Telegram Web Link
መምህር ሙሌ
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
የዛሬው ውይይት ይኸንን ይመስላል
ያልነበራችኹ በደንብ አዳምጡት ብዙ ትምሕርት ታገኙበታላችኹ
የሙስሊም ወገኖች ጥያቄም ተመልሷል ከጥያቄወቹም መካከል መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ብለው ከሚያነሱት የዘወትር ጥያቄ :-አካዝያስ ሲነግስ #የሃያ #ኹለት አመት ወይስ የ #አርባ ኹለት አመት!? የመሳሰሉት ጥያቄወች መልስ ተመልሷል።
2022-10-12
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
የመክፈቻ መዝሙር
በመምህር ሙሌ ግሩፕ በዘማሪ ዲያቆን ፍላኦል💐
2022-10-12
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
እውን ሙስሊሞች እደሚሉት መጽሐፍ ቅዱስ ይጋጫልን!?ተበርዟልን!?

መልስ//ትምህርት:-በመምህር ሙሌ
2022-10-12
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
ጥያቄ:አስተያየት ከአዳማጭ እንድኹም የማጠቃለያ ሀሳብ::

ይኸ ፕሮግራም ዘወትር እሮብ እና እኹድ ስለሚደረግ ኹላችነም በመገኘት እንማር!!!!ለዛሬው ጨርሰናል ሰላም እደሩ!!!
2022-10-16
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
ሙስሊሞች እደሚሉት መጽሐፍ ቅዱስ ይጋጫልን?

የብዙ የሙስሊሞች ጥያቄና መልስ

አዳምጡ!!!
2022-10-16
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
ሙስሊሞች እደሚሉት መጽሐፍ ቅዱስ ይጋጫልን?

  የብዙ  የሙስሊሞች ጥያቄና መልስ 
ከላይኛው የቀጠለ...!

   አዳምጡ!!!
2022-10-16
የመምህር ሙሌ የውይይትና የንፅፅር ግሩፕ
ከታዳሚያን የተነሳ ጥያቄና መልስ
በመምህር ሙሌ

ዘወትር እኹድና እሮብ በኢትዮጵያ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ውይይት እና ለጥያቄወች መልስ ይሰጣል!ኹላችንም በመገኘት እንማር እንወቅ!!!
"ከእንግዲህ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም"
ኢሳ. ፪:፬
"ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር
የሰማይና የምድር ንግሥት ድንግል ማርያም የተወደደ ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ

🌺🌻🌼 ማኅሌተ ጽጌ ፮ኛ እና የመጨረሻ ሣምንት 🌺🌻🌼

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ፡ ሃሌ ሉያ ፡ ሃሌ ሉያ ፣
ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ ፡ ሃሌ ሉያ ፡ ሃሌ ሉያ ፣
ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡፡
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ ፡ ሃሌ ሉያ (2)
አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ፡ ሃሌ ሉያ (2)
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡
ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡
ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡
ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡

ማንሻ፦

ስቡህ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ በአሐቲ ቃል... /ጸንጽል/

ነግሥ

ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤
ለወልድ ሰላም ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም ፤
ለሰማእታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም፡፡

ዚቅ

ዛቲ ይእቲ ትንቢቶሙ ለነቢያት ፣
ስብከቶሙ ለሐዋርያት ፣
እሞሙ ለሰማዕት ፣
ወእኅቶሙ ለመላእክት፡፡

ማኅሌተ ጽጌ

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃልቀ። ዘኢየኃልቅ ስብሐተ (ስብሐተኪ)እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ።
ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ።
ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ።
ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ።
(በእጅጉ የማያልቀውን ምስጋናሽን እያመሰገንኩሽ የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም። ማርያም ተአምርሽ እንዳስረዳ ስምሽን መጥራት የወደቀውን ያነሣል፤ ኃጥኡን ጻድቅ ያደርጋል)

ወረብ

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ "ስብሐተ"/፪/ እንዘ እሴብሐኪ/፪/
(በእጅጉ የማያልቀውን ምስጋናሽን እያመሰገንኩሽ የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም)

ዚቅ

እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤
ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤
ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ፤
ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤
ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፤
መርዓተ አብ ወእመ በግዑ።
(የተቀመጣችሁ ተነሡ፤ ዝም ያላችሁ ተናገሩ፤ ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሩ፤ የድንግልን ተአምር ትሰሙ ዘንድ ቆማችሁ አድምጡ በበጉ እናት በአብ ሙሽራ በቅድስት ድንግል ሥዕል ፊት ጸልዩ)

ወረብ ዘዚቅ

እለ ትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ
ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል
መርዓተ አብ ወእመ በግዑ/፪/

ማኅሌተ ጽጌ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
(በንጽሕናና በተአምር ዕለት ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን ታቅፈሽው ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ከለቅሶ ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ፤ መልካማዬ ከደስተኛው ከገብርኤልና እንዳንቺ ርህሩህ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ)

ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ "ለሕፃንኪ"/፪/
ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/

ዚቅ

ይዌድስዋ ትጉሃን ፤ ይቄድስዋ ቅዱሳን ፤
ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤
ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ፡፡
(ትጉኃን ያመሰግኗታል፤ ቅዱሳን ይቀድሷታል፤ ሰሎሞን መልካሟ ርግቤ ይላታል፤ ጳውሎስም ፍጽምት ድንኳን ይላታል፤ ዳዊትም ልጄ ሆይ ስሚ በጆሮሽ አድምጪ ይላታል)

ማኅሌተ ጽጌ

ሶበ ዴገነኪ አርዌ በሊዓ ሕጻንኪ ዘኀለየ ፤
በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጐይየ፤
አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤
ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ፡፡
(ልጅሽን መብላት ያሰበ አውሬ በተከተለሽ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ በምትበሪበት፤ መሸሽን በምታፈጥኚበት ገንዘብ ዮሐኒ ክንፍን እንዳበበ ክንፎችን ያበብሽ ፀሐይን የለበስሽ የሰማይ ብላቴና ማርያም ተአምርሽን ያየ ዮሐንስ ጻፈ)

ወረብ

አመ አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ/፪/
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ዘርእየ ተአምረኪ/፪/

ዚቅ

በሊአ ህጻናት ሶበ ሀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ
ዘምስለ ዮሴፍ አረጋዊ ነገደት ቁስቋመ ናዛዚተ ኀዘን ወብካይ።

ማኅሌተ ጽጌ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ዚቅ

አክሊሎሙ ለሰማዕት
ተስፋ መነኮሳት፤
ሠያሚሆሙ ለካህናት፤
ነያ ጽዮን መድኃኒት።

ዐዲ ዚቅ

ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤
መራኁቱ ለጴጥሮስ፤
አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤
አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ።

ማኅሌተ ጽጌ

ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ፤
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ፤
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡

ወረብ

ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ፤
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት፡፡

ዚቅ

ሃሌ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ
ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ወርቅ ፡፡

ሰቆቃወ ድንግል

ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤
ወኢትጐንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤
በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤
ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤
በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡

ወረብ

ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ፤
ወኢትጐንድዪ በግብጽ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፡፡

ዚቅ

ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ፨
ወንርአይ ብኩ ሰላመ ፨
ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት ፨
እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር ፨
ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ፡፡

ወረብ

ሃሌ ሉያ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤
ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ፡፡

መዝሙር ዘሰንበት

ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤
ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ፤
አዕጻዳተ ወይን ጸገዩ፤ ቀንሞስ ፈረየ፤
ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ ፩ እምእሉ።

ዓራራይ

በሰንበት እውራነ መርሐ፤
በሰንበት አጋንንተ አውጽአ፤
እለ ለምጽ አንጽሐ፤
ቃለ ማዕነቅ ተሰምዓ በምድርነ፤
ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት።

ዕዝል

መንክር ግብሩ ለ፩ እግዚአብሔር አብ ዘላዕለ ኲሉ፤
መንክር ግብሩ ለዘሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤
መንክር ግብሩ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤
መንክር ግብሩ ለዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ባሕቲቱ።

ሰላም

ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤
እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤
ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤
ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤
ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤
ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

✥ የዕለቱ የሰንበት መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ (በ፭) ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን ፥
ወፈርዪ ኲሉ ዕፀወ ገዳም ፥ ቀንሞስ ዕቊረ ማየ ልብን ፥
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጎላት ፥
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር። ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ፥ ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር።
እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት ፥
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር፤
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት።

✥ አመላለስ ዘመዝሙር፦

ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ /2/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት። /2/

፠ ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ !፠

ይህን የተወደደ ማኅሌተ ጽጌ አስጀምሮ ላስፈፀመን ለእርሱ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው። ሀገራችንን እና ሕዝቧን ይጠብቅልን።
አሜን!

#ጼጥሮስ
እንኩዋን አደረሰን

"" ነገሠ : ቅዱስ ሚካኤል ነገሠ::
የጠላትን ምክር ፈጥኖ አፈረሠ:: ""

አንተኑ ሚካኤል ለእስራኤል መና ዘአውረድከ::

☞እስራኤልን በበርሃ . . .
❀በደመና የመራህ::
✿መና ያወረድህ::
❀ክንፍህን የጋረድህ::
✿ውሃን ያፈለቅህ::
❀የብርሃን ምሰሶን ያቆምህ . . . ርሕሩሑ መልአክ ሚካኤል አንተ ነህን?!

☞ለኢትዮዽያም እንጂ ረዳት ነህ::

ዛሬም ረድኤትህ ፈጥኖ ይደረግልን
2024/05/22 00:56:35
Back to Top
HTML Embed Code: