Telegram Web Link
ዛሬ የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ማድረግ ላይ እንደሚገኙ ከተለያዩ ሆስፒታሎች ከሚላኩልን መረጃዎች መመልከት ችለናል።

ሆኖም የስራ ማቆም አድማውን ያልተቀበሉ መኖራቸውን ተመልክተናል።


@Yenetube
👍552
የቡና ላኪዎች የመነሻ ካፒታል በ900 በመቶ እንዲጨምር ያደርጋል የተባለው ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ!

የግብርና ሚኒስቴር የቡና ላኪዎች የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት የሚጠይቀውን ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል በግለሰብ ደረጃ በ900 በመቶ እንዲሁም ለአክሲዮን ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ጭማሪ የተደረገበትን ረቂቅ መመሪያ አዉጥቷል።

በዚሁ ረቂቅ መሰረት፣ የግል የቡና ላኪዎች ከዚህ ቀደም ይጠበቅባቸው የነበረው አንድ ሚሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ወደ 10 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ታቅዷል። በተጨማሪም፣ አመልካቾች የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴን የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ለአክሲዮን ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት የሚፈለገው ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል ከ 1 ሚሊዮን 500 መቶ ሺህ ብር ወደ 15 ሚሊዮን ብር ከፍ እንዲል የቀረበ ሲሆን፣ ከማህበሩ መስራቾች መካከል ቢያንስ ሁለቱ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይላል።


Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍173🔥1
📲iPhone 11promax
💾Internal Storage:256GB
🔋battery:87%
👌Original almost new
💲PRICE-46000birr
♦️Dont miss out on this!
☎️Contact: @Endalk4240 0929008292
Join channel: https://www.tg-me.com/phonestore_2
😁9👍6👎1😭1
ጎንደር ዪንቨርስቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሰራተኞቹ ማስጠንቀቂያ ለጥፏል። የስራ ክፍላችሁ ላይ አለመገኘታችሁን አረጋግጠናል ይላል ማስታወቂያ።

ከዛሬ 8:00 ጀምሮ በስራ ክፍላቹ እንድትገኙ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።


ጎንደር
👎104😁13👍91👀1
በኢትዮጵያ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንዴት ምላሽ ያግኝ?

የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ያነሱ የጤና ባለሙያዎች መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ ያለበለዝያ አድማ እንደሚመቱ ካስጠነቀቁ ሳምንታት ተቆጠሩ። የጤና ባለሞያዎቹ የመንግሥትን ምላሽ ለመጠበቅ ያስቀመጡት የሰላሣ ቀናት ቀነ ገደብም ዛሬ ተጠናቋል። በምናገኘዉ ደሞወዝ "መኖር አቅቶናል" ሲሉ እስከዛሬ በተለያዩ መንገዶች ቅሬታቸዉን ሲያሰሙ ከዘለቁት የጤና ባለሙያዎች መካከል የታሰሩም እንዳሉም ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት እንዲፈቱ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠይቋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የጤና ባለሞያዎች ከተወሰኑ አንገብጋቢ የሥራ ክፍሎች በስተቀር ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀው ነበር። በሀገር አቀፍ ደረጃ ይደረጋል የተባለው የሥራ ማቆም አድማው መጀመሩን የሚጠቁሙ መረጃዎች መኖራቸውን ዶይቼ ቬለ ለመገንዘብ ችሏል።

ከባለሙያዎቹ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢያችሁ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምን ታዘባችሁ? በኢትዮጵያ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንዴት ምላሽ ያግኝ? አስተያየቶን ይጻፉልን!

@Yenetube @Fikerassefa
👍423👀3👎1
የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በማንሳት ለመንግሥት የሰላሳ ቀናት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥተው የነበሩት የጤና ባለሙያዎች ምላሽ ባለማግኘታቸው ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

ባለሙያዎች ከጥቂት "የተመረጡ የሕክምና ክፍሎች" ውጪ ያሉ ክፍሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ከዛሬ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ማቆማቸውን ገልፀዋል።

የቢቢሲን ዘገባ ያንብቡ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9893ed807po
👍643👎2👀2
የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊል የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ የተጀመረውን የከፊል የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ ሲሞክሩ ከመንግሥት አካላት ማስፈራሪያና ጫና እንደደረሰባቸው አስታወቁ።

#በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ በሚገኘው የማዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና የሰራተኛ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች አድማውን ለማድረግ ሲሞክሩ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጫና እንደገጠማቸው አስረድተዋል።

ባለሙያው "ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው" ያሉ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ ከማለዳ ጀምሮ "በመንግስት የስራ ሀላፊዎች የተሞላ" እንደነበር ጨምረው ተናግረዋል።

ሌላኛው በአማራ ክልል ደቡብ #ወሎ ዞን በአቀስታ ከተማ የአቀስታ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ በበኩላቸው በድንገተኛ ክፍል የተመደበ አንድ ሀኪም "በፀጥታ ሀይሎች" ተይዞ የተለመደውን የህሙማን ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አልያም "ወደ እስር ቤት እንዲሄድ" እንደተነገረው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተጠርቷል የተባለውን የህክምና ባለሙያዎች አድማ ለመታዘብ በሶስት ዋና ዋና የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #በየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ቅኝት ያደረግን ሲሆን በእነዚሁ ተቋማት ከሰዓት በኋላ ስራ የተጀመረ ይሁን እንጂ ጠዋት ላይ የከፊል የስራ ማቆም መካሄዱን ታዝበናል።

የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ይመልከቱ

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7748
👍40🔥5👀32😭2
ከቆሙ ተሽከርካሪዎች ላይ ሠሌዳ በመፍታት የሚሸጡ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

በረከት ማዕረጉ እና ሚኪያስ ባየልኝ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 7:00 ሠዓት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ለገሀር ግቢ ውስጥ በአጥር ዘለው በመግባት ከሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ የፊትና የኋላ ሠሌዳ ፈትተው ሲወጡ በወቅቱ የነበሩት የጥበቃ ሠራተኞችም ሊይዟቸው ባለመቻላቸው አምልጠዋል።

ነገር ግን በሠዓቱ በአካባቢው በስራ ላይ የነበሩ የወንጀል መከላከል አባላት በዚያ ሌሊት ሚኪያስ ባየልኝ ሲሮጥ በማግኘታቸው በቁጥጥር ስር አውለው ሲፈትሹት የተሽከርካሪ ሠሌዳ በማግኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋሉን በቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፖፑላሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል።

ፖሊስም ከሚኪያስ ባየልኝ ጋር አብሮት በወንጀሉ ተሳታፊ የነበረውን በረከት ማዕረጉን በቀጣዩ ቀን በመያዝ ባደረገው ምሪት የሠረቀውን ሠሌዳ ከደበቀበት የመኖሪያ ቤቱ ኮርኒስ ውስጥ መርቶ ሊያመጣም ችሏል።የምርመራ ክፍሉም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተገቢውን ምርመራ የማስፋት ተግባር እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ግለሠቦቹ አንዱን ሠሌዳ በ4ሺህ ብር እንደሚሸጡም የወንጀል ምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

በየጊዜው የወንጀል ድርጊቶች መልካቸውንና ጸባያቸውን እየቀያየሩ እየተፈጸሙ ሲሆን በተለይም አንዳንድ ጊዜ በከተማችን የሚከሰቱ የሿሿና ሌሎች ወንጀሎች፤ በመሠል ሁኔታ የሚሠረቁ ሠሌዳዎችን በመጠቀም ስለሚሆን ህብረተሠቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጀምሮ መረጃ የመስጠት ተግባሩን ማጠናከር እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍333😁1
“ የዲኤችኤል/DHL ሰራተኞች ነገ ወደ ስራ ይመለሳሉ፡፡ ለሰራተኞቹ የ 35 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ይደረጋል”


ባለፈው ሐሙስ ከአሰሪው ድርጅት ጋር ባለመግባባታቸው ስራ ያቆሙት የዲኤችኤል/DHL ሰራተኞች ስራ ማቆማቸውን ተከትሎ ከዛ በኋላ በተደረገ ድርድር የሰራተኛ ማህበሩና ድርጅቱ የ35% የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ከስምምነት ላይ በመድረሳቸው በነገው ዕለት ወደ ስራ ይመለሳሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
👍26
የጤና ባለሞያዎችን በማስታወቂያ ወደ ስራ መደባቸው እንዲገብ የተለያዩ ሆስፒታሎች ቢያስጠነቅቁም የጤና ባለሙያዎች አድማውን እንደሚቀጥሉ አንድ አንድ ያናገርናቸው ባለሙያዎች ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍44👎31
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ  (Direct/ Whatsapp) ፦ በ
0909253426 / 0940407294 ይደውሉ
1👍1
2025/07/13 14:38:04
Back to Top
HTML Embed Code: