የሥላሴ እሳቤ 2ኛ ዕትም የምትፈልጉ ልጆች
አዲስ አበባ አየርጤና በ 0920781016
አዳማና አካባቢው @arhmanu
ደሴ :– ሸርፍ ተራ አህመድ ኪታብ ቤት
አረብ ገንዳ ሸህ አብዱ መክተባ
ሸርፍ ተራ ፋጡማ መክተባ
ዘካህ ለሠለምቴዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው።
“ማል” مَال ማለት “ሀብት” ማለት ሲሆን የማል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አምዋል” أَمْوَال ነው፥ ከተቀማጭ ሀብት ላይ ወይም ከትርፍ ላይ የሚሰጠው ዘካህ “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال ይባላል። በነቢያችን”ﷺ” ሸሪዓህ ግን ዘካቱል ማል ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

“ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏

“ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው።

ዘካቱል ማል ከቤት ለተባረሩ ሠለምቴዎች መቋቋሚያ መስጠት ከፈለጋችሁ እና ዘካቱል ፊጥር ለመሣኪን ሠለምቴዎች ማስፈጠሪያ መስጠት ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች ያሉትን አድሚናት አናግሩ፦
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://www.tg-me.com/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://www.tg-me.com/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://www.tg-me.com/Zhara_mustefa

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ኢየሱስ በቀጣይ እሑድ ይመጣል"

ልደታ ቤተክርስቲያን መምህርት አስካለ በልጅነታችን ኢየሱስ፦
፨በዕለተ እሑድ
፨በእሑደ ደብረ ዘይት
፨በቀኑ 29 ቀን
፨በወሩ መጋቢት ወር
፨በዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ከገጠመ ይመጣል" ብላ አስተምራናለች።
ባሕረ አሳብን ቀምረው የአገራችን ሊቃውንት "በዘመነ ዮሐንስ፣ እሑድ በደብረ ዘይት፣ በመጋቢት 29 ቀን ይመጣል" ባሉት መሠረት እየጠበቅን ነው። ይህን ካልሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሐሰተኛ ነቢያት ተለይታ አትታይም።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ!

እንኳን የዒዱል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ!
ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው።

አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበለን! አሚን።

ዒድ ሙባረክ!
የሰው ሥጋ ይበላልን?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ

አምላካችን አሏህ በመልእክተኞች በኩል "ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ" ብሎ ነግሮናል፥ እነዚህ መልካም ምግቦት የሰጠን ሲሳይ ናቸው፦
23፥51 እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡ يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
2፥172 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደኾናችሁ አሏህን አመስግኑ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ وَاشْكُرُوا لِلَّهِ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ሰዎች ሆይ! አሏህ መልካም ነው፥ እርሱ መልካም እንጂ አይቀበልም። አሏህ ምእመናንን መልእክተኞችን ባዘዘው መሠረት አዘዛቸው። እርሱም፦ "እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ" አለ፥ እርሱም፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ" አለ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ اللَّهَ طَيِّبٌ وَلاَ يَقْبَلُ إِلاَّ طَيِّبًا وَإِنَّ اللَّهَ أَمَرَ الْمُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ الْمُرْسَلِينَ فَقَالَ ‏:‏
‏(‏يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ ‏)‏ وَقَالَ أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ‏)‏ ‏"‏ ‏.‏

በተቃራኒው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ሐራም ነው፦
2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና በእርሱም ማረድ ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ

በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ቢሆንም በረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው ሕይወት ለማትረፍ ተፈቅዷል፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም። አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

ነገር ግን በማንኛውም ወቅት እና ሁኔታ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም መብላት ሐላል ነው፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆኑ ዓሣ እና አንበጣ የማይታረዱ ሥጋ ናቸው። ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ናቸው፦
16፥14 እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ሥጋን ልትበሉ እና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ ያገራ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا
5፥96 የባሕር ታዳኝ እና ምግቡ ለእናንተ እና ለመንገደኞችም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ የየብስ አውሬ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ صَيْدُ الْبَحْرِ وَطَعَامُهُ مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِلسَّيَّارَةِ ۖ وَحُرِّمَ عَلَيْكُمْ صَيْدُ الْبَرِّ مَا دُمْتُمْ حُرُمًا ۗ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 64
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም ለእኛ ተፈቅዶልናል፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆን ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ أُحِلَّتْ لَنَا مَيْتَتَانِ وَدَمَانِ فَأَمَّا الْمَيْتَتَانِ فَالْحُوتُ وَالْجَرَادُ وَأَمَّا الدَّمَانِ فَالْكَبِدُ وَالطِّحَالُ ‏"‏ ‏.‏
ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ባሕር እንዲህ አሉ፦ "እርሱ ውኃው ንጹሕ ነው፥ ሙታኑ እንስሳት ለመብላት ሐላል ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏- رضى الله عنه ‏- قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-فِي اَلْبَحْرِ: { هُوَ اَلطُّهُورُ مَاؤُهُ, اَلْحِلُّ مَيْتَتُهُ }

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦
7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ
7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ
7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا
አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦
49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106
አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏

እዚህ ቁርኣን እና እዚህ ሐዲስ ላይ ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ሐራም ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ሐራም ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል፦
ሡነን እብኑ ማጃህ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كَسْرُ عَظْمِ الْمَيِّتِ كَكَسْرِهِ حَيًّا ‏"‏ ‏

ኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪሥ አሽ ሻፊዒይ "የሞተ ሰው ሥጋ ሕይወትን ለማትረፍ በረሃብ ጊዜ ይፈቀዳል" ብለዋል፥ ለዚህ አባባል ምንም ዓይነት የቁርኣን ሆነ የሐዲስ ደሊል እንከሌለ ድረስ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል። እርሳቸው በ 204 ዓመተ ሒጅራህ በትህትና "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት" ብለዋል፦
"የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት"። إذا صح الحديث خلاف قولي فاعملوا بالحديث واتركوا قولي
ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 106
አቢ ሠዒድ አል ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ይሁን መልካሙን የበላ፣ በሡናህ የተገበረ እና ሰዎች ከሚያስከትለው መዘዝ የታደገ ወደ ጀናህ ይገባል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَنْ أَكَلَ طَيِّبًا وَعَمِلَ فِي سُنَّةٍ وَأَمِنَ النَّاسُ بَوَائِقَهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏

"ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን በተቃራኒው "ሐራም" حَرَام "የተከለከለ" ማለት ነው። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚቻለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በቁርኣን የነገረን እና ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የነገሩን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦
7፥157 "መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏

አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708
አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏

"መሽቡህ" مَشْبُوه የሆኑ ነገሮችን መተው ተመራጩ ሒክማህ ነው። አምላካችን አሏህ በግልጠተ መለኮት "ሐላል" ያለው "ሐላል" ማለት "ሐራም" ያለው "ሐራም" ማለት ትልቅ ታዛዥነት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 117
ሠልማን አል ፋርሢይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ስለ ቅቤ፣ ስለ ዓይብ እና ስለ አህዮች ተጠየቁ፥ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "ሐላል አሏህ በመጽሐፉ የፈቀደው ነው፥ ሐራም አሏህ በመጽሐፉ የከለከለው ነው። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ السَّمْنِ وَالْجُبْنِ وَالْفِرَاءِ قَالَ ‏ "‏ الْحَلاَلُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ وَالْحَرَامُ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ "‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 12ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://www.tg-me.com/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://www.tg-me.com/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://www.tg-me.com/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://www.tg-me.com/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
Photo
ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ

ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል"Bishop Mar Mari Emmanuel" በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው የአሦራውያን ቤተ ክርስቲያን"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት "ክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን"Christ The Good Shepherd Church" ውስጥ ያገለግሉ ነበር።
የአሦራውያን ቤተክርስቲያን የምሥራቅ ሶርያዊ ሥነ መለኮት አቀንቃኝ ሲሆን መሠረቱ የንስጥሮስ ትምህርት ነው፥ የንስጥሮስ ትምህርት "አንዱ ኢየሱስ ሁለት ማንነት"Hypostasis" አለው፥ በፍጹም አምላካዊ ማንነት የአብ ልጅ በፍጹም ሰዋዊ ማንነት የማርያም ልጅ ነው። ማርያም የወለደችው ሰው እንጂ አምላክ አይደለም" የሚል ትምህርት ነው። ይህ ትምህርት በ 431 በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ የኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል የንስጥሮስ እሳቤ አራማጅ ናቸው።

በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ኦርቶዶክሶች እኚህን አባት እንደ ኦርቶዶክስ አባት አርገው የሚመለከቱት ትምህርታቸው ከራሳቸው ትምህርት ጋር አነጻጽረው በቅጡ መረዳት የማይችሉ ስለሆኑ ናቸው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የንስጥሮስ ትምህርት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ በጽብሐዊ ኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት የተወገዘ ምንፍቅ ና ነው።

ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በእንግሊዝኛ መርሐ ግብር የተለያ እሳቦትን በመተናኮል እና በመጎንተል በዓለም ላይ ይታወቃሉ። እስራኤልን፣ ምዕራባውያንን፣ አሜሪካንን፣ ግብረ ሰዶማ ውያንን ሳይቀር ይተቻሉ፥ አልፎ አልፎ ካቶሊክን፣ ፕሮቴስታንትን ሲላቸውም ዲኑል ኢሥላምን ሲወርፉ ይሰማል።

ትላንት አንድ ሰው በሚያስተምሩበት ቤተክርስቲያን አደጋ አድርሶባቸው ህክምና ላይ እዳሉ እየተሰማ ነው። አደጋ ያደረሰባቸው ማንነት እስካሁን እንዳልተጣራ እየታወቀ ሆኖ ሳለ ክርፋታቸውን እና ልጋጋቸውን በተገኘው አጋጣሚ የሚያዝረከርኩ ክርስቲያኖች ለሙሥሊም ያላቸው ጥላቻ ምን ያክል የከፋ እና የከረፋ መሆኑን የምታውቁት ሰውዬውን "ሙሥሊም ነው" በማለት ዲናችንን መዝለፍ እና ማብጠልጠል ተያይዘውታል። ሰውዬው ሙሥሊም ቢሆንስ? ሰውዬውን "ትክክል አይደለም" ብሎ እራሱን ማውገዝ እንጂ ዲናችንን ለምን አሳቻ ሰዓት ላይ ጠብቃችሁ ትጎነትላላችሁ? ስንት እና ስንት ሙሥሊሞች በክርስቲያኖች ተገለው እንደ ኖርማል እየታየ አንድ ክርስቲያን ስለተገደለ ክርስትናን የእውነት ሚዛን አርጎ መውሰድ ቂልነት ነው።

በእርግጥም ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል ለዲኑል ኢሥላም ያላቸው ጥላቻ አይጣል ነው፥ በአገኙት አጋጣሚ ዲናችንን በማበሻቀጥ እና በማብጠልጠል የዘመኑን የውረፋ ዋንጫ ወስደዋል። ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ተከታዮቻቸው "ዓይን ስለ ዓይን ጥርስ ስለ ጥርስ" የሚለውን ሕግ ይዘው "የእጁን እንስጠው" ብለው ግብግብ ሲይዙ ነበር። "ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት" የሚለው የሚሠራው ስብከት ላይ ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 5፥38 ‘ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት።

አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምንከተል ድረስ እንዳይወዱን አሏህ በቁርኣኑ ነግሮናል፦
2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ

አሏህ ለእነርሱ ልብ ይስጣቸው! ለእኛም ትእግስቱን ይስጠን! አሚን።

አንብበው ሼር በማድረግ አስነብቡ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል ማን ናቸው?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል "ኢየሱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፥ ከኢየሱስ ውጪ አምላክ የለም" በማለት አብ እና መንፈስ ቅዱስን በማሽቀንጠር የሰባልዮስ ትምህርት እያራመዱ ነው። "ኢየሱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፥ ከኢየሱስ ውጪ አምላክ የለም" የሚል ባይብል ላይ ሽታው የለም።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ!

መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!

መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom
ሸፊዕ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦
53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦
19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا

ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦
10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

“ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት!
ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦
10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ
6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ

እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦
6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع

"ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ አሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦
32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” በመጀመሪያው ሐረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦
30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ

ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ሸፊዕ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአሏህ ፈቃድ ለሙእሚን የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው። ለምሳሌ መላእክት፦
53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነቢያት ናቸው፦
19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا

ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦
10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

“ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦
10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ
6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦
6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع

"ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ በአሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦
32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው። “ማ” مَا የሚለው "ሐርፉን ነፍይ" حَرْف النَفْي በመጀመሪያው ሐረግ ላይ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉን ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው። በዚህ ምክንያት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦
30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ

ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው።
( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع )
أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه .

"መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለሙእሚን ያማልዳሉ" ማለት እና "እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ" ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው።  "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"የተደበቀዉ እዉነት" የሚል መጽሐፍ Abdu Book Delivery እኛም ጋር ያገኙታል።

አድራሻችን፦
አዲስ አበባ ፒያሳ
ለበለጠ መረጃ በ 0929574133 ይደዉሉልን!

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።

በቴሌግራም👇👇👇
https://www.tg-me.com/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9
1. ጥያቄ ካላችሁ፣
2. መረጃ ከፈለጋችሁ፣
3. መሥለም ከፈለጋችሁ በዚህ አድራሻ አግኙኝ፦ https://m.me/Wahidapologist
ግርዶ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ

ጭሮ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ጸብ አጫሪ መሆንን ምርጫቸው ያረጉ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች "ጸብ በደላላ ካልሆነልን" ብለው ለገላይ በማያመች "ያዙኝ ልቀቁኝ ደግፉኝ ጣሉኝ" በማለት መፎለሉን፣ ማቅራራቱን፣ መሸለሉን፣ መፎከሩን ተያይዘውታል። "አሏህ እንደ እንስት ሒጃብ ይለብሳል" በማለት የሌለ አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of equivocation" ያፅፃሉ። ምሁራን "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" እንደሚሉ ስለ ሒጃብ ከሥር መሠረቱ ኢንሻላህ እንመልከት!
"ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ሸፈነ" "ጋረደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ"cover" "መጋረጃ"curtain" "ግርዶ"screen" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ መርየም ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦
19፥17 ከእነርሱም "መጋረጃን" አደረገች፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "መጋረጃ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب እንደሆነ ልብ አድርግ! በተጨማሪ የጀነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከል ያለው አዕራፍ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦
7፥46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ

ስለዚህ "ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል እንደ ዐውዱ የተለያየ ትርጉም አለው። ለተጨማሪ ግንዛቤ እነዚህ አናቅጽ ተመልከት፦ 17፥45 38፥32 41፥5
ሌላው ሴት ልጅ የምትሰተርበት ጉፍታ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦
33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህ እና ለምእምናን ሚስቶች ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 312
ዑመር"ረ.ዐ." እንደተናገረው፦ "እኔ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ሰናይ እና እኩይ ሰዎች ወደ እርሶ ይገባሉ፥ ለምእመናን እናቶች በሒጃብ እንድታሰትራቸው አስጤናለው" አልኩኝ፥ ከዚያም አሏህ የሒጃብ አንቀጽ አወረደ"። قَالَ قَالَ عُمَرُ ـ رضى الله عنه ـ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، يَدْخُلُ عَلَيْكَ الْبَرُّ وَالْفَاجِرُ، فَلَوْ أَمَرْتَ أُمَّهَاتِ الْمُؤْمِنِينَ بِالْحِجَابِ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ آيَةَ الْحِجَابِ‏.‏

እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ አንድን ሰው ነቢይ አርድጎ ለማስነሳት በግልጠት ከሚያናግርበት መንገድ አንዱ ከግርዶ ወዲያ ነው፦
42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ግርዶ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب ሲሆን አሏህን ሳያዩ በድምፅ ብቻ መስማት ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በለይለቱል ኢሥራእ ወል ሚራጅ ጊዜ አምስት ወቅት ሶላትን ሲቀበሉ ያዩት ይህ ሒጃብ ብርሃን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 350
አቢ ዘር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛን”ﷺ” ጌታህን አይተከዋልን? ብዬ ጠየኳቸው። እርሳቸው፦ "ያየሁት ብርሃን ነው፥ እንዴት እርሱን ማየት እችላለው? አሉ። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم هَلْ رَأَيْتَ رَبَّكَ قَالَ ‏ “‏ نُورٌ أَنَّى أَرَاهُ ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 201
አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አሏህ አይተኛም፥ እርሱ መተኛት አይገባውም። እርሱ ሚዛኖችን ዝቅ ያረጋል ያነሳልም፥ የእርሱ ግርዶ ብርሃን ነው። أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنَامُ وَلاَ يَنْبَغِي لَهُ أَنْ يَنَامَ يَخْفِضُ الْقِسْطَ وَيَرْفَعُهُ حِجَابُهُ النُّورُ

"መንጦላዕት" የሚለው የግዕዙ ቃል "አንጦልዐ" ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥረወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጋረጃ" ማለት ነው። የፈጣሪ መጋረጃ ብርሃን ነው፥ ፈጣሪ ማንም ሊቀርበው በማይችል በብርሃን መጋረጃ ይኖራል፦
መዝሙር 31፥20 በፊትህ "መጋረጃ" ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ። תסתירם בסתר פניך מרכסי איש
መዝሙር 4፥6 በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። ያህዌህ ሆይ! የፊትህ "ብርሃን" በላያችን ታወቀ። רַבִּ֥ים אֹמְרִים֮ מִֽי־יַרְאֵ֪נוּ֫ טֹ֥וב נְֽסָה־עָ֭לֵינוּ אֹ֨ור פָּנֶ֬יךָ יְהוָֽה׃
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፥ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል። አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።

አንድ ሰው እንኳ ያለየው እና ሊያየው የማይቻለው በብርሃን መጋረጃ ስለሚኖር ነው። ከመስማት እና ከመስማማት ይልቅ የመደናቆር እና የመጻረር አባዜ ስለተጠናወታቸው እንጂ በትውፊት እና በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ "ሰባቱ መንጦላይት" የሚባሉት "ሰባቱ የእሳት መጋረጃ" ሲሆኑ አምላክ በእነዚህ ሰባት የእሳት መጋረጃ የተሰወረ ነው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘዓርብ ቁጥር 14
"ሥላሴ "በእሳት መጋረጃ" ውስጥ የተሰወረ ነው"።
መዓዛ ቅዳሴ ምዕራፍ 1 ቁጥር 51
"በሱራፌል መካከል "የእሳት መጋረጃ" በፊቱ ጋረደ፥ አሳቡን የሚያውቅ የለም። አኳኃኑን የሚረዳ የለም፥ ስውር በሆነ መሰወሪያው እራሱን ሰወረ"።

እንግዲህ ቅንፍጥፍ በማለት ከማዛግ ይልቅ ቅልጥፍጥፍ ብላችሁ በአርምሞ እና በጥሞና ብትመረምሩ እና ብትመራመሩ የአሏህ ምሪት ለማግኘት መደንርደሪያ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"የስላሴ እሳቤ" እና "የተደበቀው እውነት" መጻሕፍ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ አዳማ እና ደሴ ይገኛሉ።

አዳማ ማግኘት የምትፈልጉ call +251966640370

ደሴ ማግኘት የምትፈልጉ፦
አረብገንዳ ሸህ አብዱ መክተባ
  ሸርፍተራ ፋጡማህ መክተባ 
አሕመድ መክተባ ይገኛል

አዲስ አበባ ደግሞ call 0920781016
2024/05/01 06:25:52
Back to Top
HTML Embed Code: