Telegram Web Link
የ ራስ አርክቴክቶች ስራ፡፡

የዝነኛዋ ኢትዮጵያዊ ህንጻ ነዳፊ የ ራሄል ሻውል ቢሮ የ ናሚቢያ ሪፓብሊክ ኤምባሲን እድሳት በዚህ መልክ ነድፎታል፡፡

ፎቶ ምንጭ። ሩት ታከለ
@ethiopianarchitectureandurbanism
Forwarded from NArcHome Architecture
Transition of Female Architecture Students from classroom to professional practice

A coffee round discussion with
- Tatiana Pinta
- Belilta Asfaw &
- Rahel Shawl, all architects.


Via Abren

#Event, #Architecture, #Ethiopia

📌 Design for Humanity!
@NArcHomeArchitecture
የቆዩ የከተማ ምስሎች።

ድሬደዋ በ1965 ዓም።


Diredawa in February 1973 G.C

Ludo Kuipers Photographs/Images of the World/Eastern Ethiopia/Diredawa:
ouzutback.com.au/Ethiopia/index.html

ምንጭ፡፡ HITTCL 1860s-1990s @ethiopianarchitectureandurbanism
Forwarded from Ketema Journal
Koba Patisserie

Bringing natural daylight into a restaurant or coffee shop can greatly enhance the ambiance and overall customer experience. The recently opened ‘KOBA’ coffee shop in Addis Ababa is a prime example of this, featuring a cutting-edge roofing system.

ketemajournal.com/story/koba-patisserie/

@ketema_journal
Forwarded from UUAS - Architecture (|||)
The evolution of the Trinity Cathedral, Addis Ababa.

We can witness that the cathedral got changed two times. It was first built before the Italian occupation, then given its neo-baroque form after liberation and finally it was expanded in the 60s by Yugoslavian architects and a contractor. At the moment it is undergoing renovation works under the supervision of Prof. and Architect Fasil Ghiorgis.

Via: Dawit benti

@unityarch
የጣልያን ግዜ የአዲስ አበባ ካርታ፡፡

በጣልያን አገዛዝ ወቅት ሁሉም የአዲስ አበባ መንገዶች የጣልያንኛ ስም ወጥቶላቸው ነበር፡፡ አደባባዮችም እንደዚሁ ነበር የሚጠሩት፡፡ የባቡር ጣብያ መንገድ ቪያሌ ሞሶሎኒ ሲባል ከነጻነት በኋላ ቸርችል ጎዳና ተብሏል፡፡ አራት ኪሎ አደባባይ ፒያዛሌ ቺንኩዌ ማጂዮ ሲባል ከነጻነት በኋላ ሚያዝያ 27 አደባባይ ተብሎ ቀርቷል፡፡

ስሙን ሳይለቅ በትንሹ በአንድ ፊደል ለውጥ ብቻ የቀረው ቦታ ፒያሳ የሚባለው ሲሆን ጣልያን ፒያዛ ሊቶሪዮ ብሎ ስም ሰጥቶት ነበር፡፡ ይህ ቦታ ትክክለኛ ስፍራው ሲኒማ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት ቼንትሮ ባር ያለበት ቦታ ያለው ከፍት ቦታ ሲሆን ከጣልያን በፊት የስላሴ ኮከብ አደባባይ ይባል ነበር፡፡ ሊቶርዮ ማለት ፋሺስት ማለት ሲሆን ፒያዛ ሊቶሪዮ ማለት ደግሞ የፋሽስቶች አደባባይ ማለት ነበር፡፡
@ethiopianarchitectureandurbanism
የ 1961/62 ዓም የአዲስ አበባ ካርታ፡

በ1950ዎቹ የተጀመረው ዘመናዊው ኪነህንጻ ዘይቤ ጫፍ ነክቶ አዲስ አበባን በአንድ አስርት አመታት ሊቀይራት ችሎ ነበር፡፡

ይህ የ አስርተ አመታት ዘመን የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ቀኃስ አውሮፕላን ማረፍያ፣ የአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ)፣ ቸርችል ጎዳና፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ ተቋም እና የኬኔዲ ቤተመጻህፍት፣ የካርታ ስራ ድርጅት ህንጻ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አፓርትመንት 82 ሂልተን ጋር፣ አፓርትመንት 69 ፒያሳ፣ ኪዳኔ በየነ ህንጻ፣ ጽጌ በሻህ ህንጻ፣ ባንኮ ዲሮማ ህንጻ፣ ሻሎም ሸለማይ አፓርትመንት አትክልት ተራ፣ ሞዝቮልድ ህንጻ፣ አድቬንቲስት ቤተክርስትያን፣ የጀርመን ቤተክርስትያን፣ የመካነኢየሱስ እና ሉተራን ቤተክርስትያኖች፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ፖስታ ቤት፣ የቤቶች ባንክ (ሞርጌጅ ባንክ) በድሉ ህንጻ፣ አውራ ጎዳና ህንጻ፣ ጠማማ ፎቅ፣ ራሽያ አፓርትመንት፣ ፍላሚንጎ አፓርትመንት፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የቤተ ክህነት ህንጻዎች፣ ኢትዮጵያ፣ አፍሪካ ዋቢ ሸበሌ እና ሂልተን ሆቴሎች፣ አክሱም ጺዮን ማርያም ቤተክርስትያን፣ ደብረሊባኖስ ገዳም፣ ቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስትያን፣ ስላሴ ካቴድራል መስፋፋት እና እድሳት፣ መስቀል በዓል ከጊዮርጊስ አደባባይ ወደ ራስ ብሩ ሜዳ ወደ መስቀል አደባባይ መምጣት እና የአደባባዩ መሰየም፣ የአሰብ የነዳጅ ማጣርያ፣ የባህርዳር ፖሊቴክኒክ ኢንስቲትዩት፣ የአባይ ግድብ ቦታ ውሳኔ፣ ጎንደር ጎሀ ሆቴል፣ ላሊበላ ሮሀ ሆቴል፣ ባህርዳር ጣና ሆቴል፣ ትግራይ የሀ ሆቴል ወዘተ በፍጥነት እና በጥራት የተሰሩበት አስደናቂ የኪነህንጻ ወርቃማ ዘመን ነበር፡፡

ከታች በፒዲኤፍ የተያያዘውን ካርታ ማውረድ የሚቻል ሲሆን በካርታው ላይ ያሉት አብዛኞቹ በጥቁር የተመለከቱት ህንጻዎች ክ1950፟-60 የተገነቡ የዚህ የወርቃማው ዘመን ግንባታ ውጤት ነበሩ፡፡ እነዚህ አሁን ክ55 አመታት በላይ ያስቅቆጠሩት እድሜ ጠገብ ህንጻዎች አሁንም በውበትና ባረፈባቸው ጥበብ የሚያንጸባርቁ ህንጻዎች ናቸው፡፡

በ50ዎቹ ምን ተገኝቶ ነው ይሄ ሁሉ በብዛትና በጥራት ሊገነባ የቻለው? ከ50ዎቹ በፊት ለምን አልተገነቡም? ብሩ ከየት መጣ? ገፊ ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው? እስከአሁን እጅግም መልስ አልተገኘላቸውም፡፡ እየጠየቅን እንቀጥላለን፡፡
@ethiopianarchitectureandurbanism
2025/06/30 17:36:53
Back to Top
HTML Embed Code: