የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበሩን ዶ/ር ራሄል ባፌን ከሃላፊነታቸው ማንሳቱን ገልጿል።
ፓርቲው ዶ/ር ራሄልን ያገደበት ምክንያት ከፓርቲው "ዕውቅና ውጪ" እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በመጥቀስ ነው።
ባለፈው እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ፤ ዶ/ር ራሄል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምክትል ሊቀ መንበርነት ሃላፊነት መያዛቸውን ጠቅሶ፣ "የፓርቲውን አሰራር ደንብ ባልተከተለ ሁኔታ እንዲሁም አንድ የፓርቲ አባል ሊወጣ የሚገባ ግዴታ" አለመወጣታቸውን አመልክቷል። አያይዞም፣ ገዢው ፓርቲና መንግስት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንደሚያበረታቱ በማንሳት፣ ዶ/ር ራሄል ባፌ ግን "የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት በሚጎዳ መልኩ" ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዕውቅና ውጪ "ፓርቲውን አደጋ ላይ የሚጥል" ዕንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አስረድቷል።
ይህ "ፓርቲውን አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ያለውን ዕንቅስቃሴ ፓርቲው ሲያብራራ፣ ከሰሞኑ በአቶ ልደቱ አያሌው አስተባባሪነት በበይነ መረብ በተካሄደውና በርካታ ፖለቲከኞች ከአገር ውስጥና ከባሕር ማዶ የተሳተፉበት የተቃውሞ ዕንቅስቃሴ ላይ ዶ/ር ራሄል ንግግር ማድረጋቸውንና መሳተፋቸውን ያነሳል። እንዲሁም በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን "መደመር ምን ፈየደ?" የሚልና የመሳሰሉ "ግልብ" ትችቶችና አባባሎችን "ተናግረዋል" ያለ ሲሆን፣ እነዚህም የፓርቲው ዕምነቶችና አቋሞች አለመሆናቸውን አስገንዝቧል።
በመሆኑም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ "ባልተለያየ ድምጽ" ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ዶ/ር ራሄል ባፌን ከፓርቲው ማገዱን አስታውቋል። በእርሳቸው ምትክ የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ አጫሞ ቦቄ፣ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ፓርቲውን እንዲመሩ መወሰኑን ነው የገለጸው።
በመጨረሻም፣ "ዶ/ር ራሄል ባፌ በየትኛውም ፖለቲካዊና ሕዝባዊ መድረኮች በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ በማናቸውም መገናኛ ብዙሃን የምታቀርባቸው ሃሳቦችና አቋሞች፣ መግለጫዎችና ቃለ መጠይቆች ፓርቲያችንን የማይወክሉ መሆኑን እንገልጻለን" ብሏል፣ ኢሶዴፓ።
@YeneTube @FikerAssefa

የነዳጅ ዋጋ በአለም ገበያ ሊወሰን ነው!
-መንግስት የነዳጅ ድጎማን ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ
ከሳምንት በፊት የበጀት ንግግራቸውን ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ መንግስት በድጎማ እንደማይቀጥል ማስታወቃቸው አይዘነጋም።የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ መንግስት ላለፉት ሶስት ወራት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ሙሉ በሙሉ አቁሟል። ይህ ውሳኔ ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅን፣ ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ነጭ ናፍጣና ሌሎች የነዳጅ ውጤቶችን ይመለከታል ተብሏል።
መግለጫው እንደሚያመለክተው፣ መንግስት የውጭ ምንዛሬ በመጨመሩ ምክንያት ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ሲል ጥቅል ድጎማ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል። ሆኖም፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ባለው የዋጋ ልዩነት ምክንያት የሚፈጠረው የኮንትሮባንድ ንግድ እና በመንግስት ላይ ያለው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ፣ ድጎማውን ለማንሳት ባለፉት 11 ወራት ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን አስታዉሷል።
በተጨማሪም፣ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች የነዳጅ ማደያዎች ላይ ያልተገባ ወረፋ እየፈጠሩ መሆኑን ገልጿል፤ ይህም መንግስት ከድጎማው እንዳልወጣና ተጨማሪ ታክስ እንደሚጥል የሚገልጹ መረጃዎችን ውድቅ አድርጓል።
@YeneTube @FikerAssfa

እስራኤል በየቀኑ ለሚሳኤል መከላከያ 285 ሚሊየን ዶላር እያወጣች ነው ተባለ።
የእስራኤል ሚዲያና የቴክኖሎጂ ተቋማት ኢራን በዚህ መጠን ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ማስወንጨፍ ከቀጠለች የመከላከያ ስርዓቷ በ12 ቀናት ውስጥ ሊዳከም ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
እስራኤል በመጀመሪያዎቹ የሁለት ቀናት ውጊያ እና መከላከል ብቻ 1.45 ቢሊየን ዶላር አውጥታለች ሲባል ኢራንን ለማጥቃት የምትጠቀምበት የጀት ነዳጅና ተተኳሽ ብቻ በቀን 300 ሚሊየን ዶላር ያስወጣታል ተብሏል።
የቀድሞ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ አመራር ጀነራል ራሂም አሚናች እስራኤል በየቀኑ ለቀጥተኛ ወታደራዊ ወጪ ብቻ 725 ሚሊየን ዶላር እንደምታወጣ አንስተዋል።
እስራኤል ከኢራን በተጨማሪ ከሄዝቦላህ፣ ሃማስ እና ሁቲ ጋር ጦርነት ውስጥ የቆየች እና ያለች ሲሆን ኢኮኖሚዋ ጦርነቱን እስከመቼ እንደሚሸከመው የብዙሃኑ ጥያቄ ሆኗል።
@Yenetube @Fikerassefa

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግዙፍ መርከብ እና ጀልባ በስዊዝ ካናል ተጋጩ
ትላልቅ ሸክሞችን እና የውሃ ውስጥ የመጥለቅያ መሳሪያዎችን ለመያዝ የተሠራው ሬድ ዜድ 1 የተሰኘው የጭነት መርከብ በመሪ ሲስተም ብልሽት ከጀልባ ጋር ተጋጭቷል።
እንደ ዘገባዎች ከሆነ መርከቡ በሰሜን አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ከመንገዱ ወጥቷል። የነፍስ አድን ሠራተኞች ሁኔታውን በፍጥነት በመቆጣጠር ጉዳት እንዳይደርስ እና የተለመደው የስዊዝ ካናል ትራፊክ ፍሰት እንዳይስተጓጎል አድርገዋል።

ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ
እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሌላ የኒውክሌር ሳይንቲስት መሞቱን፤ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህም በእስራኤል የተገደሉ የኢራን ኒውክሌር ሳይንቲስቶችን ቁጥር 10 አድርሶታል።
ኢሳር ታባታቤይ የተባለው ተመራማሪ ሞት ይፋ የሆነው በቴህራን ሻሪፍ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጣ ሲሆን፤ ኢሳር የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ ነበር ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ኢራን ቀደም ሲል ሌሎች ዘጠኝ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መሞታቸውን ማረጋገጧ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 'ቻናል 12' የተባለው የእስራኤል ሚዲያ እስራኤል በኢራን በጀመረችው ዘመቻ፤ 9 የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን በአንድ ጊዜ፤ እንዲሁም አሥረኛውን የኒውክሌር ሳይንቲስት በሌላ ጥቃት መግደሏን ዘግቧል።

አሜሪካ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎችን አጠቃች!
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳስታወቁት የሀገራቸው አየር ሀይል በሶስት የኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ማለትም ፎርዶው፣ ናታንዝ እና እስፋሃን ላይ የአየር ጥቃት አድርሰዋል። የኢራንን የኒውክሌር አቅም ለማዳከም ፎርዶው የሚባለውን ጣቢያ ማውደም የምትችለው ብቸኛ ሃገር አሜሪካ እንደሆነች ሲነገር መቆየቱ የሚታወስ ነው።

Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልእልት ብራይዳል ሰርጋችሁን የሚያድምቁትን ቅሚሶች አስግብተን እየጠብቅናችሁ ነው።
አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/leeltbridal
Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A
አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/leeltbridal
Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A
Forwarded from YeneTube
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ
👉1መኝታ 75ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር
ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር
👉2መኝታ 94ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር
ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር
👉2መኝታ 103ካሬ
10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር
ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር
👉3መኝታ 132ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር
ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር
👉3መኝታ 146ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር
ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር
‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ
https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN
በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ

Forwarded from The Urban Center ( Kebet Eske Ketema)
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Final Week – Week 4 Sessions
We're closing out our 14-part expert-led workshop series with two crucial technical sessions in Week 4:
🧱 Concrete Design & Specifications
📏 Technical Specs & Measurement Methods
📅 Tuesday, June 24, 2025
📍 The Urban Center, Addis Ababa
🖥 Live on TUC Facebook page & Google Meet (link shared 30 min before each session)
☕️ Free sessions with refreshments
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Let’s finish strong, join the conversation, contribute your perspective, and help shape Ethiopia’s future building code.
Many thanks to all our incredible partners for making this journey possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #EngineeringEthiopia #ConstructionStandards #UrbanDevelopment #ProfessionalEngagement

የኑክሌር ፕራግራማችን ይቀጥላል:-ኢራን
አሜሪካ ትናንት ለሊት በኢራን የኑክሌር ማበልፀጊያ ቦታዎች ላይ ድብደባ ከመፈፀሟ በፊት ኢራን ሁሉም የኑክሌር ጣቢያዎች ባዶ ተደርገዋል። ሁሉንም ዋና ዋና የኑክሌር ማበልፀጊያ እቃዎችን አሽሽታለች። የኑክሌር ጨረር ይፈጠራል ተብሎ አይጠበቅም።
@Yenetube @Fikerassefa
አሜሪካ ትናንት ለሊት በኢራን የኑክሌር ማበልፀጊያ ቦታዎች ላይ ድብደባ ከመፈፀሟ በፊት ኢራን ሁሉም የኑክሌር ጣቢያዎች ባዶ ተደርገዋል። ሁሉንም ዋና ዋና የኑክሌር ማበልፀጊያ እቃዎችን አሽሽታለች። የኑክሌር ጨረር ይፈጠራል ተብሎ አይጠበቅም።
@Yenetube @Fikerassefa
“ዘመቻው ከተጠናቀቀ በኋላ ከትራምፕ ጋር አውርተናል፣ የሞሳድን ጥንካሬ አድንቀናል” - እስራኤል።
እውቀት በቦምብ አይጠፋም:: የኢራን ፓርላማ አፈጉባዔ አማካሪ ማህዲ ሞሀመድ
እስራኤል እና ኢራን ከአሜሪካ ጥቃት በኋላ ምን አሉ?
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ “በፕሬዝዳንት ትራምፕና እኔ ትብብር፣ በእስራኤል ጦር እና የአሜሪካ ጦር ትብብር የፎርዶው፣ ናንታዝና ኢስፋሃን ኑክሌር ጣቢያዎችን አጥቅተናል” ብለዋል።
“ዘመቻው ከተጠናቀቀ በኋላ ከትራምፕ ጋር አውርተናል፣ የሞሳድን ጥንካሬ አድንቀናል” በማለት ገልጸዋል።
የኢራን ፓርላማ አፈጉባዔ አማካሪ ማህዲ ሞሀመድ፣ “ኢራን ከአሜሪካ የተቃጣባትን ጥቃት በብቃት ተከላክላለች” ብለዋል።
“በኑክሌር ጣቢያው የነበሩ ግብዓቶች ወደሌላ ስፍራ ስለተወሰዱ ጉዳት አልደረሰባቸውም” ሲሉ ተናግረዋል።
“ሁለት ነገሮች እርግጠኛ ነኝ” ያሉት ማህዲ፣ “መጀመሪያ እውቀት በቦምብ አይጠፋም፣ ሲቀጥል ወራሪዎች ሽንፈት ገጥሟቸዋል” ብለዋል።

የኢራን ጦር ቴል አቪቭ፣ እየሩሳሌም እና ሃይፋ የተባሉትን የኢስራኤል ከተሞች መደብደቡን አስታወቀ።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "አሜሪካ በኢራን ሰላማዊ የኒውክሊየር ተቋማት ላይ የፈጸመችው አስነዋሪ ጥቃት የማያባራ መዘዝ ያስከትላል" ሲሉ ካስጠነቀቁ በኋላ ኢራን በእስራኤል የተለያዩ ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት እያደረሰች መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።
የኢራን የዋእዱ አስ ሷድቅ 3 የኦፕሬሽን ቃል አቀባይ ኮሎኔል ኢማን ታጂክ እንደገለፁት፤ ኢራን በእስራኤል የተለያዩ ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት አድርሳለች።
በጥቃቱ ቴል አቪቭ፣ እየሩሳሌም እና ሃይፋ ከተሞች በህንፃዎች እና በመሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ቃል አቀባዩ እንደገለፁት፤ የሚሳኤል ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው የቤን ጉሪዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን፣ የባዮሎጂካል ምርመራ ማዕከላትን እና የወታደራዊ ትዕዛዝ ተቋማት ላይ ነው።
ሃሬትዝ እና እየሩሳሌም ፖስት እንደዘገቡት፤ በአብዛኛዎቹ የእስራኤል ከተሞች ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።
የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት (ማጌን ዴቪድ አዶም) በሚሳኤል ጥቃት ቢያንስ 10 ቦታዎች ላይ ለደረሰው አደጋ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የአደጋ ጊዜ ቡድኖች ጉዳት የደረሰባቸውን በማውጣት እሳቱን ለማጥፋት እየሰሩ ነው ተብሏል።

የኢራን ፓርላማ በአለም ላይ በጣም ወሳኝ ከሆኑ የነዳጅና ጋዝ መተላለፊያዎች ተጠቃሹን ‘ ሆርሙዝ ባህር ‘ ለመዝጋት ያቀረበውን ረቂቅ ፀደቀ
ይህ የኢራን እርምጃ ወደ ተግባር ለመግባት ከኢራን ከፍተኛ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የመጨረሻውን ይሁንታ እየጠበቀ ነው ።
ውሳኔው ተተግብሮ ሆርሙዝ ቢዘጋ አለም አቀፍ የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ላይ አስከፊ መዘዞች የሚያስከትል ሲሆን - ይህ የ Hormuz መተላለፊያ 21 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ዘይት እና አንድ ሦስተኛው የዓለማችን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ በእያንዳንዷ ቀን የሚጓጓዝበት ነው።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከ110 ሺህ በላይ ደርሷል - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
በየጊዜው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ተጠቃሚዎች ቁጥር እና ያለው ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለፀ።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እንደገለፁት በኢትዮጵያ አሁን ላይ በአጠቃላይ ከ110 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይገኛሉ።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ማደግ ከነዳጅ ወጪ ቁጠባና ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር ለተያዘው እቅድ ትልቅ እመርታ መሆኑም ተገልጿል፡፡ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለነዳጅ ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምታወጣ መረጃዎች ያመለክታሉ።