ብቻውን ያለ ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

39፥45 አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፡፡ وَإِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَحْدَهُ اشْمَأَزَّتْ قُلُوبُ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ

"ሞኖስ" μόνος በባለቤት የሚገባ ቅጽል ነው፣ "ሞኖ" μόνῳ በርቱዕ ተሳቢ የሚገባ ቅጽል ነው፣ "ሞኖን" μόνον ደግሞ በኢርቱዕ ተሳቢ የሚገባ ቅጽል ሲሆን "ብቻ" ማለት ነው፥ ይህ ገላጭ ቅጽል ለአብ ብዙ ቦታ ገብቷል፦
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ἵνα γινώσκωσιν σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.
ሮሜ 16፥27 "ብቻውን" ጥበብ ላለው "ለ-"አምላክ" "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። μόνῳ σοφῷ Θεῷ, διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ᾧ ἡ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.

ኢየሱስ የላከው ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው እስከ ዘላለም ድረስ ክብር በኢየሱስ በኩል የሚቀርብለት ከሆነ የተላከውን ኢየሱስ እና ብቻውን ጥበብ ያለው አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት ይለያያሉ፥ ብቻውን ለሆነ አምላክ ክብር፣ ግርማ፣ ኃይል እና ሥልጣን በኢየሱስ አማካኝነት ይቀርብለታል፦
ይሁዳ 1፥25 "ብቻውን "ለ-ሆነ አምላክ እና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። μόνῳ Θεῷ Σωτῆρι ἡμῶν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν δόξα μεγαλωσύνη κράτος καὶ ἐξουσία πρὸ παντὸς τοῦ αἰῶνος καὶ νῦν καὶ εἰς πάντας τοὺς αἰῶνας· ἀμήν.

ይህ ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው፣ ብቻውን ጥበብ ያለው የማይሞት እና አንድ ሰው እንኳ ያላየው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 "ብቻውን" አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው፣ ለማይታየው፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። Τῷ δὲ Βασιλεῖ τῶν αἰώνων, ἀφθάρτῳ ἀοράτῳ μόνῳ Θεῷ, τιμὴ καὶ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። ὁ μόνος ἔχων ἀθανασίαν, φῶς οἰκῶν ἀπρόσιτον, ὃν εἶδεν οὐδεὶς ἀνθρώπων οὐδὲ ἰδεῖν δύναται· ᾧ τιμὴ καὶ κράτος αἰώνιον· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና "ብቻውን የሆነ ገዥ" የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ያሳያል። ἣν καιροῖς ἰδίοις δείξει ὁ μακάριος καὶ μόνος Δυνάστης, ὁ Βασιλεὺς τῶν βασιλευόντων καὶ Κύριος τῶν κυριευόντων,

1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ላይ "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም 1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ላይ "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለውን ማንነት ተክቶ የመጣ ነው፥ ስለዚህ "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም" የተባለው አብ ሲሆን ይህም "ብቻውን የሆነ ገዥ" ነው። "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለው አብ ይሁዳ ላይ "ብቻውን ያለውን ጌታ" ተብሏል፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον Δεσπότην καὶ Κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴስ" δεσπότης ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ያህዌህ" יְהוָ֣ה የሚለው ቴትራግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፦
ኢሳይያስ 1፥24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ያህዌህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ לָכֵ֗ן נְאֻ֤ם הָֽאָדֹון֙ יְהוָ֣ה צְבָאֹ֔ות אֲבִ֖יר יִשְׂרָאֵ֑ל
ኢሳይያስ 1፥24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ ጌታ እንዲህ ይላል፦ διὰ τοῦτο τάδε λέγει Κύριος ὁ δεσπότης σαβαώθ, ὁ δυνάστης τοῦ ᾿Ισραήλ·
ልብ ብላችሁ ከሆነ "አዶን" אָדוֹן֙ ለሚለው በግሪኩ ያስቀመጡት "ኩርዮስ" Κύριος ሲሆን "ያህዌህ" יְהוָ֣ה ለሚለው ደግሞ "ዴስፖቴስ" δεσπότης ነው፥ ለዚያ ነው "ብቻውን ያለውን ጌታ" የተባለው ኢየሱስ ስላልሆነ ኮዴክስ ቤዛይ ላይ፦ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ" በማለት አብ ለማመልከት የተቀመጠው፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον δεσπότην θεὸν καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ቴዎን" θεὸν የሚለውን ቃል አትለፉት! ለዚያ ነው በ 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ "and denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ" ብለው ያስቀመጡት። "ዴስፖቴን ቴዎን" δεσπότην θεὸν እና "ኩርዮን ቶን ቴዎን" ማለት "ጌታ አምላክ" ማለት ሲሆን "ያህዌህ ኤሎሂም" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፦
ማቴዎስ 4፥10 "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ" Κύριον τὸν θεόν σου προσκυνήσεις καὶ αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις.
ዘዳግም 6፥13 ያህዌህ አምላክህን ፍራ እርሱንም አምልክ በስሙም ማል። אֶת־יְהוָ֧ה אֱלֹהֶ֛יךָ תִּירָ֖א וְאֹתֹ֣ו תַעֲבֹ֑ד וּבִשְׁמֹ֖ו תִּשָּׁבֵֽעַ׃

ስለዚህ በቀላሉ "ብቻውን ያለውን ያህዌህ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ" ማለት ነው። ይህን ከተረዳን ግራንቪል ሻርፕ የተሰኘ የግሪክ ስድስት ሰዋስው መርሕ መካከል አንደኛ መርሕ ላይ፦ "ሁለት ነጠላ የማዕረግ ስሞች "እና" በሚል መስተጻምር ተያይዘው ተመሳሳይ ሙያ ካላቸው እና የመጀመሪያው የማዕረግ ስም ከፊቱ ላይ ውስን መስተአምር ካለ በተቃራኒው ሁለተኛው የማዕረግ ስም ከፊቱ ላይ ውስን መስተአምር ከሌለ የሚያመለክተው አንድ ማንነትን ነው" የሚል ነው።

በዚህ ሕግ ይሁዳ 1፥4 የመጀመሪያው የማዕረግ ስም "ዴስፖቴን" δεσπότην ሲሆን ከፊቱ ላይ "ቶን" τὸν የሚል ውስን መስተአምር አለው፥ በተቃራኒው ሁለተኛው የማዕረግ ስም ደግሞ "ኩርዮን" Κύριον ሲሆን ከፊቱ ላይ "ቶን" τὸν የሚል ውስን መስተአምር የለውም። "ዴስፖቴን" እና "ኩርዮን" በሚል ሁለት የማዕረግ ስሞች መካከል "ካይ" καὶ የሚል መስጻምር አለ፥ ቅሉ ግን ከካይ በፊት ያለው "ዴስፖቴን" ሙያው ተሳቢ ሙያ ሲሆን ከካይ በኃላ ያለው "ኩርዮን" ደግሞ "ሄሞን" ἡμῶν ማለትም "የእኛ" የሚል አገናዛቢ ሙያ ስላለ ሁለት የተለያየ ሙያዎች ናቸው። ስለዚህ "ጌታ" እና "ጌታችን" ሁለት የተለያየ ሙያ ሆነው ስለመጡ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ" የተባለው አብ እና ጌታችን የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት
ለየቅል የሆኑ ምንነት እና ማንነት ናቸው።

በአዲስ ኪዳን ተዛማች ጥቅስ "ዴስፖቴስ" δεσπότης የሚለው ቃል "ጌታ" በሚል ለአብ ብዙ ቦታ መጥቷል፥ አረጋዊ ስምዖን ሕፃኑን አቅፎ የሕፃኑን አምላክ አብን እየባረከ "ዴስፖቴስ" በማለት ተናግሯል፦
ሉቃስ 2፥28-29 እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው አምላክንም እየባረከ እንዲህ አለ፦ "ጌታ" ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ። καὶ αὐτὸς ἐδέξατο αὐτὸ εἰς τὰς ἀγκάλας καὶ εὐλόγησεν τὸν Θεὸν καὶ εἶπεν Νῦν ἀπολύεις τὸν δοῦλόν σου, Δέσποτα, κατὰ τὸ ῥῆμά σου ἐν εἰρήνῃ·

ሐዋርያት ወደ አንዱ አምላክ ወደ አብ ሲጸልዩ "ዴስፖቴስ" በማለት እና ኢየሱስ ደግሞ በዲስፓቴስ የተቀባ የዲስፓቴስ ባሪያ እንደሆነ ተናግረዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 4፥24 እነርሱም በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ወደ አምላክ ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ እንዲህም አሉ፦ "ጌታ" ሆይ! አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ። οἱ δὲ ἀκούσαντες ὁμοθυμαδὸν ἦραν φωνὴν πρὸς τὸν Θεὸν καὶ εἶπαν Δέσποτα, σὺ ὁ ποιήσας τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν καὶ τὴν θάλασσαν καὶ πάντα τὰ ἐν αὐτοῖς,

"ብቻውን ያለው ጌታ" የተባለበት በጌትነቱ የሚጋራው የሌለው እንደሆነ ለመግለጽ ነው፥ ይህ በጌትነቱ እና በአምላክነቱ ማንም የማይመስለው ብቻውን ያለ ነው፦
ነህምያ 9፥6 አንተ ብቻ ያህዌህ ነህ። אַתָּה־ה֣וּא יְהוָה֮ לְבַדֶּךָ֒
ኢዮብ 23፥13 እርሱ ግን ብቻውን ነው፥ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?

ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ኢየሱስ ከመካድ ይልቅ ኢየሱስ "በአምላክ እመኑ" "በእኔም እመኑ" በማለት እርሱ እና አምላኩ ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት እንደሆኑ አበክሮ እና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥1 በአምላክ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። πιστεύετε εἰς τὸν Θεόν, καὶ εἰς ἐμὲ πιστεύετε.

"በእኔ" በሚለው ቃል ላይ “ም” የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ለማሳየት የገባው በግሪኩ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚለውን መስተጻምር ለማሳየት የገባ ነው፥ ይህም አምላክ እና መልእክተኛው ሁለት የተለያዩ ሃልዎት እና ኑባሬ እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል።
አምላካችን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሏህ ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፦
2፥163 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ
39፥45 አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፡፡ وَإِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَحْدَهُ اشْمَأَزَّتْ قُلُوبُ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘቡር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥55 ጌታህም በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አብልጠናል፡፡ *"ለዳውድም ዘቡርን ሰጥተነዋል"*፡፡ وَرَبُّكَ أَعْلَمُ بِمَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَلَقَدْ فَضَّلْنَا بَعْضَ النَّبِيِّينَ عَلَىٰ بَعْضٍ ۖ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

አላህ በቁርኣን ስማቸውን ካነሳቸው ሃያ አምስት ነቢያት መካከል አንዱ ዳውድ ሲሆን በስም ካነሳቸው አራት መጽሐፍት መካከል ደግሞ አንዱ ዘቡር ነው፦
17፥55 ጌታህም በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አብልጠናል፡፡ *"ለዳውድም ዘቡርን ሰጥተነዋል"*፡፡ وَرَبُّكَ أَعْلَمُ بِمَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَلَقَدْ فَضَّلْنَا بَعْضَ النَّبِيِّينَ عَلَىٰ بَعْضٍ ۖ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን፡፡ *"ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው"*፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
21፥105 *"ምድንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመገሰጫው በኋላ በዘቡር በእርግጥ ጽፈናል"*፡፡ وَلَقَدْ كَتَبْنَا فِي الزَّبُورِ مِن بَعْدِ الذِّكْرِ أَنَّ الْأَرْضَ يَرِثُهَا عِبَادِيَ الصَّالِحُونَ

“ከተብና” َكَتَبْنَا የሚለው ቃል “ቁልና” قُلْنَا ማለትም "አልን" ወይም “አውሐይና” َأَوْحَيْنَا ማለትም "አወረድን" በሚል ተለዋዋጭ ቃል የመጣ ነው። እዚህ ዐውድ ላይ “ዚክር” ذِكْر የተባለው ተውራት ሲሆን አላህ በተውራት፦ "ምድር ለአላህ ናትና፡፡ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል፡፡ ምሰጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት" የሚል ቃል አውርዷል፦
21፥48 *"ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው"*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ
7፥128 ሙሳ ለሰዎቹ፡- «ለአላህ ተገዙ ታገሱም፡፡ *ምድር ለአላህ ናትና፡፡ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል፡፡ ምሰጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት»* አላቸው፡፡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ اسْتَعِينُوا بِاللَّهِ وَاصْبِرُوا ۖ إِنَّ الْأَرْضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ ۖ وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ

ከተውራት በኃላ በዘቡር "ምድንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል" የሚለው ንግግር በእርግጥ ተነግሯል። "ዘቡር" زَّبُور ማለት "ጽሑፍ"script" ማለት ነው፤ ይህ ቃል "ጽሑፍ" በሚል ስድስት ጊዜ መጥቷል፦
3፥184 ቢያስተባብሉህም ከአንተ በፊት በግልጽ ተዓምራት እና *"በጽሑፎች"*፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡት መልክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል፡፡ فَإِن كَذَّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَ رُسُلٌ مِّن قَبْلِكَ جَاءُوا بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ وَالْكِتَابِ الْمُنِير
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና *"በመጻሕፍት"* ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ
26፥196 እርሱም ቁርኣን በቀድሞዎቹ *"መጻሐፍት"* ውስጥ የተወሳ ነው፡፡ وَإِنَّهُ لَفِي زُبُرِ الْأَوَّلِين
35፥25 ቢያስተባብሉህም እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩት በእርግጥ አስተባብለዋል፡፡ መልክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎችን፣ *"በጽሑፎችም"*፣ አብራሪ በኾነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል፡፡ وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كَذَّبَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِالْبَيِّنَاتِ وَبِالزُّبُرِ وَبِالْكِتَابِ الْمُنِيرِ
54፥43 ከሓዲዎቻችሁ ከእነዚህ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ *"በመጽሐፎች"* ውስጥ የተነገረ ነፃነት አላችሁን? أَكُفَّارُكُمْ خَيْرٌ مِّنْ أُولَـٰئِكُمْ أَمْ لَكُم بَرَاءَةٌ فِي الزُّبُرِ
54፥52 የሠሩትም ነገር ሁሉ *"በመጽሐፎች"* ውስጥ ነው፡፡ وَكُلُّ شَيْءٍ فَعَلُوهُ فِي الزُّبُرِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "መጽሐፎች" "መጻሐፍት" "ጽሑፎች" "መጽሐፍት" ለሚለው የገባው "ዙቡር" زُّبُر ሲሆን የዘቡር ብዙ ቁጥር ሆኖ ነው። ነገር ግን እነዚህ አናቅጽ ላይ "ዙቡር" የሚለው ለዳውድ የተሰጠውን ዘቡር ሳይሆን "ኩቱብ" كُتُب ለሚለው ተለዋዋጭ ነው።
"ሚዝሙር" מִזְמוֹר በብዜት "ዘሚር" זָמִיר በነጠላ ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ዘመረ" זָמַר ማለትም "አወደሰ" "አመሰገነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምስጋና" "ውዳሴ" "ማህሌት" "መዝሙር" "ዜማ" ማለት ነው።
ዘቡር የተሕሚድ፣ የተህሊል፣ የተሥቢሕ ነሺድ ነው፥ "ተሕሚድ" تحميد ማለት "አልሓምዱ ሊላህ" الحَمْد لله‌‎ ማለት ነው፣ "ተህሊል" تهليل‌‎ ማለት "ላ ኢላሃ ኢለላህ" لا اله الاّ الله ማለት ነው፣ "ተሥቢሕ" تسبيح‌‎ ማለት "ሡብሓን አላህ" سبحان الله ማለት ነው። "ነሺድ" نشيد ማለት "ዜማ" ማለት ሲሆን "ሙነሺድ" منشد ደግሞ "አዛሚ" ማለት ነው።

ዛሬ በመጽሐፉ ሰዎች እጅ ባሉት መዝሙራት ውስጥ የዳውድ ዘቡር ቅሪት ቢኖርም ነገር ግን ከዳድው መዝሙር ላይ የተጨመሩና የተቀነሱ ቃላት አሉ። ዛሬ ያሉት መዝሙራት የሰባት ሰዎች መዝሙራት ናቸው፤ እነርሱም፦ የዳዊት 73 መዝሙራት፣ የሰለሞን 2 መዝሙራት፣ የሙሴ 1 መዝሙር፣ የአሳፍ 12 መዝሙራት፣ የቆሬ 11 መዝሙራት፣ የሄማን 2 መዝሙራት፣ 49 መዝሙራት ደግሞ የማይታወቁ ሰዎች ናቸው።
ቁርኣን እውቅና የሰጠው ለዳዊት የተሰጠውን መዝሙር ብቻ ነው፣ ነገር ግን እነዚህን 150 መዝሙራት ሰብስቦ የጻፈው ዳዊት ሳይሆን በባቢሎን ምርኮ ጊዜ 586-538 BC የነበረ ሰው ነው፦
መዝሙር 137፥1 *"በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን"*።
ዳዊት ደግሞ የነበረው ከባቢሎን ምርኮ በፊት ማለት ከ 384 ዓመት በፊት በ 1040–970 BC ነው። በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በምርኮ ተቀመጦ ጽዮንንም ባሰባት ጊዜ ያለቀሰው ሰው ዳዊት ሳይሆን ሌላ ሰው ነው። የዚህ ሰው ንግግር የአምላክ ንግግር ነውን? በፍጹም! በዳዊት መዝሙር ላይ የተጨመረ ንግግር ነው። እንዲሁ በተቃራኒ ከዳዊት መዝሙር ላይ የተቀነሱ መዝሙራት አሉ። የምዕራብይቱ ቤተክርስቲያን እና አይሁዳውናን፦ "መዝሙራት 150 ብቻ ናቸው" ቢሉም ከ 150 በላይ ናቸው የሚሉ ምሁራን አልጠፉም፣ ማስረጃቸው የሰፕቱጀንት መዝሙራትና የምስራቋ ቤተክርስቲያን መዝሙራት 151 መዝሙራት ነው ያላቸው፣ የዐረማይኩ በርሺታ 152 መዝሙራት ሲኖረው፣ የሙት ባህር ጥቅል ደግሞ 155 መዝሙራት ነው።
ዋቢ መጽሐፍትን ይመልከቱ፦
1. James D. Nogalski, “From Psalm to Psalms to Psalter,” in An Introduction to Wisdom Literature and the Psalms: Festschrift Marvin E. Tate.
2. A Brief Introduction to the Old Testament: The Hebrew Bible in its Context. (Oxford University Press: Oxford 2009).
3. The Editing of the Hebrew Psalter (Chico, CA: Scholars Press, 1985).
4. Introduction to the Old Testament as Scripture (Philadelphia: Fortress, 1979)
5. Studies on the Book of Psalms (Edinburgh: T. & T. Clark, 1888).

ቁርኣን ከወረደበት ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና አንዱ ከአላህ ወደ ነቢያት ያወረደውን መለኮታዊ እውነት ለማረጋገጥ እና በዚህ በወረደው እውነት ላይ ቀጥፈው የጨመሩትን ሐሰት ሊያርም ነው፤ ከአላህ ወደ ነቢያት ያወረደውን እውነትን ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا ማለትም “አረጋጋጭ” ሲባል፤ የሰዎች ንግግር የገቡበትን በማረሙ ደግሞ “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለትም “አራሚ” correcter” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” የሚል ስም አለው፦
5፥48 *ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ ና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ

በወንድም ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዳእዋህ… ወደ አላህ ጥሪ ማድረግ
ጥሪያችን
🎙 የድምፅ ትምህርት | 20 MB

ዳእዋህ… ወደ አላህ ጥሪ ማድረግ | ጥሪያችን | ኡስታዝ ወሒድ ዑመር

#Tiriyachen
#ንፅፅር_ሐይማኖት

በኡስታዝ ወሒድ ዑመር

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
ኢየሱስ ፍጡር ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

19፥35 ለአሏህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ግሪካውያን "አምላክ አንድ ነው" ብለው ስለማያምኑ "እኛ የአምላክ ውልደት ነን" ብለው ያምናሉ፥ ለምሳሌ፦ ከ 315-310 ቅድመ ልደት ይኖር የነበረው ባለ ቅኔው አራተስ"Aratus" እራሱ ይህንን ይናገር ነበር፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥28 "ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ "እኛ ደግሞ ውልደት ነንና" ብለው እንደ ተናገሩ። τινες τῶν καθ’ ὑμᾶς ποιητῶν εἰρήκασιν Τοῦ γὰρ καὶ γένος ἐσμέν.

"ጌኖስ" γένος ማለት "ውልደት" ማለት ሲሆን ጳውሎስ ከአራተስ ጠቅሶ "የአምላክ ውልደት ከሆንን" በማለት አጽድቆላቸዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥29 እንግዲህ የአምላክ ውልደት ከሆንን..። γένος οὖν ὑπάρχοντες τοῦ Θεοῦ
1ኛ ዮሐንስ 5፥1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከአምላክ "ተወልዶአል"። Πᾶς ὁ πιστεύων ὅτι Ἰησοῦς ἐστιν ὁ Χριστὸς ἐκ τοῦ Θεοῦ γεγέννηται,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተወልዶአል" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሳንታ" γεννήσαντα ሲሆን ሥርወ ቃሉ በተመሳሳይ "ጌናኦ" γεννάω ነው፥ ኢየሱስ በጊዜ ውስጥ ለተወለደበት የሚጠቀምበት ቃል በተመሳሳይ ይህንን ነው፦
ዕብራውያን 1፥5 እኔ ዛሬ "ወልጄሃለሁ"። ἐγὼ σήμερον γεγέννηκά σε;

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወልጄሃለሁ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ጌኔካ" γεγέννηκά ሲሆን ሥርወ ቃሉ በተመሳሳይ "ጌናኦ" γεννάω ነው። ኢየሱስ ከአምላክ ለተወለዱት "በኵር" ነው፦
ዕብራውያን 1፥6 ደግሞም "በኵርን" ወደ ዓለም ሲያገባ። ὅταν δὲ πάλιν εἰσαγάγῃ τὸν πρωτότοκον εἰς τὴν οἰκουμένην,
ሮሜ 8፥29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል "በኵር" ይሆን ዘንድ፥ εἰς τὸ εἶναι αὐτὸν πρωτότοκον ἐν πολλοῖς ἀδελφοῖς·

"በኵር" ማለት "የመጀመሪያ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ የወንድሞቹ የኢዲስ ፍጥረት በኵር ስለሆነ የፍጥረት በኵር ተብሏል። ወንድሞቹ አዲስ ልደት ያገኙ አዲስ ፍጥረት ከሆኑ "ተወለዱ" ማለት "ተፈጠሩ" ማለት ነው፦
ቆላስይስ 1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና "የፍጥረት በኵር" ነው። ὅς ἐστιν εἰκὼν τοῦ Θεοῦ τοῦ ἀοράτου, πρωτότοκος πάσης κτίσεως,
2 ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን "አዲስ ፍጥረት" ነው። ὥστε εἴ τις ἐν Χριστῷ, καινὴ κτίσις·
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን "ለአዲስ ልደት" በሚሆነው መታጠብ እና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን። οὐκ ἐξ ἔργων τῶν ἐν δικαιοσύνῃ ἃ ἐποιήσαμεν ἡμεῖς ἀλλὰ κατὰ τὸ αὐτοῦ ἔλεος ἔσωσεν ἡμᾶς διὰ λουτροῦ παλινγενεσίας καὶ ἀνακαινώσεως Πνεύματος Ἁγίου,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሲስ" γένεσις ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "የሆነ" ማለት ነው፥ "ልደት" የሚለው ቃል "ፍጥረት" በሚል ተለዋዋጭ ቃል "አዲስ ፍጥረት" "አዲስ ልደት" በሚል መጥቷል። በተመሳሳይ "ዘፍጥረት" እራሱ "ዘልደት" ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 የሰማይ እና የምድር "ልደት" መጽሐፍ ይህ ነው። Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς,

"ጌኔሴኦስ" γενέσεως ማለት "ልደት" ማለት ሲሆን ዘፍጥረት በግዕዝ "ዘልደት" የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፥ "ዘ" ማለት "የ" ማለት ሲሆን "ዘ-"ፍጥረት" ማለት "የ-ፍጥረት" እንዲሁ "ዘ-"ልደት" ማለት "የ-ልደት" ማለት ነው። ሰማይ እና ምድር ደግሞ የተፈጠሩ እንጂ በእማሬአዊ የተወለዱ አይደሉም፥ ልደቱ በፍካሬአዊ ፍጥረቱን የሚያሳይ ከሆነ ኢየሱስ ሆነ ወንድሞቹ የተፈጠሩ እንጂ ቃል በቃል የተወለዱ አይደሉም። አምላክ ፆታ የለውም፥ አይባዛም አይከፋፈልም። ተራሮች የተፈጠሩ ቢሆንም በፍካሬአዊ እንደተወለዱ ይናገራል፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ ተራሮችን "የሠራ"፥
መዝሙር 89(90)፥2 ተራሮች "ሳይወለዱ"፥ πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι
"ሳይወለዱ" ማለት "ሳይሠሩ" "ሳይፈጠሩ" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ "ወልጄሃለሁ" ሲል "ፈጥሬካለው" ማለት ነው። ዓለም ሳይፈጠር በመለኮታዊ ዕቅድ ውስጥ የወለደው(የፈጠረው) ከማርያም ማኅፀን ነው፦
መዝሙር 109(110)፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን "ወለድኩህ"። ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.

"ጋስትሮስ" γαστρὸς ማለት "ማኅፀን" ማለት ሲሆን ፈጣሪ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ በመለኮታዊ ዕቅድ ከማርያም ማኅፀን እንደፈጠረው ያሳያል፦
መዝሙር 22፥9 አንተ ግን "ከሆድ" አውጥተኸኛልና።
መዝሙር 22፥10 "ከእናቴ "ሆድ" ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ።

ግዕዙ "ከርሥ" ሲለው "ማኅፀን" ማለት ነው፥ "ከእናቴ "ሆድ" የሚለው ይሰመርበት! አምላክ ኢየሱስን ከሴት እንዲገኝ ያረገው ፍጡር ነው፦
ገላትያ 4፥4 አምላክ “ከ-ሴት የተወለደውን” ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ። ἐξαπέστειλεν ὁ Θεὸς τὸν Υἱὸν αὐτοῦ, γενόμενον ἐκ γυναικός, γενόμενον ὑπὸ νόμον,

“የተወለደው” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጌኖሜኖን” γενόμενον ሲሆን “ጊኖማይ” γίνομαι ማለትም “ሆነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሆነውን” ማለት ነው፥ "የሚያስሆን" አምላክ ሲሆን "የሚሆን" ደግሞ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ "ልደት" ያለው ፍጡር ሲሆን ይህ ልደቱ እናቱ ማርያም ማኅፀን ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ መፀነሱ ነው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ Χριστοῦ ἡ γένεσις οὕτως ἦν. μνηστευθείσης τῆς μητρὸς αὐτοῦ Μαρίας τῷ Ἰωσήφ, πρὶν ἢ συνελθεῖν αὐτοὺς εὑρέθη ἐν γαστρὶ ἔχουσα ἐκ πνεύματος ἁγίου.

በተመሳሳይ እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሲስ" γένεσις ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "የሆነ" ማለት ነው፥ ኢየሱስ ያለ ወንድ ዘር ከማርያም የማኅፀን ፍሬ የሆነ ተአምር ነው። ይህ የገባት ማርያም "ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና" በማለት ብርቱ የሆነ አንድ አምላክ በማኅፀኗ ያለ ወንድ ዘር ታላቅ ሥራ ኢየሱስን ሠርቷል፦
ሉቃስ 1፥49 ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ "ታላቅ ሥራ" አድርጎአልና።
ወላዲ እና ተወላዲ ግብር ነው፥ "ግብር" ማለት "ሥራ" "ግኝት" ማለት ነው። ግብር ገባሪን እና ግቡርን የያዘ ድርጊት ነው፥ "ገባሪ" ማለት "ሠሪ" "አስገኚ" ማለት ሲሆን "ግቡር" ደግሞ "ተሠሪ" "ተገኚ" ማለት ነው። የአብ ግብሩ መውለድ(መሥራት ማስገኘት) ስለሆነ እርሱ "ገባሪ" ነው፥ የወልድ ግብሩ መወለድ(መሠራት መገኘት) ስለሆነ "ግቡር" ነው።
እዚህ ድረስ ከተግባባን መርየም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? ስትል አሏህ በጂብሪል "አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦
3፥47 ፡-"ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
19፥35 ለአሏህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ይህንን በቀላሉ ከተረዳችሁ ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen?mibextid=ZbWKwL

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሦስት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

“ትራይ-ቴእይዝም” τριθεισμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ትራይ” τρι “ሦስት” እና “ቴኦስ” θεισμός “አምላክ” የሚል ውቅር ነው፤ ትርጉሙም “ሦስት አምላክ”triple deity” ማለት ነው፤ ይህ “አምላክ ሥስት ነው””tritheism” የሚባለው ትምህርት ከአንድ አምላክ ትምህርት ጋር ይጋጫል፤ “ሞኖ-ቴእይዝም” μονοθεϊσμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ሞኖ” μονο “ብቸኛ” እና “ቴኦስ” θεισμός “አምላክ” የሚል ውቅር ነው፤ ትርጉሙም “ብቸኛ አንድ አምላክ”only one deity” ማለት ነው፤ “ሥላሴ” ማለት “ሥሉስ” ማለትም “ሦስት” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ሦስትነት” ማለት ነው፤ አምላክ በስም፣ በግብር፣ በአካል ሦስት ሲሆን በህላዌ፣ በኑባሬ፣ በመለኮት አንድ ነው የሚለው ተስተምህሮት “ሥላሴ” ይባላል፤ “እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ፤ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት” ትርጉሙ፦ “አንድ ሲሆን ሦስት ደግሞ ሦስት ሲሆኑ አንድ፤ በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮት አንድ ናቸው” ምንጭ የዘወትር ፀሎት። አምላክ አንድም ሦስትም ትምህርት “Triune God” ይባላል፤ “እግዚአብሔር ሦስት አካል አንድ ባህርይ ነው” ምንጭ ሰይፈ ሥላሴ ቁጥር 5 ።
ሦስት ፊት እና ሦስት መልክ ያላቸው እነዚህ ሥስት አካላት፦
1ኛ. “ሆ ቴኦስ ሆ ፓቴራስ” Ο Θεός ο πατέρας ማለትም “እግዚአብሔር አብ”God the father”
2ኛ. “ሆ ቴኦስ ሆ ሁዎስ” Ο Θεός ο γιος ማለትም “እግዚአብሔር ወልድ”God the son”
3ኛ. “ሆ ቴኦስ ሆ ኑማቶ ሃጂኦን” Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ”God the holy spirit” ናቸው።
አምላካችን አላህ “ሦስት ናቸው” አትበሉም፤ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናል፤ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው በማለት ሥስትነትን ይቃወማል፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

ነጥብ አንድ
“አማልክት”
ዶክተር ሻቢር፣ ዶክተር ቢላል፣ ዶክተር ዛኪር ካልክ በኃላ አይ አንድ ዶክተር ነው ብትል ቂልነት ነው፤ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ካልክ በኃላ አንድ እግዚአብሔር ማለት ቂልነት ነው፤ እነዚህ ሥስት አካሎች “ጌቶች” ይባላሉ፤ “አጋዕዝተ-ዓለም ሥላሴ” ማለት “የዓለም ጌቶች ሥላሴ” ማለት ነው፤ “እግዚእ” በነጠላ “ጌታ” ማለት ሲሆን “አጋዕዝት” ማለት ደግሞ በብዜት “ጌቶች” ማለት ነው፤ ስለዚህ ሥላሴ ሦስት ጌቶች ናቸው፤ እነዚህ ሥስት አካሎች “አምላኮች” ወይም “አማልክት” ናቸው፤ “ኤሎሂም” אלהים ማለት ብዜት ሲሆን “አምላኮች” ወይም “አማልክት” ማለት ሲሆን “ኤሎሃ” אלוהּ ደግሞ “አምላክ” ማለት ነው፤ “ኤሎሂም” ሥላሴን ካመለከተ ሥላሴ ሥስት አምላክ ናቸው፤ ሥላሴን “ፈጣሪዎች” ማለታችሁ በራሱ ይህንን ያሳያል፦
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! የአደምና የሔዋን *”ፈጣሪዎቻቸው እንደመሆናችሁ”* መልክአ ሥላሴ ቁጥር 39

አንድ ሰው ሦስት ማንነቶች ካሉት ያ ሰው ሦስት ሰዎች እንጂ አንድ ሰው አይባልም፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ያሰኘው ማንነቱ ነውና፤ በተመሳሳይ አንድ አምላክ ሦስት ማንነቶች ካሉት ያ አምላክ ሦስት አምላክ እንጂ አንድ አምላክ አይባልም፤ ምክንያቱም አንድ አምላክ ያሰኘው ማንነቱ ነውና፤ “አካል” ማለት “ማንነት” ሲሆን “ህላዌ” ደግሞ “ምንነት” ማለት ነው፤ ሥላሴ በማንነት ሦስት ሲሆኑ በምንነት አንድ ናቸው፤ ሰዎች በማንነት ሰባት ቢሊዮን ሲሆን በምንነት ግን አንድ ናቸው፤ ምክንያቱም ሁሉ ምነታቸው ሰው ሰለሆነ። በሁለቱ ማለትም በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአንዱ ማንነት ከአላህ ሌላ አማልክት የሆኑ ማንነቶች በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፤ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፤ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፤ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 በሁለቱ ውስጥ *”ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር”*፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልያዘም፤ *ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር*፡፡ አላህ “ከሚመጥኑት” ሁሉ ጠራ፡፡ مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٍۢ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنْ إِلَٰهٍ ۚ إِذًۭا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍۢ ۚ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

“ከሚሉት” ወይም ‘ከሚመጥኑት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የሲፉነ” يَصِفُونَ ማለት “ባህርይ ካደረጉለት”they attribute” ነገር ሁሉ የጠራ ነው።
ነጥብ ሁለት
“አካላት”
“አካል” ሲባል “ማንነት” ተብሎ መቀመጥ ሲኖርበት ነገር ግን መልክአ-ሥላሴ የተባለው መጽሐፍ “አካል” ማለት “ተክለ-ሰውነት”body” አድርጎ ሥላሴ “ደም” “ወርች” “ጎን” “ከርስ” “ኩላሊት” “ወገብ” “አብራክ” “ተረከዝ” “ጫማ” “ጥፍር” “ጣት” እንዳላቸው ይናገራል፤ ይህንን ጉድ እስቲ እንይ፦
“ደም”
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! *ስርየተ ደማችሁ* ስርየተ ኃጢኣት ነውና የነፍሴን ቤት መቃን በስርየት *”ደማችሁ”* እርጩት።”
“ወርች”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የአዳምን ወርች ላጸና መለኮታዊ *ወርቾቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጎን”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የወርቅ አስፈላጊያቸው ላይደለ መለኮታዊ *ጎኖቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ከርስ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጡራንን ሆድ ለፈጠረ ለማይመረመር *ከርሳችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ኩላሊት”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ *ኩላሊታችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ወገብ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መታጠቂያው የቸርነት ሰቅ ለሆነው *ወገባችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“አብራክ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጥረት ሁሉ አብራክ ለሚያሰግድ *አብራካችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ተረከዝ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ብርሃናት ለተጎናፀፈው *ተረከዛችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጫማ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ለሚራመድ *ጫማችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጥፍር”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! *ከጥፍሮቻችሁ* ጋር ያለመነጣጠል ተባብረው ተመሳስለው ላሉ *ጣቶቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”

ሌላው ይሁን እሺ “ከርስ” እና “አብራክ” ምን ያረግላቸዋል? ከርስ እኮ የምግብ ማከማቻ ሆድ ነው፤ ይበላሉን? አብራክ እኮ የዘር ከረጢት ነው፤ ይወልዳሉን? እስቲ በባይብል አምላክ ሦስት አካል ነው ወይም ሦስት አካል አለው የሚል ጥቅስ ይፈለግ፤ እስቲ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው የሚል ጥቅስ ይፈለግ፤ የለም፤ አምላክ አንድ “ነው” እንጂ “ናቸው” የሚል የለም፦
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ *”ነው”*፥

“እርሱ” “አንተ” “አለ” እና “ነው” ተብሎ የሚመለክ አምላክ እንጂ “እነርሱ” “እናንተ” “አሉ” እና “ናቸው” ተብሎ የሚመለክ አምላክ ባይብል ላይ ሽታው እንኳን የለም፤ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል የሆነ ቃል በመጽሐፋችሁ “አምላክ አንድ ብቻ ነው” የሚል ነው፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *”አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው”*፤
ዘዳግም 6፥6 እኔም ዛሬ አንተን *”የማዝዘውን ይህን ቃል”* በልብህ ያዝ።
ዘዳግም 4:2 *”እኔ ያዘዝኋችሁን”* የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን *”ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም”*።

“እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” ብሎ ያዘዘውን ቃል በልብህ ያዝ፤ ይህ ታላቁና ፊተኛይቱ ትእዛዝ አንድ በሚለው ላይ ሁለት ወይም ሶስት አሊያ ከዚያ በላይ አትጨምር፤ አንድ ከሚለው ላይ ካጎደልክ የለም ማለት ነውና አትቀንስ ግን አንድ የሚለውን ብቻ ያዝ፤ ትክክል ወደ ኾነች “አንድ ብቻ ነው” ወደሚለው ቃል ኑ፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው”*፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ كَلِمَةٍۢ سَوَآءٍۭ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِۦ شَيْـًۭٔا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًۭا مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُولُوا۟ ٱشْهَدُوا۟ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አል-ሓምዱሊሏሂ ረቢል ዓለሚን ዐላ ኒዕመተል ኢሥላም!

በኡስታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen?mibextid=ZbWKwL

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

"ሸይእ" شَىْء ማለት "ነገር"thing" ማለት ሲሆን ማንኛውንም ነገር ሁሉ የፈጠረ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
39:62 አላህ *"የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው"*። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው። ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ وَكِيلٌۭ
40:62 ይሃችሁ፣ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *"የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?። ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
6:102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *"ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፡፡ ስለዚህ አምልኩት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٌۭ وَلَمْ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٌۭ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
13፥16 *«አላህ ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው"*፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ

ያ ማለት ከነገር ሁሉ ተቃራኒ ነገርን የፈጠረው አላህ ብቻ ነው፤ ለምሳሌ ሰማይንና ምድርን፣ ብርሃንንና ጨለማን፣ ሞትና ህይወትን፣ ወንድና ሴትን ሁሉ ማለት ነው፦
51፥49 ትገነዘቡም ዘንድ *"ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ዓይነትን ፈጠርን"*፡፡ وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
6፥1 ምስጋና ለዚያ *"ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው፤ ጨለማዎችንና ብርሃንንም"* ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَ
67፥1 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ *"ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው"*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ
75፥39 ከእርሱም *"ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ"*፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰٓ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ዞራስተርያን ወይም ኖስቲዝም፦ "ሰማይን፣ ብርሃንን፣ ህይወትን፣ ወንድን የፈጠረው "አሁራ" የተባለው አምላክ ነው ሲሉ፤ በተቃራኒው ምድርን፣ ጨለማን፣ ሞት፣ ሴትን የፈጠረው "አንግራ" የተባለው አምላክ ነው ብለው ሁለት አምላክ ያመልካሉ፤ ይህ የሁለት አምላክ ጥምረት ትምህርት "ዱአ-ቴእይዝም"duotheism" ይባላል፤ "ዱአ-ቴእይዝም" δυοθεισμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ዱአ" δυο "ሁለት" እና "ቴኦስ" θεισμός "አምላክ" የሚል ትርጉም ነው፤ ትርጉሙም "ሁለት አምላክ"dual deity" ማለት ነው፤ ይህንን ትምህርት ቁርአን ክፉኛ ይቃወማል፦
16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ
ይህ ትምህርት ከሥላሴ የሚለየው አምላክ በምንነት ሆነ በማንነት ሁለት ነው ሲሉ፤ ሥላሴያውያን ደግሞ በማንነት ሦስት በምንነት አንድ ናቸው ብለው ያምናሉ፤ ነገር ግን አንዱ አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው፤ በምንነቱ ሆነ በማንነቱ ተጋሪ የለውም፦
18፥110 ወደ እኔ የሚወረድልኝ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ" ማለት ነው፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ *"አንድንም"* አያጋራ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

"አንድ አምላክ" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለውን የተጠቀመበት "ዋሒድ" وَٰحِد ሲሆን አላህ በምንነቱ ላይ ምንም ምንነት ተጋሪ እንደሌለው ያሳያል፤ "አንድንም አያጋራ" በሚለው ቃል የተጠቀመበት ቃል "አሐድ" أَحَد ሲሆን በአላህ ምንነት ላይ ማንም ማንነት ተጋሪ እንደሌለ ያሳያል፦
72፥20 «እኔ የምግገዛው ጌታየን ብቻ ነው፡፡ በእርሱም *"አንድንም"* አላጋራም» በል፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُوا۟ رَبِّى وَلَآ أُشْرِكُ بِهِۦٓ أَحَدًۭا
112፥1 በል «እርሱ አላህ *"አንድ"* ነው፡፡ قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ

"አላህ አንድ ነው" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለው "አሐድ" أَحَد መሆኑ በራሱ አላህ አንድ ማንነት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ከእርሱ ማንነት ጋር መለኮትን የሚጋራ አንድም ማንነት የለም፦
112፥4 ለእርሱም *"አንድም"* ብጤ የለውም፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

"ለም" لَمْ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለማንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ ለእርሱ ማንም ብጤ የሌለው መሆኑን ያሳያል፤ "ለይሠ" لَيْسَ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለምንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ አላህ የሚመስለው ምንም ምንነት የለም፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም *ሰሚው ተመልካቹ* ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ ያለ የተውሒድ ትምህርት ከተረዳን በክርስትናው አንጃ ውስጥ የይሆዋ ምስክሮች ደግሞ፦ "ዓለማት ከመፈጠራቸው በፊት ያህዌህ ኢየሱስ ፈጠረውና በኢየሱስ ሁሉን ነገር ፈጠረ" ብለው ያምናሉ፤ ይህ እንጥል ከመቧጠጥ ምንም አይተናነስም፤ ኢየሱስን አናመልክም ሲሉ ተውሒደል ኡሉሂያን ሲያሟሉ፤ ግን ዓለማትን ሲፈጥር ግን አጋዥ ነበረው ብሎ ማለት ተውሒደ አር-ሩቡቢያን ላይ ማሻረክ ነው፤ ከአላህ ጋር በምንነት ተለይቶ ግን ፍጥረትን ሲፈጥር ሆነ ዓለማትን ሲያስተናብር የሚያግዘው አጋዥ የለውም፤ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ እንላለን፦
34፥22 እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ *"የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም"*፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ *"ምንም ሽርክና የላቸውም"*፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ *"ምንም አጋዥ የለውም"*» በላቸው፡፡ قُلِ ٱدْعُوا۟ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍۢ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍۢ وَمَا لَهُۥ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍۢ

በኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen?mibextid=ZbWKwL

ወሠላሙ ዐለይኩም
2024/06/08 08:52:44
Back to Top
HTML Embed Code: