YeneTube
Photo
ስስ ፌስታል ይዞ የተገኘን ሰዉ እስከ 5 ሺህ ብር እንዲቀጣ የሚያዘዉ አዋጅ ጸደቀ!
ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ፤ ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2000 እስከ 5000 ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡
የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡
አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም መባሉን ሰምተናል፡፡አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታን ያስቀምጣል፡፡አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa

አቶ ታዬ ደንደአ ጉዳያቸውን ማረሚያ ወርደው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ!
የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው እንዲከታተሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል።አቃቤ ህግ በታዬ ደንደአ ላይ ከዚህ ቀደም አቋርጦት የነበሩ ሁለት ክሶችን ዳግም አንቀሳቅሷል።
ተከሳሹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡አቶ ታዬ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ በነበሩበት ወቅት የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደ ጎን በመተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 257 ንዑስ አንቀጽ (ሠ) በመተላለፍ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡
በዚህም በአሽባሪነት የተሰየመው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የታጠቁ ፀረሰላም ኃይሎች በአማራ ክልል ከመንግስት ጋር ጦርነት ላይ ባሉበት ጊዜ የእነዚህን ፀረሰላም ኃይሎች ፕሮፖጋንዳ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማሰብ በራሳቸው ስም በተከፈተ ማህበራዊ ሚዲያዎች የፕሮፖጋንዳ መልክቶችን ያስተላለፉ በመሆኑ ክስ ቀርቦባቸዋል።
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀርቦባቸው በነበረው ሁለት ክሶች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተው እንደነበር ይታወሳል።ተከሳሹ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ በመስጠት የመከላከያ ምስክርን ለመስማት ለሰኔ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

«የህወሓት አመራሮች ትግራይን ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ» ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ አሳሰበ!
የህወሓት አመራሮች ካለፈ ጦርነት ያላገገመች ትግራይ ዳግም ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ ሲል ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ገለፀ።በሌላ በኩል በክልሉ ተደቅኖ ያለ ፖለቲካዊ እና የፀጥታ አደጋ የሚያስቀር እውነተኛ ፖለቲካዊ ውይይ እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።
በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ እንዳለው ከኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት ባህሪ እንዲሁም እያካሄዱት ካለ የሚድያ ዘመቻ በመነሳት ሲታይ ወደ ጦርነት እያመሩ መሆኑ መረዳት ይቻላል ያለ ሲሆን፥ እነዚህ በጋራ በትግራይ ላይ ጦርነት ከፍተው የነበሩ ሐይሎች ዳግም ትግራይ የጦርነት አውድማ እንዳያደርጓት ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑ አመልክቷል።
የትግራይ ጉዳይ አጀንዳዎች ያለሆኑ የህወሓት መሪዎች፣ ትግራይ ካለፈው ጦርነት ጠባሳ ሳታገግም ወደ ሌላ ጦርነት የምትገባበት ፖለቲካዊ አካሄድ ከጀመሩ ቆይተዋል በማለት የከሰሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፥ በተለያየ አቅጣጫ ተሰልፈው ትግራይን ወደጦርነት እየገፉ ያሉ ቡድኖች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ብሏል።

Forwarded from YeneTube
የቻናል ጥቆማ!
የonline ስራዎችን ታገኙበታላችሁ!
🚀 Upwork Profile Mastery
Standout & land high-paying Upwork gigs!
✅ Profile Tips
✅ Proposal Templates
✅ Niche Strategies
📂 Free Tools + Examples
👉 Join: https://www.tg-me.com/UpworkProfilePro
መረጃዎችን ለመላክ @honelegn19
🎯 For Beginners:
• Profile Setup & Review
• Proposal Writing Help
• First Job & Rate Strategy
• Client Communication Tips
• Niche & Rules Guidance
• Contract & Tool Support
• Q&A Mentorship
🌟 Empowering freelancers with real strategies.
✨ መልካም እድል ለሁላችሁም!

🗝️ እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ
60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ
❇️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :
⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል
💸ቅድመ ክፍያ
💎ባለ 1 መኝታ በ 431 ሺ ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 619 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 751 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,051,626 ብር
🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ
🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)
➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ
➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ
➡️☎️ 09 31 14 82 42
➡️@Novi_03 (telegram)
➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242

#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው
🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል
👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision
The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.
Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.
📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here
#EthiopianBuildingCodeStandards
✅ Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector

ተቋሙ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትና ኃይል ላይ በተፈፀመ ስርቆት ከ199 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደረሰበት!
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትና ከኃይል ስርቆት ጋር በተገያያዘ 199 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብ ጉዳት እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ኢሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ጉዳቱ የደረሰው፤ በኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮች፣ ትራንስፎርመሮች፣ ኬብሎች ላይ በተፈፀመ ጉዳትና ስርቆት እንዲሁም ቆጣሪ በመነካካት፣ የኃይል ሰርቆት በመፈፀምና የተቋሙ ሰራተኞችን ስራ እንዳይሰሩ በማወክ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጧል።
በዚህም በዲስትሪቡሽን ትራንስፎርመሮች፣ በኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች፣ በኬብሎችና በሌሎች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመ ጉዳትና ስርቆት ብቻ 52 ሚሊዮን 33 ሺህ 123 ብር የሚገመት የገንዘብ ጉዳት በተቋሙ ላይ ደርሷል ተብሏል፡፡አገልግሎት አክሎ እንዳስታወቀው፤ መሰል እኩይ ተግባር በፈፀሙ ግለሰቦች ላይ 208 የክስ መዝገቦችን በመክፈት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ 27 የሚሆኑት መዝገቦች ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረግ ወንጀለኞቹ ላይ ከ2 ወር እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደረስ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል ብሏል፡፡ተቋሙ ህብረተሰቡ መሰረተ-ልማቶችን ከእኩይ ድርጊት እንዲጠብቅ እና ጉዳት የሚያደርሱና ስርቆት የሚፈፅሙ ግለሰቦችም ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለህግና ለፀጥታ አካላት እንዲያጋልጡ ተማፅኗል፡፡
ባሳለፍነው መጋቢት ወር በአማራ ክልል ከ ባህርዳር - ወልዲያ - ኮምቦልቻ በተዘረጋው ባለ 400 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት 129 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪሳራ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡በተመሳሳይ በሚያዚያ ወር ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ዝርፊያ መፈፀሙንና በአንዳንድ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡ ይታወሳል፡፡

ወጋገን ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን አገልግሎት መስጠት ጀመረ!
ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ በኢትዮጵያ በቅርቡ በተጀመረው የካፒታል ገበያ የመጀመሪያው የግል ኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።የባንኩ አገልግሎት ጅማሮ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ሲገለፅ የኢንቨስትመንት ባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አክሊሉ ውበት (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ በ385 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን፣ የካፒታል ገበያውን በቀዳሚነት ተቀላቅሏል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ብሩታዊት ዳዊት በበኩላቸው፣ ባንኩ በዘርፉ ፈር-ቀዳጅ በመሆን በታማኝነትና ጥራት የላቀ አገልግሎት በመስጠት የካፒታል ገበያውን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።ባንኩ የካፒታል አሰባሰብን በማመቻቸት ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ መድረኩ ተገልጿል።
Via Capital

“ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ቀንድ በኩሽ እና ሴም ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል ጥላቻን በመፍጠር ውጥረት እና ግጭት እንዲፈጠር እየሰሩ ነው” - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአፍሪካ ቀንድን ለማተራመስ እየጣሩ ነው፣ በሴም እና ኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች መካከል ጥላቻን በመፍጠር ውጥረት እና ግጭት እንዲፈጠር እየሰሩ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተቹ።
ፕሬዝዳንቱ “ኢትዮጵያን እና ሰፊውን የአፍሪካ ቀንድ ለማተራመስ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም” ሲሉም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሆርን ሪቪዩ ድረገጽ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት “የኢሳያስ አፈወርቂ የወቅቱ ፕሮጀክት ዋነኛ ትኩረት የአማራ እና የትግራይ ሚሊሻዎችን በማስተባበር እና በማቀናጀት የኢትዮጵያን የፌደራል መንግስት ለመጣል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
አምባሳደር ዲና በጽሁፋቸው የኤርትራው ፕሬዝዳንት “የኦሮሞ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጠላ ለማድረግ እየሞከሩ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፤ አምባሳደሩ ለዚህም ፕሬዝዳንቱ “ፍጹም ያልተረዱትን ፅንሰ ሀሳብ፣ ኦሮሙማን” በንግግራቸው ጠቅሰዋል ሲሉ ተችተዋል።
Via AS

ብሔራዊ ባንክ ሰባተኛውን የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ በ50 ሚሊዮን ዶላር ሊያካሂድ ነው!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና የውጭ መረጋጋትን ለመቆጣጠር ያለመ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ሐሙስ ግንቦት 28 እንደሚያካሂድ አስታውቋል።ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ ጨረታዎች ሰባተኛው ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና የውጭ መረጋጋትን ለመቆጣጠር ያለመ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ሐሙስ ግንቦት 28 እንደሚያካሂድ አስታውቋል።ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ ጨረታዎች ሰባተኛው ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ተጨማሪ 200 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ለመግዛት ልዑኳን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን አስታወቀች!
ኬንያ ተጨማሪ 200 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ለመግዛት ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳን አስታወቀች፤ የኬንያ የኢነርጂ እና ሃይል ሚኒስቴር የቴክኒክ ልዑካን በኤሌክትሪክ ግዢው ዙሪያ ለመደራደር ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ተጠቁሟል።
ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው የኬንያ ልዑክ በኤሌክትሪክ ሀይሉ የክፍያ ታሪፍ፣ አቅርቦቱ የሚከናወንበትን ግዜ፣ የማስተላለፊያዎቹ ደህንነት አጠባበቅ መንገዶች ዙሪያ የመጨረሻ ስምምነቱን እንደሚፈጽም ተገልጿል።ለኬንያ የሚቀርበው ተጨማሪ መጠባበቂያ ሀይል ከህዳሴ ግድብ ከሚመነጨው እንደሚሆን ከኬንያው ኬዲአርቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከሶስት አመታት በፊት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ለ25 አመታት የሚቆይ የሀይል ግዢ ስምምነት መፈጸማቸው የሚታወስ ሲሆን ኢትዮጵያ ለኬንያ ኤሌክትሪክ በማቅረብ በኪሎ ዋት ስድስት ነጥብ አምስት የአሜሪካን ሳንቲም እንደምታስከፍል ተቀምጧል፤ ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታስከፍላት የኬሎዋት ክፍያ ለማምረት ከምታወጣው ወጪ እጅግ ያነሰ ነው ተብሏል።
ኬንያ ከጂኦተርማል ኢነርጂ አንድ ኪሎ ዋት ለማመንጨት 20 የአሜሪካ ሳንቲም ወጪ እንደምታደርግ ተጠቁሟል። ኬንያ አጠቃላይ ከጎረቤቶቿ የምታስገባው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 400 ሜጋ ዋት ለማድረስ እየጣረች መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ይህም አመታዊ 10 ሚሊየን ዶላር እንድታድን ያደርጋታል ተብሏል።በአሁኑ ወቅት በኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ከፍተኛ በሚሆንበት ሰዓታት 283 ሜጋዋት እጥረት እንደሚያጋጥማት መረጃዎች አመላክተዋል።

🌺🌸 #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
@geezdistance15
የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።

በርካቶች ኢትዮጵያ የምትከተለው አይነት የፌደራል ስርዓት ሲተቹ የዚችን ሀገር መጨረሻ እንደምሳሌ ያነሳሉ። ከግዙፍ አገዛዝ ፍርስራሽ የተነሳች፣ ግርማ ሞገስ ባለው መሪ ስር የአለምን ትኩረት የሳበች በመጨረሻ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈራርሳ የጠፋች ሀገር። ታሪኩን ሊንኩን ተጭነው ይከታተሉ!
👇👇
https://youtu.be/BjMW4RZUbHY
👇👇
https://youtu.be/BjMW4RZUbHY
YouTube
ከአለም ካርታ ላይ የጠፋችው ሀገር
ከግዙፍ አገዛዝ ፍርስራሽ የተነሳች፣ ግርማ ሞገስ ባለው መሪ ስር የአለምን ትኩረት የሳበች በመጨረሻ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈራርሳ የጠፋች ሀገር ።
🗝️ እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ
60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ
❇️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :
⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል
💸ቅድመ ክፍያ
💎ባለ 1 መኝታ በ 431 ሺ ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 619 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 751 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,051,626 ብር
🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ
🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)
➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ
➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ
➡️☎️ 09 31 14 82 42
➡️@Novi_03 (telegram)
➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ
❇️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :
⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል
💸ቅድመ ክፍያ
💎ባለ 1 መኝታ በ 431 ሺ ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 619 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 751 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,051,626 ብር
🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ
🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)
➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ
➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ
➡️☎️ 09 31 14 82 42
➡️@Novi_03 (telegram)
➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው
🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል
👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው
🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል
👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision
The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.
Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.
📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here
#EthiopianBuildingCodeStandards
✅ Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
Private Sector Engagement in Building Code Revision
The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.
Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.
📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here
#EthiopianBuildingCodeStandards
✅ Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ በ12 አገራት ላይ የጉዞ እገዳ ጣሉ!
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ የ12 አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ የሚከለክለውን አዋጅ መፈረማቸውን ዋይት ሐውስ አስታወቀ።ፕሬዚዳንቱ የጉዞ እገዳ የጣሉባቸው አገራት የአፍሪካ ቀንዶቹ አገራት ኤርትራና ሶማሊያን ጨምሮ፣ ሱዳን፣ አፍጋኒስታን፣ ኢራን፣ ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሄይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ምንያማር እና የመን ናቸው።
ፕሬዚዳንቱ "የብሔራዊ ደህንነት አደጋን በመጋረጥ" የወነጀሏቸውን የነዚህ አገራት ዜጎች ላይ የጣሉት የጉዞ እገዳ ከሰኔ 2/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።ከነዚህ ሙሉ የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው በተጨማሪ ሰባት አገራት፣ ብሩንዲ፣ ኩባ፣ ላኦስ፣ ሴራሊዮን፣ ቶጎ፣ ቱርኬመኒስታን እና ቬንዙዌላ ከፊል የጉዞ እገዳ ተጥሎባቸዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለዚህ የጉዞ እገዳቸው መነሻ የሆናቸው በቅርቡ በኮላራዶ የተፈጸመን ጥቃት ዋቢ አድርገው የውጭ ዜጎች ወደ አሜሪካ በሚገቡበት ወቅት "በአግባቡ ማንነታቸው ሳይጣራ" መሆኑን ያሳየ ነው ሲሉ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ በለጠፉት ቪዲዮ ተናግረዋል።ግለሰቡ ለእስራኤል ታጋቾች ድጋፋቸውን ለመግለጽ በወጡ ሰልፈኞች ላይ ጥቃት ፈጽሟል ተብሏል።
ጥቃቱን ፈጽሟል የተባለው ግብጻዊ ዜግነት ያለው ሲሆን፤ ግብጽ በዚህ የጉዞ እገዳ አልተካተተችም።ትራምፕ በተጨማሪም በጊዜያዊ (ቱሪስት) ቪዛ ወደ አገሪቱ መጥተው የሚቆዩ ሰዎችንም በተመለከተ "አንፈልጋቸውም" ሲሉ ተናግረዋል።ዋይት ሐውስ እነዚህ ገደቦች አሜሪካውያንን "ከውጭ አገራት አደገኛ አካላት" ይጠብቋቸዋል ብሏል።
ምንም እንኳን አገራቱ ሙሉ የጉዞ እገዳ ቢጣልባቸውም በኢራን ውስጥ በእምነታቸው እና ጎሳቸው ጭቆና እየደረሰባቸው ላሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲጓዙ ተፈቅዶላቸዋል።በተጨማሪም ለትላልቅ ስፖርታዊ ዝግጅቶች የሚሳተፉ አትሌቶች እና ውስን ለሆኑ የአፍጋኒስታን ዜጎችም እገዳው እንደማይመለከታቸው ተጠቅሷል።
Via BBC

የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ከደመወዛቸው ላይ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲያዋጡ የሚያስገድድ ድንጋጌ ተሰረዘ!
ወደፊት ለሚቋቋመው “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ”፤ ከመንግስት እና ከግል ተቋማት ሰራተኞች ደመወዝ መዋጮ እንዲሰበሰብ የሚያስገድደው የአዋጅ ድንጋጌ ተሰረዘ። ድንጋጌው በዛሬው ዕለት በፓርላማ ከጸደቀው “የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ” ውስጥ እንዲወጣ የተደረገው፤ በሰራተኞች ላይ “ተደራራቢ ጫና እንዳያስከትል” ታስቦ መሆኑ ተገልጿል።
ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ይኸው አዋጅ፤ የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧቸው 15 አይነት አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ገቢ እንዲሰበሰቡ የሚያስገድድ ድንጋጌ በውስጡ ይዞ ነበር። ፈንዱ “ለአደጋ ስጋት ቅነሳ፣ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም” ተግባራት የሚውል እንደሆነ በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።
በገቢ ምንጭነት በአዋጁ ተዘርዝረው ከነበሩት መካከል “የመንግስት እና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኞች ከሚከፈላቸው የተጣራ ደመወዝ ላይ” መዋጮ እንዲሰበሰብ የሚያስገድደው ድንጋጌ አንዱ ነበር። አዋጁ ለውይይት በቀረበበት ወቅት፤ ከደመወዝ ላይም ሆነ ከተለያዩ አገልግሎቶች ለፈንዱ ገቢ የሚሆን ገንዘብ መሰብሰብ “የግለሰቦችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ነው ወይ?” የሚል ጥያቄ አስነስቶ ነበር።
Via Ethiopia Insider