#ጪጩ(#ዳግማዊ_ዮርዳኖስ)#ወንዝን _የአለም_ህዝብ _የሚከትምበት _የቱሪስት _መዳረሻ_እናድርግ"

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩኝ በዲላና አካባቢዋ የምትገኙ ክርስቶሳዊያን በ11/05/2016 በዕለተ ጥምቀት ጠዋት ላይ የጥምቀት ስነ ሥርዓቱን የት ተገኝታችሁ ልትጠመቁ አሰባችሁ? እነሆ አንድ ድንቅ ስፍራ ልጠቁማችሁ
ጌታ እንደተጠመቀበት እንደዮርዳኖስ ወንዝ ሁለቱ ወንዞች በሚገናኙበት በጪጩ (ዳግማዊ ዮርዳኖስ) ወንዝ መጥታችሁ ብትጠመቁ ነፍሳችሁ ሀሴት አድርጋት ትመለሳላችሁ።
ለቀጣዩ ደግሞ እግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመናበብ የአለም ህዝብ መጥቶ የሚጎበኝበትና የሚያከብርበት ስፍራ ብናደርገውስ ?ይቻላል አይደል? እንግዲያውስ ማስተዋወቁን ካኑኑ እንጀምር በሉ እንግዲህ ሼር ይደረግ
እንኳን አደረሳችሁ !
ሊ/ዲ/ን መባጽዮን (ኢ/ር )
ዲላ
ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
በኢየሱስ ልደት ወቅት ስጦታ ይዘው የመጡት የሶስቱ ጠቢባን ሰዎች ስም____ነው።
በተስፋ ማጣት እየከሰሙ ላሉ ...

“ሰይጣን ተስፋ የለውም ፣ ግን ተስፋ አይቆርጥም ፤ ሰው ተስፋ አለው ፣ ነገር ግን ተስፋ ይቆርጣል ።” እግዚአብሔርን በሰው ሚዛን ይለካዋል ። ሰዎች አጠገባችን የሉም ማለት እግዚአብሔር ከሰው ጋር አደመ ማለት አይደለም ። እርሱ የራሱ ሚዛን አለው ። በእኛ ላይ ያለውን የራሱን ዓላማ ያያል ። እርሱ አይተወንም ። ሰዎችን ስንለካ ፣ ስንመዝን ፣ ስንመትር መኖር ዋጋ የለውም ። የማይታበል ፍቅር ከእኛ ጋር ነው ። ሊወድቅ ያለውን የሕይወት ምሰሶ እንደገና እናጽናው ። መተው የማያውቀው አምላክ ከእኛ ጋር ነው ። ታሪክ እገሌን ጣለ ብሎ አልጻፈለትም ፣ ክርስቶስ ሰውን መጣል በእኛ አይጀምርምና ተስፋችን ይለምልም።

ምስጋና ለማይተወን ፣ ለማይረሳን በዘላለም ፍቅር ለወደደን አምላክ ይሁን ! አሜን !
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
የሕይወት ሥነ ሥርዓት 6

5-  ጸልይ

ስታገኝም ጸልይ ፣ ባለህ ነገር ትረካለህ ። ስታጣም ጸልይ ተስፋን ይዘህ ትነሣለህ ። ስትስቅ ጸልይ ፣ ሳቅህን እውነተኛ ያደርግልሃል ። ስታለቅስም ጸልይ ፣ ከኀዘን ሸለቆ ያወጣሃል ። ስትወድድ ጸልይ ፣ ያረፈደው ፍቅር ያመሽልሃል ። ስትቀየምም ጸልይ ፣ ልብህን ያጥብልሃል ። በአገርህ ስትሆን ጸልይ ፣ ከወገን ጠላት ይጋርድሃል ፤ በሰው አገር ስትሆንም ጸልይ ፣ ባዕዱን ዘመድ ያደርግልሃል ። ስታሸንፍ ጸልይ ፣ ጋሻህ እግዚአብሔር ይሆናል ። ስትሸነፍም ጸልይ የእንደገና ዕድል ይሰጥሃል ። ስትደፍር ጸልይ ፣ መለኮት ድጋፍ ይሆንሃል ። ስትፈራ ጸልይ ፣ እምነትን ይሰጥሃል ። ሲሳካልህ ጸልይ ፣ የመኸር ደስታ ታገኛለህ ። ሳይሳካም ጸልይ ፣ ፈቃደ እግዚአብሔር ልብህን ያሳርፈዋል ። አስታመህ ሲድንልህ ጸልይ ፣ ፈውስ የእግዚአብሔር ገንዘብ ናትና ። አስታመህ ሲሞትብህም ጸልይ ፣ ሞት ዕረፍት ነውና ። ደግ ንጉሥ ሲነሣ ጸልይ ፣ ደግ ሰው ዘመኑ አጭር ነውና ። ክፉ ንጉሥ ሲነሣም ጸልይ ፣ ለቅጣት ይላካልና ። ስትቀደስ ጸልይ ፣ ከኃጢአት የሚያድን ኢየሱስ ነውና ። ስትቆሽሽም ጸልይ ፣ በደሙ ያጥብሃልና ። ደም በባሕርይው ያቆሽሻል ። የእግዚእ ኢየሱስ ደም ግን አምላካዊ ደም ነውና ያነጻል ። ደም ሲያዩት ያስደነግጣል ፣ የአማኑኤል ደም ግን መሢሐዊ ደም ነውና የተዘጋውን  በር ይከፍታል ።

ተደርጎልህ እንደሆነ የምታመሰግነው በጸሎት ነው ። የሌሎች ጉዳት አስጨንቆህ ከሆነ የምትማልደው በጸሎት ነው ። ኃጢአትህ ከብዶህ ከሆነ ንስሐ የምትገባው በጸሎት ነው ። አጥተህ ከሆነ የምትለምነው በጸሎት ነው ። ጸሎት ለንጉሥ አቤት ማለት ነው ። ጸሎት  ለዳኛ ይግባኝ ማለት ነው ። ጸሎት ለሰጪው ጌታ እጅን መዘርጋት ነው ። ጸሎት ለወዳጅ የፍቅር መልእክት መላክ ነው ። ጸሎት ለተዋጊው ጀግና መንገድ መልቀቅ ነው ። ጸሎት ለቤትህ ራስ ጉድለትህን ነግረህ መተኛት ነው ። ጸሎት ምግበ ሥጋ ፣ ምግበ ነፍስን የምንጠይቅበት ነው ። ጸሎት ወደ ሰማይ መደወያ ቍጥር ነው ። ጸሎት የሃይማኖት መሣሪያ ነው ። ጸሎት ሀልወተ እግዚአብሔርን የምንመሰክርበት ነው ።

ከሕይወት ሥነ ሥርዓት አንዱ መጸለይ ነው ። ስለዚህ አፍ ከልብ ሆነህ ፣ ስፍራና ጊዜ ለይተህ በማለዳና በምሽት ጸልይ ። ከበረታህ በሃያ አራት ሰዓት ሰባት ጊዜ ጸልይ ። ከቤትህ ስትወጣ የመንገድ ጸሎት ፣ ስትመገብ የማዕድ ጸሎት አትርሳ ። ወደ ወዳጅህ ቤት ስትሄድ ፣ ደግሞም ስልክ ስትደውል ጸልይ ። የእግርህ ኮቴ እንዲናፍቀው ያደርጋል ። ወደ ሥራ ስትገባና ሥራህን ስትጀምር ጸልይ ። ሐኪም ሆነህ እንደሆነ ሳትጸልይ በሽተኛ አትንካ ። እውቀቱን የሰጡህ ፈረንጆች ቀዶ ጥገና ከማድረጋቸው በፊት ተንበርክከው ይጸልያሉ ፣ “አንተም በእምነትህ ጸልይ” ብለው በሽተኛውን ይጠይቃሉ ። የአገሬ ሐኪም ሬሳ የምታመርተው ስለማትጸልይ ነው።  ሠራተኞችህ ሊጋጩህ ሲፈልጉ ዘወር ብለህ ጸልይ ፣ ሚስትህ ለግጭት ስትፈልግህ በልብህ ጸልይ ። በማለዳ አፍህን በጸሎት ሳታሟሽ ከሚስትህም ጋር ቢሆን አትነጋገር ። ላንተ ማንጋት አልረሳምና በማለዳ ተነሥተህ አመስግን ። ታርፍ ዘንድ ላንተ ማስመሸት አልረሳምና ሲመሽ ጸልይ ። በመንገድ ስትሄድ ፣ ብቻህን ስትሆን ፣ ወደ መታጠቢያ ሄት ስትገባ ፣ ገላህን ስትታጠብ ጸልይ ። ከጸሎት ሁሉ አውራው “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ - አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን” የሚለው ነው ። ያለማቋረጥ ይህን ጸሎት ጸልይ ። ፈተናና ትግሉ ሲበዛ መዝሙር 22ን እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚለውን ደጋግመህ ጸልይ ። ደግሞም ጸሎተ ማርያምን ታዐብዮ ነፍስዬን- ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች የሚለውን ደጋግመህ ጸልይ (ሉቃ. 1፡47-55)። የመቍጠሪያ ጸሎት እጅግ ጠቃሚ ነው ። ከመዝሙረ ዳዊትም በጸሎትህ ደባልቅበት ። የልብህን ሙቀት ለጌታህ አፍስስለት ።

የግል ጸሎት ፣ የቤተሰብ ጸሎት ፣ የማኅበር ጸሎት እንዳለ አስታውስ ። የአጋንንት ፍላጻ ሲበዛ መዝሙር 90ን ደጋግመህ ጸልይ ። “በልዑል መጠጊያ የሚኖር…” የሚለውን ማለቴ ነው ። አባቶችህ ስታገኝ ጸሎት ተቀበል ። አንተም ትባረካለህ ፣ እነርሱንም ታተጋለህ ። በማለዳ ጸሎትህ ላይ ውኃ በብርጭቆ አድርገህ ጸልይ ። ራስህንና ቤተሰብህን በተባረከው ውኃ ቀድስ ። ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ስላገኘህም ጸልይ ። የሚፈልጉትን የማያውቁና የሚፈልጉትን ያጡ በዓለም ላይ አሉ ። የሚያድናቸው ጸሎት ብቻ ነው ። ወደ ወዳጅህ ቤት ስትገባ ሳትቀመጥ ጸሎት አድርሱ ። ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትገባ ሳትቀመጥ ጸሎት አድርስ ። ወደ ጉባዔ ስትሄድ በቃሉ እንዲናገርህ ጸሎት አድርስ ። በታላቅ መከራ ውስጥ ስትሆን ዝም ብለህ ጸልይ ። ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ ጸልዮአልና ። ጸሎት ለሥጋዊ ጤና ፣ ለአእምሮ መታደስ ፣ ለመንፈስ እረፍት ወሳኝ ነውና ጸልይ ። እባክህ ጸልይ ።
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሕማማቱ ወቅት ሊሰማ የሚገባ ዝማሬ ሙሉውን በ @Meba_tube ላይ ታገኙታላችሁ
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ስለሁሉ ሞተ ሲባል ቀላል እንዳይመስለን ! "
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
+++ ክርስቶሳዊያን ደስ ይበለን !+++

ባሕር ተከፈለ በአማናዊው ሙሴ በክርስቶስ ሞት የጀርባ ታሪክ ሆነ ። ልጆቻችንን የበላ ፣ በውዶቻችን ደም ጡብ የሠራ ፣ ኖረንለት የገደለን ፈርዖን ዲያብሎስ ድል ተነሣ ። ላንገናኝ ከሰይጣን ተለያየን ። በሕልማችን እንዳያውከን የፈርዖን ሬሳ በቀይ ባሕር ታየን ። እባቡ እንዳያስደነግጠን ራሱ ተቀጠቀጠልን ። በደምመላሽ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በጠላት ራስ ላይ ቆመን ዘመርን ። የወይራው ቀንበጥ መንፈስ ቅዱስ መዳናችንን አረጋገጠልን ። እውነትን በእውነት ተቀበልን ። መንፈሱ ለመንፈሳችን መሰከረልን ። ስለነገሩን ሳይሆን ስለተሰማን በእውነት በእርሱ ዐረፍን ። ባሕር ተከፈለ ሰዎች ደስ ይበለን !!!

@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ክርስቶሳዊያን !

"በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ የተሰበሰቡ ደቀ መዛሙርት ወዳሉበትም ገባ "ሥ/ቅ 18:38

ከመገኘቱ የማንለይበት መልካም በዓል ይሁንልን !

@Yahiwenesei
ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው !

(የወጣት አገልጋይ ፈተና)

ዲያቆን ማለት የዋህ ፣ ትሑት ፣ የልጅ አዋቂ ፣ ክንፉ የቀለለው ፣ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት “ወዴት?” ባይ ፣ የመለኮት ልዑክ ፣ የመላእክት አምሳል ፣ የካህኑ የመቅደስ ልጅ ፣ ማዕረግ ያለው ተላላኪ ፣ እውቀት ያለው እውቀት ፈላጊ ፣ የሕፃን ምሥጢረኛ ፣ የጳጳስ ምርኩዝ ፣ የኤጲስ ቆጶስ ሰነድ ጠባቂ ፣ በንጹሕ ልብ እግዚአብሔርን አምላኪ ፣ ድንግል ፣ ቤተ ክርስቲያን እናቱ የሆነች ፣ እናትን በእናት የለወጠ ፣ የምሥጢራት አገልጋይ ፣ የቤቴል በር ከፋች ፣ ቢያዜም የሚያምርበት ፣ ቢስቅ የሚያስደንቅ ፣ ቢናገር የሚኮላተፍ አፈ ማር ፣ የገባሬ ሠናዩ ቄስ አዋጅ ነጋሪ ፣ ሰግዶ የሚያሰግድ ፣ የሊቁ አዳሪ ተማሪ ፣ የነገው ቄስ ፣ የነገው መነኰስ ፣ የነገው ጳጳስ ፣ ሁሉ የሚወደው ፣ ለመማር ማልዶ የወጣ ፣ አእይንተ እግዚአብሔር ካህናት የሚጠነቀቁለት ፣ ብዙ መካሪ ያለው ፣ የሚገሥጹት ልጅ ፣ የሚገርፉት ሹም ፣ በዓይን በጆሮ የሚማር ፣ የልብ አውቃ ፣ የወንጌል አክባሪ ፣ ዘመኑን ያተረፈ ፣ የአዲስ ኪዳን ነቢይ ሳሙኤል ፣ የዓመተ ምሕረት ነቢይ ኤርምያስ ፣ ታናሽነቱ የማይናቅ ፣ መሥዋዕት ቀማሚ ፣ በዕርፈ መስቀል ደመ ኢየሱስን አቀባይ ፣ የሥልጣን መሠረት ፣ ዕደግ ተብሎ የሚመረቅ ፣ ቢረግጡት ምንጣፍ ፣ ቢደገፉት መከዳ የሆነ ፣ እያፈረ የሚቀድስ ፣ እየፈራ የሚያስተምር ፣ የትምህርት ሱሰኛ ፣ በልጅነት የዘመተ ፣ የአባቱን ቤት ለጽድቅ የመነነ ፤ የእናቱን ጓዳ በልመና እንጀራ የለወጠ ፣ ተንቀሳቃሽ ተማሪ ፣ የብሉይ ጓደኛ ፣ የሐዲስ መሽራ ነው።

ዲያቆንን የማይወድ ማን አለ ? እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ይወደዋል ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። የልጅነት ጨዋታን ለጌታው የሠዋ ፣ ከአብሮ አደጎቹ ይልቅ በዕድሜ የገፉትን አባቶች የመረጠ ፣ በየዕለቱ በአበው የሚመረቅ ፣ የየዋሃን የጸሎተኞች ቱፍታ ያረፈበት ነው ። ዲያቆን ቢያዜም ያምርበታል ፣ አንድ ልብ ነውና የኑሮ ሸክም አልመጣበትምና እውቀት ይጠልቅበታል ። የቄስ ፣ የጳጳስ ፣ የፓትርያርክ መሠረት ነው ። ሁሉም ዲያቆን ጳጳስ አይሆንም ፣ ሁሉም ጳጳስ ግን ዲያቆን ነበረ ። ዲቁናን ሁሉ ሊያከብረው ይገባል ። ዲያቆናት ሠልጣኝ ወታደር ፣ ተማሪ ደቀ መዛሙርት ፣ ወራሽ  ልጆች ናቸው ። የነገዋ ቤተ ክርስቲያን በዛሬዎቹ ዲያቆናት ትታያለች ። ዲያቆናት አበባ ናቸውና እንክብካቤ ይፈልጋሉ ፤ የከተማ መናኝ ናቸውና ጥበቃ ይሻሉ፣ ቆብ አልባ መነኮስ ናቸውና ከሴት ርቀው ንጽሕ ጠብቀው መኖር ይገባቸዋል ። ዲቁና መሠረት ነውና መሠረቱ የጸና መሆን አለበት ። ዲቁና ከተበላሸ ሁሉም ነገር እየተበላሸ ይመጣል።

ዲያቆናት ጭምት መሆን አለባቸው ። እኮ  ጭምት ማለት ምን ማለት ነው ? ጭምት ማለት ጣፋጭ ዝምታ ፣ ጣፋጭ ዝግታ ፣ ጣፋጭ ዕይታ ያለው ማለት ነው ። ጭምት ዱዳ አይደለም፣ ጭምት ለፍላፊ አይደለም ፤ ጭምት በቦታው ተገቢ ነገርን የሚናገር ነው ። የበደለ ሲያይ “የእኔን መጨረሻ አሳምርልኝ” ብሎ እያለቀስ የሚመክር ነው ። ድምፁ  እንደ አዋጅ ድምፅ አይደለም ። ያልሰማህ ስማ ፣ የሰማህን ላልሰማ አሰማ አይልም ። ዲያቆን የበላዩም የበታቹም ሲሳሳት በጭምትነት ይጸልያል ፣ በወዳጅነት ይመክራል። የቤተ ልሔም ምሥጢር ጠባቂ ነው ። የቤተ ልሔም ድንግል ሁሉን ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር ። ዲያቆንም ብዙ የማይደነቅ ፣ ብዙ የማይደነግጥ ነው ። ጭምት ለነገው የሚያስብ ፣ መጨረሻው እንዲያምር የሚጸልይ ነው ። ጭምት የሁል ጊዜ ተማሪ ነው ። ጆሮው እንደ ዝኆን ጆሮ ሁሉን የሚያደምጥ ፣ መልካሙን የሚቀበል ነው ። ጭምት ጊዜ ሰጠኝ ብሎ ማንንም ድጦ የማያልፍ ነው ። ጭምት ባይርበውም ለራበው ያዝናል። ራሱን ብቻ ሳይሆን ዙሪያውን ያያል።

ዲያቆን የሚያሰክር መጠጥ  አይጠጣም ። እንደ ውኃ እናት ከውኃ አይለይም ፣ ከውኃ ውጭ አይደፍርም ። አለልክ መብላትም የመስከር ያህል ነው ። ዲያቆን መጥኖ የሚበላ ፣ በምግብ ብዛት ዕድሜውን የማይጐዳ ነው ። ዲያቆን ከብዙ ሴቶች ጋር ወዳጅ የሚሆን ፣ የቆነጃጅት አጃቢና አጫዋች አይደለም ። መፍራት ገደሉን ሳይሆን የሚያዳልጠውን ስፍራ ነው ። አርቆ ማጠር የዲያቆን መገለጫ ነው ። አንድ ዲያቆን እውቀት ፣ ምሥጢር ጠባቂነት ፣ ጠንቃቃነት ያስፈልገዋል ። እንደ ወታደር የሚዘምት ፣ እንደ ሰላይ ለቤተ ክርስቲያት ጆሮ የሆነ ነው ። መጠጥና ሴት የሚወድድ ወታደርም ደኅንነትም መሆን አይችሉም ። ሁለቱም ጎበዙን ሁሉ ወንፊት ያደርጉታልና ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። ብሉይ ሐዲስን ነገር መለኮትን ላላወቀ አይሰጥም ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። ምእመናን ሊያከብሩት ይገባል ። ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ዲያቆን ነበረ ። የቤተ ክርስቲያን አባት ለመባል ሦስት ነገሮች ያስፈልጋሉ፡-

1-  ክህነት ያለው ፣
2-  ኢአማንያንን አሳምኖ የመለሰ ፣
3-  መንፈሳዊ መጻሕፍትን የጻፈ መሆን አለበት ። ዲያቆን ሆነው የቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አሉ ። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ዲያቆን ቢሆንም የቤተ ክርስቲያን አባት ነው ። ዲያቆናት አባት ሊሆኑ ይችላሉ ።

አዎ መስፈርት ያስፈልጋል ። የቃል ትምህርትና ዜማ ብቻ መስፈርት አይሆንም ። ዲያቆን የሚያነበውን መተርጎም ፣ የተረጎመውን መኖር ያስፈልገዋል ። እኔ ጢሞቴዎስ ወደፊት መስፈርት የሌለው ዘመን እንደሚመጣ ፣ ከአላውያን ነገሥታት ይልቅ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶችዋ አገልጋዮች ይሆናሉ ። የቄስ ክብር ፣ አጥሩ ዲያቆን ነው ። የካህኑ ልጅ ነውና ሊያለብሰው ፣ ሊያበላው ፣ ሊያስከትለው ፣ ሊያሰለጥነው ይገባል ።

👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
Forwarded from Sinekneshe Wolde
ድንቅ ዝማሬ በዘማርት ስንቅነሽ ወልዴ....ወንታካ ምናድ
https://youtube.com/watch?v=TcnSmZsdJb0&feature=shared
ዘመኗን በሙሉ በቤተ እግዚአብሔር በዝማሬ ስታገለግል ኖራለች። በአገልግሎትም በእድሜም አሁን በዲላና አካባቢው ለምንገኝ የዝማሬ አገልጋዮች ቀዳሚት አገልጋይ ናት።
ገጠር ከተማ ሳትል ታገለግላለች በተለይም ገጠር አካባቢ ስትጠራ በደስታ ሄዳ ታገለግላለች የሚገርመው "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" እንዲል ቅዱስ ቃሉ የጎደሉ ንዋዬ ቅድሳትን ገዝታ በማሟላት ለብዙ አገልጋዮች አርአያ የምትሆን አገልጋይ ናት።
ለሰ/ት/ቤት ያላት ፍቅር ልዩ ነውና የዜማ ዕቃዎችን በብዙ አድባራት ገዝታ አበርክታለች። ታላቋ እህታችን ዘማሪት በረከት ደግፌ።
እነሆ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር እረድቷት በቤተክርስትያናችን ሥርዓትና አስተምህሮ መሰረት ያዘጋጀችውን የዝማሬ አልበም የፊታችን እሁድ ሰኔ 9/2016 ዓ/ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌ/ኮ/ቡ ሀ/ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሌሎችም የሀ/ስብከታችን ሰራተኞች በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደ/ሰ/ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ ስ/ወ/አዳራሽ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በልዩ ድምቀት ልታስመርቅ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች ስለሆነም የተዋህዶ ልጆች በስፍራው ተገኝተን በዝማሬ አምላካችንን እናከብር ዘንድ ኑ ብላናለች ስለሆነም ይህ መልዕክት የደረሰን ሁሉ የጥሪ ካርድ አንጠብቅ በዕለቱ ተገኝተን በብፁዕ አባታችን ቡራኬ ፣ በዝማሬውም እየተባረክን እህታችንን እናበረታታ።
ለዚያ ዕለት ያድርሰን !
ለብዙዎች ሼር በማድረግ የእህታችንን አገልግሎት እናግዝ ....
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ዘመኗን በሙሉ በቤተ እግዚአብሔር በዝማሬ ስታገለግል ኖራለች። በአገልግሎትም በእድሜም አሁን በዲላና አካባቢው ለምንገኝ የዝማሬ አገልጋዮች ቀዳሚት አገልጋይ ናት።
ገጠር ከተማ ሳትል ታገለግላለች በተለይም ገጠር አካባቢ ስትጠራ በደስታ ሄዳ ታገለግላለች የሚገርመው "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" እንዲል ቅዱስ ቃሉ የጎደሉ ንዋዬ ቅድሳትን ገዝታ በማሟላት ለብዙ አገልጋዮች አርአያ የምትሆን አገልጋይ ናት።
ለሰ/ት/ቤት ያላት ፍቅር ልዩ ነውና የዜማ ዕቃዎችን በብዙ አድባራት ገዝታ አበርክታለች። ታላቋ እህታችን ዘማሪት በረከት ደግፌ።
እነሆ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር እረድቷት በቤተክርስትያናችን ሥርዓትና አስተምህሮ መሰረት ያዘጋጀችውን የዝማሬ አልበም የፊታችን እሁድ ሰኔ 9/2016 ዓ/ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌ/ኮ/ቡ ሀ/ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሌሎችም የሀ/ስብከታችን ሰራተኞች በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደ/ሰ/ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ ስ/ወ/አዳራሽ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በልዩ ድምቀት ልታስመርቅ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች ስለሆነም የተዋህዶ ልጆች በስፍራው ተገኝተን በዝማሬ አምላካችንን እናከብር ዘንድ ኑ ብላናለች ስለሆነም ይህ መልዕክት የደረሰን ሁሉ የጥሪ ካርድ አንጠብቅ በዕለቱ ተገኝተን በብፁዕ አባታችን ቡራኬ ፣ በዝማሬውም እየተባረክን እህታችንን እናበረታታ።
ለዚያ ዕለት ያድርሰን !
ለብዙዎች ሼር በማድረግ የእህታችንን አገልግሎት እናግዝ ....
👇👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
2024/06/16 15:44:53
Back to Top
HTML Embed Code: