Telegram Web Link
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ስልጠናውን ልዩ የሚያደርገው ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
TIKVAH-ETHIOPIA
#BahirDarUniversity ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ ሊያደርግ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በፀጥታ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በ2016 ዓ/ም አዲስ ለተመደቡለት የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ጥሪ ሳያደርግ ቆይቷል። ረቡዕ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት ያደረገው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑን ቲክቫህ…
#BahirDarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሬሜዲየል ተማሪዎች ጥሪ አደረገ።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ለመከታተል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23 ቀን 2016 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በ " ፖሊ ካምፓስ " ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ በ " ግሽ ዓባይ ካምፓስ " ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

Via @tikvahuniversity
Embargoed_Copy_CARD_Voice_of_Guji_Eng_Oro_Amh_HR_Situation_Report.pdf
6.3 MB
#የጉጂ_ሰቆቃ : በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል (ካርድ) ያዘጋጀው ሪፖርት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Embargoed_Copy_CARD_Voice_of_Guji_Eng_Oro_Amh_HR_Situation_Report.pdf
ካርድ "የጉጂ ሰቆቃ / Voice For Guji" በሚል ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ አደረገ።

የመብቶች እና ዲሞክራሲ እድገት ማዕከል / ካርድ በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አስመልክቶ " የጉጂ ሰቆቃ / Voice For Guji " በሚል ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

➡️ በእነዚህ አከባቢዎች እየደረሰ ያለው የህዝብ ሰቆቃ በመገናኛ ብዙኃን ችላ ተብሏል።

➡️ ጉዳት የደረሰበት ሕዝብ ድምጹ እንዳይሰማ ሆኗል።

➡️ በተለይ በ2015 መጀመሪያ ላይ የምስራቅ ቦረና ዞን መመስረትን ተከትሎ የተፈጠሩ የፖለቲካ ችግሮች ውጥረቱን አባብሰወል።

ሪፖርቱ 36 ማሳያ ታሪኮችን አካቷል።

ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም ወገኖች (የመንግሥት እና የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች) ተሳታፊ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

ሪፖርቱ በማሳያ ታሪኮቹ ፦

° ከሕግ ውጪ ንፁኃን ላይ የተፈፀሙ ግድያዎች፣
° የዘፈቀደና የጅምላ እስሮች፣
° ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣
° የንብረት ውድመት፣
° አስገድዶ የመሰወር እና የገንዘብ ማግኛ እገታ ድርጊቶች፣
° የማሰቃየት እና ኢሰብዓዊ አያያዝ የመፈፀም፣
° የማፈናቀል ድርጊት የተፈፀመባቸው ንፁኃን ዜጎችን ታሪኮች ይዟል።

በሪፖርቱ ከተካተቱ ማሳያ ታሪኮች መካከል ...

አንድ ባለታሪክ " መንግሥት የአሮሞ ነጻነት ግንባርን ወደ ኢትዮጵያ ሲጠራ  የኛ ልጆች ብለን ተቀብለናቸዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት 'ሸኔ' እያለ መጥራት ከጀመረ በኋላ ሁኔታው ተባባሰ። በሌሊት የሸኔ ተዋጊዎች ያስተዳድሩናል፣ ቀን ላይ ደግሞ የመንግሥት ኃይሎች ያስተዳድራሉ " ብለዋል።

ሌላዋ ባለታሪክ ፥ " በጉጂ የሚገኙ ማዕድናትም የግጭቱ መንስኤ ናቸው። ከጉጂ ጎሮ ዶላ ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመንግሥት ታጣቂዎች ሽኔ የሚል ስያሜ ስለተሰጣቸው ዕርዳታ ለማግኘት ተቸግረዋል " ስትል ገልጻለች።

ሌላኛው ባላታሪክ " ሁለቱም ወገኖች በጠላትነት የሚፈረጁትን ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይይዛሉ፣ ይህም የአመፅና የመፈናቀል አዙሪቱን እንዲቀጥል አድርጓል" ቃሉን ሰጥቷል።

በሪፖርቱ በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት በስፋት የተዳሰሰ ሲሆን ከ #8_ዓመት ሕጻን አንስቶ ባለትዳር እና የልጆች እናት የሆኑ ሴቶች ከአንድ በላይ በሆኑ ታጣቂዎች ተገደው መደፈራቸውን ማሳያ ታሪኮቹ ያሳያሉ።

ሪፖርቱ ወንድ ወታደሮች በጾታ ላይ የተመሰረተ ወንጀሎች ላይ የሚሳተፉት አከባቢን የመቅጣት ፤ የማዋረድ እና የመቆጣጠር ፍላጎቶች ምክንያትነት መሆናቸውን በምክንያትነት ያስቀመጠ ሲሆን በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም አካላት በኩል የሚፈጸም መሆኑን አንስቷል።

በተጨማሪም፥ በሁለቱም አካላት ሰዎችን በመያዝ ለመልቀቅ ገንዘብ የመጠየቅ ተግባራት ፤ ኢሰብአዊ ድብደባና ዝርፊያ መስተዋላቸውን ተገልጿል።

በግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በአግባቡ አለመታወቁ እና ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በመኖራቸው ነዋሪው መቸገሩ በሪፖርቱ ተነስቷል።

የቀረበው ምክረ-ሐሳብ ምንድነው ?

ገለልተኛ፣ ነጻ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግ፤ ሁለቱም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የጀመሩትን ድርድር እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

ሙሉ ሪፖርት ፦ www.tg-me.com/tikvahethiopia/88262

@tikvahethiopia
የፐርፐዝ ብላክ አካውንቶች ታገዱ።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንቶች በመንግስት ታግደዋል።

ድርጅቱ አካውንት ሲታገድብኝ ይህ በዓመት ለ3ኛ ጊዜ ነው ብሏል።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጰያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ፍስሐ እሸቱ ፥ የድርጅቱ አካውንቶች ለምን እንደታገዱ ምክንያቱን እንደማያውቁት ገልጸዋል።

በአመት ውስጥ ምክንያቱ  ሳይታወቅ ለሶስት ጊዜ አካውንታቸው መታገዱን አመልክተዋል።

ስለ ጉዳዩ " ደብዳቤ እንኳን አልደረሰንም " ብለዋል።

መታደጉን የሰሙትም ከባንኮች እንደሆነ ከነሱ አገኘን ባሉት ደብደቤ ከ ' ፍትህ ሚኒስቴር ' በተጻፈ ደብዳቤ መታገዱን እንደሚልጽ አስረድተዋል።

ከድርጅቱ አካውንቶች በተጨማሪም #የራሳቸው የስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ የባንክ አካውንትም ታግዷል።

ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ ፥ " አሁን ላይ ለሰራቸኞቻችን ደሞዝ መክፈል ፤ አስፈላጊ ወጪ መሸፈን የማንችልበት ሁኔታ ላይ ነን " ብለዋል።

በአካውንቶች መታገድ ምክንያት የቤት ኪራይ ክፍያ እና የፕሮጀክት ስራዎች መቆማቸውንም አሳውቀዋል።

አሁን በተፈጠረው ችግር የድርጅቱ የቀጣይነት አደጋ ከተጋረጠ ፐርፐዝ ብላክ ተጠያቂ እንደማይሆን " ለባለአክሲዮኖቹ መግለጽ እንፈልጋለን " ብለዋል።

እግዱ ህጋዊ መንገድ ያልተከተለ በመሆኑ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

የ1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ይከበራል።

የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የሶላት ስነስርዓቱ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ነው።

ይህ ተከትሎ ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የሶላት ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት ፦

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

- ከብሔራዊ ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን መገንጠያ ላይ

- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
2024/06/16 03:51:09
Back to Top
HTML Embed Code: