Telegram Web Link
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ  (Direct/ Whatsapp) ፦ በ
0909253426 / 0940407294 ይደውሉ
👍1
Forwarded from YeneTube
📒 ውድ የ International Student Community እና Refocus Africa ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ 🎉

International Student Community ከ Refocus Afrika ጋር በመተባበር የፊታችን 🗓 May 24 እና 25 ( ግንቦት 16 እና 17) ልዩ የ Cultural Exchange እንዲሁም የ Scholarship Process Guidance 🎆ይዞላችሁ መቷል !!!

🗺️ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 kilo Alamudin ህንፃ አዳራሽ 🏚️
ከ ጠዋቱ 2:00 እስከ 11:00 ሰአት

ትምህርታቹን ውጭ ሀገር ሄዶ የመማር ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችሁአል።

፨ በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ በማስተርስ እንዲሁም በዶክተሬት ዲግሪ👨🏾‍🎓

በዕለቱ ሲገኙ ፦
📕ፓስፖርት/ የልደት ሰርተፍኬት
📝ትራንስክሪፕት ይዘው መምጣት እንዳይረሱ

🌍የዚህ እድል ተሳታፊ በመሆን የወደፊት የትምህርት ጉዞዎን ይጀምሩ✈️

ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ ፧‼️

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ #ይጫኑ 👇👇
https://forms.gle/SJ6nzXdNAixTptGv5

Join our telegram channel
➡️ https://www.tg-me.com/isc_italy
👍8
የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማኅበር፣ የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች እንዲፈቱ ጠየቀ!

የጤና ባለሙያዎች ሙሉ የሥራ ማቆም አድማ ሦስተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማኅበር፣ የሚድዋይፎች የተጋላጭነት አበል፣ የተጨማሪ ሰዓት ክፍያና የሥራ ወሰን እንዲወሰን ጥያቄ ማቅረቡን፣ የአገሪቱ የጤና ዘርፍ ማሻሻያ የጤና ባለሙያዎችን መብት ባረጋገጠ መልኩ እንዲቀረጽና ይህንኑ የሚከታተል የጋራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በተደረገ ውይይት መጠየቁን ገልጧል።

ማኅበሩ፣ መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎቹ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሠጥና ከመብት ጥያቄው ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችም እንዲፈቱ መጠየቁን ዋዜማ ዘግባለች፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍35👎1
አውስትራሊያ በእስራኤል ካቤኔ ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ እንድትጥል ጥያቄ ቀረበ

የአውስትራሊያ የአለም አቀፍ ፍትህ ማእከል (ACIJ) የአውስትራሊያ መንግስት በቀኝ አክራሪ የእስራኤል የካቢኔ ሚኒስትሮች ኢታማር ቤን-ጊቪር እና ቤዛሌል ስሞትሪች ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጠይቋል።

የACIJ ዋና ዳይሬክተር ራዋን አራፍ በቅርቡ ከካናዳ፣ ፈረንሣይ እና እንግሊዝ የወጣው የጋራ መግለጫ እንደሚያሳየው አውስትራሊያ በእስራኤል የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ማዕቀብ እና የጦር መሳሪያ እገዳን ጨምሮ “ተጨባጭ እርምጃ እንድትወስድ” “አሁንም አልረፈደም” ብሏል።

"አውስትራሊያ ግዴታዋን በቁም ነገር የምትወስድ ከሆነ የጋዛ ሰርጥ ውድመትን በተመለከተ ስሞትሪች የሰጡትን አስደንጋጭ መግለጫ ላይ የወንጀል ምርመራዎችን መክፈት አለባት" ብለዋል። "ማዕቀቦች እንደዚህ አይነት ከባድ ጥሰቶችን ለመከላከል እና ለመቅጣት አንድ እድል ናቸው" ሲልም አክሏል።

አውስትራሊያም “በእስራኤል ላይ የሁለት መንገድ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መጣል አለባት” የሚለው ማዕከሉ ቀጣይነት ያለው ወታደራዊ ንግድ እና ትብብር የእስራኤልን ህገወጥ ወረራ ለማጠናከር እና ወታደራዊ መዋቅሯን ለማጎልበት ብቻ ነው የሚያገለግለው ሲልም አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍146👎1
YeneTube pinned a photo
የጋብቻን ወጪ የሚከለክል ደንብ

የሶማሌ ክልል አላስፈላጊ የጋብቻ ወጪዎችን የሚከለክል ደንብ አጸደቀ

ደንቡን  መጣስ የገንዘብና እስር ቅጣት ያስከትላል ተብሏል።


የሶማሌ ክልል፣ የወጣቶችን የጋብቻ ጫና ለመቀነስ  አላስፈላጊ የጋብቻ ወጪዎችን የሚከለክል ደንብ ማጽደቁ የተገለጸ ሲሆን፤ ደንቡን  መጣስ የገንዘብና እስር ቅጣት ያስከትላል ተብሏል፡፡

የክልሉ የሐይማኖትና ባህላዊ መሪዎች፣ ጋብቻን ተከትሎ የሚወጣውን የተጋነነ ወጪ በመቀነስ ወጣቶች ከትዳር እንዳይሸሹ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሀማሮ የእስልምና ምክር ቤት፣ ከጋብቻ በፊት ግመል ማረድ እንዲሁም ሴቶች በሚታጩበት ወቅት የሚሰጡ የተለያዩ ውድ ስጦታዎች ቅዱሱ የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ  አስገዳጅ የገንዘብ ጫና እንዲፈጥር አድርጎታል በሚል ስጋት አዋጁ ሊወጣ ችሏል ብሏል።

አዋጁ በተለይም ገበቲ ተብሎ የሚጠራውንና የሙሽራው ቤተሰቦች ለሙሽራዋ ጎረቤቶች የሚያከናውኑት ተመላሽ የግመል ጥሎሽ ስርዓት ማሕበራዊ ጫናን ያሳድራል በማለት ማስቀረቱ ተዘግቧል።

የክልሉ የሐይማኖትና  ባህላዊ መሪዎች ሕጉን መጣስ የገንዘብና እስር ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
👍938😁7👎1
97 በመቶ የጤና ሰራተኞች ደመወዛቸው መሰረታዊ ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ!

በአፍሪካ የህዝብ ጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች ከባድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የሚያሳይ አዲስ ጥናት ይፋ ሆኗል።በአክሽንኤይድ ኢንተርናሽናል የወጣው “በአፍሪካ የመንግስት ዘርፍ ቅነሳ የሰው ልጅ ዋጋ” የተሰኘው ጥናት፣ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ላይቤሪያ፣ ማላዊ እና ናይጄሪያ) የቁጠባ ፖሊሲዎች በሰው ልጅ ላይ የሚያስከትሉትን ከፍተኛ ዋጋ አጉልቶ አሳይቷል።

የጥናቱ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት፣ 97 በመቶ የሚሆኑት የጤና ሰራተኞች ደሞዛቸው የቤት ኪራይ፣ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ የቤት ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።በተመሳሳይ፣ ከ2020 ወዲህ 84 በመቶ የሚሆኑት አስተማሪዎች እውነተኛ ገቢያቸው ከ10 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

ይህ ደመወዝ በቂ አለመሆን የሰራተኞችን የኑሮ ጫና በእጅጉ እንደጨመረ ተመላክቷል።
እንደ ግኝቱ መሰረት ፣ የመንግስት በጀት ቅነሳ እና እየጨመረ የመጣው የተማሪዎችና የታካሚዎች ቁጥር ከፍተኛ የስራ ጫና ፈጥሯል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
52👍39😭6👀3👎1
Forwarded from HuluGames Community
🎁 የ 5000 ብር ገንዘብ ሻሞ! 🎁

ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ማታ 3:00 ላይ፣ 🤖 ሁሉፔይ በዕጣ 10 አሸናፊዎች የሚያገኙ 500 ብር በጥሬ ገንዘብ ይመርጣል! 💰

በዚህ ሻሞ ለመሳተፍ:
ከዚህ በታች ያለውን "ሻሞውን ተቀላቀል" የሚለውን ይጫኑ

የማሸነፍ እድልዎን አያምልጡ!
👍81
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ፈረንሳይ ፓሪስ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ጋር በመሆን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓሪስ ሲደርሱ በብሔራዊው የጦር ኃይሎች ሙዚየም የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ተደርጎላቸዋል።

በጉብኝታቸው ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👎133👍2716😁5
#ከቴምር ሪልስቴት
🎯🎯7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

👉2መኝታ 84ካሬ 5,392,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 106ካሬ 6,869,400ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 125ካሬ 8,025,000ብር ሙሉ ክፍያ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
👍109😁1
YeneTube pinned a photo
እንኳን ወደ Refocus Afrika ከ ISC Ethiopia ጋር በመተባበር ወደ አዘጋጀው ፕሮግራም በሰላም መጡ።

Refocus Afrika የ ፖን አፍሪካን ኦርጋናይዜሽን ሲሆን በ 26 የ አፍሪካ ሀገራት በተለያዮ ስራዎች በ ኢንቨስትመንት በግብርና እንዲሁም በትምህርት ላይ አተኩሮ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።

ሰለሆነም በመጪው ግንቦት 16 እና 17 ( ቅዳሜ እና እሁድ ) በአዲስ አበባ 6ኪሎ ዮኒቨርሲት ሜን ካምፖስ በተዘጋጀው የኢንተርናሽናል ሬክሩትመንት እና ካልቸራል ኤክስቼንጅ በሚል መሪ ቃል በሚካሄድው ኢቨንት ላይ እንድትገኙ ስንል እየጋበዝን በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ አምባሳደሮች ከሀገር ውስጥና የውጭ ዮኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የክብር እንግዶች የሚገኙ ሲሆን በዚህ ታላቅ ዝግጅት ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

📆 May 24 & 25( ግንቦት 16 - 17)
🕐 2:00 - 10:00 (LT) 
📍Addis Ababa university 6 kilo

ለመመዝገብ ከታች ያለውን Link ተጠቅመው ይመዝገቡ 👇🏻

https://forms.gle/tq7wa5neLGkpPAsU9
👍9
Forwarded from YeneTube
🟥📣የመጨረሻ ዲያስፓራ ቁ3 ብሎክ 

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለውስን ቤቶች) በመጠቀም
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 72 42 75 95     

➡️@Tirsit9 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://whatsapp.com/dl/code=gsXOc8ttJB?mode=tac
👍3😭1
Forwarded from YeneTube
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍3
#በዩኔስኮ የተመዘገቡት የ #ኮንሶ አምባ መንደሮች ቅርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቀርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ።

የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ሰራዊት ዲባባ እንደገለጹት፤ ዩኔስኮ 12 የኮንሶ አምባ መንደሮችንና የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤን ዓለም አቀፍ ቅርስ አድርጎ መዝግቧል::

በእነዚህ አምባ መንደሮች ባህላዊ ቤቶች፣ ባህላዊ መሰብሰቢያ ስፍራዎች፣ የትውልድ መቁጠሪያ ትክል እንጨቶች፣ የጀግንነት መዘከሪያ ሀውልቶች እንዲሁም ሌሎች የኮንሶን ህዝብ እሴትን የሚያሳዩ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ቅርሶች እየተጠበቁ ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራ የቆየ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት ግን በአምባ መንደሮቹ ጎጆ ቤቶችን ቆርቆሮ በማልበስ ቅርስነቱን እንዲለቅ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቅርሱ ይዘት ላይ የተጋረጠው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊው፤ በአሁኑ ሰአትም ከመንደሮቹ ካሉት ቤቶች 50 በመቶ የሚሆኑት ቅርስነታቸውን በሚለቅ መልኩ ቆርቆሮ መልበሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ምክንያቱ ስለ ቅርሱ ያለው የግናዛቤ ክፍተት እንዲሁም በአካባቢው የሳር አቅርቦት አለመኖር ሲሆን፤ ይህንን ችግር ለመፍታትም ግንዛቤ የመፍጠርና በክልሉ እንዲሁም በፌደራል መንግስት የሚተዳደሩ ፓርኮች ሳሮችን የሚያቀርቡበት አሰራር መፍጠር ላይ እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው፤ ቅርሱን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ነዋሪዎች የሚያነሱት አንዱ ጥያቄ የሳር ክዳን መወደድ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ ክልሉ በሚያስተዳድረው ማዜ ብሄራዊ ፓርክ በተወሰነ ቦታ ላይ ሳር ለማልማት ፕሮጀክት እየተነደፈ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
@Yenetube
👍17😭73
ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ!

ሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ "በሀገሪቱ ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በማበር ሕገ ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ በጤና ዘርፉ ላይ ሁከት በመፍጠር እና የታካሚዎችን ሕይወት አደጋ ላይ በመጣል የተጠረጠሩ" 47 የጤና ባለሙያዎችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

እነዚህ ተጠርጣሪዎች የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የደመወዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ እንደሽፋን በመጠቀም ሕገ-ወጥ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፤ ሌሎችም ሥራ እንዲያቆሙ ለአድማ በማነሳሰት፣ የታካሚዎች ሕይወት ለሞትና ለአደጋ እንዲጋለጥ በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር የተጠረጠሩ መሆናቸውንም ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ የጤና ተቋማት የአድማ መረቦችን በመዘርጋት፤ የጤና ባለሙያ ያልሆኑ አካላትን ነጭ ጋዋን በማስለበስ የሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብተው ሁከት እንዲፈጥሩ በማድረግ፣ ያልተገባ ወሬ በመንዛት እና በተለያየ መንገድ ሰላማዊ የሕክምና ሂደትን በማደናቀፍ የሕሙማንና የጤና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማድረግ፣ በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት እና ትምህርት በሚሰጥባቸው ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲስተጓጎል ማድረጋቸውንም የፌደራል ፖሊስ ወቅታዊ መረጃን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ሙያቸውን አክብረው በሥራ ላይ በተገኙ ባልደረቦቻቸው ላይ ዛቻ እና ማስፈራራት ከማድረስ ባለፈ ሁከት እንዲፈጠር ሙከራዎችን አድርገዋል ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በመረጃና በማስረጃ በመለየት በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጤና ባለሙያዎቹ የሙያው ሥነ-ምግባርና ሕግ በማይፈቅደው ሁኔታ የዜጎችን ሕይወት ለሞትና ለአደጋ በማጋለጥ ሥራ ማቆም፣ ሌሎችም ሥራ እንዲያቆሙ ማነሳሳት እና ማስፈራራት የወንጀል ተግባር መሆኑን የገለጸም ሲሆን፤ ሌሎችም ከዚህ ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

የፌደራል ፖሊስ ሕዝባቸውን እና ሕግ አክብረው አገልግሎት እየሰጡ ላሉ የጤና ባለሙያዎች ፖሊስ አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግ ያረጋገጠም ሲሆን፤ ከዚህ ውጭ ሁከትና ብጥብጥን ለማስፋፋት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ፖሊስ እየወሰደ ያለውን ሕጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👎96👍28😁211😭1
2025/07/10 23:28:55
Back to Top
HTML Embed Code: