Telegram Web Link
#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡

ለጨረታ የሚቀርበው የውጭ ምንዛሪ መጠን 60 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ጨረታው ለሁሉም ባንኮች ክፍት እንደሚሆን ታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የ60 ሚሊየን ዶላር ጨረታ አወጣ! የዶላር ጨረታው የዶላር ዋጋን ይወስናል?

የመጀመሪያው የዶላር ጨረታ ከኢኮኖሚ ለውጡ 10 ቀን በኋላ (ነሃሴ 1/2016) ነበር አንድ ዶላር 107.9 ብር ዋጋ ወጥቶለት የነበረው!

ከ6 ወር በኋላ 60 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል! በገበያው ምን አይነት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?

የመጀመሪያው ጨረታ የሚገመት ውጤት አልነበረውም!

ከአሁኑ ጨረታ የውጪ ምንዛሬ ገበያው ለውጥ ሊኖረው ይችላል...https://youtu.be/FUqXEb_oM2c
#ለመረጃ፡ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው የዶላር ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135.61 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቀ።

ጥያቄው ንግድ ባንኮቹ ለውጪ ምንዛሬ ፈላጊው በስንት ሊሸጡ ነው?
ብሄራዊ ባንክ ገበያውን አረጋጋለሁ ብሎ ብርን ለምን ከ8-10 ብር ድረስ ለማዳከም ወሰነ?

ብሔራዊ ባንክ በዛሬው የዶላር ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135.61 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቋል!

ከዛሬው የመደበኛ ባንኮች የምንዛሬ ተመን አንፃር ብር ከ8-10 ብር ተዳክሟል!

የዚህ ጨረታ ዋጋ መጋነን ምክንያት ምንድን ነው?

የብር መዳከም ከነገ ጀምሮ በገበያው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ምን ሊሆን ይችላል?

ብሄራዊ ባንክ የምንዛሬው ዋጋው መጋነኑን ከተመለከተ በኋላ ጨረታውን ለምን አልሰረዘም?

በፍፁም የጨረታው ዋጋ ብርን በጣም ያዳክማል ብዬ አላሰብኩም ነበር! በዝርዝር እንመልከተው....https://youtu.be/Q0LmEXlEMdU
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ 27 ባንኮች በተሳተፉበት ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ136 ብር ቢሸጥላቸውም ንግድ ባንኮቹ ከ3 ቀን በኋላ አብዛኞቹ የመሸጫ ዋጋ ለውጥ አላደረጉም!

የ10 ባንኮችን የተከታታይ 3 ቀናት የዶላር የመሸጫ ዋጋ ስንመለከት ያደረጉት ለውጥ የሚጠበቅ አይደለም!

ባንኮች ዶላር ከገዙበት በታች እየሸጡ ያሉበት ድራማ መነሻው ምንድን ነው?

ከጨረታው በኋላ እድል የተከፈተላቸው ባንኮች....

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዶላር የሸጠው ገበያው ውስጥ ወርቅ ለመግዛት የበተነውን ብር ለመሰብሰብ ነው ወይስ ለወርቅ ሸመታ ብር አጥሮት ብር ለማግኘት?

በዝርዝር እንመልከተው.....https://youtu.be/LDONqlkHZMs
የራሽያ ኢኮኖሚ 28,000 ማዕቀብ ተቋቁሞ እንዴት አደገ?

ኢኮኖሚው ለ3 ዓመት ጦርነት ውስጥ ሆኖ እጥፍ የGDP እና የፖለቲካ አጋርነት እድገት አስመዝግቧል!

የራሽያ ኢኮኖሚ ( ፑቲን) በጦርነት እና በማዕቀብ ውስጥ ሆኖ ኢኮኖሚን የማሳደግ ምሳሌ ሆነዋል!

ራሽያ ላለፉት 3 ዓመታት 28,000 ማዕቀብ ቢጣልባትም ኢኮኖሚዋ ማዕቀብ ከጣሉባት ሃገራት የተሻለ እድገት ማስመዝገቡን IMF እየመሰከረ ነው!

ጠለቅ አድርገን እንመልከተው.....https://youtu.be/wkH0Ln2QgVE
#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ወለድ መጠኖች ላይ ማሻሻያ/ጭማሪ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል።

ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፦

የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣

የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣

የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣

የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል።

ይሁን እንጂ ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔ በ12 በመቶ እንደነበረው ይቀጥላል ተብሏል።

የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች በ12 በመቶ እንደነበረው እንደሚቀጥልም ታውቋል።

ምንጭ :- ካፒታል ጋዜጣ
#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባካሄደው የዶላር ጨረታ በጨረታው ተሳታፊ ከነበሩ 27 ባንኮች ውስጥ ዶላር ያገኙት #12_ባንኮች ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህ 12 ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ130 እስከ 141 ብር ዋጋ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ!
የኢትዮጵያ ብር ጉልበት የሚያገኘው መቼ ነው? ምን ያህል ዶላር ቢከማች ብር የመግዛት አቅሙ ያድጋል?

የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በፍጥነት እየተዳከመ ነው!

በገበያው ምክንያት በዋናነት ከሃምሌ 2016 ጀምሮ ብር መዳከም በያዘበት ፍጥነት ከቀጠለ ጠቅላላ ኢኮኖሚው አደጋ ውስጥ መሆኑ ይቀጥላል!

የብር የመግዛት አቅም እንዲያድግ የሚጠበቅ የዶላር ክምችት መጠን እና የሚወስድበት ጊዜ ከምንገምተው ውጪ ነው!

የሚከተለውን ትንታኔ እንመልከት....https://youtu.be/M0ngKvGpxaI
#ለመረጃ፦ የአሜሪካ መንግስት ከ6 ሳምንት ግምገማ በኋላ 5,200 የUSAID ኮንትራቶች ሰርዟል! ይህም ማለት የUSAID 83% ፕሮማራሞቹ ተሰርዘዋል።

"ቀሪው 18% ማለትም 1,000 የድርጅቱ ፕሮግራሞች በስቴት ዲፓርትመንቱ በአግባቡ እየተመሩ ይቀጥላሉ" ሲሊ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስታውቀዋል።
የPLC እና የአክሲዮን ድርጅት ልዩነት! አዋጭ የቢዝነስ ማህበራት አመሰራረት!

በኢትዮጵያ የቢዝነስ ህግ ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ድርጅት በማቋቋም መካከል ያለውን ልዩነት እንመልከት!

ድርጅት በማህበራት ሂደት ለማቋቋም ለምታስቡ በሙሉ PLC በማድረግ እና ድርጅትን በአክሲዮን በመመስረት መካከል ያለውን አንድነት እና ልዩነት እንመልከት!

በግል ይሰራ የነበረ ቢዝነስ እንዴት ወደ PLC ወይም አክሲዮን ድርጅትነት መለወጥ እንደሚችል እንመልከት!https://youtu.be/Uo7Dz49quaU
#ለመረጃ፦ የየካቲት ወር የሀገሪቷ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15% መድረሱን እና የምግብ ነክ እቃዎች የዋጋ ንረት የ14.6% እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች የዋጋ ንረት ደግሞ 15.6% መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ገልጿል።
የኢትዮጵያ ዋጋ ንረት 15 በመቶ ሆኗል (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት)!

ዋጋ ንረት መቀነሱ እውነት ነው! ነገር ግን ኢኮኖሚው ስለተጨነቀ ነው.....

የኑሮ ውድነት እያለ ዋጋ ንረት ይቀንሳል? ዋጋ ንረት ቀነሰ ማለት ምን ማለት ነው? የዋጋ ንረቱ የቀነሰው በምን ምክንያት ነው? የዋጋ ንረት መቀነሱ ለምን ተዓማኒነት አጣ? የዋጋ ንረት ስሌት አሳማኝ እንዲሆን ምን መደረግ አለበት?

በድፍረት እና በጥልቀት መልስ እንስጥበት...https://youtu.be/cS5IFY6iO8Q
#ሰበር_መረጃ፡ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 2 #የኢንቨስትመንት_ባንኮች ፍቃድ አገኙ!

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዛሬ 12/7/2017 ለአምስት አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ ሰጥቷል።

በንግድ ባንክነት የሚታወቁ 2 ትልልቅ የኢትዮጲያ ባንኮች ኢንቨስትመንት ባንክነት ፍቃድ ዛሬ ወስደዋል! የኢንቨስትመንት ባንኮች መከፈት ለካፒታል ገበያው ማርሽ ቀያሪ ነው!

መረጃውን ይመልከቱ….https://youtu.be/FwA7Av-nnKw
2025/07/12 01:15:32
Back to Top
HTML Embed Code: