Telegram Web Link
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ስራ የሚጀምረው የውጭ ባንክ! Kenya Commercial Bank (KCB)!

የየትኛውን ሃገር ባንክ ጠብቀን የየትኛው ሃገር ባንክ ፍላጎቱን ይዞ ኢትዮጵያ ድረስ መጣ?

ከባንኩ ልምድ በመነሳት በየትኛው መስፈርት ኢትዮጵያ ውስጥ የመሳተፍ እቅድ እንደሚኖረው እንመልከት!

ስለ KCB ባንክ ፈተሽ እናድርግ!https://youtu.be/VOrwwkgCyv4?si=H9FkvAHS5KBnMRhD
ድሃ መሆን ከባድ ብቻ ሳይሆን ውድ ነው! Being Poor Is Expensive!

ድህነት ውስጥ ያለ ሰው ድሃ መሆን ምን ያህል ውድ መሆኑን ይረዳል!

መንግስት ድሃ ዜጎቹ ያሉበትን ድህነት ማወቅ አለበት! የድሆች መንግስት ድሃ ነው!

ከአዲሱ መነጋገሪያ ፊልም Straw በመነሳት ሃሳቡን በምሳሌ እንመልከተው!https://youtu.be/gSE-2DjikQI
የትምህርት ቤት ክፍያ እስከ 65% ይጨምራል! ፍታዊነት፤ ስጋት፤ አማራጭ እና ቢሆን የሚሻለው…..

አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ 1,585 የግል ትምህርት ቤቶች መካከል 1,227 ማለትም 77 በመቶዎቹ ለ2018 እስከ 65 በመቶ የክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ ተፈቅዷል!

የተዘጋጀው ደንብ ቀሪዎቹ 23 በመቶዎቹ ማለትም 358 የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ የመጨመር ተራቸው በ2019 ነው!

ለትምህርት ቤቶቹ ደረጃ ተሰቷል! በደረጃ የጭማሪ ልዩነት ምን እንደሚመስል እንመልከት!

የልጆቹ የትምህርት ቤት ክፍያ በግማሽ የጨመረበት ወላጅ ምርጫው ምንድን ነው?

በዝርዝር የጥናቱን ውሳኔ እንመልከተው…https://youtu.be/nUAtp0PbgkQ
አዲሱ ግብር የሚከፈልበት የደሞዝ መጠን! የኢሠማኮ አማራጭ ቁጥሮች!

በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሰራተኞች የደሞዝ ግብር መጠን በገንዘብ ሚኒስትር ረቂቁ ቀርቦ ውይይት ላይ ነው!

ነገር ግን በመንግስት እየቀረበ ያለው የደሞዝ ግብር መጠን (ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ደሞዝ) እና የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ያቀረቡት መነሻ የሰማይ እና የምድር ያህል ልዩነት አለው!

የተቀመጠውን የደሞዝ እና የግብር መጠን በዝርዝር ከነምክንያቱ እንመልከተው....https://youtu.be/dAydraFIzwk
#ለመረጃ፡ የግንቦት ወር የዋጋ ንረት ከሚያዝያ ወር ጋር በተመሳሳይ 14.4% ሆኖ ተመዝግቧል ሲል መንግስት አሳውቋል!
አትሸወዱ! ቁጥሮች ድሃም ሃብታምም ያደርጋሉ! Purchasing Power Parity

አንዳንድ የኢኮኖሚ ለውጥ መለኪያ ቁጥሮች የህዝቡን ጓዳ በቅርበት አያውቁትም!

ኢኮኖሚክስ የሌላ ሀገር ነዋሪዎች አንድን ቁስ ለመግዛት ከሚያወጡት ወጪ ኢትዮጲያዊያን በሃገራቸው ለተመሳሳይ ቁስ የሚያወጡት የተለየ እንዲሆን አይመክርም ነበር…..

ነገር ግን በሸቀጦች ዋጋ እና በኑሮ ውድነት ኢትዮጲያዊ የሚፈተነው ከሌሎች ሀገራት ዜጎች የተለየ ሊሆን ይችላል!

ምክንያቶቹ ከምትመለከቱት የተለየ ናቸው! በዝርዝር እንመልከታቸው! https://youtu.be/0cl9lfwLR7c
ዋጋ ንረት ከቀነሰ የዜጎች ኑሮ ለምን አይሻሻልም? የቁጥሮቹን እውነት ልንገራችሁ!

በመንግስት እና በህዝብ መካከል የዋጋ ንረት ቀነሰ የሚለው ቁጥር እና ህዝቡ በሚጋፈጠው የኑሮ ውድነትን መካከል ያለው ክርክር ይቀጥላል!

ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ የክርክሩን ምክንያት አስረዳለሁ!

መንግስት እታች ገበያ ውስጥ ያለውን እውነት ተረድቶ ማስተካከያ ማድረግ አለበት!https://youtu.be/dL5LG4O_Utc
#ለመረጃ"መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ ከነዳጅ ድጎማ ወጥቷል! የነዳጅ ዋጋም በዓለም የነዳጅ ገበያ ይወሰናል! በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም" ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አስታውቀዋል!
በ2018 ወጪዬ በግማሽ ይጨምራል! ለመቋቋም ምን ላድርግ?

በየጊዜው አዳዲስ ቤተሰባዊ እና ግለሰባዊ የኑሮ ማስኬጃ ወጪዎች እየተፈጠሩ ነው!

በኢትዮጲያ የኑሮ ወጪዎች በቋሚነት የመጨመር ባህሪ አላቸው…የቤት ኪራይ፤ የአስቬዛ ዋጋ፤ የትምህርት ክፍያ፤ የትራንስፖርት ታሪፍ፤ የመንግስት አገልግሎት ክፍያዎች (ዓመታዊ ክፍያ፤ ቅጣት፤ መብራት፤ ውሃ፤….)

የምርት እና የአገልግሎት ዋጋ ባህሪው እየተለዋወጠም እየጨመረም ነው!

ገቢ በገደብ ውስጥ ያለ እና ጠንካሪ ቁጥጥር ያለበት በመሆኑ በቀላሉ የሚያድግ አልሆነም!

አዳዲስ የወጪ ምክንያቶች እየተፈጠሩ ነው! ነባር ዋጋዎችም እራሳቸውን እየጨመሩ ነው!

በ2018 ወጪ የሚጨምረውን ያህል ለመቋቋም ምን ለማድረግ አስበዋል?

በዝርዝር እና በምሳሌ እንመልከተው…..https://youtu.be/thNfRqk-eNQ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ገጥሞት ነበር! (የሚጠበቅ ኪሳራ!)


በዚህ ወቅት ኪሳራ የሚጠበቅ ቢሆንም ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው አደጋ ምን ሊሆን ይችላል?

እንዴት ብሔራዊ ባንኩ ሊከስር እንደቻለ እንመልከት!https://youtu.be/0HzI3GiDMpY

ጠቅላላ ሰነዱን ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ተያይዟል!
Audited-Financial-Statements-for-the-year-ended-30-June-2024.pdf
44.3 MB
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ኦዲት ሪፖርቱን ማንበብ ለምትፈልጉ!
#ልዩ_ለመረጃ፡ የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰኔ ወር ሲሸጥ በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል!

የነዳጅ ዋጋ በዓለም ገበያ እየተወሰነም በመንግስትም እንዴት ይወሰናል?!
የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት!

531 ቢሊየን ብር ከገበያ ተሰብስቧል! እንዴት?

የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለ3 ወር ሸመታ የሚበቃ ሆኗል! ምን ያህል?

በኢትዮጵያ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው ይቀጥላል! እስከመቼ?

የቀጣይ የብሔራዊ ባንኩ የብድር እቅድ የሚመለከታቸው ዘርፎች ተለይተዋል! የትኞቹ ሴክተሮች?

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/f7WpE_lM7yE
#ለመረጃ፡ "ገንዘባቸውን ማውጣት ለሚጠይቁ ደንበኞች (Depositors) ቅድሚያ ሰጥተው በፍጥነት ምላሽ የማይሰጡ ባንኮች ላይ ጥብቅ ዕርምጃ እወስዳለሁ!" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ።
2025/10/26 08:21:47
Back to Top
HTML Embed Code: