ዋጋ ንረት ከቀነሰ የዜጎች ኑሮ ለምን አይሻሻልም? የቁጥሮቹን እውነት ልንገራችሁ!

በመንግስት እና በህዝብ መካከል የዋጋ ንረት ቀነሰ የሚለው ቁጥር እና ህዝቡ በሚጋፈጠው የኑሮ ውድነትን መካከል ያለው ክርክር ይቀጥላል!

ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ የክርክሩን ምክንያት አስረዳለሁ!

መንግስት እታች ገበያ ውስጥ ያለውን እውነት ተረድቶ ማስተካከያ ማድረግ አለበት!https://youtu.be/dL5LG4O_Utc
#ለመረጃ"መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ ከነዳጅ ድጎማ ወጥቷል! የነዳጅ ዋጋም በዓለም የነዳጅ ገበያ ይወሰናል! በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ የለም" ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አስታውቀዋል!
በ2018 ወጪዬ በግማሽ ይጨምራል! ለመቋቋም ምን ላድርግ?

በየጊዜው አዳዲስ ቤተሰባዊ እና ግለሰባዊ የኑሮ ማስኬጃ ወጪዎች እየተፈጠሩ ነው!

በኢትዮጲያ የኑሮ ወጪዎች በቋሚነት የመጨመር ባህሪ አላቸው…የቤት ኪራይ፤ የአስቬዛ ዋጋ፤ የትምህርት ክፍያ፤ የትራንስፖርት ታሪፍ፤ የመንግስት አገልግሎት ክፍያዎች (ዓመታዊ ክፍያ፤ ቅጣት፤ መብራት፤ ውሃ፤….)

የምርት እና የአገልግሎት ዋጋ ባህሪው እየተለዋወጠም እየጨመረም ነው!

ገቢ በገደብ ውስጥ ያለ እና ጠንካሪ ቁጥጥር ያለበት በመሆኑ በቀላሉ የሚያድግ አልሆነም!

አዳዲስ የወጪ ምክንያቶች እየተፈጠሩ ነው! ነባር ዋጋዎችም እራሳቸውን እየጨመሩ ነው!

በ2018 ወጪ የሚጨምረውን ያህል ለመቋቋም ምን ለማድረግ አስበዋል?

በዝርዝር እና በምሳሌ እንመልከተው…..https://youtu.be/thNfRqk-eNQ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 10.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ገጥሞት ነበር! (የሚጠበቅ ኪሳራ!)


በዚህ ወቅት ኪሳራ የሚጠበቅ ቢሆንም ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው የሚችለው አደጋ ምን ሊሆን ይችላል?

እንዴት ብሔራዊ ባንኩ ሊከስር እንደቻለ እንመልከት!https://youtu.be/0HzI3GiDMpY

ጠቅላላ ሰነዱን ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ተያይዟል!
Audited-Financial-Statements-for-the-year-ended-30-June-2024.pdf
44.3 MB
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ኦዲት ሪፖርቱን ማንበብ ለምትፈልጉ!
የሁላችንንም ህይወት እየወሰኑ ያሉ 4 ጉዳዮች! Economy Fact!

1. Scarcity
2. Demand and Supply
3. Cost and Benefit
4. Incentives

https://youtu.be/H-1FKX11YS4
AI (ChatGPT) ስለኢኮኖሚ የምታውቃቸው 10 አስቂኝ እውነታዎች ተብሎ ሲጠየቅ የመለሰው!

ላለፉት 56 ዓመታት በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ሲሰጥ የኖረው ከባለቤቱ እውቅና ውጪ ነው ብሎ ይጀምራል!

ዝርዝሮቹ ስለኢኮኖሚ የምትገረሙባቸውን እውነታዎች ይዟል!https://youtu.be/pJCYQ9n83tw
#ልዩ_ለመረጃ፡ የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰኔ ወር ሲሸጥ በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል!

የነዳጅ ዋጋ በዓለም ገበያ እየተወሰነም በመንግስትም እንዴት ይወሰናል?!
የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት!

531 ቢሊየን ብር ከገበያ ተሰብስቧል! እንዴት?

የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለ3 ወር ሸመታ የሚበቃ ሆኗል! ምን ያህል?

በኢትዮጵያ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው ይቀጥላል! እስከመቼ?

የቀጣይ የብሔራዊ ባንኩ የብድር እቅድ የሚመለከታቸው ዘርፎች ተለይተዋል! የትኞቹ ሴክተሮች?

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/f7WpE_lM7yE
#ለመረጃ፡ "ገንዘባቸውን ማውጣት ለሚጠይቁ ደንበኞች (Depositors) ቅድሚያ ሰጥተው በፍጥነት ምላሽ የማይሰጡ ባንኮች ላይ ጥብቅ ዕርምጃ እወስዳለሁ!" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ።
#ለመረጃ፡ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ "በከፍተኛ ሁኔታ ገቢያችንን ማሳደግ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው" ብለዋል።

#ለማስታወስ፡ የፌደራል መንግስት የ2018 በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከሀገር ውስጥ ምንጮች ለመሰብሰብ የታቀደው 1.23 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ከታክስ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው 1.1 ትሪሊዮን ብር ነው!
#ለመረጃ፡ USAID ከዛሬ July 1/2025 አንስቶ ማናቸውንም የውጭ እርዳታዎችን ማቅረብ ማቆሙን የአሜሪካ መንግስት አስታወቀ፡፡
ዋጋ ንረትን ነጠላ አሃዝ ማድረግ ስኬት የማይሆንበት ምክንያቶች....

የኢትዮጵያ መንግስት የዋጋ ንረት ወደ ነጠላ አሃዝ (ከ10% በታች) እስኪሆን ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መተግበሩ ይቀጥላል ብሏል!

የዋጋ ንረት ነጠላ አሃዝ ሆነ ማለት በዜጎች ኑሮ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

ነጠላ አሃዝ የዋጋ ንረት ያለባቸው ድሃ የአፍሪካ ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ድክመት ምን እንደሆነ በምሳሌ እንመልከት....https://youtu.be/llQvikHp4xY
"IMF አሁን በያዛችሁት መንገድ ከቀጠላችሁ ብልፅግናን ታረጋግጣላችሁ ብሏል" የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር!

"በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የለውጥ ሂደት ደስተኛ ነኝ" IMF!

IMF በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ይደረግ ብሎ አዞ ያልተደረገ ምን አለ?

የመንግስት የ2017 ሪፖርት እና የIMF ኮሚቴ መግለጫን በዝርዝር እንመልከት....https://youtu.be/sMFtmB6uYDo
አዋሽ እና ዘመን ባንክ ትርፋቸው ከእጥፍ በላይ አድጓል!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ልዩ ዓመት ማሳለፉን ገልጿል!

ኢኮኖሚው ባልጠበቀው ለውጥ ውስጥ እንዴት ይህንን ትርፍ አስመዘገቡ!

የባንኮቹ የትርፍማነት ቁጥሮች ተዓማኒነት ከምን ይመነጫል?

ባንኮቹ ለባለ አክሲዮኖች መልካም ዜና አላቸው!

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/JuNCJ4sxtCQ
አንድ ዶላር 200 ብር መቼ ይገባል?

በኢትዮጵያ የምንዛሬ ገበያው ወደነፃ ስርዓት ከገባ ጀምሮ ለዓመት ቆይቷል!

በባንኮች አንድ ዶላር በ58 ብር ጀምሮ ዛሬ በብሔራዊ ባንክ በአማካይ 136 ብር ደርሷል!

ይህ የአንድ የአሜሪካ ዶላር በ200 ብር የመመንዘር ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ከቀደሙ አመክንዮዎች ተነስተን እናስቀምጥ...https://youtu.be/Rif8J7k2pLs
#ለመረጃ፡ 17ኛው የብሪክስ ጉባዔ በብራዚል በሪዮ ዲ ጄኒሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መድረክ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሀገራቱ መሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ትራምፕ ደግሞ "ከብሪክስ ፀረ-አሜሪካ ፖሊሲዎች ጋር የሚሰለፍ ማንኛውም ሀገር ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ይከፍላል። ለዚህ ፖሊሲ ምንም ልዩ ሁኔታዎች አይኖሩም" ብለዋል!
2025/07/07 20:12:23

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: