ከሁሉም የተሻልኩ አልሆን ይሆናል ግን ከሌሎቹ ይልቅ በተሻለ እወዳለሁ፡፡ ይቅርታ አድርግልኝ እናም እንደገና የአንተ ልሁን፡፡

✈️ Like_and_Share_🌐
@yefikrclinic
✒️የተከዳው የወፍጮ ቤት ሰራተኛ የጻፈው ደብዳቤ✉️

አንቺ ከረጢት ቢገባሽ አንድ መቶ ኪሎ ብልሹ ባህሪሽን ችዬ ነበር ያኖርኩሽ

የሰጠሽኝ ፍቅር አምስት ኪሎ አይሞላም ነበር ፡ልቤን ዱቄት አድርገሽው ስትሄጂ ትንሽ አታፍሪም??

የሰራሁልሽን ሁሉ ውለታ ፍጭት ታደርጊዋለሽ?? ጥፋተኛው እኔ ነኝ ልመዝንሽ ይገባ ነበር፡ ፍቅርሽ ሽርክት መሆኑን ማወቅ ነበረብኝ በበርበሬ ወፍጮ ከተሽ አነደድሽኝ

ሰፌዱ ልቤ አመልሽን ማበጠር ነበረበት አንቺ ወንፊት አድርገሽኝ ብትሄጂም የምታበረታኝ ሴት አላጣም፡ እመኚኝ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ጓያ እሆናለው እጠነክራለሁ

እንደ ጤፍ የበዛ ብዙ ኩንታል ፍቅር እንደማገኝ አትዘንጊ

ደሞ ገብስ ገብሱን ነዉ የፃፍኩልሽ
፡ አንቺ ሽንብራ 😂😂😂😂

ከተመቻቹ ÷
𝐋𝐢𝐤𝐞
𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭

          @yefikrclinic
🔹🔻🔹🔻🔹🔻🔹🔻🔹🔻🔹🔻
           😑የአንደበቴ መዝጊያ 😑

አልጋዬ ላይ ሁኜ ስለ አንች እያሰብኩ
የፍቅሬን መግለጫ ቃላት እዬመረጥኩ
በፍቅር ውቅያኖስ ገብቼ እየዋኜሁ
ብዙ ተፈላሰፍኩ በዝምታ ሰመጥኩ
የፍቅሬን መግለጫ ቃላትን አመረትኩ

አሁን አንችን ማግኘት መንገር ብቻ ቀረኝ
ልነግርሽ ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩኝ
የምትወጭበትን ሰአቱን አስልቼ
የምትገኝበት ቦታውን ገምቼ
ፍቅሬን ልገልፅልሽ ልነግርሽ መጣሁኝ

ደምሬ ቀንሸ ሒሳቤን ሰርቼ
በቅቤ ምላሴ ቁልፉን አላልቼ
ሳልሰብረው ልገባ ልብሽን ከፍቼ
ልክ እንዳገኘሁሽ እንደመጣሽልኝ
ልናገር ፈልጌ ቃላቶቹ ጠፉኝ

ብን ብሎ ጠፋ እንደ ወፍ በረረ
የአልጋ ላይ ሀሳቤ ቅዠት ሁኖ ቀረ
ገና አይንሽን ሳዬው መርበትበት ጀመርኩኝ
አንዳች ቃል መተንፈስ መናገር አቃተኝ
የአንደበቴ መዝጊያ ቁልፍ ሁነሽብኝ ።
🤍ያገኘሁሽ ለታ


እውን ይሆንና  የሌሊቱ አባዜ
እንገናኛለን አታብዥ ትካዜ


ያገኘሁሽ ለታ
ፍቅር እንሰራለን ያልታዬ ጠብታ
ፀሀይ ትደምቃለች በተለይ ሁኔታ
አለም ታወራለች ፍቅራችን በተርታ

ያገኘሁሽ ለታ
አለቀ ደቀቀ ነገር ማዟዟሩ
ናፍቆትም ይረታል በአንድ ቤት ሲኖሩ
ሀ...ብለን እንጀምር ፍቅርን ከ ጅምሩ

       🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋

      ‌‌‌‌‌‌‌  ይ 🀄️🀄️ሉን! ➢

ሼር  💚
@yefikrclinic
አለሁላት…!


#በአሌክስ_አብርሃም


እናቴ ሁልጊዜ ሁለት እጆቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ እግዜርን እንዲህ ትለዋለች፣
“አብርሽዬ የሚያገባትን ሴት ሳታሳየኝ እንዳትገለኝ፡፡


አገባሁ !
እናቴ እለት እጆቿን ወደ ሰማይ ዘርግታ እግዜርን እንዲህ አለችው፣

“ምነው ይሄንንስ ከሚያሳየኝ በገደለኝ

ሀና ምንተስኖት ትባላለች የምኮራባት ሚስቴ፡፡ እወዳታለሁ፣ አፈቅራታለሁ፡፡ ክፉ ነገር በሰፈሯ
እንዲያልፍ አልፈልግም፡፡ ሀኒዬ የእኔ ጥሩ ሱስ፣ ካላየኋት ያዛጋኛል' ስል ሰዎች አያምኑኝም፤ ሀኒ
የእኔ ልብ፣ የጠላችው ጠላቴ ነው:: ይሄ አባማ የሚባል ሰውዬ በቴሌቪዥን ያደረገው ንግግር
አስጠላኝ ብትለኝ፣ ሲ አይ ኤን ሳልፈራ፣ ኤፍ.ቢ.አይን ከቁብም ሳልቆጥረው ኦሳማ ላይ የግድያ
ሙከራ ባደርግ ደስታዬ ነው:: እንቅ አድርጌ አይኑን አፍጥጦ፣ “ኧረ አብርሽ በእናትህ የዛሬን
ማረኝ..ሁለተኛ በየትኛውም ሚዲያ ከመቅረቤ በፊት ንግግሬን ለሀና ምንተስኖት ኣሳውቃታለሁ..
ካልፈቀደችልኝ ኣላደርጎውም” ቢለኝ አልምረውም፡፡ እማምላክን አልምረውም !!

ሀናዬ የነብሴ ፍራሽ…ላያት ድሎቴ ናት። ሀና ካዘዘችኝ…አቤት ፍጥነቴ ገና ልትናገር ስትጀምር እኔ ሮጫለሁ፡፡ አልጋ ላይ ጋደም ብላ ቴሌቪዥን እያየች እኔ ቆንጆ ቡና እያፈላሁላት…የሆነ ነገር ብትፈልግል ልትናገር ስትጀምረው ነገሩን አምጥቼዋለሁ ፡፡ ለምን ትጨርሰዋለች.…ቃሏ ፍቅር
ነው..ፊደሎቾ እንደ ረሀብ ቀን እህል ያሳሱኛል፡፡

“አብርሽ " ስትለኝ በቦታህ!' እንዳሉት ሯጭ እዘጋጃለሁ፡፡ ወደ መሻቷ ተፈትልኮ በምድር
ላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ የሚሰቶቻቸውን ፍላጎት ካሟሉበት ሰዓት የተሻለውን ለማስመዝገብ፡፡
"ድ." ብላ ስትጀምር ፈትለክ ብዬ ድስት…ድራፍት…ድንች ድልህ...ድፍድፍ (ከእማማ ፈጠኑ ቤት ድመት...ድንጋይ..ድራማ (ሲዲ) ይዤላት እያለከለኩ ከተፍ ስል፣ "ውይ አብርሽዬ…በቲቪ ድብ አይቼ ድቡን እየው ልልህ ነበር እኮ" ትለኛለች በፍቅር ዐይን እያየችኝ...!! አይከፋኝም ለምን እከፋለሁ፡፡ እንደገና ድብ ባየችና “ድ ብላ ስትጀምር፣ አሁን ባመጣኋቸው ነገሮች ላይ
ድብ ጨምሬ ባመጣሁላት..የእኔ ሀኒ መክሊት ብያታለሁ፡፡ እሷ ናት ቀኝም ግራም ጎኔ፡፡

ሀኒዬን እናቴ አትወዳትም፡፡ “አንዳች አስነክታው ነው ልጄን እቺ የሰው ጉድ” ትላታለች፡፡
አባቴ ገና ሲያያት የእናቱ፣ የአባቱ፣ የሁለት እህቶቹ  ገዳይ ነው የምትመስለው አቤት ሲጠላት፡፡ በወሬ ወሬ “መንገድ ላይ አብረሃም እና... ሲሉት፣ "በቃ " ብሎ ይጮሀል።አብርሃም ካላችሁ አይበቃም….እናን ምን አመጣው?” ይላል፡፡ ያውቃል ማንም ጋር እንደማልታይ፤
ሀኒ ጋር ነኝ ቤት ውስጥ  የምትበላውን እየሰራሁላት፡፡ ሀኒ ጋር ነኝ መንገድ ላይ ቦርሳዋን ይዤላት፤….ዣንጥላዋን ይዤላት ዕቃ ከገዛን አስቤዛም ቢሆን እኔ ይዣላት ሀኒ ጋር ነኝ የትም!!

ሀኒን እህቴ አትወዳትም፡፡ ከዘመናዊ ጓደኞቿ ጋር ሆና ከሩቅ ካየችኝ በሬ እንዳሯሯጠው ሰው መንገድ አሳብራ የጓደኞቿን እጅ እየጎተተች ትሸሻለች፡፡ “ወንድሜ በሬ አገባ” እያለች ነው የምታወራው አሉ!

ወንድሜ ሀናን አይወዳትም፡፡
"ለስንት ስንጠብቅህ እዚሂች አዚፋ ጋር ትወዘፋለህ” ይለኛል፡
&አዚፋ' ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ግዴለም ሀኒዬ 'አዚፋ ከሆነች፣ አዚፉ ይባረክ ! ስድብ ሰውን ካረከሰው፡ ሰው ስድቡን ስለምን አያከብረውም? ሀኒዬ አዚፉን አከበረች… እወዳታለሁ፡፡

ሀኒ ቆንጆ አይደለችም፡፡ የኔ ቆንጆ፣ ቆንጆ አይደለችም፡፡ "ኪንኪ ፀጉሯ ጠዋት ስትነሳ ያስፈራል”
ይላሉ፣ አዎ እውነት ነው፡፡ “አፍንጫዋ በአይኗና ቀላይኛው ከንፈሯ መካከል ያለ ሁለት የሽንቁር ነጥብ ነው እያሉ ያሟታል…እውነት ነው !!

ከንፈሯ ወጣ ወጣ ባሉ ጥርሶቿ (ገጣጣ ነው እነሱ የሚሉት) ከርስቱ ተገፍቷል፡፡ በዛ ላይ
ብትስቅ ዞሮ ማጅራቷ ላይ ይዘያየራል ይላሉ፡፡ አዎ እውነት ነው !!

የጣቶቿ መዶልዶም ከዘጠኝ ዓመቷ እስከ አስራ ዘጠኝ ዓመቷ 10000000000000000000
ኩንታል ገብስ ሳታቋርጥ የወቀጠች ያስመስላታል" ቢሉም (ተጋነነ እንጂ) እውነት ነው !!

“እግሯ ከየትኛውም ጫማ እንዲጣላ ተደርጎ ነው የተፈጠረው” ያሉትም አልዋሹም፡፡

lዚህ ሁሉ መናቅ፣ በዚህ ሁሉ መገፋት ተገፍታ እኔ የምባል ጥግ ላይ ደረሰች የሀኒ ዓለም
መጨረሻ፡፡የት ትሂድላቸው? አለሁላት ወንድሟ ነኝ:: ፍቅረኛዋ ነኝ፡፡ባሏም ነኝ!! አላፍርባትም፡፡
ኮራባታለሁ !! ሀኒዬ የኔ ናት:: ማነው እኔን አልፎ የሚዘልፉት ወንድ ?' የኤሌክትሪክ አጥሯ
ጠባቂ ውሻዋ ነኝ፡፡ ከእግሯ ስር የማልጠፋ::ባለቤቱ ያላከበረው አሞሌ፡ ወላ መልኩ ወላ
ዘመናዊነቱ አያስከብረውም፡፡ አንዱ የወረወራቸው አይደሉ ሌላኛው መኪና ላይ የሚኮፈሱት!
የተናቁ አሞሌዎች !! ሀኒዬን አከብራታለሁ !! እግዜር ያውቃል ልቤን !!

“ጥርስሽ አያምርም ቢሏት ከሳቅ ተጣላችላቸው፡፡ ሰው ፊት አትስቅም ሀኒ፡፡ የመጻፍ መብታችን፣የመሰለፍ መብታችን ተነካ የሚሉ የአገሬ ልጆች፣ የህኒዩን የመሳቅ መብት በአደባባይ ነጠነቁ፡፡እስካሁን ሻይ ቡና ለማላት ካፍቴሪያ መግባት ያስፈራታል፡፡ ራሷ ቤት ውስጥ ስትቀመጥ እንኳን እግሮቿን ሶፋ ስር ልትደብቅ ይከጅላታል፡፡ በመንገድ ዳር ዘለፋ መሳቀቅን ሸልመዋታል፡፡ ሰው ለሰላምታ ስትጨብጥ ትሳቀቃለች፡፡ የመዳፏን ሻካራነት በየጭብጡ የሚጮኸ አዋጅ አድርገው
ልቧ ውስጥ ተክለውባት፡፡

ሆኒዩን ቆንጆ ካልሆንሽ ሰው ከመሆን መንበር ተንኮታኩተሻል” ብለዋታልና ቆንጆዎች አምላክ
ይመስሏታል፡፡ የሴት ልጅ የክብር ጥጉ በየሆቴሉ ወንበር ተጎትቶላት መቀመጧ ነውን ? በአደባባይ
መታቀፍስ የፍቅር ኦሜጋ ሆኖ የታወጀው መቼ ነው ? እየተውረገረጉ የወንድ ጭብጨባ
ያደነቆራቸው ሀኒዬን ቃል ሳያወጡ በድርጊት ቀበሯት፡፡

አነሆ ለአንዲት ደሀ.ለአንዲት መልከ ጥፉ ደሀ ተልኬ የምታስተናግድበት ተራ ሻይ ቤት ተከሰትኩ፡ ያውም 'አዩኝ' ብሎ የሚቆሽሽ ነጭ ሸሚዝ ባማረ ጂንስ ሱሪ ለብሼ፣ ጥቁር መነፅሬን  ሰክቼ እየተቆነንኩ በረንዳው ላይ ካሉት ወንበሮች በአንዱ ላይ ሰፈርኩ፡፡

“ምን ልታዘዝ!” አለች ሀኒዬ እየተሸቆጠቆጠች፡፡ ሳያት ላማትብ ቃጥቶኝ ነበር፡፡ እግዜር ሰውን
የት ድረስ ውብ እንደሚያደርግ አውቃለሁ፡፡ የት ድረስ መልከ ጥፉ አድርጎ እንደሚፈጥር እነሆ
የእጁን ውጤት ፊቴ አቁሞ አሳየኝ፡፡ “አቤት ችሎታው ምን ይሳነዋል!” አልኩ ::

ስራዬ በዛው ግድም ነበርና ደጋግሜ ሳያት ከቀን ወደቀን እየባሰ የሚሄድ ይሄ ጎደለው የማይባል ፍፁም የሆነ አስቀያሚነት እንዳሸከማት እየተገረምኩ ታዘብኩ፡፡ ግና የገረመኝ፣ “አቤት ስታስጠላ
እያልኩ ላያት መፈለጌ  ደንበኛ ሆንኩ፡፡

“ምን ልታዘዝ?"

"ቡና"

"ምን ላምጣልህ?"

“ቡና”

“ሰላም! ምን ላምጣልህ?”

“ቡና”

“ቡና ነው ዛሬም” (ፈገግ ለማለት እየሞከረች)

"አዎ" (በፈገግታ)

ከዛ ሳላዛት ቡና አመጣችልኝ…ቡና..ቡና….ቡና.…ሰላምታ ሀና ነው ስሟ፣ አንድ ቀን ጠየቅኳት…
ነገረችኝ፡፡ ስራ ከሌላት አጠገቤ ትመጣለች እናወራለን…እንዴት ደስ እንደምትል፡፡ ትልልቅ ጡቶቿን አልፎ ልቧ ይታያል ንጹህ ነው !

አንድ ቀን ከጎኔ የተቀመጡ ተስተናጋጆች "የሰው ጅብ” ሲሏት ጆሮዬ ጥልቅ አለ  ያዘዝነው ዘገየብን ብለው !! በመሰደቧ ሳይሆን እኔ ፊት በመሰደቧ
በመሰደቧ የቅስሟ መስተዋት
ክፍት አፍ በወረወረው የዘለፉ ጠጠር ሲንኮታኮት ፊቷ ላይ እንዴት አንጀት የሚበላ መሳቀቅ አየሁ፡፡ ተሳዳቢዎቹ ጋር
የነበረች አንዲት ሴትም ላንቃዋ እስኪላቀቅ ሳቀች፡፡ አዘንኩ፡፡ ለምን አዘንኩ  እኔንጃ !!
@yefikrclinic
ተይኝ
.
.
ጥሩንባ እያስነፍሽ ድረስልኝ ያልሽው
በእንባሽ እያጣቀሽ አርቅቀሽ የፃፍሽው

መልዕክትሽ ደርሶኛል
ህመምሽም ታውቆኛል

ግና ተይኝ ጦቢያ
ተይኝ እናት አለም

የታመመብኝን ቅዠት ህልሜን ላክም
ያስለማመድሽኝ የጅልነት አለም
ልቃርመው ልታደም
.
.

አንቺ እንደው አንቺ ነሽ
ዘመን እና ጊዜ
የማይለዋውጥሽ የማይቀያይርሽ
ያለፍሻቸው ስህተት
እርምት የማይሰጥሽ!!!

እስቲ ዞር ብለሽ ተመልከች ጥፍትሽን
ድንገት የኔ ምክንያት ይገባሽ እንደሆን

የተነካሽ እንደሁ አለሁልሽ ብሎ
ንግሥናዬን ሳይል ነፍጡን አንጠልጥሎ
በተጋደለልሽ በተዋደቀልሽ
በያዘው መሰሪያ አፈ-ሙዝ አዙረሽ
በመረረ ክፍት ጥይትን ያስጠጣሽ!!!

ስምሽ እንዳይጠፋ ክብርሽ እንዳይረክስ
ልጆችሽን ገሎ ጅበቲው እንዳይነግስ
ዘብ ሆኖሽ የቆመው

አይሆኑት አቀጣጥ
ሊወርሽ የመጣን
ጠላትሽን የቀጣው፥
ዛሬን እንድትቆሚ
ደፍ ቀና ያለው፥
ልጆችሽን ሰብስቦ
አንድነት ያመጣው

አዎ እሱ ጀግናሽ
ያላንዳች ድርድር፥ መከበር ሲገባው

አንቺ ግን ጅላጅል ቅጥ አንባሩ የጠፋሽ
በሐሰት ንግርትሽ ነብሱን ፋታ የነሳሽ!!!

ሞትሽን ከሚሹ
በዱር እና ገደል እየተዋደቀ
ከእልፍ ገዳዮችሽ እየተናነቀ
ሊገዛሽ የመጣን እያንቦቀቦቀ
'ካገር ላስለቀቀ
ለዛ ጀግና ልጅሽ
እስቲ ልጠይቅሽ
ምን ነበር ምላስሽ??
ባደባባይ መሐል
በገመድ ከመስቀል
ከማንጠልጠል በቀር!!

ይኸው ዛሬም ድረስ
እሚሳሳልሽን አስበልጦ ከራስ

ከፊሉን እያደንሽ ዘብጥያ ስትከቺው
ከፊሉን ከባህር ገፋፍተሽ ስዘፍቂው
የቀረውን ደሞ
ለያዘሽ ጋንኤል ጥሙን ልታረኪው
አንገት እየሰየፍሽ ደሙን ስታጎርፊው

አትኩሬ እያየሁሽ
ቆሜ እየታዘብኩሽ

አትላኪብኝ ቀስቃሽ ይዞ መልዕክት አድራሽ
ከእሽታዬ አጣምሮ ነብስ ይዞ ተመላሽ!!

ባይገባሽ ነው እንጂ
የተረትሽው ተረት
ያወራሽው ንግርት
ጠሪ መች ያነቃል
አውቀው የተኙ 'ለት!!!

ተይኝ እናት አለም
ልተኛ ልጋደም
ህልሞቼን ላስታምም
ቅዠቶቼን ላክም

ያስለማመድሽኝን የጅልነት አለም
ልቃርመው ልታደም!!!

ተይኝ በቃ ተይኝ
እስክትቀየሪ
ቀስቃሽ አትላኪብኝ!!

@yefikrclinic
. የእናቴ ልጅ 🫧

✧ ክፍል አንድ ✧

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
እኔና ወንድሜ ከፊት ከዋላ የሌለን ብቸኛ የእናታችን ልጆች ነን እኔም እሱም ከልጅነታችን ጀምሮ ከእናታችን በስተቀር ማንንም እንደቤተሰብ ሳናውቅ በትልቁ ቤታችን ውስጥ ከግቢ ሳንወጣ አድገናል ፣ እናታችን ብዙም ሰው ስታቀርብ አላየንም ፣ እኛን ወደትምህርት ቤት ለማድረስ ይዛን ስትወጣ እንኳ ከጎረቤቶቿጋር ስትገናኝ በጣም የሳሳ ሰላምታ ነበረ ያላት ፣  ካደግን በዋላ እንኳን እኔ ነበርኩ ከሰው የማገናኛት  በሰላም ግን አይደለም ይህን ማለት ተገቢ ባይሆንም እንኳ በፀብ ነበር ከሰው ጋር ያገናኘዋት  በቃ እኔ ከማን እንደወረስኩት አላውቅም ነገሮችን በቀላሉ ማለፍ የምችል ሰው አልነበርኩም ቀድሜ ፀብ አልጀምርም ከነኩኝ ግን በፍፁም ፀብ ማብረድ የምችል ሰው አይደለውም ፣በዚ የተነሳ ከእናቴ ጋር ሆድና ጀርባ ሆንን ፣እናቴ  ተከባብሬ በኖርኩበት ሰፈር አዋረደኝ አሰደበኝ  ለአመታት ዘግቼ ከኖርኩበት ቤቴ በሱ የተነሳ አደባባይ ወጣው ብላ ለኔ ያላት ፍቅር ተቀዛቀዘ  ከጎኗ ሆኖ የሚያፅናናት ብቸኛ ልጇ ታናሽ ወንድሜ ሆነ  ወንድሜን የምበልጠው በሁለት አመት ነው  ነገርግን ለሚያየን ሰው እሱ ነው ታላቅ የሚመስለው  እኔ የሃያ አንድ እሱ አስራ ዘጠነኛውን ይዟል  ቢሆንም እንደኔ ቅብጥብጥ አይደለም በጣም የተረጋጋ እና ነገሮችን አስቦበት አቅዶ የሚያደርግ አይነት ሰው ነው ፣  በኔ ሁሌም እንደተናደደ እንደተበሳጨ ነው  ወደ እናቴ እንዳልቀርብ የተቻለውን ጥረት ሲያደርግ ሳየው አንዳንዴ በውስጤ እታዘበዋለው እውነት እናቴን የምጎዳትእየመሰለው ነው ወይስ የሷን ፍቅር እንዳልጋራው ለራሱ ሰስቷት ፣አይገባኝም ብቻ  ፣
🎈አስታውሳለው አንድ ቀን የሰፈር ልጅ ነው  አመሻሽቼ ስመጣ አንድ ጥግ ላይ ከጓደኛው ጋር ተቀምጦ ልክ እኔ እልፍ ስል 'ሹፈው የሰፈራችንን በሬ ከፊቱ ብትቆም ወግቶ ከመግደል ወደዋላ አይልም 'ሲል ሰማውት በሱቤት ድምፁን ቀንሶ ማውራቱ ነው እኔግን ሰማውት በቃ ያለምንም ቃል ነበር ሁለቱንም በተቀመጡበት የረገጥኳቸው እስኪለምኑኝ ፈጣሪ ሲረዳቸው  አንዲት የጎረቤት ልጅ ቆማ ታይ ነበርና በጩኽት ሰው ሰበሰበች  እየተሯሯጡ የመጡ ጎረቤቶች ልጆቹን አስጣሏቸው ፣በጉልበቴ ሳይገረሙ አይቀርም 'ምን አልቻልነውም እኮ ፀብ ውስጥ ሲገባ ሴጣኖች ዘጠኝ ሆነው ሳያብሩለት አይቀርም 'ሲባባሉ ሰማው  እናቴ እንደፈረደባት መጥታ ያዘችኝ ወደቤት እንድገባ ለመነች ወንድሜ እንደታላቅ አበደብኝ ሰደበኝ  "አንተ ዘላለምህን አትማርም ተው ስትባል አትሰማም ለምንድነው እናቴን የምታሳቅቃት   ብሎ ወቀሰኝ ። እናቴ እንደዛ ሲናገረኝ አሳቢነቱ እና የኔ እንቢተኝነት ሆድ አስባሳት መሰለኝ አለቀሰች እሷ ስታለቅስ ሳይ ወደራሴ ተመለስኩ ሁሉንም ነገር ትቼ ወደቤት ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛው  ተኝቼ አስብ የነበረው ስለ እናቴ ነበር በቃ የዕንባዋ ምክንያት መሆኔን አልወደድኩትም ፣የዛኔ ነበር ለራሴ ቃል የገባውት ከዚ በዋላ ለሷ ስል ለመታገስ ፣ ግን ደስ የሚለው እኔ ፀብ አቁሜ እንኳ በቀድሞ ጭካኔዬ በሰፈሩ ሰው የተከበርኩ ሆኜ ቀጠልኩ ፣ አሁን ላይ ፀብ የለም ግን የቸገረኝ እንደቀልድ የጀመርኩት ሱስ መላቂያው ነው ፣ እናቴ ስለኔ ትታለች  ከወንድሜ ጋር ነው ነገሯ ሁሉ   ታምሜ እንኳ ዞር ብላ አታየኝም ፣  የምትጨነቀው ለታናሽ ወንድሜ አቤል ነው ፣ 

ይቀጥላል .......

@yefikrclinic
🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል ሁለት ✧

.
.
.
እናቴ ለረጅም ጊዜ ቤቷን ዘግታ ታስተዳድረን ነበርና ነገሩ እየገረመኝ የመጣው ማስተዋል በጀመርኩ ጊዜ ነበር እንዴት ሁለት ልጆቿን ያለምንም ስራ የሚፈልጉትን እያሟላች ማኖር ቻለች በእርግጥ ያትልቁ ቤታችን ከሰፊ ግቢው ጋር ከአባቷ በውርስ እንዳገኘችው አውቄአለው እሱንም ከታናሽ ወንድሜ አቤል ነው  እሱ እንዴት እንዳወቀ እንኳ ጊዜ ሰጥቼ አልጠየኩትመ በወቅቱ ነገርግን ስራ ሳይኖራት ያን ያለፈችውን አመታት እኛን ዘግታ እራሷንም ዘግታ ባኖረችን ግዜ ገንዘቡን  ማለትም ወጪዎቿን የሚሸፍንላት ማን ነበር  ይሄን ለማወቅ ስል አንድ ሁለቴ ጠይቄያት ነበር ነገርግን እናቴ ለኔ መልስ ከመስጠት ይልቅ አፌን ማዘጋት ይቀላታል !
"እናቴ ?"ስላት ገና ፊቷን እንኳ ወደኔ ሳታዞር
"አቤት" አለችኝ ደረቅ ባለ ድምፅ፣ አቤል ግን ወደኔ ዞረ ምን ሊል ነው በሚል አስተያየት ተመለከተኝ
"እኔ የምልሽ ግን ያንን ሁሉ አመታት እኔ ማስተዋል ከጀመርኩበት ጊዜጀምሮ አስታውሳለው ከቤት ወጥተሽ አታውቂም ነበረ እና እንድትመልሺልኝ የመፈልገው ነገር ቢኖር ፣ እንዴት ነው የሁለታችንንም ወጪ ሸፍነሽ ልታኖሪን የቻልሽው  እስከማስታውሰው አንድም ነገር አላጎደልሽብንም ይሄን እንዴት ማድረግ ቻልሽ ? ሌላው ለምን ብለሽ ነው ከቤት የማትወጪው የነበር ?"ብዬ ለመልሷ ተዘጋጅቼ አይኖቿን ፈልጌ ለማየት ሞከርኩ ፣ ለመልሱ ዘገየች አቤል ሲነጫነጭ ወደሱ ዞርኩ ገላመጠኝ የእናቴ አሳቢ ልጅ  ምን ብዬ ጭንቅላቴን በምልክት ነቀነቅኩ  ፣እናቴ ድንገት ብድግ ብላ " አይመለከትህም ትኩረትህን እራስህ ላይ አድርግ  ሌላውን ለኔ ተውልኝ  እሺ ሲጀመር የልፋቴን ውጤት እንኳ አንተ ላይ አላየውም ! ትልቅ ቦታ ጠብቄህ ነበር ተመልከት በአጉል ባህሪክ የተነሳ ከኮሌጅ ተማሪነት የዘለለ ውጤት አላመጣህም ፣ይባስ ብለህ እኔ በምሰጥህ የኪስ ገንዘብ አጉል ልምዶች አመጣህበት አንተ ስለምንም የመጠየቅ መብት የለህም  ያባቱ ልጅ ..."አለች ከላይ እስከታች ስትወርድብኝ ምንም አልመሰለኝም ፣ነገርግን ሞቷል ያለችንን አባታችንን ስትወቅስ ግን ለዛውም ከኔጋር አገናኝታ አልተመቸኝም  ግን የዛን ለት ምነው አፌን በዘጋው ነበር ያልኩት በላዬላይ የናቴን ጥላቻ ይብስ ጨመርኩ ፣ምግብ እንኳ ስትሰጠኝ ፊቴን አታየውም ፣
አቤል ደሞ እሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ ይችልበታል እሷ ፊት የሚያሳየኝ ባህሪና እደጅ አንድ አይደለም ፣  በዚ ትንሽ ብናደድበትም መቼም ታናሽ ወንድም ነውና እታገሳለው የሚገርማቹ እኔ እንዲ አትንኩኝ ባይ የሰፈሩ አንበሳ ተብዬ እንኳ አቤል እንደፈለገ ቢሆን እጄን አንስቼበት አላውቅም በጣም ነው የምወደው ከእናቴስ ቀጥሎ ያለሱ ማን አለኝ ፣,,,,,,,,
ዛሬ ሃያ አንድ አመቴ ነው እና ሁሉም ነገር ጥያቄ የሚፈጥርብኝ ወቅት ላይ ደርሻለው  የእናቴ ብቸኝነት ከሷውጪ ሌላ ዘመድ አለማወቅ  የወንድሜ ከኔጋር ያለው የሻከረ የመጣ ግንኙነት ,,,,,,,???
ሰኞ ቀን ጠዋት ነው ክፍሌ ውስጥ ጋደም እንዳልኩ ነው  ከሳሎን ቤት የሰአን እና የበርጭቆ ድምፅ ይሰማኛል እናቴ ለቁርስ እያዘጋጀችው መሆን አለበት ፣መሃዛው የሚያውድ የሻዪ ሽታም ይሰማኛል ፣ማታ ጠጥቼ ነው የገባውት እና በውስጤ ያለው ምግብ እልቅ ብሏል ስጠጣ እንኳ ብዙም አልበላሁም ፣እና ሆዴ በረሃብ ተላወሰብኝ ፣ወጥቼ ቁርስ ከነሱጋር እንዳልቀመጥ ይሄንን ልምድ በነሱ ግልምጫ የተነሳ ትቼዋለው ፣ ማድረግ ያለብኝ ወይ አፍንጫዬን መዝጋት ነው ወይም በቱን ጥሎ መውጣት ፣አፍንጫዬን ለመዝጋት ሞከርኩ አልሆነም ፣ስለዚ ተነስቼ ልብሴን ለባብሼ ፣ ወጣው ስወጣ እየበሉ ነበር ፣እናቴ  "ወዴት ነው  ችኮላው "አለችኝ አብሬያቸው እንድበላ የፈለገች ትመስላለች ምንም እንኳ ኮስተር ብትል ። አቤል ግን ቀበል አድርጎ "ያው በጠዋቱም ሊጋት ይሆናላ መቼም ትምህርቱም ተመርቆ ቢያልቅም ስራም አላስገኘለት እኔማ እየወሰደ የነበረው የመጠጥ ኮርስ ነበረ እንዴ ኪኪኪ"ብሎ ሳቀ ቅስሜን ሰባበረብኝ ግን ምንም አላልኩትም ከሱ ንግግር ለማምለጥ እየተጣደፍኩ ወጣው ,,,,,,,

ይቀጥላል........

@yefikrclinic
የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል ሶስት ✧


.
.
.
ከቤት ወጥቼ ሰፈር ውስጥ ከሚገኝ አንዲት አነስተኛ ሱቅ ጋር ቆምኩኝ ፣ የሱቁ ባለቤት ልጅ ፣በድሪያ ትባላለች ፣ ፈራ ተባ እያለች " ምን ልስጥህ "አለችኝ ዝምብዬ ሳያት ወደዋላዋ አፈግፍጋ ቆመች  ልጅ ናት የቀድሞ በጥባጭነቴ እሷም ጋር ተፅህኖ ሳያሳርፍ አይቀርም "እ ብስኩት ስጪኝ ካፒችኖ አለሽ "አልኳት በጨዋ ደንብ "አለኝ "ብላ ሰጠችኝ ብሯን ከፍያት ፣ልሄድስል  ከኛ ጊቢ እልፍ ብለው የሚኖሩ ሴት ቀስ እያሉ መጥተው ቆሙ  እናም ወደኔ በመዞር "ናቲ እንዴት አደርክ "አሉኝ ከዚ በፊት አናግረውኝም ሆነ ስሜን ጠርተውኝ ስለማያውቁ ደንገጥ አልኩ  በዝምታ ሳያቸው "ምነው ናታን የእግዜር ሰላምታ እኮ አይከለከልም "አሉ ለስለስ ብለው
"አይ እኔ ከዚበፊት አናግረውኝ ሰለማያውቁ ገርሞኝ ነው "አልኳቸው በግልፅ
"አሂሂሂ መቼስ ልባችን ቢፈልግስ በየት በኩል እናንተ ከሰው አትቀርቡ ፣ለነገሩ ችግሩ የእናንተም አይደለ እናታቹ ናት እንጂ እንዳትቀርቡ ያደረገች  እናንተማ ያው ልጆች ናቹ የተመራችሁትን ነው "ብለው ሽሙጥ መሰል ነገር ተናገሩ ፣ዝምብዬ አየዋቸው እንደ እውነቱ ከሆነ እማማ ሸዋዬ ትልቅ ሰው ባይሆኑ በናቴ የመጣ ቱግ ባልኩ ነበር "እማማ እሺ አሁን ሰላም ይዋሉ "ብዬ መንገድ ልጀምር ስል "ቆይ ቆይ እንደው መጀመሪያ ለደናደርኩ '  ደና ይመስገን ነው መልሱ እእእ የሆነስ ሆነና እኔስ ድንገት ሳገኝህ በውስጤ የሚመላለስ ነገር ነበርና ስለ እናንተ ቤተሰብ  ላናግርህ ነበር  መቼም አንተ በክፉም ሆነበደግ ታገናኘን ነበር ፣"አሉ
እኚሴቲዮ እየተፈታተኑኝ ነው ግን ትህግስት ላድርግ ብዬ "እሺ ቶሎ ይበሉና ይንገሩኝ"አልኳቸው ወደበድርያ ሳይ የጨነቃት ይመስላል እጇን ታፍተለትላለች  ድንቡሽቡሽ ቀይ ፊቷ ያሳዝናል ፣ወደ እማማ ሸዋዬ አተኮርኩ መልሼ
"እኔማ ምን መሰለህ መቼም እዝች ምድር ላይ በሕይወት ስትኖር ክፉ ደግ አለ እንዳማሩ ዘላለም አይኖርም ደስታም እንዳለ አዘን አለ  ማገኘትም ማጣትም እንደዛው ፣ እና ከሰው ተለይቶ ምንም ነገር አይሆንም  ምንድነው ሁልጊዜም ስለ እናንተ ሳስብ ምንም ብትሆኑ ለኔ ይጨንቀኛል ፣እነዚ ልጆች እናታቸው አንድ ነገር ብትሆን እድር የለ ምን የለ ከሰው አይግባቡ እላለው እንደው በሌላ ነገር አትይብኝ እና ሰው ነንና ነገ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም  ናቲዬ አይለኛም ብትሆን አንተን ማናገር ለኔ ይቀለኛል ፣ እስኪ አንተ እናትህን እንደምንም ጨቅጭቀ የሰፈሩን እድር እንድትገባ አድርጋት  ከሰው ቀስ በቀስ ትቀላቀል "አሉ  መጀመሪያ ስላሟረቱብን ውስጤ ደስ ባይለውም የተናገሩት ነገር ከምር አሳሰበኝ ፣ እውነት አንድነገር ቢፈጠር አይበለውና  ሆሆሆ እማማ ሸዋዬ ጭንቀት ፈጠሩብኝ
"እእእ እውነት ነው እማማ ልክ ነዎት አናግራታለው ለመልካም አሳቦት አመሰግናለው "ብያቸው ነገር ከመቀጠላቸው በፊት ፈጠን ብዬ ተራመድኩ
"ሰው ነው ብዬ ቀውስ..."ሲሉ ትንሿ በድሪያ ስትስቅ ሰማዋት "አንቺ ደሞ ጥርስሽ ይርገፍ ሻማ ስጪኝ አሁን "ብለው የውሸት እርግማን ሲያወርዱባት ፣ስትስቅ ሳልወድ በግድ ፈገግ እያልኩ ለራሴ የገዛውትን ካፒቺኖ ጨምድጄ እንደያዝኩ ሰፈሩን ለቅቄ ሌላቦታ ለመዋል ፈጠንኩ ፣ወይ እማዬ,,,,,..ኀ
እሷ እንደው ከማንም ጋር ምንም ነገር ለመነጋገር ፍላጎቱም ስሜቱም የላት እና እኔ ምን ማድረግ እችላለው  ፣ በተለይ በአሁን ጊዜ ከወንድሜ አቤል በስተቀር ሰውም የላት  እሱ ሁሉ ነገሯ ሆኗል አማካሪዋ መልህክተኛዋ አዛኟ ተንከባካቢዋ  ...እኔን ማቅረብ በጭራሽ አትፈልግም ኧረ እሱም አልፈቀደልንም  ፣አንዳንዴ እልም ብዬ ብጠፋስ እላለው እውነት ያን ያክል ለነሱ ችግር ከሆንኩ ።ሌላ ቦታ ሄጄ እራሴን ልፈትን  ብዬ አስባለው የእናቴ በሚስጥር የተሞላ ሕይወት እና የታናሽ ወንድሜ እኔላይ ያለው ጥላቻ መጨመር እያሳሰበኝ መጥቷል ለምን ይሆን?,,,,,,

ይቀጥላል........

@yefikrclinic
🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል አራት ✧

.
.
.
አንድ ቀን በጣም ደካክሞኝ ስለነበረ ምንም አይነት መጠጥ ሳልጠጣ በጊዜ ወደቤት ገባው ፣ እናቴ ቡና አቀራርባ ቤቱን ሞቅ አድርጋው ነበር  አቤል ከሷትይዩ ካለው ሶፋላይ ተቀምጦ የቡና ቁርስ ፈንድሻ እየዘገነ ወደ አፉ ይልካል የኔ መምጣት ግድም አልሰጠው እናቴ ግን ያልተለመደ ስለሆነባት አተኩራብኛለች ፣ ምንም ሳልናገር ሄጄ ከቴሌቪዠኑ አጠገብ ተቀመጥኩ የኳስ ነገር ስለማይሆንልኝ በቲቪ የሚተላለፈው ጨዋታ አይላይት ቢሆንም እራሴንአሳርፌ  ማየት ጀመርኩ  አቤል ምቾት የሰጠው አይመስልም ሲያጉረመርም ሰማውት እናቴ ደሞ ዝም እንዲል ምልክት ትሰጠዋለች ፣ ውስጤ ቢናደድም ታገስኩ ፣እንደው ይሄልጅ ከዕፃንነታችን ጀምሮ እንደ ታላቅ እነቴ ስወደው ስከላከልለት ኖሬ ያለው ድንገት ሲጎረምስ እኔላይ ያለው ጥላቻ እንዲ አብጦ ሊፈነዳ የደረሰው  ፡በኔ አይለኝነት ነው ወይስ ሌላ ችግር አለ ብዬ እራሴን መጠየቄ አልቀረም ብቻ እንደፈለገ ፡ በጣም የሚገርማቹ እኔ የዚ የተንጣለለ ጊቢ ባለቤት  ሁሉም ነገር ከየት ይምጣ ከየት የሚነግረኝ ሰው ባይኖርም ሁሉነገር የተሟላበት ቤት ባለቤት ኪኪኪ ውይ ባለቤት አልኩኝ የቆንጆዋ የቤቱ ባለቤት ልጅ እኔ ፡ በእልህ የቤቱን ምግብ አልበላም ብዬ ፡ አንድ የሚገነባ ዕንፃ ላይ የቀን ስራ ተቀጠርኩ ይኽው በዛ ምክንያት ነው ዛል ብዬ የመጣሁት ፡ከእናቴ የኪስ ገንዘብ ለመውሰድ ምን አቅለሰለሰኝ በዛላይ የአቤል ግልምጫ ፡እሱ እንደው ሁሉም የኔ ማለት ከጀመረ ቆየ እሷም የአይኗ ብሌን አድርጋዋለች ፡እናት ግን እንዲ ስታዳላ አይገርምም በርግጥ እኔ ጥፋት የለብኝም ማለት አልችልም ግን እኔን በፀባይ መክራ ከማስተካከል ውጪ ከነ ልጇ እኔ ላይ ማመፅ ተገቢ ነው  ? ይሁን እስኪ  ዞር ብዬ ወደ እናቴ አየው ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ወደ አቤል መልሳለች  ትንሽ ቀናው ምን አለ ከዚ ፍቅር ቀንሳ ትንሽ በሰጠችኝ ፡አሁን እኮ ሁሉንም ነገር ትቼ ሰላማዊ ለመሆን እየጣርኩ ነው የበለጠ የእናቴን ፍቅር ባገኝ እበረታ ነበር ፡ የቀንስራው የመጀመሪያዬ በመሆኑ እጄ ባሬላ የያዝኩበት ውሃ ቋጥሯል ፊቴ አመድ መስሏል ሰውነቴ ዝሏል እናቴ ግን በጭራሽ ግድ አልሰጣትም በርግጥ ብዙም አላየችኝም ።አቤል እኔ ስገባ ያቆመውን ወሬ ነው መሰል ቀጠለላት ፈገግ ፈገግ እያለ የእናቴን ቱኩረት በቀላሉ ነበር የሚስበው "
"እማ ታውቂያለሽ ጋሼ ግዛው ግን ምላሳቸው ምንድነው የሚባለው ጤፍ ይቆላል"ብሎ አቤል ሲስቅ ፡ እናቴ አብራው ሳቀች
"ክፉ ደላላ ነው ምን ሲል ነው የኔን ቤት ያየው መቼም ያለምክንያት አናግሮህ የማያውቀውን ልጅ ስለቤት ሽያጭ አያወራህም "ስትል ሰማዋት ልቤ ደነገጠ ምን  የቤት ሽያጭ  ፡ሲያወሩ እኔ ካለው እንኳ አልቆጠሩኝም ፡ አቤል ነገሩን ለማለስለስ ቃላት ሲመርጥ ተሰማኝ
"ኧረ እማ ሰውዬውኩ ስለ እኛ ቤት እኮ ያነሳው ጉዳይ የለም ብቻ ቡና እየጠጣው ድንገት ነው መቶ የተቀላቀለው ፡ከዛ ነው እንግዲ  የወይዘሮ ሸዋረገድን ቤት በሃያ ሚሊዮን ብር አሻሻጥኳት እያሉ ሲያወሩ የሰማውት ከዛ ወደኔ ዞረው የአበባ ልጅ አይደለህም እንዴ አሉኝ ነኝ አልኳቸው  ፡ከዛ ያወንድምህ በወጣበት አንተ ወጣህ " አሉ ሲል እናቴ የኔን ስም እንዳይጠራ እጇን አፏላይ በማድረግ አስጠነቀቀች እኔ ትኩረቴ ቲቪ ላይ የሆነ አስመስዬ ንግግራቸውን ማድመጥ ጀመርኩ "እና እማዬ ሰውዬው ያቁኛል ብዬ እንኳ አልገመትኩም  እና ምን አሉኝ መሰለሽ ከእናንተ ቤት እኮ በግማሽ ያንሳል ፡ይኽው በአንድጊዜ አብታም አደረኳት "አሉኝ ብሎ ፈገግታው ይብስ ጨመረ እናቴ"ዝም በለው ባክህ እሱ ለሷብሎ አይደለም ደላላ ለራሱ ጥቅም ነው የሚሰራው "አለችና እናቴ ቡናውን መቅዳት ጀመረች
"እሱስ እማ ባለፈው የማማ ሸዋረገድን ልጅ አይቼው ነበር የሆነች ሱቅ ተከፍቶለት የራሱን ስራ ነው የሚሰራው በዛላይ የቤት መኪናም ገዝቷል  አይገርምሽም "አላት እናቴ መልስ ሳትሰጠው የቀዳችውን ቡና ማማሰል ጀመረች ቀስብዬ ወደ አቤል ስመለከት እየተቁነጠነጠ ነው ፡እንዴ ይሄ ነገር ምንድነው የአቤል ፍላጎት አሳሰበኝ ከመቼው ትልቅ ሰው ሆኖ ነው ስለቤት ሽያጭ የሚያወራት በውስጤ ይሄንን ነው መፍራት አልኩኝ  እናቴ ወደኔ ዞራ
"ቡና ልቅዳልህ አለችኝ"
"እሺ ግን አልበላውም "አልኳት እየደበረኝ ፡ አቤል የሽሙጥ ሳቅ ሳቀ ፡እናቴ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ፡አቤል "ተይ አትነሺ እማ እኔ እሰጠዋለው "ብሎ ወደ ክችን ገባ እናቴ እሺ ብላ ቁጭ አለች
አቤል ወዲያው ነው የተመለሰው ሰአኑላይ ግማሽ እንጀራ በአንድ አይነት ወጥ አድርጎ አምጥቶ አስቀመጠልኝና ከእናቴ አጠገብ በመቀመጥ ፡የቅድሙን ወሬ ድጋሚ እያሰማመረ ያወራት ጀመር እናቴ ወሬው የጣማት አልመሰለኝም በዝምታ ታዳምጣለች ፡ እኔ ይሄኔ ነው አቤል ፍፁም ሌላ ሰው የመሰለኝ ለእናቴአዘንኩላት በሙሉ ልቧ ነው የምትወደው የሷ ምርጡ እና ልዩ ልጇ ነው ****


ይቀጥላል........


@yefikrclinic
Temesgen lela mn yebalal yematelef ylm lek 🙏🙏🙏🙏
የእናቴ ልጅ

      ✧ ክፍል ስምንት ✧

.
.
.
ለካንስ የሰው ልጅ አንዴ ውሸትን መለማመድ ከጀመረ  እንደ እውነት ነውና የሚቆጥረው ፡ ሌላው ቀርቶ ሰው ሲዋሽ ፊቱ ላይ የሚገለፅ አንዳች እንቅስቃሴ አለ ይባላል  ኖኖ ግን እሱ የሚሰራው ድንገት ተቸግሮ የሚዋሽ ሰው ሲሆን ብቻ ነው ፡ እንጂ ሆነ ብሎ ውሸትን መጠጊያው አድርጎ የሚኖረው ላይ አይደለም  በጣም የሚገርመኝ ደሞ ሰውየው እራሱ ውሸቱን እስከማመን የሚደርስበት ነገር ነው ፡  እውነት ለመናገር የወንድሜን ያላንዳች የገፅታ መለዋወጥ ፡ሁሉንም ነገር በኔላይ ማላከኩ ትልቅ ፍራቻን ፈጥሮብኛል ፡ፍራቻዬ ለራሴ ብቻም አይደለም ፡ ለሱም  ለእናቴም  ጭምር ነው ፡ምክንያቱም ይህን ልምድ ድንገት ያገኘው አይመስለኝመሰ እየተለማመደው ነው የመጣው ፡በዚ አይነት እናቴ በኔላይ ጥላቻ እንዲያድርባት ሰርቷል ማለት ነው ፡ እናቴ በበፊቱ እረባሽነቴ ብቻ ሳይሆን እሱ ፈጥሮ በሚነግራት ነገር ነው ልትጠላኝ የቻለችው ብዬ ደመደምኩ ፡ ይሄ ባህሪ ደሞ ፡ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን አልፎ ወጥቶ የቀረቡትን በሙሉ ሊያሳዝን እንደሚችል ተሰማኝ ፡ከባድ ነገር ነው ፡
👉ዕፃኗን ታቅፌ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ዘጋው ፡ እናቴ እርግማኗን ስታዥጎደጉድብኝ ይሰማኛል ፡በቃ እናቴን መከራከሬ እንደማያዋጣኝ ተገነዘብኩ ፡ምንም ያክል እውነት ብናገር የአቤልን ውሸት መደምሰስ እና የእናቴን ቀልብ መመለስ እንደማልችል ገብቶኛል ፡ ከኔ ይልቅ የታማኙ ለስላሳ ልጇ ቃላት ልቧን ይሞላዋል ፡አይለኛና ጉልበተኛ አልሸነፍ ባይ ብሆንም ፡ይሄ ነገር እናቴ ላይ እና ወንድሜላይ ሲሆን አይሰራልኝም ፡ በተለይ እናቴ የቱንም ያክል ብትጠላኝ ፡ እሷላይ መጨከን የሚችል አንጀት የለኝም ፡ እንኳንስ አንድ ነገር ሆና አይቼ ቀርቶ ፡መንገድ ላይ እንኳ ከሷ ዕድሜ የምትቀርብ ሴቴ አንዳች ችግር ገጥሟት ካየው ውስጤ ስፍስፍ ነው የሚልብኝ ፡  ወንድሜ በዚመጠን ቢጎዳኝም እሱላይ እጄን ማንሳት ይከብደኛል ፡እንደው በጩኽት እንኳ ሳናግረው እናቴ ስለምትከፋ ለሷ ስል ነገሮችን የምተው ነኝ ፡
ዕፄኗ አልጋዬ ላይ ፍልስስ ብላ አንቀላፍታለች ፡ጠጋ ብዬ ሳያት በአንድ ጎን ባለው ጉንጯ ላይ ፈገግ ያለች ትመስላለች ፡ ይሄን ፈገግታ አውቀዋለው አቤል ነው ወደጎን ፈገግ የሚለው  ልጅ እያለን በጣም ነበር የምወድለት ፡ ቅላቷ ልክ እንደ እናታችን ነው እኔም ሆንኩ አቤል ጠይም ነን ፡ ሁለታችንም መልከመልካም ፡ብንሆንም ፡ አቋምን በተመለከተ እንግዴ እኔ ረዘም ያልኩኗ የተስተካከለ አቋም ነው ያለኝ ፡ አቤል ወፈርፈር በማለቱ ቁመቱ ባያሳጣውም ከጊዜ በዋላ የመጣበት ውፍረት ትንሽ የቀነሰበት ነገር አለ ፡ እናታችን ቆጆ ናት ዕድሜዋ ወደ አርባ አምስት ነው ነገር ግን አሁንም ከፈለገች ፡ የምትወደውን ወደ ሕይወቷ ማምጣት የሚችል አቋም ላይ ናት ፡ 
የዕፃኗ መልክ ግን ከፈገግታዋ በቀር እኛ ቤት አይደለም ፡ የማላውቃትን እናቷን ቁንጅና ሳትወርስ አትቀርም ፡በጣም ታሳሳለች ፡ ገና ናት ከሶስት እና ከአራት ወር አታልፍም ፡ ምስኪን ከማይረቡ ሁለት መናጢዎች ተወልዳ ፡በእናቷ እቅፍ ውስጥ መሆን ሲገባት ፡ ምንም በማያውቀው እብዱ ነን ታኒየም ላይ ተጥላለች ፡  ለሊቱን ሙሉ ሳስብ ነበር እንዴት ነው የማደርጋት ፡ እኔም አንዱ ጥግ ወስጄ ጥያት ሕይወቴን ልቀጥል ፡ ወይስ እዚሁ ቤት ጥያት ልጥፋ፡ ወይስ አዝያት እያባበልኩ ፡ልመና ልውጣ ፡ ግራ ገባኝ ፡ እንቅልፍ እሚባል ባይኔ ሳይዞር ነው ያደርኩት ፡  ከለሊቱ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ፡የክፍሌ በር ተንኳኳ ደንግጬ ተነስቼ ከፈትኩ ፡ አቤል ነበር ኮስተር እንዳለ
"እስካሁን እዚ ነህ ከመነሳቷ በፊት ዲቃላህን ይዘህ አትሄድም "አለ ፡ማመን አቃተኝ
"የኔ ልጅ እንደሆነች ታስባለህ ?"አልኩት በጩኽት እኔ እንደሱ ቀስብሎ ማውራት አልችልም ለዛም ነው ሰው የማይረዳኝ
"ስለሱ አይመለከተኝም እናቴ ያለችህን ሰምተሃል እሷ ከመነሳቷ በፊት ከዚ ብትሄድ ይሻላል"አለኝ ግድ ሳይሰጠው
"ለምን ዲሄንሄ አናስመረምርም "
"ገንዘብ ካለህ አስመርምራ "አለኝ አይኑን እንደማርገብገብ ብሎ ስለዚ ጉዳይ ያሰበበት አይመስልም
"እሱ ወደፊት የማይቀር ነው እኔ ምንም እንዳላረኩ አውቃለው እናቴ እንድታምነኝ ስል ግን ተመልሼ መጥቼ ማስመርመሬ አይቀርም እንዳትረሳ ፡እኔ እንኳን ላስወልድ ቀርቶ የሴት ልጅ ከንፈር በቅጡም ስሜ አላውቅ  "አልኩት ፡በጣም ሳቀ መልሶ አፉን እጁ ላይ በመጫን ወደክፍሉ ገባ ።  ጭንቅላቴን ይዤ አሳብ እንዲመጣልኝ ወተወትኩ ፡ድፍን አለብኝ ፡ ወደ ዕፃኗ ተጠግቼ ቆምኩ ከእንቅልፏ ነቅታ አይኖቿ ይንከራተታሉ ፡ እልህ ያወኝ ፡ማንንም አልለማመጥም የሆንነውን እንሆናለን በቃ ፡ መንጃ ፍቃድ አወጣለው ብዬ ያስቀመጥኩት ጥቂተሰ ብር ነበረኝ እሱንአውጥቼ ያዝኩ ወፈር ያሉ ልቅሶቼን በሻንጣ ከተትኩ  እናቷ የላከችውን የዕፃኗን በቁጥር ያልበዛ ልብስ ያዝኩና  በፎጣ ጥቅልል አድርጌያት ተነስቼ ፡ወደበሩ አመራው እናቴ እንዳትሰማ በጥንቃቄ ነበር የምጓዘው ከግቢው ስወጣ አቤል ተከትሎኝ ኖሮ በፍጥነት ለዘላለሙ ይመስል በሩን ዘጋብኝ ጨለማው ገና አልገፈፈም ፡አምላኬን አንድ ነገር ለመንኩ እባክህ እናቴን ከዚ መሰሪ ልጅ ጠብቃት ፡ ,,,,
ይቀጥላል........

@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል አምስት ✧

.
.
.
የቀንስራ ከጀመርኩ ቆየው ይኸው እንዳይለመድ የለም ለመድኩት ፡እንደበፊቱ ከመድከም ባለፈ አጠነከረኝ አይምሮይንም አሳምኜ ልክ እንደ ስፖርት በመውሰድ ሰጥ ለጥ ብዬ መስራት ጀመርኩ ፡ እናንተዬ ለካ  ፡የነገሩ ክብደት ሳይሆን ኑሯችንን የሚያከብድብን የኛው የመቀበል ጉዳይ ነው  ወሳኙ፡
ይኽው አምኜ በምሰራው ስራ ይበልጥ ጠንካራ ሆኛለው  እንደበፊቱ መጠጣት መቃም ቀርቷል ግን ትንሽ የከበደኝ የሲጋራው ነገር ነው ጨርሶ ለማቆም አልቻልኩም በርግጥ መጠኑን ከበፊቱ ቀንሻለው  ፡ በምግብ በኩል ሆድ ለቆብኛል አብዛኛው ገንዘቤ በምግብ ነው የሚያልቀው ፡እውነቴን ነው በዚ የኑሮ ውድነት መቆጠብ አይታሰብም ፡ምን አልባት ቆጥበህ ጫማ ትገዛ ይሆናል እንጂ  ቆጥበህ ቤት አትገዛም ኪኪኪ እንኳን ታራ ስራ ሰርተኽ ደና ደሞዝ የሚከፈላቸው እንኳ  እኔ ከምገዛው የተሻለ ጫማና ልብስ ቢገዙ እንጂ ሌላ ነገርማ እንጃ  ፡
እኔ በገዛ ፍቃዴ ከእናቴ ጡረተኝነት ለመውጣት እየታገልኩ ነው  ፡ አቤል ግን ከእናቴ ጋር እንደተጣበቀ  ነው  መርካቶም ስትሄድ መከተል ነው  ቤት ውስጥም አብሮ መንጎዳጎድ ነው  ለራሱ የሚሰጠው ጊዜ ያለ አይመስልም ፡ በተቻለው መጠን እየተንከባከባት ነው ፡የሚገርመኝ ደሞ ይህን እንድታውቅለት ይፈልጋል ፡እናቴን የግሉ አድርጎ ነው የቆጠራት ከኔጋ ለማውራት እድሉንም አይሰጣት ፡ እሷም ብትሆን ለሱ ያላት ነገር ከመንሰፍሰፍም በላይ ነው ፡ ,,,,,
ወቅቱ ዝናባማ ነበርና ብርዱም ውጪ የሚያስመሽ ስላልነበረ  ትንሽ ጨለም ከማለቱ ነበር ወደቤቴ ለመግባት የሰፈሬን መንገድ የተያያዝኩት ፡በአካባቢው ላይ የሚጫወቱ ዕፃናትን ሳይ ኑ ግቡ የሚልም የለም እንዴ ፡ምነው የዚን ያክል ሰው ቸልተኛ ይሆናል ፡በርግጥ እንደኛ ሰፋፊ ጊቢ እና ትንሽ የሀብታም ልጅ የሚባሉ ልጆች የሉበትም ፡  ከትናንሽ ቤቶች ውስጥ የወጡ ልጆች ናቸው ቤታቸው አጥር ስለሌለው ሰፈር ውስጥ ከላይ ታች እያሉ ነው የሚጫወቱት ፡ቢሆንም ግን ሲመሽ ግቡ እና አጥኑ የሚል ወላጅ ከሌለ ለነገ ማንነታቸው ከባድ ነው  ፡መብትና ግዴታቸውን የማያውቁ ልጆች ካደጉ በዋላ  ልመልስህ ብትለው ፡ አትችለውም ፡ ስለነሱ እያሰብኩ አንዱ የሰፈራችን ቅያስ ጋር ስደርስ ጉድ አየው ምን አትሉም ወንድሜን ከሴት ጋር ሲነታረክ በዛላይ ዕፃን ልጅ ከተሸከመች ልጅ እግር ሴት ጋር ትንሽ ሸሸግ ብዬ አውቃት እንደሆን ለማረጋገጥ ሞከርኩ ጨርሶ አይቻት አላውቅም ፡ በጣም ተቆጥታ ነው የምታወራው ፡እሱደሞእየለመናት ነው  ምንድነው ጉዳዩ,,,,,,,,,


ይቀጥላል........

@yefikrclinic
🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል ስድስት ✧
.
.
.
ቤት ከገባው በጣም ቆየው አቤል ግን አልመጣም እናቴ በተደጋጋሚ ወጣ እያለች ትመለሳለች እንደጨነቃት ያስታውቃል ልጇ እንዲ ሲያመሽ የመጀመሪያው ነው ፡ እኔ ብሆን ባድርም ግድ የላት የኔ ነገር ድሮ ነው የበቃት እኔም ብሆን አዘኔታዋን አልፈልገውም ፡ምክንያቱም ለዚሁሉ መገፋት የኔም ድርሻ አለበት ፡ ፍቅሯን ፈልጌ አንዳንዴ ብወቅሳትም ፡ ስህተቱ የኔም መሆኑን ካመንኩ ቆይቻለው እና ዛሬ ላይ ዝቅ ብዬ እየሰራው እራሴን ለማስተካከል መወሰኔ ከዛ አንፃር ነው  ,,,,,,,,,
እናቴ በጣም ሲብስባት ወደ እኔ ዞረች
"ስማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት ሆኗል ወንድምህ አልገባም !አንተ ግን እዚ ተቀምጠሃል  ትንሽ እንኳ አይጨንቅህም?!" ብላ አፈጠጠችብኝ
"ምን ማድረግ እችላለው ከመጠበቅ ውጪ ፡እኔና እሱ እንደው ከተራራቅን ቆይተናል ፡ምን እንደሚያደርግ ምን እንደሚያስብ ከነማን ጋር ጓደኛ እንደሆነ አላውቅም ፡ ስለዚ  አዲስ ያመጣው ባህሪም ካለ እንግዲ ከኔ ይበልጥ የሚቀርበው አንቺን ነው "ብያት ፊቴን ወደቲቪው መለስኩ
"ምን ማለት ነው ?!"ብላ ቱግ አለች
"እንዴ ካንቺ ጋር ቀን ላይ የተነጋገራችሁት ነገር ካለ አስታውሺ ፡ ወይም ጓደኛ ካለው ከነሱ ጋር የሚያከብረው ነገር ካለው ፡ አይታወቅም  ትልቅ ልጅ ነው አንዳንዴ የሚያምረው ነገር ሊኖርም ይችላል"ብዬ ዝም ።እናቴ ልትመታኝ የፈለገች መሰለች ተጠግታኝ በቁጣ ስታየኝ ቆይታ
"እሱ እንዳንተ አይደለም ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም ደጁን አያውቀውም ከመሸ ልጄን አውቀዋለው ይሄኔ አንድ ቦታ ተጨንቆ ነው የሚሆነው ወይኔ ልጄን ተነስ አሁን አፍህን መክፈትህን ትተህ ፍለጋ እንውጣ ፡ "ብላ ጎተተችኝ ፡ወይ እናቴ ምንአለ ከዚሁሉ ፍቅር ትንሽ ቀንሳ በሰጠችኝ ብዬ ተመኘው ፡
  ወደ በሩ ስትጣደፍ ስስ ነገር መልበሷን ልብ አልኩ ለማንኛውም ብዬ ወደክፍሌ ገብቼ ወፈር ያለውን ጃኬቴን ያዝኩላት እና ቀድማኝ የጊቢውን በር ከፍታ እየወጣች "ፍጠን" አለችኝ የቤቱን በር እየዘጋው ፡ መጣው ከማለቴ እናቴ ስትጮኽ ሰማዋት ፡በፈጣሪ ሰውነቴ ለሁለት የተተረከከ ነበር የመሰለኝ ፡ እናንተ ድንጋጤ ለካ ያስሮጣል ከመቼው ፡እናቴ አጠገብ እንደደረስኩ እኔነኝ የማውቀው  ፡እናቴ ደግማ ግን አልጮኽችም ፡አካባቢውን በጥንቃቄ እየቃኘች ከቆየች በዋላ በትልቅዬ ዘንቢል የተቀመጠ ነገር አነሳችና ወደግቢ ገብታ በሩን ዘጋች እኔ እንኳ ከጊቢ ውጪ መሆኔን የዘነጋች ነው የምትመስለው ፡
"እናቴ ኧረ በሩን ክፈቺልኝ"አልኳት ፡
"ናግባ ይሄ ምን ጉድ ነው!"ብላ በሩን ከፍታ አስገባችኝ ወደ ዘንቢሉ እየተጠጋው
"ምንድነው"አልኳት
"ዕፃን ልጅ ነው አይታይኽም "አለችኝ
"አአ አዎ አአ የውት"አልኩኝ በድንጋጤ ቃላቴን እየጎተትኩ ፡ ጉድ ፈላ አቤልን ዕፃን ልጅ ከታቀፈች ሴት ጋር አይቼው ነበር  ይህን ለእናተሰ ብነግራት አታምነኝም ፡በቃ በታማኙ ልጇ የሚመጣባት ሰው አትፈልግም ፡ እናቴ ለአቤል ያላት ፍቅር ጥልቅ ነው ፡እንዲነው እንዲያነው  ብሎ ለእናቴ መንገር ከበደኝ..
"ና ወደቤት ይዘነው እንግባ ማነው አምጥቶ የጣለብኝ ሆሆ ብለው ብለው የትም ሲልከሰከሱ ወልደው መጣያ ያድርጉኝ እኔ ከሰው አልቀርብ አልደርስባቸው ምን ፍለጋ ነው ሀብታም ናት ብለው ነው ፡እስኪ ከዚ ሁሉ ጊቢ የኔ በምን ታያቸው ፡ ልጄን ልፈልግ ወይስ የነሱን ዕፃን ላስተናግድ ምን አይነት ቀን ነው ዛሬ"እያለች እያጉረመረመች ከዘንቢል ውስጥ ድንገት ንቅት ብላ አይኗን የምታቁለጨልጭ ዕፃን አውጥታ ወደላይ በመያዝ "ውይ ጭካኔ ሴት ናት "ብላ ወደኔ ዞረች  ፡እኔ አይምሮዬ ሁሉ አቤል ጋር ነው በቃ አቤል እሱ ቀርቶ ልጁን ልኮልናል ፡ የት ተደብቆ ይሆን ይህን ድራማ የፈጠረው ጉድ ነው አልኩ ፡ እናቴ ዕፃኗን ሶፋው ላይ አጋድማ ዘንቢል ውስጥ ጡጦ ይኖር እንደው ብላ ስትፈላልግ በዛውም አንድ ደብዳቤ አገኘች ደብዳቤውን ይዛ ወደኔ ስትዞር ፡የጊቢ በር ተንኳኳ ሁለታችንም ለአፍታ በድንጋጤ ተያየን ፡ከዛ እኔ እሮጥ ብዬ በር ከፈትኩ አቤል ነበር ምንም ነገር አልሆነም ለመጀመሪያ ጊዜ አከበረኝ ይቅርታ የጓደኛዬ ልደት ነበር አለ ዝም አልኩ ።እናቴ አቤል መምጣቱን ስታይ እፎይ አለች  ፡እና ወደ ዕፃኗ እያሳየች "ጉድ ሆንን እኮ አቡ ተመልከት የጣሉብንን "ስትለው እንደ አዲስ ተገረመ እኔ የፊቱ ገፅታ አስገረመኝ ምንም አልመሰለውም ከጉዳዩ ለመሸሽ እራሱን አሳምኖ እንደመጣ ገባኝ ፡እናቴ የያዘችውን ደብዳቤ ለማንበብ ተዘጋጀች  ,,,,,,,,,,


ይቀጥላል........


@yefikrclinic
የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል ሰባት ✧

.
.
.
በሕይወቴ ውስጥ እንደዛን ቀን የማይነጋ ለሊት አይቼም አላውቅ ፡እናቴ የተፃፈውን ደብዳቤ እጆቿ እየተንቀጠቀጡ ስትገላልጠው ፡ የወረቀቱ ድምፅ በራሱ ሽብርን ለቀቀብኝ ፡ አቤል ተረጋግቶ ወደ እናታችን ተጠግቶ ቆመ ፡ ለራሴ በቃ ለሚመጣበት ነገር ሁሉ ተዘጋጅቷል ማለት ነው ፡በይሆንማ ኖሮ ጉዱን ከቤት ውስጥ አምጥቶ እንዲ ግድ የለሽ አይሆንም ስል አሰብኩ ፡ግን እኔ የሱ ሁኔታ ብዙም አላሳሰበኝም ከዛ ይልቅ እናቴ  በጣም የምታምነውን ልጇን ማጣቷን ስታውቅ የሚሰማት መሰበር ነው ያስጨነቀኝ ፡   እናቴ ደብዳቤውን ማንበብ ስትጀምር ይበልጥ ተንቀጠቀጠች ፊቷ ተለዋወጠ ፡ ጉድ ፈላ አልኩኝ ፡በቃ አቤልን ከማነቋ በፊት አንድ ነገር ለመፍጠር ተዘጋጀው ፡እሱን ካጠገቧ አርቄ ነገሮችን ለማረጋጋት...
"እናቴ ደና ነሽ"ብዬ ስጠጋት ደብዳቤውን ጥላ በሕይወቴ አይቼ የማላውቀውን ጥፊ አሳረፈችብኝ፡በድንጋጤ ወደዋላ ተመለስኩ ፡ እንዴ የእናት ጥፊ እንደዚ ያማል እንዴ ? እንጃ ... አፍንጫዬ አካባቢ እርጥበት ተሰማኝ በእጄ ጠርጌ ሳይ ደምቻለው ፡ምንድነው ጉዱ የወንድሜን ንዴት እኔ ላይ እየተወጣችብኝ መሰለኝ ፡ ወንድሜ ደሞ ይባስ ብሎ ከሷ አራቀኝ እና እንዳልጠጋት አስጠነቀቀኝ ፡ በዚ ጊዜ ዕፃኗ ለቅሶዋን አሰማች ፡ሁሉም ነገር ድንግርግር አለብኝ  የአፍንጫዬን ስር በጥፊ የበጠሰችኝ ይመስል ደሙ አልቆም አለኝ ፡ እናቴ የዕፃኗን ጩኽት ላለመስማት ሁለቱንም ጆሮዎቿን በመሸፈን
"ዲቃላኽን ይዘኽልኝ ውጣ አንተ አሰዳቢ"ብላ አንቧረቀችብኝ ፡ ማን እኔ ጉድ ነው እንዴት ነው ነገሩ  ልጅቷ የኔ እንደሆነች ነው እንዴ የምታስበው ፡ በፍጥነት የጣለችውን ወረቀት አንስቼ አነበብኩት፡"ለናታኒየም     ሚጡ  ነኝ  አዝናለው ልጅህን የማሳድግበት ምንም አቅም የለኝም  የፈለከውን አድርገህ  እኔን መከራ ውስጥ ከተህ መተኛት ካማረህ ተሳስተሃል ሳልፈልግ የሰጠኸኝን ዘር ልኬልሃለው  እንደፈለክ ማድረግ ትችላለህ  ቻዎ"እኔ አላምንም ለረጅም ደቂቃ አፌን ከፍቼ አቤልን ማየት ጀመርኩ ፡ ወንድሜ በኔ ላይ አላከከው በትክክል የሱ አሳብ መሆኑን አውቄሃለው ፡ምን ቢጠላኝ የዚን ያክል ግን በኔላይ ያምፃል ብዬ አላሰብኩም እናቴን ለማስረዳት አስቤ ደግሜ ተጠጋዋት ፡ በፍፁም ጥላቻ ተሞልታ ጣቷን ቀስራ
"ዲቃላህን ይዘህ ውጣ አሁኑኑ"አለችኝ ፡አስተያየቷ ስብርብር አደረገኝ ፡በተራዬ እኔ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ ፡ ሕይወቴ ይበልጥ ሲመሰቃቀል ታየኝ ፡አቤል እናቴ ደግፎ እያስቀመጣት ማፅናናት ጀመረ ፡ ግራ ገባኝ እውነት ይሄ የ እናቴ ልጅ ወንድሜ ነው ፡ እስኪ ምን ብበድለው ነው እንዲ የሚያደርገኝ  እኔ ላይ ከሚያላክክ ፡ምን አለ ተጥላ ነው ያገኘዋት ቢል ፡ ፍፁም ጤንነቱን ተጠራጠርኩ ፡የምታምነውን እና የምትሳሳለትን እናቱን ፡እንዴት ይዋሻታል ፡ ጠጋ አልኩትና
"አቤል ወጣ ብለን እናውራ"አልኩት ፡
"ከኔጋር የምታወራው ነገር የለም ፡እሷ የምትልህን አድርግ አለኝ አፉን ሞልቶ።ተስፋ ቆረጥኩ ፡ወደበሩ አየው ከምሯን በዚ በለሊት ዕፃን አሲዛ ልታባርረኝ ነው እናቴ ለዛውም ባልወለድኩት ልጅ  ይሄን ማመን ከበደኝ ፡ዕፃኗ ለቅሶዋን አላቆም አለች ፡
"ስማ እማዬን አልሰማሃትም ልጅህን ይዘሃት ውጣ"አለኝ አቤል አይኑን በጨው አጥቦ
"እናቴ እሱ ድሮም አይወደኝም እቺ ልጅ ግን....."
"ምን እቺ ልጅምን የኔ አይደለችም ልትል ነው እናትየው በፃፈችው ደብዳቤ አረጋገጠችልን እኮ"አለ አቤል፡እናቴ ድጋሚ በንቀት እያየቺኝ ወደበሩ አሳየቺኝ ከኔጋ ለማውራት ፍላጎት አጥታለች ፡ተስፋ ቆረጥኩ ፡ዕፃኗን አንስቼ አቀፍኳት በጣም ዕፃን ናት የት ነው በዚ ለሊት ይዣት የምሄደው ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎርምስና ጀግንነቴ ተፈተነ አይኖቼ ዕንባ አቀረሩ  ፡በዘምቢሉ ውስጥ ተጎዝጉዘው ከነበሩት ወፈር ያለውን ፎጣ ሸፋፍኛት ፡ ወደበሩ ተራመድኩ ፡ እናቴ
"ስማ ዛሬ ለሊት ይለፍልህ ነገር ግን እኔ ከመነሳቴ በፊት ቤቱን ለቀ ጥፋልኝ "አለች እናቴ አሳዘነችኝ ከፊት ከዋላዋ ተኩላው ልጇ በፍቅር ሰበብ ሰቅዞ ይዟታል ምንም የምትመረምረውም ነገር የላት ፡ ,,,,,,,,

ይቀጥላል........

@yefikrclinic
🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል ዘጠኝ ✧

.
.
.
አንዳንዴ ወዴት እንደምትሄድ ሳታውቅ፡ ግን እግርህ መራመዱ አይገርምህም ? በቃ አንተ መድረሻህን አላሳወከውም ፡እሱ ግን ይንቀሳቀሳል ፡ እግራችን አመፀኛ ሆኖ  'የት እንደምንሄድ ካልነገርከኝ ካልወሰንክ አልንቀሳቀስም 'ቢል ኖሮ ምን ይውጠን ነበር ? በእርግጠኝነት ብዙ ሆቻችን አንድ ቦታ ተዘፍዝፈን እንቀር ነበር😂 ጥሩ እነቱ እግር አልሄድ አይል ፡ የት እንደምሄድ ሳላውቅ ዕፃን ልጅና ሻንጣ ተሸክሜ የሌሊቱን ብርድ ቻል አድርጌ  ጉዞዬን ቀጠልኩ ፡  ሰፈራችን ውስጥ አንድም ነብስ አለመንቃቱ ጠቀመኝ  ማንም አላየኝም  ሌላው ቀርቶ ውሾቹ እንኳ እንቅልፍ ጥሏቸው ጥግጥጉን ተረፍርፈዋል ፡ ተመስገን አይለኛና ተፈሪ በሆንኩበት ሰፈር ልጅ ታቅፌ በለሊት ብታይ ፡እናቶቹ የቡና ማጣጫ ፣ አባቶቹ የመጠጥቤት ውሎ ማድመቂያ ፣ጎረምሶቹ የጫት ቤት ሙድ መያዣ ነበረ የሚያደርጉኝ ፡ 
   ከሰፈራችን ለቅቄ ስወጣ እፎይ አልኩ ፡ የመስቀል አደባባይን አስባልት ይዤ ወደፊት ተራመድኩ  ፡ያው ሰፈራችን ከኢግዝብሽን ማህከል ጀርባ እንደመሆኑ መጠን ፡ በለሊት ወደ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሚሄድ ሰው አይታጣም እና ጠንቀቅ ማለቱን አልዘነጋሁትም ፡ አልፎ አልፎ ነጠላ የለበሱ እናቶች ባጠገቤ እልፍ ሲሉ እራሴን ሰብሰብ አደርጋለው ፡  ይህ ሁኔታዬ ለራሴ አሳዘነኝ ፡እራስህን በሌላ ሰው መነፅር አይተህ ለራስህ አዝነህ አታውቅም ? አዎ በቃ እንደዛ ....በእስጢፋኖስ በኩል ሳልፍ ቆም ብዬ ተሳለምኩና ፀሎት አደረኩ ' ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአምላኬ ጋር አስታርቀኝ ፈጣሪዬ ፈተናዬን ይቀንስልኝ ዘንድ እርዳኝ 'አልኩ  አንድም ቀን ፀልዬ ስለማላውቅ ምን እንደምል ፣እንዴት እንደሚለመንም አላውቅ ፡ግን በራሴ መንገድ ለፈጣሪዬ እንዲደርስልኝ ዕንባ ዘለላዎችን በለሊት አንጠባጠብኩ ፡  የታቀፍኳትን ዕፃን አየዋት የሰላም እንቅልፍ ላይ ነች ፡ በዚ በዚ አድናቂዋ ነኝ አንዴም አላለቀሰች ፡ እኔን ማስጨነቅ አለመፈለጓ ጥሩ ነው ፡ ምን አልባት ፈጣሪዬ በዚ እየረዳኝ ይሆናል ተመስገን ማለትን በዚ አጋጣሚ ተማርኩ ...
👉ለካ ላይችል አይሰጥም የሚሉት እናቶቻችን ወደው አይደለም ፡የአለምን አዙሪት ትችለዋለህ ስቃዩ ከብዶ አልቻልኩም ብትልም ችለህ ቆመ ትራመዳለ ፣ርሃብ አልችልም ብትል ብቸኝነት አልችልም፣ ከሰው መለየት አልችልም  ሰው ማስቸገር አልችልበትም ብትል ፡ ምንም አታመጣም እስትንፋስህ እስካለች ፡አለመቻልን እራሱ ትችለዋለ ......
ከማማ ጋር ጎዳና ከወጣን ሰነባበትን ፡ ቤት ንብረት ያለው ሰው ብቻ አይደለም ለካ የሚያስጠጋህ ፡እነሱንማ አየናቸው ከንፈር ከመምጠጥ በዘለለ ምንም አይፈይዱልህም ፡  ካላቸው ሚሊዮን ብሮች መሃል አስር ብር ሰጥተው ላንተ ባደረጉት ነገር አካብደው ፅድቅ የሚጠብቁ ስንቶቹ መሰሉህ ፡አንድ ስንዝር ሕይወትህን የማይቀይር ሳንቲሞች ሰጥተው ፡ለምን አትሰራም ብለው የምክር አገልግሎት የሚሰጡህ በቱ የሚሉ ቁጠራቸው ፡  ከእነሱ በተሻለ መጠጊያ የሰጠችኝ እትዬ ባዩሽ ምስጋና ይድረሳት ፡ኮልፌ ላስቲክ ወጥራ ነው የምትኖረው ፡ ብዙ ነገር ያየች ናት ፡የኑሮ አጋጣሚ ባዶ እጇን አስቀርቶ ጎዳና ያወጣት ፡ ፊቷ እንደ ከሰል ቢጠቁርም ልቧ የነፃ ፡ አዛኝ ፡ የነበረኝን ገንዘብ በሁለት ወር ውስጥ ለክራይ እና ለሚበላ ለማማ ወተት ስገዛ ጨርሼ መግቢያው ጠፍቶኝ ስንከራተት ውዬ ደክሜ ድልድይ ስር ቁጭ ብዬ  ሳዛጋ ነበር ያገኘችኝ ዕድሜዋ ልክ እንደ እናቴ ነው አርባዎቹ ውስጥ ፡ አጠገቤ መጥታ ስትቆም እብድ መስላኝ ነበር ፡በዋላ ስረዳት ለካንስ አሳዝኛት ኖሯል ፡  ስላለውበት ሁኔታ ጠየቀችኝ ነገርኳት ዕፃኗን ግን የራሴናት ነው ያልኳት ፡ከዚ በዋላማ የማንም ልትሆን አትችልም ፡ ከዛ ነው እንግዲ ወደቤቴ ና ብላኝ የወሰደችኝ ፡መጀመሪያ የእውነት ቤት መስሎኝ ነበር በዋላ ግን የላስቲኳን ቤት ሳይ ቀፈፈኝ እንዴት በዚ መጠን ወርጄ እገኛለው ብዬ ተናነቀኝ ፡ ግን ምን አማራጭ አለኝ ምንም የስቃዬ መጀመሪያ ሊጀምር ነው አልኩ ፡ ባዩሽ ግን ሁሉም ደና ይሆንልሃል አለችኝ ለጊዜው እዚ እረፍ  የጨካኞቹን ቤት አከራዮች ሆድ የምትሞላበት አቅም ላይ አይደለም ያለኽው ከጠበበንም ሰፋ እናደርገዋለን ፡ አለችኝ  አዘን ብሶቴን ዋጥ አድርጌ ይሁን አልኩ ፡  ለጊዜው ነው እንጂ ማማንማ እዚ እንድታድግ አላደርግም ፡ ብዬ ወሰንኩ
   ከባዩሽ ጋር በጣም እየተለማመድን ስንመጣ የዋህ ልቧ ይገርመኝ ጀመረ  ያገኘችውን ሁሉ እኛን ለማስደሰት ብላ ይዛ ትመጣለች ደግ ነች ፡ ይሄ ደግነቷ እንዳምናት አደረገኝና ፡በቃ ማማን እሷ ጋር እያስቀመጥኩ ለምን አልሰራም ብዬ ወሰንኩ  እና ስራ መስራት ከባዩሽጋር ተስማምቼ መንቀሳቀስ ጀመርኩ  ኮልፌ አካባቢ ሰፊዎች አሉ እና ለነሱ ጣቃ ከመኪና ላይ ማውረድ መጫን በቃ ያገኘውትን ነገር ሰራው ፡ ጎዳና ላይ ወጥቶ ላስቲክ ቤት ከመኖር የከፋ ነገር አለ እንዴ ሂሉኝታ ደና ሰንብት አልኩ ፡ጉልበቴን ተጠቀምኩት ፡ ገንዘብ አገኝ ጀመር ፡ እና ገንዘብ ሳገኝ የመጀመሪያ እቅዴ ማማንና ባዩሽን ከላስኪቱ ቤት ማላቀቅ ነበር እናም ተሳክቶልኝ አነስተኛ ቤት ተከራይተን ገባን ፡ ባዩሽ ትንሽ አስቸግራኝ ነበር እኔ ግን አንቺ ማለት የእናቴ ምትክ ነሽ አንቺ በሕይወቴ ውስጥ ቦታ አለሽ ስለዚ መቼም ትቼሽ አልሄድም አልኳት በመጨረሻ ተስማማች ፡ ኑሮ ተጀመረ ፡ አንድቀን ባዩሽ  እንዲ አቸኝ
"እኔ የምልህ ናቲ እንደው የዝህች ልጅ እናት በቃ ዝም ነው የምትባለው ?ምን ልባት እኮ ወደ እናትህ ቤት ተመልሳ መጥታ ልጄን ብላ ጠይቃ ይሆናል ፡መቼም ሴት ልጅ እንዴት እንዳማጠች ስታውቅ ሁሉን ትረሳለች ማለት ከባድ ነው "አለችኝ
"ባያ ዝም በይኝ እሷ በጭራሽ አትመጣም አረብ አገር ሳትሄድ አትቀርም "አልኳት ውሸት ቀላቅዬ ፡እንዴት ብዬ ወንድሜ አላኮብኝ ነው ብዬ አወራለው ለሰሚውም ግራ ነው
"አይ እንደው እኮ ብትመጣ አንዴ እንኳ ጥሩ ነበር ፡የልደት ቀኗን እንኳ አታውቀውም "ስትለኝ በጣም ተገረምኩ ፡እውነት ለመናገር ትዝ ብሎኝም አያውቅ ነበረ ከችግር ለመውጣት ከመፍጨርጨር በቀር
"ባክሽ አንዱን ቀን ማክበር ነው የሦስት ወር ነበረች እሱን አስልቼ ማክበር ነውኪኪኪኪ እንደውም ለምን በሃያ ሰባት አናከብርላትም በቃ የመዳኒዓለምን ቀን ያዢውና ሁለተኛ ዐመቷን እናከብርላታለን"አልኳት ባዩሽ ወይ አንተ ልጅ ብላ ሳቀች "ሌላው ክትባት ወስዳ አታውቅም አይደል በቅርቡ አኪም ሊያያት ይገባል"ብላ አከለች ፡ወይጉድ ማማዬ በዛ መሰሪ ወንድሜ የተነሳ ስንት ነገር ቀርቶባታል ,,,,,,,,,,

ይቀጥላል........

@yefikrclinic
🫧 የእናቴ ልጅ 🫧

      ✧ ክፍል አስር ✧

.
.
.
ይገርማል እንደ ቀልድ ቀን ቀንን እየተካ አመታት ይቆጠራሉ !! ዕፃናት ያድጋሉ ወጣቶች ጎልማሳ ይሆናሉ ጎልማሶች ያረጃሉ  አዳዲስ ሕይወት ይመጣል የቆየውም ያልፋል ፡ ለሁሉም ወር ተራ ነው ፡
👉ዛሬ ለማማዬ ሁለተኛ አመቷን አከበርንላት ፡እኔና ባዩሽ ብቻ በትንሿ የክራይ ቤታችን !!ሁለት ቁጥር ሻማ ሳበራ ፡ ድንገት የባነንኩ ይመስል ያሳለፍኩት ምስቅልቅል ከፊቴ መጥቶ ተደቀነ ፡ የወንድሜ ጭካኔ የእናቴ  ጥላቻ አሁን እንደተደረገ ይታየኝ ጀመር ፡ እንደ አዲስ አንገበገበኝ ያምሽት፡  እናቴ እሩሩ ልብ ቢኖራት ኖሮ  ጨክና  አትተወኝም ነበር  ይቅር ትለኝ ነበር ፡ ለሊቱ ከመንጋቱ በፊት ዲቃላህን ይዘህልኝ ጥፋ በጭራሽ እንዳላይህ የሚለው የእናቴ የቁጣ ቃል ዳግም አይምሮዬላይ ተንጫጫብኝ ፡የአቤል ያፈጠጠ ውሸት እና ማስመሰል ሁሉም ተመላለሰብኝ ፡በጣም ተከዝኩ ፡  .....
ባዩሽ ነበረች ያባነነችኝ "አንተ ምን ሆነሃል ሻማውን ጎትታ ልትጥለው ነበር እኮ "አለችኝ
"ውይ የሆነ አሳብ ውስጥ ገብቼ እኮ "አልኳት
"ምንድነው እሱ ናቲዬ ስራቦታ ችግር አለ እንዴ?"አለችኝ እያሳሰባት ፡
"አይ ስለ ስራ አይደለም እንደው እናቴ ትዝ ብላኝ ...."ብዬ ቀእንጥልጥል ተውኩት
"እንደው ናቲዬ ካመጣህው አይቀር እንደው እኔም ብሆን እያስብኩልህ ነው እስከመቼ ነው ከእናትህ ተደብቀህ ልጅ የምታሳድገው በጣም ያሳስባል?!"አለች
"አይ አይ ተደብቄ አይደለም እሷ ናት በለሊት ከነ ዕፃን ልጅ ያባረረችኝ  ምንም እርህራሄ አነበራትም ይህን ያደረገችው ለክብሯ በማሰብ ነበር  የኔ ነገር ምንም አላስጨነቃትም ፡ በዛላይ የኔ ..."ብዬ ዝም አልኩ
"ያንተ ምን?"
"ተይው በቃ እንደው ስሜታዊ ሆኜ ነው"አልኳትና ዝም ብዬ አየዋት ፡እስከዛሬ ትክክለኛውን ሚስጥሬን አልነገርኳትም ፡
"ንገረኝ ነገርን በውስጥ መያዝ ጥሩ አይደለም ፡"አለችኝ
"አይ እንደው ነገሩ ትንሽ የሚከብድ ነው ፡በእርግጥ እንደሞኝ ካላየሺኝ የደበኩሽን ሚስጥር ዛሬ እነግርሻለው ፡"
"ናቲዬ አንተን እንደሞኝ ላይ በጭራሽ አንተ እኮ ሰው ያደረከኝ ሰው ነህ ፡ "አለችኝ ዕንባ ባዘሉ አይኖቿ እያየችኝ
"እነግርሻለው ግን ያለማቋረጥ ስሚኝ እና ደሞ የምነግርሽ ነገር ለማመን ቢከብድም እውነት ነው "አልኳት ፡አንገቷን ነቅንቃ በጉጉት ጆሮዋን አቅንታ ታዳምጠኝ ጀመር ፡ባዩሽ የኔንና የወንድሜን አስተዳደግ ከመጀመሪያ ጀምሮ ስነግራት ፡ፈገግ እያለች አንዴም ኮስተር እያለች ተከታተለችኝ ፡ በመጨረሻም የአቤልን ለውጥና ፡ በድንንገት የልጅ አባት መሆንና ፡ በኔላይ ያለምንም አፍረት እንዳላከከብኝ ፡እናቴም ይህን አምና መቀበሏንና ፡ሁለቱም ተጋግዘው ከቤት እንዳስወጡኝ ስነግራት ፊቷ በአንዴ ተለዋወጠ ፡ሰውነቷ የተንቀጠቀጠ መሰለ ፡በመገረም እንደ አዲስ ሰው ታየኝ ጀመር ፡ ዝምብዬ የምትለኝን ለመስማት ስጠባበቅ ድንገት ከተቀመጠችበት ተነስታ "እውነትም ሞኝ ነህ የሞኝ ሞኝ ፡እንዴት ባልወለድከው ልጅ የኔናት ብለህ ትሰቃያለህ ፡እንዴት እንዲ እንዲያደርግህ ትፈቅድለታለህ እንዴት ፡ እሺ የሆነስ ሆነና ተመልሰህ ሄደህ እናትህን ማሳመን አልነበረብህም ፡ እንደዛ በዚች ዕፃን ልጅ የተነሳ እንደሴት አዝለህ ወተት እያፈላህ  የተሰቃየኽው ባላረከው ነገር ነው ፡ያሳዝናል ፡ "ብላ ወቀሳም አዘኔታም ያለበት ጩኽት ጮኽችብኝ
ግራገባኝ ነገሩ ከኔ በቀር ለማንም አይገባውም ማለት ነው እኔ እኮ ስለ እናቴ ነው ይህን የምከፍለው  እሷ ከኔ ይልቅ ለአቤል ቦታ አላት ያ ስሜት እንደተጠበቀ ካልኖረ የምታብድ ነው የሚመስለኝ ,,,,,, አይኔን ጨፍኜ ነገሮችን እንደ አዲስ ለማየት ሞከርኩ.......

ይቀጥላል........

@yefikrclinic
Forwarded from Button Bot
◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል።  Join 👇
https://www.tg-me.com/addlist/CmCbgOfbjoI3ZjA0
https://www.tg-me.com/addlist/CmCbgOfbjoI3ZjA0
Forwarded from ኢትዮ ቀልዶች™
እርግጠኛ ነኝ ፎቶ ለመነሳት ፈልገው የአነሳስ style ጠፍቶብዎት  ተቸግረው ያውቃሉ።የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/addlist/Panp-a3S08djMDM0
bak_I0.gif
119.6 KB
Who's here?

We've asked for a free link to a paid channel, for our subs.
x2-x3 Signals here


👉 CLICK HERE TO JOIN 👈
👉 CLICK HERE TO JOIN 👈
👉 CLICK HERE TO JOIN 👈


❗️JOIN FAST! FIRST
1000 SUBS WILL BE ACCEPTED
2024/05/04 07:28:11
Back to Top
HTML Embed Code: