Telegram Web Link
በመንግስት ግዥ ሂደት ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች የይግባኝ ዉሳኔ ቢያገኙም ዉሳኔዉ ተፈፃሚ እየሆነ አይደለም ተባለ!

አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በይግባኝ ቦርዱ የሚሰጣቸዉን የይግባኝ ዉሳኔ እንደማይተገብሩ ተገልፆል።የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በበጀት አመቱ 148 ይግባኝ እንደቀረበ አስታዉቋል።

ከቀረቡት ዉስጥ መረጃ ተሟልቶ ለቀረቡ ምርመራ በማድረግ ለ 142 የይግባኝ ጥያቄዎች ዉሳኔ መሰጠቱን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ተናግረዋል።የይግባኝ ጥያቄዉ በግዥ አፈፃፀም እና ንብረት ሽያጭ ላይ የመንግሥት መስሪያ ቤቱ የሕግ ጥሰት አለበት ብሎ የሚያምን ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች እንዲመረመርለት የሚያቀርበዉ ቅሬታ ነዉ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆኖም የቦርዱን የይግባኝ ዉሳኔ ተቀበሎ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳሉ ገልፀዋል።መስሪያ ቤቶቹ የይግባኝ ቦርዱ የተቋቋመዉ በአዋጅ እንደመሆኑ የተሰጠዉን ዉሳኔ መቀበል ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

አያይዘዉም በይግባኝ የተሰጡ ዉሳኔዎች አተገባበር ላይ በልዩ ሁኔታ ኦዲት ተደርጎ ሪፖርት እንዲወጣ ለማድረግ መታሰቡንም ጠቁመዋል።የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር በህጉ መሠረት መከወኑን ለመለየት 62 ተቋማት ላይ የህጋዊነት ኦዲት መደረጉን የመንግስት ግዢ እና ንብረት ባለስልጣን አሳዉቋል።ባለስልጣኑ የበጀት አመቱን ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት በ 16 የመንግስት ተቋማት ላይ የኦዲት ጥቆማ እንደቀረበለት ሰምተናል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስታቱ ድርጅት በአማራ ክልል የረድኤት ሰራተኛ መገደሏን ተከትሎ ድርጊቱን አወገዘ፣ የረድኤት ድርጅት ሰራተኞች ከለላ እንዲሰጣቸው ጠይቋል!

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን “አንጎት” ወረዳ “በመንግስት ሃይሎች እና በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መካከል” ተከስቶ በነበረው ግጭት በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በከፍተኛ ሁኔታ ቆስላ የነበረች የረድኤት ድርጅት ሰራተኛ ማህሌት ስጦታው አበራ መሞቷን አስታውቋል፤ ድርጊቱንም አውግዟል።

የማስተባበሪያ ቢሮው ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማህሌት “በተኩስ ልውውጡ ጉዳት የደረሰባት በአከባቢው የእርዳታ እህል አቅርቦት የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በተመለከተ መረጃ እያሰባሰበች፣ በስራ ላይ በነበረችበት ወቅት ነው” ብሏል።

ሃላፊዋ አቢባቶ ዋነ-ፎል ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ባልደረቦቿ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ “የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን የማስተላልፈው ለሟች ቤተሰብ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ የሰብአዊ ረድኤት ሰራተኞች ነው” ሲሉ ገልጸዋል፤ “ንጹሃንን እና ለተቸገሩ ሰዎች እርዳታ ለማቅረብ የሚጥሩ ሰራተኞችን ከጉዳት ለመጠበቅ ሁሉም እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ተጨማሪ ሁለት አባላቱ መታሰራቸውን አስታወቀ!

-ክልሉ በበኩሉ በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ሲል አስተባብሏል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ሁለት ተጨማሪ አባላቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ኧርገታ ወርቁ የተባሉ በቡለን ወረዳ የፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና አቶ ታምራት ጉዴሶ የተባሉ የፓርቲው አባል መሆናቸው ተገልጿል።

"በዚህ ወንጀል ተብሎ የተጠረጠሩበት የደረሳቸው የወንጀል ክስ የለም" ያሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የፓርቲው አመራር አክለውም የፓርቲው አባል በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ለእስር ተዳርገዋል ሲሉ ገልጸዋል። በክልሉ በተለይም በቡለን ወረዳ በፓርቲያችን አባላቶች ላይ እስር እና ወከባ ቀጥሏል ያሉት አመራሩ "ይህም ለቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ በቂ ዝግጅት እንዳናደርግ የታለመ ነው" ሲሉ አመልክተዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የጠየቅናቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ "በክልሉ እስከአሁን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር የለም" ሲሉ አስተባብለዋል።

“ማንኛውም ግለሰብ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣን ይሁን አልያም የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር፣ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ተሳታፊ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ ላይ የክልሉ መንግስት ህግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
ሚኒስትሩ በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተባለ!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው በማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ሲሰራጭ ሰንብቷል፡፡ ሚኒስትር መ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ ሚኒስትሩ የመጂና አደጋ እንደደረሰባቸው አረጋግጧል፡፡

ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከምሽቱ 1:00 አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው የሚገኝበት ካርል አደባባይ ላይ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ነበር ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፤ በእለቱ ሚኒስትሩ ወደ ሆስፒታል አምርተው በቂ ህክምና እንዳገኙና አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ሚኒስትሩ ከበቂ የጤና እረፍት ቆይታ በኋላ ወደ መደበኛ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱም መግለጫው ጠቁሟል፡፡"እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሁነቱን ለርካሽ ፖለቲካዊ ግብ ለመጠቀም ከአውድ ውጪ ባልተረጋገጠ መረጃና በአሉባልታ የሚናፈሰው የማህበራዊ ሚዲያ ዘገባ የተሳሳተና መሰረተቢስ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር አበክሮ ለመግለጽ ይወዳል" ብሏል፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መግለጫ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ተወሰነ!

ሦስተኛ ስብሰባውን ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ያካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ዛሬ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውስኔዎችን አሳልፏል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ያሳለፈው ወሳኔ ተጠቃሽ ነው።

"አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል።

ኮሚቴው ያመነበት ይህ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ሌሎች ለብሔራዊ ባንክ ቦርድ ቀርቦ መጽደቁንም መግለጫው አመልክቷል።ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ በሚያስገድደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ባንኮች መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 2022 ጀምሮ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ብድራቸው አምስት በመቶ የሚሆነውን ለዚህ የቦንድ ግዥ ሲያውሉ ቆይተዋል። በዚህ መመሪያ መሠረት የገዙት ቦንድ የሚመለሰው (ለቦንድ ግዢ ያዋሉት ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው) ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ ሲሆን ፣ ባንኮቹ መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ወር አንስቶ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2024 ድረስ የገዙት የቦንድ መጠን 94 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት ዕዳ መግለጫ ያመለክታል።

በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ያሳለፈው ሌላኛው ውሳኔ በባንኮች ላይ የተጣለውን የብድር ዕቀባ የተመለከተ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት በባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ጣሪያ እስከ መጪው መስከረም 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጠል ኮሚቴው ወስኗል።ለዚህም የሰጠው ምክንያት አሁን ላይ የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ እየተስተዋለ ቢሆንም ይህንን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በባንኮች ላይ የተጣለው የብድር ዕድገት ጣሪያ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልጽ ነው።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
"በ11 ወራት 815 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰብኩ" -የገቢዎች ሚኒስቴር

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ታክስና ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ከ900 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ባለፉት 11 ወራት 815 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል ፡፡

በወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ላይ በተደረገው የቁጥጥር ስራ 19 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል ፡፡

የሥነ ምግባር ጉድለት የታየባቸው 405 ሰራተኞች ከጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከ ስንብት የሚደርስ ርምጃ ከመውሰድ ባለፈ በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጉን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በህወሓት እና ሻዕቢያ መካከል የተፈጠረው ጥምረትና ግንኙነት በፌደራል መንግሥቱ መቋረጥ አለበት ሲሉ የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ!

በቅርቡ ህወሓትና ሻዕቢያ ጥመረት እየፈጠረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ የሁለቱ አካላት ጥምረት በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሊቋረጥ ይገባል ሲሉ የቀድሞ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አሳስበዋል፡፡የቀድሞዋ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፤ "ይህንን ለጦርነት የተደረገ ጥምረት መንግሥት ሊያቋርጠው ይገባል" ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላው የቀድሞ የድርጅቱ አባልና ከፍተኛ አመራር እንዲሁም የዲሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ መስራች ውስጥ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት በበኩላቸው፤ "የሁለቱ አካላት ጥምረት ዓላማ ግልፅ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ህወሐትና የኤርትራ መንግሥት ጥምረት መፍጠር ለጦርነት ዓላማ የተደረገ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል።

በተጨማሪም በትግርኛ "ፅምዶ" ወይንም "ጥምረት ለሀቀኛ ሰላም ለትግራይ እና ኤርትራ" በሚል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እየተደረገ መሆኑንም መመልከት ተችሏል።ይህንን ጥምረት በሚመለከት ሀሳባቸውን የሰጡት የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም "በግልፅ ለጦርነት የተደረገ ጥምረት ነው" ብለዋል።

"ሕዝብን ከተደቀነበት ጦርነት ማዳን ላይ መስራት አለብን" ያሉ ሲሆን፤ ጦርነቱ የማይቀር እንኳን ቢሆን ዱላው ሕዝብ ላይ እንዳያርፍ መስራት አለብን" ሲሉም ገልጸዋል።"አሁን ላይ በግልፅም ይሁን በድብቅ ጥምረቱ ይታያል" ያሉት ወይዘሮ ኬሪያ፤ "ይህንን ማስቆምና መቁረጥ ያለበት የትግራይ ሊሂቃንና ፌደራል መንግሥት ነው በማለት ሀሳባቸውን" ሰጥተዋል።

ሌላው ሀሳባቸውን ለአሐዱ የሰጡት የቀድሞ የህወሕት አባልና ከፍተኛ አመራር ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፤ "በአንድ ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ ከሌላ ሀገር ጋር ማን ግንኙነት መፍጠር እንዳለበት ይታወቃል" ብለዋል፡፡"ሕገ-ወጥ ግነኙነት ሲኖር ደግሞ ማስቆም ያለበት ማን እንደሆነም ግልፅ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።"ይሁን እንጂ ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት ያልጠራ ነው፤ ነገር ግን ግንኙነቱ በመርህ ላይ ካልተመሰረተ ትክክል አይለም" ሲሉም ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህ ጥምረት ዙሪያ የፌደራል መንግሥት በግልፅ ያስታወቀው ነገር ባይኖርም፤ ባለፈው ሳምንት አርብ በትግራይ ሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ የሚጠይቅ ወይይት ተካሂዶ ነበር።የፌደራል መንግሥት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከልን በመወከል የተገኙት አቶ መለሰ አለሙ፤ "የፌደራል መንግሥት ኃላፊነት እንዳለ ሆኖ የትግራይ ፖለቲከኞችም ለሰላም ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል።"የድንበር ጉዳይን በተመለከተ መንግሥት ሉዓላዊነቱን በፍፁም አሳልፎ አይሰጥም" ያሉም ሲሆን፤ የውስጥ ችግሮች ከተፈቱ ሌላውን ማስተካከል እንደሚቻል ተናግረዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🎨 Graphic Design Course Registration Now Open!
Unlock your creativity and learn the skills to design stunning visuals for social media, branding, and more.
Beginner-friendly
Hands-on projects
Certificate included

📅 Limited seats – Register today!

Call us:
          ☎️
0989747878
0799331774

@merahyan
Forwarded from YeneTube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምሽት አይበግረንም!

ለሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ
📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት

👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።

ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35

Telegram username
@Ruthtemersales

Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
Forwarded from YeneTube
አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ

https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN

በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
  44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
  አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ
Forwarded from YeneTube
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Final Week – Week 4 Sessions


We're closing out our 14-part expert-led workshop series with two crucial technical sessions in Week 4:

🧱 Concrete Design & Specifications
📏 Technical Specs & Measurement Methods


📅 Tuesday, June 24, 2025
📍 The Urban Center, Addis Ababa
🖥 Live on TUC Facebook page & Google Meet (link shared 30 min before each session)
☕️ Free sessions with refreshments

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7

🔗 Let’s finish strong, join the conversation, contribute your perspective, and help shape Ethiopia’s future building code.

Many thanks to all our incredible partners for making this journey possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #EngineeringEthiopia #ConstructionStandards #UrbanDevelopment #ProfessionalEngagement
በአሜሪካ እርዳታ ስረዛ ምክንያት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የ14 ሚሊዮን ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ እንደሚችል ተጠቆመ!

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለውጭ ሰብዓዊ እርዳታ ትሰጥ የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ መሰረዛቸው በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ ሊያደርግ እንደሚችል ዘ ላንሴት የተባለው ተቋም የሕክምና ሪፖርት ጠቆመ።ካለ እድሜያቸው ሕይወታቸው ከሚያልፉት ውስጥ ሲሶ ያህል ሕፃናት መሆናቸውን የጥናቱ ግኝት አሳይቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈው መጋቢት የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) የሚሰጡ 80 በመቶ መርሐ ግብሮችን መሰረዙን ተናግረዋል።ከጥናቱ ፀሐፊዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዴቪድ ራሰላ "ለበርካታ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገራት ውጤቱ ከዓለም አቀፍ ወረርሽኝ አሊያም ከግዙፍ ግጭት ጋር የሚነፃፀር ነው" ብለዋል።

የረድኤት ድጋፉ "ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በተጋላጭ ሕዝቦች ጤና ላይ የታየው እድገት በአፋጣኝ እንዲገታ ወይም ወደነበረበት እንዲመለስ አደጋ ደቅኗል" ሲሉ በባርሴሎና ዓለም አቀፍ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ዴቪድ ራሰላ አክለው ተናግረዋል።ሪፖርቱ የወጣው የዓለም መሪዎች በስፔን ሰቪል ከተማ በዚህ ሳምንት በመንግሥታቱ ድርጅት የተመራ እና ከአስር ዓመታት በኋላ ግዝፉ የሆነው ጉባኤ ከመካሄዱ አስቀድሞ ነው።

ከ133 አገራት የተገኘ መረጃን የተመለከተው የተመራማሪዎች ቡድን በግመታው እ.አ.አ ከ2001 እስከ 2021 ድረስ በማደግ ላይ ባሉ አገራት የዩኤስኤአይዲ ድጋፍ 91 ሚሊዮን ሰዎችን ከሞት የታደገ ነው።ተመራማሪዎች ከወራት በፊት በአሜሪካ መንግሥት ይፋ የተደረገው 83 በመቶ ድጋፍ መቀነስ የሞት ምጣኔን ከፍ እንደሚያደርግም ግመታቸውን አስቀምጠዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የእርዳታ መሰረዙ ሕይወታቸውን መታደግ እየተቻለ 14 ሚሊዮን ሰዎችን ወደ ሞት ይመራል ብለዋል።ይህ አኃዝ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 4.5 ሚሊዮን ሕፃናትን ጨምሮ ሲሆን ይህም ማለት 700 ሺህ ሕፃናት በየዓመቱ ሕይወታቸው ያልፋል ማለት ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በአንድ ማዕከል ብቻ 7 ሺህ 500 የሚሆኑ የልብ ህሙማን ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል 7 ሺህ 500 የሚሆኑ የልብ ህሙማን ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ አስታወቀ።ወረፋ እየጠበቁ ከሚገኙት ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከተወለዱ ጀምሮ በሚከሰት የልብ ህመም ተጠቂ ህፃናት መሆናቸውን የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ኤልኤዘር ሃይሌ ገልጸዋል።

የልብ ህሙማኑን ለመርዳት ለማዕከሉ የሚበረከቱ ግብአቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውቀው፤ ለማዕከሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ ከውጪ የሚገቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በተለይ አላቂ የህክምና ግብዓቶች በየህፃናቱ የክብደት መጠን ልክ እንደሚገዙ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በድጋሚ መጠቀም የማይቻሉ ግብዓቶች በመሆናቸው የህክምናውን ሂደት አደገኛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ግብአቶቹ ዋጋቸው እጅግ በጣም ውድ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የልብ ቫልቮች፣ ልዩ ልዩ ማሽኖች፣ ልዩ ልዩ መድሀኒቶች እንዲሁም ልብን በማቆም ለሚሰሩ ቀዶ ጥገናዎች የሚውሉ የተለያዩ ግብአቶች ለማዕከሉ ወሳኝ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች 6710ን በመጠቀም፤ በግልም ሆነ በቡድን ታማሚዎችን በመጎብኘት፣ ታማሚዎችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ስፖንሰር በማድረግ እንዲሁም ከማዕከሉ በሚያገኙት ዝርዝር መሰረት በግብዓት አቅርቦት መደገፍ እንደሚችሉ መጠቆማቸውን ከፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
“በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስራት እየተፈጸመ ነው” - ሂዩማን ራይት ፈርስት

ሂዩማን ራይትስ ፈርስት የተሰኘ የሃገር ውስጥ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች በከተማዋ ባለስለጣናት ኢላማ ተደርገው፣ ያለምንም መደበኛ ክስ እና ፍርድ ሂደት በማንነታቸው ምክንያት “የዘፈቀደ እስራት” እየተፈጸመባቸው ነው” ሲል ክስ አቀረበ።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ትላንት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በፀጥታ ሃይሎች በዘፈቀደ እየታፈሱ እና በህገወጥ መንገድ እየታሰሩ እንደሚገኙ ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል።

ለእስር ተዳርገው በኋላ ላይ መፈታታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ያስታወቁ አንድ በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ለምን እንደታሰርን ስንጠይቃቸው ምንም አይነት ማብራሪያ አልሰጡንም ብለዋል፤ “ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ ነው” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን፤ ክስ አልተመሰረተብንም፣ ፍርድ ቤትም አለቀረብንም” ብለዋል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) እንዲሁም ሂዩማን ራይት ፈርስት “ዜጎችን ስማቸውን ወይም ብሄራቸውን መሰረት በማድረግ ለእስር መዳረግ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ህግጋትን የሚጻረር እና መጣስ ነው” ሲል በመኮነን “ያለ ፍርድ ሂደት ለእስር የታዳረጉት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” ሲሉ በተናጠል ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢባትሎ አዳዲስ መርከቦችን በሀገር ውስጥ ባንኮች ድጋፍ ሊገዛ ነው!

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) የአስር መርከቦች ባለቤት የመሆን ግቡን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት፣ አዳዲስ መርከቦችን ለመግዛት ማቀዱን እና ለዚህም ከሀገር ውስጥ ባንኮች የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን አስታውቋል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ እና ዳሽን ባንክ ይህንን ግዙፍ ግዢ በጋራ ለመደጎም መስማማታቸው ተገልጿል።

ኢባትሎ አዲስ ሁለት የአልትራማክስ ሁለገብ የደረቅ ጭነት መርከቦችን ለመግዛት ጨረታ ያወጣ ሲሆን፣ በተጨማሪም አራት ያገለገሉ መካከለኛ መጠን ያላቸው መርከቦችን በመርከብ ደላሎች በኩል ለመግዛት ማቀዱን ካፒታል ሰምቷል።

የፋይናንስ ስምምነቱ ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ አዋሽ ባንክ እና ዳሽን ባንክ ለአንድ ሁለገብ መርከብ እና ለአንድ የአልትራማክስ ደረቅ ጭነት መርከብ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሌላ በኩል አዲስ የአልትራማክስ ሁለገብ እና ሁለቱን ያገለገሉ ኮንቴይነር መርከቦችን ጨምሮ የሦስት ተጨማሪ መርከቦችን ግዥ ለመደገፍ ተስማምቷል።

በአጠቃላይ፣ ኢባትሎ ለአምስቱ መርከቦች ጠቅላላ ወጪ 30% የሚሆነውን በራሱ የሚሸፍን ሲሆን፣ ቀሪው 70% በባንኮቹ ይሸፈናል። ከዚህም ባሻገር፣ አንድ መርከብ በሙሉ በተቋሙ ፋይናንስ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ኢባትሎ ያገለገሉትን አራት መርከቦችን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለመረከብ ሲጠብቅ፣ የአዲሶቹ ሁለት ሁለገብ መርከቦች ግንባታ ግን የጨረታ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ቢያንስ ሁለት ዓመታትን ይወስዳል ተብሎ ይገመታል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
2025/07/01 11:10:27
Back to Top
HTML Embed Code: