Telegram Web Link
ፎቶ ፦ በአማራ ክልል ፣ ባህር ዳር ከ60 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ድልድይ የተካው በታላቁ የዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው " የዓባይ ድልድል " ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

የግንባታው ውል በ2011 ነበር የተፈረመው።

ስራውን #የቻይናው ኮምኑኪዬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ በኃላፊነት የወሰደ ሲሆን ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የቱርክ ድርጅት እና ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ስራዎች የተባለ ሀገር በቀል ተቋም በጋራ ሆነው የማማከር ስራ ሰርተዋል።

ድልድዩ የ380 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡

የጎን ስፋቱ 43 ሜትር ሲሆን በግራ እና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽርካሪዎች ማስተናገድ ይችላል።

5 ሜትር የእግረኛ መሄጃ የተሰራለት ሲሆን በሁለቱም አቅጣጫ ለብስክሌት ተጠቃሚዎች የሚሆን መስመርን አካቷል።

ግንባታው በአጠቃላይ 1,437,000,000 ብር ወጪ እንደወጣበትና ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት እንደተሸፈነ ተገልጿል።

#AmharaCommunication
@tikvahethiopia
" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ከሌቦች የሚረከብ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ማሞ ድልድይ አካባቢ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከማለዳ 12 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ግለሰብ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ባደረገው ክትትል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከሌቦቹ ላይ የሚረከብ " ታምራት ፍቅረማርያም " የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በእለቱ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክና በልዩ ልዩ ጊዚያት ከሌቦች የተረከባቸውን ፦
➡️ 61  ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣
➡️ 251 የታብሌት ስልክ ሽፋኖችን ፣
➡️ 2 ላፕቶፖችን እና በጥሬ 60 ሺ አንድ መቶ ብር ከሌባ ተቀባዩ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ መያዙን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከሌቦች ተቀብሎ የሚያስቀምጠው በተከራየው ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።

ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራይን ማንነነት እና በምን ስራ ላይ እንደተሰማራ የማረጋገጥ ግዴታ እንደለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

" የሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል / ተሰርቂያለሁ " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ስልኩን በመለየትና አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

በአሜሪካ በተካሔደ ዓለም አቀፍ የሮቦፌስት ውድድር ታዳጊ ኢትዮጵያውያን የሮቦቲክስ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆኑልን።

በውድድሩ 23 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን በተለያዮ ዘርፎች የተሳተፉ ሲሆን ከ10 ዓመት በታች በሮቦፓሬድ ምድብ የተወዳደረው ታዳጊ ማሸነፉ ተሠምቷል።

ሌላኛው ታዳጊ ተወዳዳሪ ከ14-16 ዓመት ምድብ ተሳትፎ ስፔሻል አዋርድ ሽልማትን ማግኘት ችሏል።

በየውድድሩ ከ1-3 ድረስ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Via @tikvahuniversity
#GondarUniversity

ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ #በተለያየ_ጊዜ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ #አንጋፋ የሚባሉ ምሁራን ፤ መምህራንን ፣ ሰራተኞችን ፣ ተመራቂ ተማሪ እና የዩኒቨርሲቲው ታላቅ #ባለውለታ የሆኑ አባትን በሞት ተነጥቋል።

አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እነማንን #በሞት ተነጠቀ ?

🕯አባሆይ አሰፋ ዘለቀ🕯

የመሬት ርስታቸውን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ካበረከቱት 59 አርሷደሮች መካከል አንዱ ነበሩ። በ1963 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ቁጥር መጨመር እና የሚሰጠውም የትምህርት ዓይነት እየሰፋ በመምጣቱ ግቢውን ወደ ማራኪ አካባቢ ማስፋፋት ሲፈልግ አባሆይ አሰፋ ዘለቀ ከሌሎች ልበቀናዎች ጋር በመሆን በማራኪ ከፍተኛ ቦታ አካባቢ የነበራቸውን የመሬት ይዞታ ለማስፋፊያ እንዲሆን በመፍቀድ ትውልድ እንዲቀረጽበት በማድረግ ዘመን ማይሸረው አበርክቶ አድርገዋል፡፡ በ94 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

🕯ፕሮፌሰር ሞገስ ጥሩነህ🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ መምህር ፣ ተመራማሪ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልጋይ ነበሩ።

🕯ዶ/ር ሰለሞን ይርዳው🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ ባልደረባ ነበሩ። ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ በህክምናው ሙያ በመተማ ሆስፒታል አገልግለዋል። ከ1992/93 ዓ.ም ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሙያቸው አገልግለዋል። በማስተማርም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በጤና እክል ህይወታቸው አልፏል።

🕯መምህር ደመቀ ደሱ 🕯

አንጋፋ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህር ነበሩ። በጡረታ እስከተገለሉበት ድረስ ለ40 ዓመታት ገደማ  በማስተማር ሙያ እንዲሁም በትምህርት ክፍል እና በዲን ኃላፊነት አገልግለዋል።

🕯አቶ ፍስሃ ሞሴ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም Nutrition & Dietetics Department ውስጥ የChief laboratory Technical Assistant ባለሙያ ነበሩ። ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄዱበት በደንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ተቀጥፏል።

🕯አቶ አታለል ምስጋናዉ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚዮሎጂ ት/ክፍል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ መምህርና በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ነበሩ። በ31 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

🕯ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ🕯

የኪነህንፃ / #Architecture / ተመራቂ ተማሪ ነበር። የትንሳዔ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር ባሄደበት ከፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል ነበር።

🕯አቶ ሙሉአለም ይትባረክ🕯

በህክምናና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተማሪዎች አገልግሎት ውስጥ የተማሪዎች ምኝታ ቤት አስተባባሪ ነበሩ። በህመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አጠቃላይ 8 አንጋፋ ምሁራን ፣ መምህራን ፣ ሰራተኞች ፣ ተማሪ እንዲሁም የተቋሙን ባለውለታ ታላቅ አባት በሞት ተነጥቋል።

የጤና እክል ፣ ድንገተኛ አደጋ ፣ የመኪና አደጋ የህልፈተ ህይወት መንስኤዎቹ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው ካገኘው መረጃ ተረድቷል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
2024/05/13 10:09:13
Back to Top
HTML Embed Code: