፈራራት ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ የኢንተርኔት ላይ መግባቢያ መንገድ ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከ21 በመቶ በላይ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ፣ ጥቃት ፈጻሚዎች፣ ሃይማኖትን እንደሽፋን ተጠቅመው ጥቃት እንዳደረሱባቸው አንስተዋል።

በደረሰባቸው ጥቃት በማህበራዊ ትሥሥር ድረ-ገጾች ላይ እንዲሁም ከኢንተርኔት ውጪ ያሉ ማሀበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያቆሙ እና ዝምታን እንዲመርጡ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ጥናቱን በዚህ ያገኛሉ👇
https://www.info-res.org/tfgbvinethiopia

@tikvahethiopia
#ትግራይ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር ትናንት ሌሊት በራያ ዓዘቦ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ ወገኖች " በግፍ ተጨፍጭፈው መገደላቸውን " ገለጸ።

አስተዳደሩ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና ግድያ የተፈጸመበትን ልዩ ስፍራ በተመለከተ በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም ድርጊቱን " ዘግናኝ ወንጀል " ብሎታል።

" ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት ከዓፋር አከባቢ የመጡ ናቸው " ብሎ " ማንነታቸውን በሚመለከት ጥብቅ ክትትል እያደረግን ነው " ሲል አሳውቋል።

የአፋር ክልል መንግስትና የፌደራል ፖሊስም ወንጀለኞችን ተከታትለው በመያዝ ወንጀል ወደ ፈፀሙበት አከባቢ መጥተው ይዳኙ ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ " የራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ እና አስተዳደር ሁኔታውን ለማረጋጋት እና ለመቆጣጠር ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት  እጅግ የሚበረታታ ነው " ብሏል።

ወንጀለኞችን በመያዝ እና ለሕግ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ለህዝቡ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃለማርያም ሀገር ጥለው ከወጡ ዛሬ ድፍን 33 ዓመት ሆኗቸዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ/ም ነው ከሀገር የወጡት።

የድርግ ውድቀትን እና የ #ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ መቃረብን ተከትሎ ከሀገር እንደወጡ የሚነገርላቸው ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃለማርያም በአንድ ወቅት ፤ " እኔ ኮብልዬ አልወጣሁም " ሲሉ ነበር ቃላቸውን የሰጡት።

ኬንያ የሄዱትም ' #አሰብ ' በሻዕብያ በመያዙ ለመልሶ ማጥቃት የሚሆን ሌላ በር እንዲኖር ከኬንያ፣ ከጅቡቲ እና ሰሜን ሶማሊያ መንግስታት ጋር ለመነጋገርና ለመመለስ እንደነበረና ይህም ጥብቅ ሚስጥራዊ ጉዞ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ጥዋት 2:20 ወደ ኬንያ ጉዞ እንደጀመሩ እዚህ ስብሰባ መጀመሩና ኬንያ እንዳሉ ከቀን 7:00 ሰዓት ከስልጣን እንደወረዱ እንደሰሙ ገልጸው ነበር።

በራሳቸው አንደበትም ፥ ምንም አይነት #ገፊ ምክንያት በሌለበት በአሻጥር ከሀገር እንዲወጡ መገደዱን ነው በአንድ ወቅት ሲናገሩ የተደመጡት።

ዛሬ ላይ ሀገር ጥለው ከወጡ 33 ዓመት የደፈናቸው ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም በዚምባቡዬ ውስጥ ይኖራሉ።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳት ከዓመታት በፊት ፦
° በዘር ማጥፋት ፣
° በግድያ፣
° ከህግ ውጪ ሰዎችን በማሰር
° ንብረትን በመውረስ ጥፋተኛ ተብለው በሌሉበት #የሞት ፍርድ ተወስኖባቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃለማርያም ሀገር ጥለው ከወጡ ዛሬ ድፍን 33 ዓመት ሆኗቸዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ/ም ነው ከሀገር የወጡት። የድርግ ውድቀትን እና የ #ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ መቃረብን ተከትሎ ከሀገር እንደወጡ የሚነገርላቸው ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃለማርያም በአንድ ወቅት ፤ " እኔ ኮብልዬ አልወጣሁም " ሲሉ ነበር ቃላቸውን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ #ታሪክ

የቀድሞው ፕሬዜዳንት ሀገር ጥለው ከወጡ በኃላ ለ7 ቀናት ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ናቸው።

የ7 ቀኑ መንግሥት በወቅቱ ' የተስፋዬዎች መንግስት ' የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር። ይህ ስያሜ የተሰጠው ፦

- ተስፋዬ ገ/ ኪዳን ➡️ ተጠባባቂ ፕሬዜዳንት
- ተስፋዬ ዲንቃ ➡️ ጠቅላይ ሚኒስትር
- ተስፋዬ ወልደስላሴ ➡️ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር
- ተስፋዬ ታደሰ ➡️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው ነው።

ሌ/ጄነራል ተስፋዬ በተለይም ፦

" #የኢትዮጵያ_ህዝብ_ሰላም_ጠምቶታል። የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሰላም መታጣት በመሆኑ ቀዳሚው ጉጉቱና ናፍቆቱ ሰላም ነው።

በሰሜንም ሆነ በደቡብ፣ በምስራቅም ሆነ በምዕራብ በመሃልም ሆነ በደንበር ኢትዮጵያዊ እናት፣ ኢትዮጵያዊ አባት፣ የወደፊት ባለተስፋ የሆነው ወጣት ሁሉ ከምን ጊዜ በላይ ምኞቱ ሰላም ነው። " በሚለው ንግግራቸው ይታወሳሉ።

ከ7 ቀናት የ ' ተስፋዬዎች መንግሥት ' በኃላ ኢህአዴግ ሀገሪቷን ተቆጣጠረ ፤ 17 ዓመታትን በስልጣን ላይ የቆየው ደርግም እስከወዲያኛው ላይመለስ አከተመ።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉንም የግንባታ ባለሙያዎች እየጠራን ነው።

በቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2016 ለይ የሚሳተፉ ከ150 በላይ የግንባታው ዘርፍ ብራንዶችን ይተዋወቁ።

ዩናይትድ አረብ ኢምሬት፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ኢትዮጵያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ህንድ፣ ቱርክና ኦስትሪያን ጨምሮ ከተለያዩ 20 ሃገራት ተወክለው ከሚመጡ ተሳታፊዎች(አቅራቢዎች) ጋር ይገናኙ።

የአቅራቢ ድርጅቶችን ዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/44BfWyw

ይህ በዘርፉ መልካም ስም ካተረፉ ድርጅቶች ጋር የመገናኘት አስደሳች አጋጣሚ አያምልጥዎ!

በነጻ ለመግባት እዚህ ይመዝገቡ https://bit.ly/3UsrL5I

በቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G በአስገራሚ ቴክኖሎጂዎች እና በአገልግሎቱ ልቆ የቀረበ የዘመኑ ምርጥ ስልክ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
#ኢትዮጵያ #አካልጉዳተኞች

“ አጠቃላይ የሆነ የአካል ጉዳተኞች የህግ ማዕቀፍ እንፈልጋለን ” - የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር  “ ስለረቂቅ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ አያያዝ በኢትዮጵያ የመወያያ መነሻ ሀሳብ ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከፍትህ ሚኒስቴር የሕግ ማርቀቅ ባለሙያዎቸ ጋር ከሰሞኑን የምክክር አውደ ጥናት አድርጓል።

የምክክር አውደ ጥናቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ20 ሚሊዮን በላይ አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ያልሆኑባተቸውን፦
- የኢኮኖሚ፣
- የትምህርት፣ 
- የቅጥር፣ 
- የማኅበራዊ ተሳትፎዎችና የመብት ጥሰቶች ችግሮችን እንዲቀረፍ “ ሁለንተናዊ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ” ለማውጣት ማኀበሩ ከአጋር አካላት ጋር በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ማድረግ ነበር።

በመርሀ ግብሩ የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ያሉት አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ ህጎችስ በትክክል እየተፈጸሙ ነው ወይ ? ይህ ረቂቅ አዋጅስ በዘርፉ  ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ምን ጉልህ ሚና አለው ? ሲል ማኀበሩን ጠይቋል።

የማኀበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ጥላሁን በሰጡት ቃል፣ “ አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ የተወሰኑ (ጥቅል/ግልፅ ያልሆኑ) ህጎች አሉ። በአጠቃላይ አካል ጉዳተኞችን በማስመልከት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ህጎች በርካታ ችግሮች አሉባቸው ” ብለዋል።

የተወሰኑ ህጎች ቢኖሩም፦
- ጥቅል/ግልጽ ያልሆኑ፣
- አስፈጻሚ አካል የሌላቸው፣
- ተጠያቂነትን የማያሰፍኑ፣ 
- ዝርዝር መመሪያ የሌላቸው በመሆናቸው የነበሩት ህጎች አስቻይ ሁኔታ እንዳይፈጥሩ አድርጓቸዋል ” ነው ያሉት።

“ ወቅቱን የዋጀ የወቅቱን የአካል ጉዳተኞች ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እንቅስቃሴን መሠረት ያደረገ አዋጅ የለም ” ያሉት አቶ ሙሴ፣ በሂደት ላይ ያለው “ ሁለንተናዊ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ” ሲወጣ ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚይችል አስረድተዋል።

ረቂቅ አዋጁ፦
- የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ግልጽ የሆነ በጀት እንዲኖር፣
- የአካል ጉዳተኛ ቤተሰቦች የሚደርስባቸውን መገለልና አድሎ ችግር የሚቀርፍ፣ 
- አካል ጉዳተኞች በህንፃ፣ ትምህርት፣ በትራንስፖርት ተደራሽነታቸው እንዲረጋገጥ የሚያደርግ፣ 
- ከውጩ ሀገራት የሚገቡ አካል ጉዳተኞች የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ጭምር የሚደነግግ መሆኑን ተናግረዋል።

#TiavahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ነው አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት ፣ ትዕግስት ማጣት የሚመጣ ነው " - ኢዜማ በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያለውን ግምገማ በተመለከተ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። …
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" አሁን ላይ ያሉ ችግሮች ምፍትሄ እስካላገኙ  ስለ ምርጫ ማሰብ #ቀልድ ነው " - አቶ ግርማ በቀለ

የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሕብር) ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድረገዋል።

Q. የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ጥሰትን በተመለከተ ስለሚነሱ ጉዳዮች የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይላል ?
 

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በእጅጉ ተጥሰዋል።

መንግሥት የፓለቲካ ምህዳሩን ያስፋልን ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይደረግ፣ በአገሪቱ ስለተፈጠሩት ችግሮች በጠረንጴዛ ዙሪያ እንወያይ እያልን ስንጮህ ነበር።

አሁን ከዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አልፎ ፦
° የፓርቲ መሪዎችን ከቤት አውጥቶ ገድሎ የመጣል፣
° የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ሕገ መንግስቱ የሰጣቸውን መብቶች ተገፈው ምን እንዳጠፉ ሳይነገር የሚታሰሩበት ከባድ ደረጃ ላይ የደረስንበት ጊዜ ነው። "

Q. ስለ ሀገሪቱ የጸጥታና ደኀንነት ሁኔታ የፓርቲያችሁ ግምገማ ምንድን ነው ? 

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" ለ6 ዓመታት በብልጽግና፣ ከኢህዴግም በከፋ ሁኔታ አገራችን ያልተረጋጋችበትና በሰላም ረገድ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የወደቅንበት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።

የአገራዊ እሴቶችንና ገንቢ አስተሳሰቦችን ወደ ኋላ ጥሎ ከውጪ የሚመጣውን የወቅቱ ፓለቲካ አስተሳሰብ ይዞ፣ በዛም ተሞክሮ ላይ አግላይና ጠቅላይ የሆነ የፓለቲካ ስርዓት ነው። 

ይህ በመሆኑም አገራችን ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማኀበራዊ ምስቅልቅሎችና ከፍተኛ ችግሮች ዳርጓታል።

የተፈጠረውን ምስቅልቅል ለማስወገድ ፦
- በአገሪቱ ውስጥ አገራዊ መግባባት መፍጠር፣ 
- በሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መናቆርና ልዩነት የማራገብ ሂደት ማርገብ፣
- ብሔራዊ እርቅ የሚወርድበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለብን፤
- ሁሉም ባለድርሻ አካላት ባለቤት ሆነው የመፍትሄው አካል መሆን አለባቸው። "

Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን ፈትኖታል። ፓርቲዎ ለመንግስት ያለው መልዕክት ምንድን ነው ?

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" በፓለቲካ መሪነት ሳይሆን እንደ አንድ የኢትዮጵያ ዜጋ እየኖርን ያለነው በአንዳች ተዓምር እንጂ የእውነት የወር አስቤዛ ለአንድ ቀን እንኳ የማይሆንበት ደረጃ ላይ የደረስንበት ሁኔታ ነው ያለው። 

የዛሬ 20 ዓመት በአንድ ብር አንድ ሊትር ወተት ገዝቼ ነው ልጅ ያሳደኩት። አሁን ዋጋውን ሁላችንም እናውቀዋለን። ሕዝቡ ግን ይሄ ሁሉ እየሆነ በፈጣሪ እርዳታ አለ። "

Q. በቀጣዩ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመመቅረብ ምን ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" ➡️ የብሔራዊ መግባባትና የሀገራዊ እርቅ ጉዳይ ላይ ቁጭ ብለን እስካልተነጋገርን ድረስ፣

➡️ አገሪቱ ውስጥ ላሉት ፓለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ምስቅልቅሎች መፍትሄ እስካላበጀን ድረስ፤ 

➡️ ዋና ዋና የባለድርሻ አካላት ለዚች አገር ችግር መፍትሄ እስካልነደፉ ድረስ፣ እዚህ አገር ስለምርጫ ማሰብ ቀልድ ነው። "

Q. መልካም አስተዳደርን ስለመረዘው ብልሹ አሰራር ፓርቲዎ ምን ይላል ? 

አቶ ግርማ በቀለ ፦

" የዚህ አይነት ብልሹ አሰራር በአገራችን በታሪክ ውስጥ የገጠመን ጊዜ የለም በአጭሩ። አመሰግናለሁ ! "

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#HiberEthiopia #ሕብር

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Palestine

ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ።

" የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል።

የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " #በሚቀጥሉት_ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል።

የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል።

የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል።

የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል።

" ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል።

" ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል።

የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል።

ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል።

መረጃው የስካይ ኒውስ ነው።

More - @thiqahEth
ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ላይ የዕሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማረፊያው አጥር ውጭ ባሉ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደነበረ ገልጿል።

አሁን ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉንም አመልክቷል።

" በኢትዮጵያ አየር መንገዱ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል አልነበረም " ሲልም አክሏል።

@tikvahethiopia
#ዓዲግራት

በንዋየ ቅዱሳን ሰርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቦቹ የመቐለ ነዋሪ ናቸው።

5 የወርቅ መስቀሎችን ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ወስደው ሊሸጡ ሲደራደሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓዲግራት ፓሊስ ፅ/ቤት አስታውቀዋል።

የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ የማነ ኪዳኑ  ፥ " ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ/ም የግል ተበዳይ ከመቐለ ወደ ሽረ ከተማ የወርቅ መስቀሉን ጭኖ በመውሰድ ላይ ሳለ ነው ተጠርጣሪዎቹ ሰርቆቱን ፈጽመው የተሰወሩት " ብለዋል። 

ግለሰቡም በመቐለ ከተማ ለቀዳማይ ወያነ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ያመለከተውን መረጃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው ክትትል ተጠርጣሪዎች በዓዲግራት ከተማ ውስጥ ሊያዙ እንደቻሉ ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎች የሰረቁትን አንዱ ብር 25 ሺህ የሚያወጣ መስቀል ፤ በ15 ሺህ ሊሸጡት ተሰማምተው በዋጋው ማነሰ የተጠራጠረ ገዢ በኩል መረጃው ወደ ፓሊስ በመድረሱ ግለሰቦች ከነእግዚብታቸው በፓሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ 4 ሲሆኑ ነዋሪነታቸውም መቐለ ነው።

የዓዲግራት ፖሊስ ፤ እንዲገዛ ግብዣ የቀረበለት ግለሰብ ጊዚያዊ ጥቅም እና ትርፍ ሳያሸንፈው ለፓሊስ ያደረገው ትብብር ሌላው እጅግ አርአያ የሚሆነው ሲል አወድሷል።

መረጃው ይህ ሆኖ ሳለ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዓዲግራት ወጣቶች የሆኑ ከቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ ንዋየ ቅዱሳን ዘረፉ "  እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#AmanuelMentalHospital

ወደ አማኑኤል ሆስፒታል የሚገቡ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ አዳዲስ ታካሚዎች እየጨመሩ መጥተዋል ብሏል።

አማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምን አለ ?

- ከሚመጡ ታካሚዎች ከሴቶች በበለጠ ወንዶች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ።

- ከሆስፒታሉ ደህና ሆነው ወጥተው ከወጡም በኋላ ያለው ሁኔታ የተስተካከለ ስለማይሆንላቸው ተመልሶ የማገርሸት እና ተመልሶ የመምጣት ነገር እየጨመረ ይገኛል።

- አንድ ክፍተት እየፈጠረ ያለው የተጠኑ ጥናቶች ባለመኖራቸው መንግስትም ትኩረት እየሰጠው ባለመሆኑ ነው።

- ወደ ሆስፒታል የሚመጡ አብዛኞቹ ታካሚዎች ፦
° #ድባቴ
° #ባይፖላር
° #ከባድ_የአእምሮ_ህመም
° #በአደንዛዥ_እፅ_ሱስ ሳቢያ የሚመጣ የአዕምሮ ህመም የተጠቁ ናቸው።

- በሆስፒታሉ ከሚታከሙ ታካሚዎቸ ውስጥ በብዛት ከ20-40 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቁጥራቸው ከፍ ይላል።

- የሆስፒታሉ ግንባታ በጣም የቆየና ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ በተደጋጋሚ የአልጋ እጥረቶች እየገጠሙ ነው።

- ለሚፈጠሩት ክፍተቶች እንደማስተንፈሻ እንዲሆን በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በሆስፒታሉ ግቢ ሌላ ህንፃ ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ ተጥሏል። በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ያልቃል ተብሎ እቅድ ተይዟል።

- የአእምሮ ህመም ታክሞ መዳን የሚችል በመሆኑ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#Tecno #Camon30Pro5G

ፍጥነት እና ቅልጥፍና መገለጫው የሆነውን MediaTek Dimensity 8200 ፕሮሰሰር አካቶ Tecno Camon 30 pro 5G ቀርቦሎታል

#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
#ወጋገን_ባንክ

ወጋገን ባንክ ባዘጋጀው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ጠቀም ባሉ አጓጊ ሽልማቶች አሸናፊዎችን ማንበሻበሹን አሁንም ቀጥሏል !!

ታዲያ እርስዎስ ምን ይጠብቃሉ
?

አሁኑኑ ከስር የተቀመጡትን የወጋገን ባንክ ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፅ ሊንኮች ተጭነው በመቀላቀል እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ ፣ ጥያቄዎችን አስቀድመው እየመለሱ አጓጊ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ !

በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ

|
Facebook | Telegram

ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው

https://www.tg-me.com/WegagenBanksc
2024/06/16 08:51:16
Back to Top
HTML Embed Code: